Bench Sheko Tv

  • Home
  • Bench Sheko Tv

Bench Sheko Tv Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bench Sheko Tv, TV Channel, .

10/02/2024
03/02/2024

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። አቶ ሀብታሙ ካፍቲን

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን የሚዛን አማን ከተማ አየር ማረፊያ ግንባታ በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ለሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከሚያስፈልገው መሬት ውስጥ 1 መቶ 27 ሄክታሩ የካሳ ክፍያ ተጠናቋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ለዞናችን ብሎም ለሀገሪቱ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር የዞኑ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

ግንባታው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ቦታውን ከይገባኛል ጥያቄ ነፃ ለማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ለግንባታው ከሚያስፈልገው 2 መቶ 53 ሄክታር ቦታ 1 መቶ 27 ሄክታሩን ካሳ በመክፈል ከይገባኛል ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ለካሳ ክፍያ ከሚያስፈልገው 300 ሚሊዮን ብር በበጀት አመቱ ብቻ ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ መከፈሉን አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ገልፀዋል።

ተለዋጭ የቤት ቦታ ለሚያስፈልጋቸው 5 መቶ 29 አባወራዎችና እማወራዎች ውስጥ ለ 1 መቶ 68ቱ ብቻ የተሰጠ መሆኑንና ገና ቀሪ 3 መቶ 61 አባወራዎችና እማወራዎች ተለዋጭ ቦታ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

አክለውም ጥናት ካልተደረገላቸው ውጪ ቀሪ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚከፈል የካሳ ክፍያ መኖሩን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው ቀሪው ዞኑ ካለው የበጀት እጥረት አንፃር የፌዴራል፣ የክልልና የዞን የህብረተሰብ ክፍልና የመንግስት ሰራተኛው የተጠናከረ ድጋፍ በማድረግ ከዞኑ ህዝብና መንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለውን የካሳ ገንዘብ የዞኑ ህዝብና የመንግስት ሰራተኞች ከመጀመሪያው እስካሁን ድረስ እያደረጉ ላሉት ድጋፍ አመስግነው በቀጣይ ላልተነሱ እማወራዎችና አባወራዎች የሚደረገው ድጋፍ በተጀመረው ልክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፍያ መሰረት ድንጋይ ሰኔ 13/2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መቀመጡ ይታወሳል።

"ቲካሻ ቤንጊ" ለሸኮ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ፣ የአዲስ ተስፋ ፣ የአዲስ ብስራትና እንዲሁም ለመጪው ዓመት በሰላምና በጤና ጠብቆ እንዲያቆያቸው በጋራ ተሰባስበው ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀር...
26/01/2024

"ቲካሻ ቤንጊ" ለሸኮ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ፣ የአዲስ ተስፋ ፣ የአዲስ ብስራትና እንዲሁም ለመጪው ዓመት በሰላምና በጤና ጠብቆ እንዲያቆያቸው በጋራ ተሰባስበው ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡበት በአል ነው።

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

19/01/2024

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለከተራና ጥምቀት በዓል አስመልክተው እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተከበሩ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በመልዕክታቸው
በዓሉ የሰላም ፤የፍቅር ፤የመተሳሰብና ለአብሮነት በአንድነት የምንቆምበት የደመቀና የተዋበ ይሁን ብለዋል።

የጥምቀት በዓል በአለም የማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገቡት ውስጥ አንዱና ሀገራዊ አንድነታችን የሚፀባረቅበት በዓል ነው ብለዋል።

የጥምቀት በዓል ህዝቡ የሚሰበሰብበት የአብሮነት መድመቂያ እና አንድነትን የሚያጠናክር ዉብ በዓል ነው ብለዋል።

ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም ሰላምንና አብሮነት በሚያጠናክር መልኩ ማክበር ያስፈልጋል ብለዋል።

በዞናችን በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም በጋራ በመሆን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል።

"በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በማብላት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ የአልጋ ቁራኛዎችን በመጎብኘትና ያለንን በማጋራት ሊሆን ይገባል" አቶ ቀበሌ መንገሻየቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀ...
06/01/2024

"በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በማብላት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ የአልጋ ቁራኛዎችን በመጎብኘትና ያለንን በማጋራት ሊሆን ይገባል" አቶ ቀበሌ መንገሻ

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ለመላው የዞናችን ነዋሪዎች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

የዘንድሮውን የገና በዓል የምናከብረው ሀገራችን የወደብ ባለቤት የምትሆንበትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር በተፈራረመችበት ወቅት በመሆኑ በዓሉን ደማቅ ያደርገዋል።

መንግስት በዚህና መሰል የህዝብ ጥቅም ሊያረጋግጥ በሚችሉ ስራዎች ላይ በሚያሳየው ቆራጥ አቋም ሀገራችን በዓለም የነበራት ገናና ስምና ክብር ከልጆቿ ጥረት ጋር የሚመለስበት ጊዜም ሩቅ አይደለም ።

