22/03/2022
በዘይትም እንጹም?
ቅቤ ትቶ መጾም ከድሮም ነበረ፣
በዘይት መጾምም ይኸው ተጀመረ፣
ለምን ዓቢይ ጾም ቀኖና ቀየረ?
ቅቤና ዘይትን እንዴት አጣመረ?
ቅቤውን እየተውን መጾሙን ለምደነው፣
ዘንድሮ ቀን ጠፍቶ በዘይትም ጾምነው፣
የቅቤን ማስገደፍ ዘይት እንዲሽረው።
በቅቤም፣ በዘይት ለመቀማጠሉ፣
እስኪ መጀመሪያ የሚበላ ይኑር ሠላም ይሁን በሉ።
ሙቅ ላኝክ ካላለ የደላው ባለሟል፣
ምግቡ ራሱ ሳይኖር ዘይት ምን ይሰራል?