ኢትዮ-ሩጫ/Ethio-Athletics

  • Home
  • ኢትዮ-ሩጫ/Ethio-Athletics

ኢትዮ-ሩጫ/Ethio-Athletics Ethiopian Athletes News & History
የኢትዮጵያ ሯጮች ዜናና ታሪክ

➡️አትሌት አልማዝ አያና በቬንዳታ ደልሂ  የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፋለች።  (1:07:59 )⏱️
15/10/2023

➡️አትሌት አልማዝ አያና በቬንዳታ ደልሂ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፋለች። (1:07:59 )⏱️

➡️በ35ኛው የዓለም ኮከብ አትሌት ሽልማት ጉዳፍና ትግስት ታጭተዋል፤ 7ኛውን ሽልማት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት? ➡️ኃይሌ ገብረስላሴ (በ1998 እኤአ)➡️ቀነኒሳ በቀለ (በ2004 እና በ2005...
15/10/2023

➡️በ35ኛው የዓለም ኮከብ አትሌት ሽልማት ጉዳፍና ትግስት ታጭተዋል፤ 7ኛውን ሽልማት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት?
➡️ኃይሌ ገብረስላሴ (በ1998 እኤአ)
➡️ቀነኒሳ በቀለ (በ2004 እና በ2005 እኤአ)
➡️መሰረት ደፋር (በ2007 እኤአ)
➡️ገንዘቤ ዲባባ (በ2015 እኤአ)
➡️ አልማዝ አያና (በ2016 እኤአ)
👉የዓለም አትሌቲክስ ማህበር በ2023 የውድድር ዘመን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶችን በሚያወዳድርበት የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ላይ World Athletics Award የድጋፍ ድምፅ ማሠባሠብ ጀምሯል። በሴቶች ምድብ በእጩነት ከቀረቡት 11 ምርጥ አትሌቶች ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና አትሌት ትግስት አሰፋ ናቸው።
👉ከ2023 በፊት በተካሄዱት ያለፉት 34 የዓለም ኮከብ አትሌት የሽልማት ስነስርዓቶች የኢትዮጵያ አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች 6 ጊዜ ለመሸለም በቅተዋል።በወንዶች ምድብ 3 ጊዜ እንዲሁም በሴቶች ምድብ 3 ጊዜ በማሸነፍ ነው፡፡ በወንዶች ምድብ ያሸነፉት በ1998 ኃይሌ ገብረስላሴ እንዲሁም በ2004ና በ2005 እኤአ ቀነኒሳ በቀለ ናቸው። በሴቶች ምድብ ደግሞ በ2007 መሰረት ደፋር ፤ በ2015 እኤአ ገንዘቤ ዲባባና በ2016 እኤአ አልማዝ አያና ተሸልመዋል። በዓለም አትሌቲክስ የኮከቦች ምርጫ በልዮ ዘርፍ የተለሸሙም አሉ። በ2006 እኤአ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ብቸኛውን የአይኤኤኤፍ የህይወት ዘመን ስኬት ሽልማት አግኝተዋል። በ2005ና በ2008 ጥሩነሽ ዲባባ ፤ በ2006 እኤአ መሰረት ደፋር በሴቶች ምድብ እንዲሁም በ2019 ሰለሞን ባረጋ በወንዶች ምድብ የዓመቱ ምርጥ ብቃት ሽልማትን አሸንፈዋል። በዓለም ኮከብ አትሌት ሽልማት ላይ ደራርቱ ቱሉም ልዮ ክብር አግኝታለች።

➡️አትሌት መሠረት በለጠና አትሌት መሠረት አበባየሁ ከአሠልጣኙ ሐጂ አዴሎ ጋር ናቸው። በ2023 አምስተርዳም ማራቶን አንደኛና ሁለተኛ ወጥተዋል።
15/10/2023

➡️አትሌት መሠረት በለጠና አትሌት መሠረት አበባየሁ ከአሠልጣኙ ሐጂ አዴሎ ጋር ናቸው። በ2023 አምስተርዳም ማራቶን አንደኛና ሁለተኛ ወጥተዋል።

13/10/2023

ውድ ቀነኒሳ ውድ ጋሼ...

