ፋኖ ለሰላም/Fano for PEACE

  • Home
  • ፋኖ ለሰላም/Fano for PEACE

ፋኖ ለሰላም/Fano for PEACE ሰላም ለሁሉም!! PEACE for all!!

ጃውሳ በጎጃም በርካታ አርሶ አደሮችን በግፍ ረሽኗቸዋል! የአማራ ህዝብ ስቃይ እና መከራ ለማራዘም የሚፍጨረጨረው ጃውሳ በህዝቡ ላይ ያልፈፀመው የግፍ አይነት የለም ብሎ መናገር ይቻላል። ቡድኑ...
06/03/2024

ጃውሳ በጎጃም በርካታ አርሶ አደሮችን በግፍ ረሽኗቸዋል!

የአማራ ህዝብ ስቃይ እና መከራ ለማራዘም የሚፍጨረጨረው ጃውሳ በህዝቡ ላይ ያልፈፀመው የግፍ አይነት የለም ብሎ መናገር ይቻላል። ቡድኑ የዋህውን ህዝብ ከመግደል አልፎ በቁሙ በርሃብ እንዲንገላታ እህል በክምር አጋይቶም ታይቷል።

ይህን ሁሉ የሚያደርገው የአማራ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊት ስንቅ አቅርቧል፣ ስለ እንቅስቃሴው መረጃ ለሰራዊቱ አቀብሏል በሚል ምክንያት ነው።
ሰሞኑንም ከመከላከያ ሰራዊት በተወሰደበት እርምጃ በመደናገጥ የፈሪ ዱላውን በምስኪኑ አርሶ አደር ሲያሳርፍ የተስተዋለ ሲሆን በዳንግላ እና በአጎራባች አካባቢዎች ላይ በክምር ላይ ያለ እህል አመድ ሲያደርግ ተስተውሏል።

የቡድኑ ግፍ በዚሁ አላበቃም በዱርቤቴ፣ ደጋዳሞት፣ አዴት እና አቸፈር አካባቢዎች “ስንቅ አላቀረባችሁልኝም”፣ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ነበራችሁ በሚል በርካታ አርሶ አደሮችን በልጆቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ፊት ገደላቸው።

Eenyu inni??ማን ነው??
05/12/2023

Eenyu inni??

ማን ነው??

04/12/2023
ዮውሃንስ ቧ ያለው የንፅህና ችግር እንጂ የምግብ ችግር የገጠመው አይመስልም!!አይዞሽ ገለቴ!
04/12/2023

ዮውሃንስ ቧ ያለው የንፅህና ችግር እንጂ የምግብ ችግር የገጠመው አይመስልም!!

አይዞሽ ገለቴ!

ሰላምን አልፈልግም ያለው ሸኔ በመረጠው ቋንቋ እየተገረፈ ነው! የፀጥታ ሃይሉ በሚወስደው እርምጃ መደናገር ውስጥ የገባው የሸኔ ሽብር ቡድን እርስ በርሱ እየተባላ መበታተን ጀምሯል። አንዱ በሌ...
04/12/2023

ሰላምን አልፈልግም ያለው ሸኔ በመረጠው ቋንቋ እየተገረፈ ነው!

የፀጥታ ሃይሉ በሚወስደው እርምጃ መደናገር ውስጥ የገባው የሸኔ ሽብር ቡድን እርስ በርሱ እየተባላ መበታተን ጀምሯል። አንዱ በሌላኛው ላይ በአባባቢ እየተከፈለ ጥቃት መፈፀም ከጀመረም ሰነባብቷል። ይህ እርስ በርሱ እየተባላ ያለው ቡድን በርካታ ታጣቂዎችን የፀጥታ ሃይሉ በሚወስደው እርምጃ እያጣ ይገኛል። በዚህም ሰሞኑን በአርሲ ሽርካ በሚባል አከባቢ በመንቀሳቀስ ማህበረሰቡን እረፍት ከነሱት የቡድኑ ታጣቂዎች መካከል 22 የሚሆኑት የፀጥታ ሃይሉ በወሰደው እርምጃ ሲደመሰሱ ከ10 በላይ የሚሆኑት በሰላም እጃቸዉን ለወገን ሃይል ሰጥተዋል።

ጠንካራና ቅቡልነት ያለዉን መንግስት ለመገንባት እንትጋ !!ጠንካራ እና ተቀባይነት ያለው ሃገራዊ መንግስት ለመገንባት የሁሉም ትብብር ወሳኝ ነው።ሃገራችን ኢትዮጵያ የብሔር ማንነት እና አንድነ...
04/12/2023

