Abyssinia News Source አቢሲኒያ የዜና ምንጭ

  • Home
  • Abyssinia News Source አቢሲኒያ የዜና ምንጭ

Abyssinia News Source

አቢሲኒያ የዜና ምንጭ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abyssinia News Source

አቢሲኒያ የዜና ምንጭ, Media/News Company, .

የሩሲያ ፌደሬሽን ፓርላማ (ዱማ) ምክትል መሪ በመንበረ ፓትርያክ ጽ/ቤት ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጋር ተወያዩ ፡፡  አስቻለው...
03/02/2023

የሩሲያ ፌደሬሽን ፓርላማ (ዱማ) ምክትል መሪ በመንበረ ፓትርያክ ጽ/ቤት ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ጋር ተወያዩ ፡፡
አስቻለው ሽፈራው
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
በሩሲያ ፌደሬሽን ፓርላማ ምክትል መሪ ሚስተር ኒኮላይ ኖቪችኮቭ የተመራና በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን አምባሳደር ኢቭገኒ ተርክኽንና ሌሎች አባላት ያሉበት የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት ተገኝተው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን ጎበኙ።
በጉብኝታቸው ወቅት ሚስተር ኒኮላይ ኖቪችኮቭ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተላከ ልባዊ ፍቅርና መልዕክት ለቅዱስነታቸው አቅርበዋል። ሚስተር ኖቪችኮቭ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ችግር አስመልክቶ ሲናገሩ የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ክርስቲያኖች አያሌ ፈተናና ተግዳሮቶችን እያሳለፉ መጥተዋል አሁንም በጸሎታቸው ይወጡታል ብለውል። ሩሲያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እሴቶች ለረዥም ዘመን ድጋፏን ስታሳይ መቆየቷን ጠቅሰው አሁንም በያለውን ወቅታዊ ችግር ህዝበ ክርስቲያኑ በጸሎትና በጥበብ እንዲወጣው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በተያያዘም ከልዑካን ቡድኑ ጋር በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙት በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን አምባሳደር ኢቭገኒ ተርክኽን በበኩላቸው ሀገራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጉዳይ በቅርበት እንደምትከታተል ገልጸው ወንድም በሆነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በተፈጠረው ችግር የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል። የታሪክና ሥልጣኔ ምንጭ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ የሚደረገው ሙከራም ሀገርና መንግሥትን እንደማፍረስ ነው ብለዋል። ይህ ተግባር ፈፅሞ መፍቀድ የለበትም ያሉት አምባሳደሩ ቤተ ክርስቲያን እና ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ቀደም እንደተወጡት ሁሉ በአሸናፊነት እንደሚያልፉት በፅኑ አምናለሁ ብለዋል። በተመሳሳይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልዑካን ቡድን በመጪው ሳምንት ወደ ሞስኮ ለጉብኝት እንደሚጓዝ ሚስተር ኒኮላይ ኖቪችኮቭ አረጋግጠዋል ።
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
📡 የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel
➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/
➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo
➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/
➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=

13/01/2023
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከአማርኛ እና ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ አፋን ኦሮሞን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደ ተጨማሪ ቋንቋ እንዲሰጥ የመድብለ ቋንቋ ሥርዓተ-ትምህርት  በማዘጋጀት አ...
12/01/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከአማርኛ እና ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ አፋን ኦሮሞን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደ ተጨማሪ ቋንቋ እንዲሰጥ የመድብለ ቋንቋ ሥርዓተ-ትምህርት በማዘጋጀት አዲስ መርሃ ግብር ይፋ አደረገ።

Photo: Addis Abeba Mayor's office. Addis Abeba - The Addis Abeba City Administration cabinet has announced new multi-lingual education curriculum by adopting Afaan Oromoo as supplementary language to be taught in all schools in addition to Amharic and English. The curriculum also sees Amharic as [.....

በእስር ላይ በሚገኙት የኢሰመጉ ሰራተኞች ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ
12/01/2023

በእስር ላይ በሚገኙት የኢሰመጉ ሰራተኞች ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ

በአማኑኤል ይልቃል ላለፉት ስድስት ቀናት በእስር ላይ በሚገኙት አራት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሰራተኞች ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤ.....

10/01/2023

የክርስቲያን የሰብአዊ መብቶች ቡድን የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የሰብአዊ መብት ፋውንዴሽን ክርስቲያን ሶሊዳሪቲ ዎርልድዋይድ (CSW) በጎረቤት ኢትዮጵያ በተፈጠረው ሁከት የኤርትራ “ከፍተኛ” ተሳትፎ እንዳሳሰበው ገልጾ የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ጠይቋል።

በሲኤስደብሊው አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ቡድን መሪ የሆኑት ካታዛ ጎንድዌ የኤርትራ ጦር በተለይ ትግራይ ውስጥ መግባቱ በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ሂደት እየጎተተው ነው ብለዋል።

"በአለም አቀፍ ከፍተኛ ወንጀሎች ላይ የተሳተፉት ወታደሮች ቀጣይነት ለሰላም ሂደቱ እና ለትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ህይወት ግልጽ የሆነ ስጋት ነው" ሲሉ ጎንድዌ ሐሙስ ጥር 5 ባወጡት ዘገባ ላይ ተናግረዋል።