"We're always Behind you man... forever yours in running"
አመሠግናለሁ።
የጆስ ሔርማንስ መልዕክት

Like this on World Athletics to vote for Gudaf Tsegay Desta
11/10/2023

Like this on World Athletics to vote for Gudaf Tsegay Desta

Female Athlete of the Year nominee ✨

Like to vote for Gudaf Tsegay Desta 🇪🇹 in the .

Like this on World Athletics to vote for Tigist Assefa
11/10/2023

Like this on World Athletics to vote for Tigist Assefa

Female Athlete of the Year nominee ✨

Like to vote for Tigist Assefa 🇪🇹 in the .

👉የዓለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤቷ ትግስት አሰፋና በ5ሺ ሜትር የዓለም ሪከርዱን የያዘችው ጉዳፍ ፀጋይ በ2023 የዓለም አትሌቲክስ World Athletics  የዓመቱ ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ላ...
11/10/2023

👉የዓለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤቷ ትግስት አሰፋና በ5ሺ ሜትር የዓለም ሪከርዱን የያዘችው ጉዳፍ ፀጋይ በ2023 የዓለም አትሌቲክስ World Athletics የዓመቱ ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ላይ በሴቶች ምድብ እጩ ሆነው ቀርበዋል።
መልካም እድል!

08/10/2023
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ  በ45ኛው የቺካጎ ማራቶን ላይ መሮጧ አጓጉቷታል።  ስለ ማራቶን ሪከርድ የተነሳ ነገር ባይኖርም ፈጣን ሰዓት ለማስመዝገብና ለፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የሚያበቃትን ውጤት ...
05/10/2023

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ45ኛው የቺካጎ ማራቶን ላይ መሮጧ አጓጉቷታል። ስለ ማራቶን ሪከርድ የተነሳ ነገር ባይኖርም ፈጣን ሰዓት ለማስመዝገብና ለፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የሚያበቃትን ውጤት ለማግኘት እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
አትሌት ገንዘቤ የመጀመርያ ማራቶን ውድድሯን የሮጠችው ከዓመት በፊት በአምስተርዳም ማራቶን ነበር። አትሌት አልማዝ አያና ስታሸንፍ 2፡18፡05 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ሆናለች።
አትሌት ገንዘቤ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሶስት የዓለም ክብረወሰኖች እንደያዘች ነው። በ1 ማይል (4:13.31)፤ በ3000 ሜ (8:16.60) እንዲሁም በ5000 ሜ ( 14:18.86 ) ሪከርዶቿ ተመዝግበዋል።

በ45ኛው ቺካጎ ማራቶን ላይ በሴቶች ምድብ ሱቱሜ ከበደ ፤ ታዱ ተሾመ፤ ትግስት ግርማና አባቤል የሻነህ ሌሎቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ሲሆኑ ያለፈው ዓመት አሸናፊ ሩዝ ቼፕቴጊ ከኬንያ እንዲሁም ሆላንዳዊቷ ሲፋን ሐሰንም ይወዳደራሉ። በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊያኑ ተሳታፊዎች ዳዊት ወልዴ፤ ሰይፉ ቱራ፤ ሚልኬሳ መንገሻና ሁሰይዲን መሐመድ ናቸው።
📸

Great pic!courtesy of Ethiopian Athletics Federation
04/10/2023

Great pic!
courtesy of Ethiopian Athletics Federation

04/10/2023
02/10/2023

WORLD RECORD

🇪🇹's Diribe Welteji blazes to a 4:20.98 world record* to grab a surprise gold in the women's to road mile 😮‍💨



*Subject to the usual ratification procedures

01/10/2023

Ethiopia to the world ‼️

Hagos Gebrhiwet sprints to 5km glory as he overtakes his compatriot Yomif Kejelcha in the finishing straight 🔥

12:59 on the clock, take a bow 👑

World Athletics Road Running Championships Riga 23Live World Athletics
01/10/2023

World Athletics Road Running Championships Riga 23
Live World Athletics

27/09/2023

A look back on a monumental marathon world record.