እንደሚታወቀው ዞናችን ቤንች ሸኮ የኢትዮያዊነት ትልቁ ማሳያ ፣ የህብረ ብሔራዊነት ተጨባጭ ማረጋገጫና በቀጠናው የንግድ ፣ የኢንቨስትመንት ፣ የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል የመሆኗ ትልቁ ሚስጥር በጋራ ለመልማትና ለማደግ ያለን ቁርጠኝነትና ይህንኑ በተግባር ለማረጋገጥ በህብረትና በቅንጅት መስራታችን ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በህዝባችን የሚነሱ የልማትና ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ በራሳችንና የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍና ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር እየሰራን እንገኛል፡፡

እንደ ዞናችን በግብርናው ዘርፍ አብዮት መፍጠር ችለናል ። በክልሉ ቡና ፣ ሰብል ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቅመማ ቅመምን በስፋት በማምረትና ወደ ማዕከላዊ ገበያ በመላክ በቀዳሚው ደረጃ ላይ እንገኛለን። በመሰረተ ልማት ረገድ በመንግስት በርካታ ልማቶችን እንዲሁም ህዝቡ ላይ በተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ዛሬ ላይ እንደ ሀገር ሞዴል ሊሆን በሚችል መልኩ በርካታ ግዙፍ ድልድዮች ፣ የመንገድ ከፈታና ጥገና ፣ ትምህርት ቤቶችና መሰል የልማት ትሩፋቶችን በህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና ድጋፍ መከወን ችለናል።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶት ራሱን ዝቅ አድርጎ በመስቀል የዋለው ስለ ሰዎች ሰላም ፣ ፍቅርና አንድነት ብሎ ነው፡፡ በአምሳያው የተፈጠርነው እኛ ሰዎችም አንዳችን ለሌላችን መከታ ፣ አጋርና ደጋፊ ሆነን ፍቅርን በመስጠት ፣ ስለ ሰላም አብዝተን በመስበክ ፣ ሰላማዊ መንደር ፣ ቀበሌ ፣ ከተማ ፣ ወረዳና ሰላማዊ ዞን በመፍጠር ቃሉን በተግባር ልንፈጽም ይገባል እላለሁ፡፡

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በማብላት ፣ የታረዙትን በማልበስ ፣ የአልጋ ቁራኛዎችን በመጎብኘትና ያለንን በማጋራት በዓሉን በጋራ ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በተለይም በዓላትን ተከትሎ ከሚፈጠሩ የትራፊክ አደጋና ራሳችንን ለአደጋ አጋላጭ ከሆኑ ነገሮች በመጠበቅ እንዲሁም ስናሽከረክርም ሆነ መንገድ ስናቋርጥ ርቀታችንን በመጠበቅና አልኮል ጠጥቶ ባለማሽከርከር በዓሉን ያለምንም ችግር በሰላምና በፍቅር ልናሳልፍ ይገባል እላለሁ፡፡

በድጋሚ ለመላው የዞናችን ነዋሪዎች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም ፣ የጤናና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
መልካም በዓል
አቶ ቀበሌ መንገሻ
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

01/01/2024

ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት በመሆኗ እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ። አቶ ቀበሌ መንገሻ

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት ጋር የባህር በር ባለቤት ለመሆን ታሪካዊ የሆነ የምግባቢያ ሰንድ በመፈራረማቸው እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ኢትዮጵያዊ ቀደምት የባር በር ባለቤት መሆኗን አስታውሰው ከ30 አመት በፊት የባህር በር ባለቤትነትን ብንነጠቅም በገዢው መንግስት ጥረት በድጋሚ ባለቤት መሆን በመቻላችን ደስታችን ድርብ ነው ብለዋል።

በመንግስታችንና ህዝባችን ብርቱ ሰላማዊ ትግል የበር ባለቤትነትን አረጋግጠናል ይህ ደግሞ ለሀገራችን ህዝቦች ታሪካዊ ድል መሆኑንም ገልፀዋል።

ክቡር አስተዳዳሪው በእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸው ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የበር ባር እንድታገኝ ህዝቡ ላሳየው ተግባር አድናቆት ይገባቸውላ ብለው በቀጣይም በሌሎች ተግባር መደገም አለበት ብለዋል።

ይህንን ታሪካዊ ስኬት ሀሳቡን ከማመንጨትና ሂደቱን በብቃት በመምራት ስኬት ላበቁት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ልባዊ ምስጋና አድናቆት አቅርበዋል።

08/12/2023

የሚዛን አማን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የዞኑ መንግስት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በዚህም በቅርቡ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከአካባቢው ለልማት ተነሺዎች ቀሪ ካሳ የሚከፈል ከ263 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ ኮሚቴ ተቋቁሞ የሀብት ማሰባሰብ ስራ ተጀምሯል።

እንደሚታወቀው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ሰኔ 10/2013 ዓ.ም ማስቀመጣቸው የሚታወስ ነው

ለዚህ ሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ ያላችሁ የዞኑ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ፐብሉክ ሰርቫንቱ፤ ወጣቱ፤ ባለሀብቱ፤ አርሶ አደር ብሎም ሁሉም የዞናችን ህዝቦች ከዞኑ መንግስት ጋር በመሆን ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በመክፈል የአየር መንገዱ በፍጥነት ግንባታ እንዲጀምር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አድርጋቹሀልና ምስጋና ይገባችኋል።