ጠንካራና ቅቡልነት ያለዉን መንግስት ለመገንባት እንትጋ !!
ጠንካራ እና ተቀባይነት ያለው ሃገራዊ መንግስት ለመገንባት የሁሉም ትብብር ወሳኝ ነው።ሃገራችን ኢትዮጵያ የብሔር ማንነት እና አንድነትን የሚያስጠብቅ ጠንካራ እና ተቀባይነት ያለው ሃገራዊ መንግሥት በመገንባት ላይ ትገኛለች።
ጠንካራ ሃገራዊ መንግስት ሲገነባ ህዝቡ ላይ የሚደርሱ ቀጥተኛ ችግሮች ተቀርፈው ልማቱ እና ዕድገቱ፣ እኩልነት እና ነጻነቱ እንዲረጋገጥ ነጻና ቀልጣፋ ሃገራዊ አደረጃጀቶችን ለመገንባት ይረዳል።

✍️የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ አለ የሀገሬ ሰው...“ዐብይ ወላሂ ወላሂ ብሎ ግድቡን ሽጦታል” አሉ ከአራት አመት በፊት። በዐብይ እና በኢትዮጵያ ጥላቻ ያበዱ አካላት ይህንን በሚሉበት ጊዜ ግድ...
29/08/2023

✍️የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ አለ የሀገሬ ሰው...

“ዐብይ ወላሂ ወላሂ ብሎ ግድቡን ሽጦታል” አሉ ከአራት አመት በፊት። በዐብይ እና በኢትዮጵያ ጥላቻ ያበዱ አካላት ይህንን በሚሉበት ጊዜ ግድቡ በሚያሳዝን ቅርቃር ውስጥ ነበር። በአምስት አመት ይጠናቀቃል ተብሎ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ጥለውበት የነበረው ግድብ የተያዘለትን ብዙ እጥፍ በጀት ቅርጥፍ አድርጎ በልቶ በሚያሳዝን ሁኔታ የነበረው የፕሮጀክት አፈጻሰም ግን በእቅድ ከተያዘው በእጅጉ ያነሰ ነበር።

👉ዐብይ ታዲያ በሚገርም የፕሮጀክት አመራር ብቃት፣ በሚገርም የፋይናንስ አሰባሰብ፣ በሚገርም የዲፕሎማሲ ቁርጠኝነት ግድቡን ከተወሸቀበት የአፈጻጸም ቅርቃር አስፈንጥሮ አውጥቶ አሁን ላይ ግድቡ 95% በላይ እንዲጠናቀቅ አድርጓል፣ የተወሰኑ ተርባይኖች ተገጥመውለት ሃይል ማመንጨት ጀምሯል።

👏ኢትዮጵያውያን እንደ ምፅዓት ቀን ናፍቋቸው የነበረው የህዳሴው ግድብ መጠናቀቂያ ቀን አሁን ላይ እውን ለመሆን በእጅጉ ቀርቧል።

ቆሞ ቀሮች ታዲያ ዛሬም በለመዱትን ህዝብን የማደናገሪያ የሞኝ ለቅሶ “ዐብይ ግድቡን ሸጦታል” እያሉን ነው።

ወዳጄ ዐብይ ዲፕሎማሲን ያውቃታል ሳይሆን ይጠበብባታል፣ የራቀቅባታል ነው የሚባለው። ስለዚህ ይህ የድርድር ዜና እኛን ከቶ አያሳስበንም። ምክንያቱም አብይ ግድቡን ከምንም ወደ ሚጨበጥ ደረጃ ያደረሰ ጀግ ና ነው። ይህንን ያደረገው ደግሞ በአስደናቂ የዲፕሎማሲ ጥበብ ነው። አሁንም በርሱ ትልቅ እምነት አለን። ከአይናችን ይልቅ ጆሯችችንን አናምንም። ሰርቶ አሳይቶናል እና ዐብይን እናምነዋለን።

ከዐብይ ወዲያ ለኢትዮጵያ...ሊያውም ሮጦ ጎጥ እና ሰፈር ውስጥ ለሚወሸቅ ጽንፈኛ? አንሰማም እኛ!

ቀጥል ዐብይ ከጎንህ ነን!💪

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፋኖ ለሰላም/Fano for PEACE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share