Take a bow for 🇪🇹's Tigst Assefa 🙌

25/09/2023
ትግስት አሰፋ 2:11:53 የዓለም ማራቶን ሪከርድ
24/09/2023

ትግስት አሰፋ 2:11:53 የዓለም ማራቶን ሪከርድ

24/09/2023

WORLD RECORD

🇪🇹's Tigst Assefa obliterates the women's marathon world record* in Berlin 🤯

2:11:53 🚀

*Subject to the usual ratification procedures

23/09/2023

Ethiopia’s Sporting Success: A Source of Inspiration for Japan The Budapest World Athletics Championships have attracted attention worldwide, with thrilling competitions taking place since the 19th. Among the participating nations, Ethiopia stands out as a country renowned for its remarkable achie...

👉 ይህ በላቲቪያዋ ከተማ ሪጋ በሚካሄደው 1ኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ነው ።  በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ...
21/09/2023

👉 ይህ በላቲቪያዋ ከተማ ሪጋ በሚካሄደው 1ኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ነው ። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና በግማሽ ማራቶን፤ በ 5 ኪሜ እና በማይል ውድድሮች ይደረጋሉ ። 57 አገራትን የወከሉ 347 አትሌቶች (152 ሴቶች እና 195 ወንዶች) ይሳተፉበታል።

20/09/2023

World record glory 🔥

We're celebrating the 5000m world record set by 🇪🇹's Gudaf Tsegay at Sunday's Prefontaine Classic with a Wednesday Wallpaper ⬇️

Feature: buff.ly/3Lxq4zY

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ  ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክቷል።ክቡር ዶ/ር ቀነኒሣ በቀለ በዓለም አትሌቲክስ የምንጊዜም ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጭ እንደተባለ ይታወቃል። በኦሎም...
20/09/2023

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክቷል።ክቡር ዶ/ር ቀነኒሣ በቀለ በዓለም አትሌቲክስ የምንጊዜም ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጭ እንደተባለ ይታወቃል። በኦሎምፒክ፤ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ በዓለም አገር አቋራጭ ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ለኢትዮጵያ 23 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰብስቧል። ሶስት የኢትዮጵያ ሪከርዶችን በ5ሺ፤ በ10ሺና በማራቶን እንደያዘ ነው፡፡ የ10ሺ እና የ5ሺ የዓለም ሪከርዶችን ከ15 ዓመታት በላይ ተቆጣጥሮ ቆይቷል፡፡ የማራቶን ምርጥ ሰዓት በ2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከአርባ አንድ ሰከንድ ያስመዘገበ ነው። በሩጫ ዘመኑ ከ120 በላይ ውድድሮችን አሸንፏል፡፡

👉ምንያህል ከኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ደጋፊዎች ማህበር"ቡዳፔስት ላይ አትሌቶቻችን በማራቶንና በሴቶች ሺ ላይ ካሳዩት መደጋገፍ ብዙ እንማራለን፡፡ ማህበራችን የተቋቋመው በአሜሪካ ዩጂን ከተመዘገበው...
17/09/2023

👉ምንያህል ከኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ደጋፊዎች ማህበር
"ቡዳፔስት ላይ አትሌቶቻችን በማራቶንና በሴቶች ሺ ላይ ካሳዩት መደጋገፍ ብዙ እንማራለን፡፡ ማህበራችን የተቋቋመው በአሜሪካ ዩጂን ከተመዘገበው ውጤት በኋላ ነው፡፡ ለአትሌቶች የምንስጠው ክብር ያንሳል፡፡ መሻሻል ማደግ ይኖርበታል፡፡ አትሌቶችን በውድድር ሰሞን ብቻ ይሆን ሁሌም የምናወድስበት የምናደንቅበት ነው፡፡ አትሌቶቻችን አምባሳደሮቻችን ናቸው፡፡ በየትኛውም የዓለም አገር ይታወቃሉ፡፡"