በአካባቢው ያለው ማህበረሰብና ተቋማት በማስተባበር የገቢ ማሰባሰብ ሥራ በመስራት ለልማት ካላቸው ፍላጎት አንፃር ካሳ ሳይከፈላቸው ለልማት ለተነሱ ከ263 ሚሊዮን ብር በላይ በማስፈለጉ ይህንኑ ለመክፈል ገቢ ማሰባሰቢያ አካውንት ተከፍቶ ልዩ ልዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራዎች ተጀምሯል።

ከዚህ ጋርም ተያይዞ ቀድመው ድጋፍ ያደረጉልን የአየር ማረፊያው ግንባታ ተቋራጭ የሳምሶን ቸርነት ሀገር አቀፍ ተቋራጭ የ1ሚሊዮን ብር ገቢ ስለደረጉ በዞኑ መንግስት ስም እናመሠግናለን።

አየር ማረፊያው ለዞኑ ብሎም ለሀገሪቱ ከሚያመጣው ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አንፃር ለልማት ቅድሚያ የምትገኙ የዞናችን ህዝቦች ብሎም መላው የሀገራችን ህዝቦች የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናስተላልፋለን።

የባንክ አካውንት ቁጥሮች ከዚህ በታች የተቀመጡ ሲሆን ገቢ ያደረጋችሁትን የባንክ ስሊፕ በዚህ ቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/+7gCCWkwHds8xYTg0 አሊያም በነዚህ ስልክ ቁጥር ቴሌግራም አማራጭ

#0910137627 ሙባረክ አበበ
#+251917152084 ተስፋዬ ጊስካር እንድትልኩልን እያልን እኛም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የምናሳውቅ ይሆናል።

የባንክ አካውንት
- 1000223211848
- 5091657806011
- 1500290170783
- 165661265
እናመሠግናለን!

የቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ 6 ዞኖች አንዱ ነው፡፡ የሚዛን አማን ከተማም የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ መቀመጫ ከተማ ሲሆን ከሀገሪቱ ርዕሰ መ...
22/08/2023

የቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ 6 ዞኖች አንዱ ነው፡፡

የሚዛን አማን ከተማም የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ መቀመጫ ከተማ ሲሆን ከሀገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ በ583 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን በጠቅላላ 1932659 ሄክታር የቆዳ ስፋት ሲኖረው ከባህር ጠለል በላይ 500 - 3000 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ዓመታዊ የሙቀት መጠኑ ከ15 - 27 ዴ.ሴ ሲሆን አማካይ የዝናብ መጠኑ እስከ ከ200 - 400 ሚሊ ሜትር ይደርሳል፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት የሚሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦች ባለቤት ነው፡፡ከዚህም ባለፈ በዞኗ የሚገኙ የነባር ብሔረሰቦች ያልተነካና ያልተበረዙ ትውፊቶች ፣ ቱባ ባህሎች ዛሬም ድረስ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን ቀልብ እንዳሰቡ መዝለቅ ችለዋል፡፡

በቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ረገድ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ግንባታ እንዲሁም ለኢኮ ቱሪዝም ፣ ለአግሮ ቱሪዝምና ለመሳሰሉት ኢንቨስትመንቶች ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች የተመቻቸ የቱሪዝም ኢንቬስትመንት አቅም ያለው ዞን ነው፡፡

በተለይም ዞኑ በመልካም አስተዳደርና በተረጋጋ የፖለቲካ ስርአት ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋትና በተደራሽነቱ እያደገ የሚገኝ መሰረተ ልማት ፣ ሰፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚደረግበት ከመሆኑም በላይ አሁን ላይ የኢንቨስትመንትና የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻ የሆነት ዞን ናት፡፡

በዚህም ከተለያዩ ቦታዎች ለስራ ፍለጋና ለመኖሪያ ወደ ዞኑ የሚመጣው የሰው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣት ችሏል፡፡

ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች ምክንያት የዞኑ የቱሪስት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ወደ አካባቢው የሚመጡ ጎቢኝዎችን ፍላጎት ለማሟላት ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በጥራትና በብዛት በመገንባት ላይ የሚገኝ ዞን ነው፡፡

ይህም በተለያዩ ዘርፎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ፣ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘትና የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማስፋፋቱ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል " እየተጫወተም ይገኛል ፡፡

በ19ኛው የቡዳፔስት አትሌቲክስ ሻምፒዮና  ፍጻሜ 3ኛ ደረጃን አግኝተናል።ሰለሞን ባረጋ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የወንዶች በ10ሺ ሜትር ፍፃሜ  ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያን አምጥቷል።
20/08/2023

በ19ኛው የቡዳፔስት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍጻሜ 3ኛ ደረጃን አግኝተናል።

ሰለሞን ባረጋ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የወንዶች በ10ሺ ሜትር ፍፃሜ ለኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያን አምጥቷል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share