👉"ወደፊት ቡዳፔስት ኦሎምፒክ ማስተናገዷንም እጠብቃለሁ፡፡"ቲቦር ከካናዳ"የምኖረው ቡዳፔስት ውስጥ ነው፡፡ ባለቤቶ በካናዳ ቶሮንቶ የምትኖር ሲሆን ማራቶን ሯጭ ነች፡፡ ቡዳፔስት የዓለም ሻምፒዮ...
17/09/2023

👉"ወደፊት ቡዳፔስት ኦሎምፒክ ማስተናገዷንም እጠብቃለሁ፡፡"

ቲቦር ከካናዳ
"የምኖረው ቡዳፔስት ውስጥ ነው፡፡ ባለቤቶ በካናዳ ቶሮንቶ የምትኖር ሲሆን ማራቶን ሯጭ ነች፡፡ ቡዳፔስት የዓለም ሻምፒዮናውን በሚያኮራ ሁኔታ ነው ያስተናገደችው፡፡ የሃንጋሪ ህዝብ ስፖርት ወዳድነቱን አሳይቷል፡፡ የስፖርት መሰረተ ልማቶቹ እና የትራንስፖርት አገልግሎቱ ለሻምፒዮናው ምቹ መስተንግዶ ፈጥሯል፡፡ የአውሮፓ መናሐርያ ስለሆነች ወደፊት ቡዳፔስት ኦሎምፒክ ማስተናገዷንም እጠብቃለሁ፡፡"

የኢስቶኒያው ፎቶግራፈር"በዓለም ሻምፒዮናው የተገኘሁት ለኢስቶኒያ አትሌቶቾች የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ነው፡፡ በማራቶን የሚሮጥ አንድ አትሌት አለን፡፡ ብዙ የምንታወቀው በዴካትሎን ስፖርት ነው፡...
17/09/2023

የኢስቶኒያው ፎቶግራፈር
"በዓለም ሻምፒዮናው የተገኘሁት ለኢስቶኒያ አትሌቶቾች የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ነው፡፡ በማራቶን የሚሮጥ አንድ አትሌት አለን፡፡ ብዙ የምንታወቀው በዴካትሎን ስፖርት ነው፡፡"

👉ማንፍሬንድ ስቴፋኒ  18 የዓለም ሻምፒዮዎች የዘገቡት ፎቶግራፈር"ቡዳፔስት ላይ ስገኝ ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ነው፡፡ ብቸኛው ያመለጠኝ ዩጂን ያስተናገደችው 18ኛው የዓለ...
17/09/2023

👉ማንፍሬንድ ስቴፋኒ 18 የዓለም ሻምፒዮዎች የዘገቡት ፎቶግራፈር
"ቡዳፔስት ላይ ስገኝ ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ነው፡፡ ብቸኛው ያመለጠኝ ዩጂን ያስተናገደችው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲሆን ችግሩም ከኮቪድ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ በአትሌቲክሱ ዓለም የምታወቀው በማራቶን ውድድሮች ፎቶግራፈርነት ነው፡፡ ከብዙ የኢትዮጵያ አትሌቶችም ጋር እንተዋወቃለን፡፡ በአንድ ወቅት አዲስ አበባ መጥቼ ኃይለ ገብረስላሴን በቢሮው አግኝቸዋለሁ፡፡ ከቀነኒሳ በቀለ እና ከወንድሙ ጋርም ልዩ ቃለምልልስ አድርጊያለሁ፡፡ ቀነኒሳ ለእኔ የዓለማችን ምርጥ አትሌት ነው፡፡ እሱን በትልልቅ ውድድሮች ላይ ለመመልከት መታደሌን በኩራት ነው የምናገረው፡፡ በ2009 አኤአ ላይ በበርሊን ማራቶን በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር ድርብ ድል ያስመዘገበበትን ብቃት አልረሳውም፡፡


👉"ስለማራቶን ሳስብ በጭንቅላቴ የሚመጣው በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ ማራቶንን ያሸነፈው አበበ ቢቂላ ነው፡፡ "ሮናን ከእስራኤል"በዓለም ሻምፒዮና ላይ በማራቶን  ለእስራኤል የሜዳልያ ...
17/09/2023

👉"ስለማራቶን ሳስብ በጭንቅላቴ የሚመጣው በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ ማራቶንን ያሸነፈው አበበ ቢቂላ ነው፡፡ "
ሮናን ከእስራኤል
"በዓለም ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ለእስራኤል የሜዳልያ ድል ማስመዝገብ ታላቅ ታሪክ ብቻ ሳይሆን እውነት የማይመስል ልቦለድ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ስለማራቶን ሳስብ በጭንቅላቴ የሚመጣው በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ ማራቶንን ያሸነፈው አበበ ቢቂላ ነው፡፡ አበበ የመጀመርያውን የማራቶን ድል የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገበ የማራቶን ነብይ ለማለት ይቻላል፡፡ ከዚያም በኋላ የማሞ ወልዴን ታሪክ አውቃለሁ፡፡ ኃይለ ገብረስላሴንም እጅግ የማደንቀው አትሌት ነው፡፡ ማራቶን የአትሌቲክስ ንግስት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመላው አለም በበርካታ ከተሞች የማራቶን ውድድሮች ይዘጋጃሉ፡፡ በርካታ ተሳታፊዎችንም ያገኛሉ፡፡ በእኔ እምነት አትሌቲክስ የዓለማችን አንጋፋውና ተወዳጁ ስፖርት ነው፡፡ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ በዓለም ዙርያ የገነኑ ስፖርቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አትሌቲክስ ግን በእነ አበበ ቢቂላ፤ ፓቮ ኑርሚ እና ኪፕኬኖ ዘመን ሲጠቀስ እንድም ኳስ ተጨዋች ስሙ አይታወቅም ነበር፡፡"


👉ማራቶንን ስትወዳደር ፉክክሩ ከራስህ ጋር ነው፡፡ ጃፓናዊ የማራቶን ደጋፊ"የጃፓን ማራቶን ሯጮችን ለመደገፍ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቡዳፔስት ተገኝተናል፡፡ ማራቶን እጅግ አስደናቂ ስፖርት ነው፡፡ ...
17/09/2023

👉ማራቶንን ስትወዳደር ፉክክሩ ከራስህ ጋር ነው፡፡
ጃፓናዊ የማራቶን ደጋፊ
"የጃፓን ማራቶን ሯጮችን ለመደገፍ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቡዳፔስት ተገኝተናል፡፡ ማራቶን እጅግ አስደናቂ ስፖርት ነው፡፡ ማራቶንን ስትወዳደር ፉክክሩ ከራስህ ጋር ነው፡፡ ራስን ለማሸነፍ በቂ ዝግጅትና ጥንካሬ ያስፈልጋል፡፡ ራስህን ካሸነፍክ ማራቶኑን ድል ታደርጋለህ፡፡"


👉በጀግኖች አደባባይ የተገኘነው የኢትዮጵያን አትሌቶችን ለመደገፍ ነው፡፡ ፍቃዱና ቤተሰቡ "ነዋሪነታችን በቡዳፔስት ነው፡፡ በጀግኖች አደባባይ የተገኘነው የኢትዮጵያን አትሌቶችን ለመደገፍ ነው፡...
17/09/2023

👉በጀግኖች አደባባይ የተገኘነው የኢትዮጵያን አትሌቶችን ለመደገፍ ነው፡፡
ፍቃዱና ቤተሰቡ
"ነዋሪነታችን በቡዳፔስት ነው፡፡ በጀግኖች አደባባይ የተገኘነው የኢትዮጵያን አትሌቶችን ለመደገፍ ነው፡፡ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ከሆነበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጲያ ባህላዊ ስፖርት ለመሆን የበቃ ነው፡፡ ማራቶን ጠንካራ ዝግጅት የሚያስፈልገው፤ ጥሩ የሚጠይቅና የአትሌቱን ጀግንነት የሚያሳይ ስፖርት ነው፡፡ በቡዳፔስት የምንኖር ኢትዮጵያውያን በቡድናችን እጅግ ደስተኞች ነበርን፡፡እኔ እንደውም የኢትዮጲያ ቡድን ከመምጣቱ በፊት ስለቡዳፔስት ሙቀት ለፌደሬሽኑ መረጃ በመላክ ሁሉ ቡድኑን ለመደገፍ ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ ማራቶን የእኛ ባህል መገለጫ ሆኗል፡፡ በዓለም ዙርያ በበርካታ ከተሞች ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያን አትሌቶች በቡዳፔስት ጎዳናዎች ላይ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ የእኛ ሯጮች ከሙቀቱ አንፃር በጣም ጠንካሮች ናቸው፡፡ ሩጫ በጣም እወዳለሁ፡፡

👉"እያንዳንዱ ማራቶን የራሱ ታሪክ አለው"ፋብዮ ከቤልጅየም ዓለም ሻምፒዮናውን ስከታተል ሳምንቱን ሙሉ በቡዳፔስት ነው ያሳለፍኩት፡፡ በተለይ ደግሞ የማራቶን ውድድሮችን ለማየት የመጣሁት የማራቶ...
17/09/2023

👉"እያንዳንዱ ማራቶን የራሱ ታሪክ አለው"

ፋብዮ ከቤልጅየም
ዓለም ሻምፒዮናውን ስከታተል ሳምንቱን ሙሉ በቡዳፔስት ነው ያሳለፍኩት፡፡ በተለይ ደግሞ የማራቶን ውድድሮችን ለማየት የመጣሁት የማራቶን ሯጭ በመሆኔ ነው፡፡ በዓለም ሻምፒዮናው ላይ ቤልጅዬም በጉዳት ሳቢያ በርካታ ምርጥ አትሌቶችን አለማሳተፏ ይቆጫል፡፡ ማራቶን እጅግ ልዩ ስፖርት ነው፡፡ እያንዳንዱ ማራቶን የራሱ ታሪክ አለው፡፡ 7 ማራቶኖችን ሮጫለሁ፡፡ 34 ኪሜ ከሸፈንክ በኋላ የማራቶን ውድድር ክብደትን ትረዳዋለህ፡፡በባዶ እግሩ ማራቶንን የሮጠውን አበበ ቢቂላ ታሪክ አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጲያ በማራቶን ብቻ ሳይሆን በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር የዓለማችንን ታላላቅ ሯጮች ማፍራቷን አውቃለሁ፡፡ በስም እየጠራሁ ባላውቃቸውም፡፡"

👉"አትሌቲክስ ቁጥር አንድ ስፖርት ነው፡፡"ኤድዊን ከሆላንድ"የዓለም ሻምፒዮናውን በስታድዬም በመገኘት በሙሉ ተከታትየዋለሁ፡፡ በመጨረሻዎቹ ቀናት የተካሄዱት የማራቶን ውድድሮች ደግሞ ዋና ትኩረ...
17/09/2023

👉"አትሌቲክስ ቁጥር አንድ ስፖርት ነው፡፡"

ኤድዊን ከሆላንድ
"የዓለም ሻምፒዮናውን በስታድዬም በመገኘት በሙሉ ተከታትየዋለሁ፡፡ በመጨረሻዎቹ ቀናት የተካሄዱት የማራቶን ውድድሮች ደግሞ ዋና ትኩረቶቼ ናቸው፡፡ ማራቶን ለእኔ የምንግዜም ምርጥ ስፖርቴ ነው፡፡ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ ያገኘውና የሮተርዳም ማራቶንን ያሸነፈው የሆላንድ ሯጭ አብዲ ነገዬ ደጋፊ ነኝ፡፡ በርካታ የኢትዮጵያ ሯጮችንም አውቃለሁ፡፡ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች በረጅም ርቀት ፤ በጎዳና ላይ ሩጫዎችና በማራቶን ተፎካካሪ ያጡት የተሻሉና ምርጦች በመሆናቸው ነው፡፡ ማራቶንን ያወቅኩት በአቴንስ ከተማ የጥንቱ ግሪክ ወታደር የሮጠውን ርቀት ከሸፈንኩ በኋላ ነው፡፡ አትሌቲክስ ቁጥር አንድ ስፖርት ነው፡፡"

👉የእስራኤል ማራቶን ሯጭ ደጋፊ ከደቡብ አፍሪካ "ወደ ሃንጋሪ የመጣሁት ከባለቤቴና ሁለት ልጆቼ ጋር ነው፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን በስታድዬም ገብተን ብንከታተልም ዋናው ቀጠሯችን ከማራቶን ውድድ...
17/09/2023

👉የእስራኤል ማራቶን ሯጭ ደጋፊ ከደቡብ አፍሪካ
"ወደ ሃንጋሪ የመጣሁት ከባለቤቴና ሁለት ልጆቼ ጋር ነው፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን በስታድዬም ገብተን ብንከታተልም ዋናው ቀጠሯችን ከማራቶን ውድድሮች ጋር ነበር፡፡ ቡዳፔስት ከተማ የተገኘነው ከደቡብ አፍሪካ ተነስተን ነው፡፡ በማራቶን የሚሳተፍ አንድ እስራኤላዊ ጓደኛችንን ለመደገፍ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከኃይሌ ገብረስላሴና ከቀነኒሳ በቀለ ጋር ተገናኝቻለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሯጮች የዓለም ምርጦች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡"


10/09/2023

Just INCREDIBLE! 🤩
Well done to our Elite Men today

🥇Tamirat Tola 00:59:58
🥈Bashir Abdi 01:01:20
🥉Muktar Edris 01:01:54

09/09/2023

Two Golds 2022 OREGON 5000M and 2023 Budapest 10000m

ሁሴን ማኬ በአለም አትሌቲክስ ማሕበር ፈቃድ የተሰጠው የአትሌቶች ተወካይና የአትሌቲክስ ማናጀሮች ማህበር አባል ነው። ሁሴን በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የአትሌት ውክልና ካምፓኒዎች መካከል አን...
09/09/2023

ሁሴን ማኬ በአለም አትሌቲክስ ማሕበር ፈቃድ የተሰጠው የአትሌቶች ተወካይና የአትሌቲክስ ማናጀሮች ማህበር አባል ነው። ሁሴን በዓለም ላይ ግንባር ቀደም የአትሌት ውክልና ካምፓኒዎች መካከል አንዱ የሆነው የElite Sports Marketing & Management (ESMM) ዳይሬክተር ነው። በዩናይትድ ስቴትስ፣ በሞሮኮ፣ በፈረንሳይ፣ በዶሃ፣ በቻይና እና በኢትዮጵያ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን ከ150 በላይ አትሌቶች ከ13 የተለያዩ ሀገራት አሰባስበው በልዮ ውክልና በመስራት ላይ ይገኛሉ። ላለፉት 2 አስርት አመታት ESMM ስፍር ቁጥር የሌላቸው የኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፒዮኖችን በማፍራት ላይ ነው።
www.addisadmassnews.com

Address


Telephone

0911486040

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ-ሩጫ/Ethio-Athletics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኢትዮ-ሩጫ/Ethio-Athletics:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share