አክለውም “የአፍሪካ ህብረት እና የተቀረው አለም አቀፉ ማህበረሰብ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ ኢላማ የተደረጉ ማዕቀቦችን በመቅረፅ እና አጠቃላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በማዘጋጀት ጨምሮ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይፋዊ እና የጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋን ለማጣጣም እየሰራ ነው።ኢትዮጵያ በኦፊሴላዊው እና በጥቁር ገበያ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እርም...
10/01/2023

የኢትዮጵያ መንግስት ይፋዊ እና የጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋን ለማጣጣም እየሰራ ነው።

ኢትዮጵያ በኦፊሴላዊው እና በጥቁር ገበያ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እርምጃዎችን እየወሰደች ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን ጨምሮ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ተወካዮችን ያቀፈ መንግስት ኮሚቴ አቋቁሟል። ይህ እርምጃ ይፋ የሆነው የአንድ ዶላር ኦፊሴላዊው ምንዛሪ በ54 ብር ሲሆን የጥቁር ገበያ ዋጋው 100 ብር በመሆኑ በሁለቱ መካከል ከፍተኛ ልዩነት በመፈጠሩ ነው።

ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ እና የታመመውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ጫና ገጥሟታል። እጥረቱ በባንኮች ረዣዥም ሰልፎች እንዲፈጠሩ እና የንግድ ድርጅቶች እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት መቸገራቸው የዋጋ ንረት እና የእቃ አቅርቦት እጥረትን አስከትሏል። በተጨማሪም መንግስት ብዙ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጭ ኢንቨስትመንት ነፃ ለማድረግ መወሰኑን በቅርቡ አስታውቋል፡፡ ይህም ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እና የስራ እድል ለመፍጠር ያስችላል። ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ለማሳደግ መንግስት ተስፋ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ለማረጋጋት እና በኦፊሴላዊው እና በጥቁር ገበያ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ያስችላል።

ኮሚቴው ከገጠሙት ተግዳሮቶች አንዱ በይፋዊው የምንዛሪ ተመን ላይ እምነት ማጣት ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይፋዊው ዋጋ ደረጃ ዝቅተኛ እንደሆነ እና መንግስት የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታት በቂ ስራ እየሰራ አይደለም ብለው ማመናቸው ነው። ይህም የዶላር ጥቁር ገበያ እንዲያድግ በማድረግ በኦፊሴላዊው እና በጥቁር ገበያ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት አስፍቶታል።

እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት መንግሥት እንደ ቬንዙዌላ፣ አርጀንቲና እና ዚምባብዌ ባሉ ኦፊሴላዊ እና ጥቁር ገበያ ምንዛሪ ዋጋዎች መካከል ትልቅ ልዩነት ያጋጠማቸው የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ እየተመለከተ ነው። ኮሚቴው የነዚህን ሀገራት ልምድ በማጥናት የሰሩትን እና ያልሰሩትን በመለየት በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት ውጤታማ ስትራቴጂ ለመንደፍ አቅዷል።

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ የጥቁር ገበያ ንግዱን ለመግታት የውጭ ምንዛሬን በማከፋፈል እና ተደራሽነቱን በማጥበብ የገበያ መረጋጋትን ለማረጋገጥ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ነው። በተጨማሪም የዋጋ ንረትን መቆጣጠር በተቻለ መጠን የምንዛሪ ዋጋ ክፍተቱን በማጥበብ ረገድ ወሳኝ ነው።

በቅርቡ የፋይናንስ ሴክተሩን ለውጭ ኢንቨስትመንት ነፃ ለማድረግ የተደረገው ውሳኔ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ነፃ ለማድረግ ያለመ ነው። ነገር ግን ይህንን ችግር ለመቅረፍ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ በመያዝ ለልዩነቱ ዋና መንስኤዎችን ማለትም የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና በይፋ የምንዛሪ ተመን ላይ እምነት ማነስን የሚፈታ ዘርፈ ብዙ አካሄድ ይጠይቃል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች፤ በዚህ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ መታቀዱ ተገለጸየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ከጸጥታ ጋር በተያያዘ” ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካ...
10/01/2023

በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች፤ በዚህ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ መታቀዱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ከጸጥታ ጋር በተያያዘ” ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች፤ በተያዘው በጀት ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ማቀዱን ገለጸ። ቦርዱ በአካባቢዎቹ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ ማብራሪያ እንዲሰጠው ክልሎችን መጠየቁንም አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው ትላንት ሰኞ ጥር 1፤ 2015 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ ነው። መግለጫውን የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምርጫ ያልተደረገባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች መኖራቸውን እናውቃለን፤ የቦርዱ ሃሳብ እና ዕቅድ ምርጫ ባልተደረገባቸው አካባቢዎች በዚህ በጀት ዘመን ምርጫ እንዲደረግባቸው ማድረግ ነው” ሲሉ ለጋዜጠኞች የተቋማቸውን ዕቅድ ገልጸዋል።

“እያንዳንዱ ክልል በእነዚህ አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ተመልክቶ ለምርጫ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጠን ጽፈናል” ያሉት ብርቱካን፤ እስካሁን ከሶስት ክልሎች ምላሽ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ምላሽ የሰጡት ክልሎች አማራ፣ አፋር እና ደቡብ ናቸው።

በአማራ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት ሰኔ 14፤ 2013 ምርጫ ያልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች አስር ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪም “በአሰራር ግድፈት” ምክንያት ስድስት ምርጫ ክልሎች ላይ ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወን ቦርዱ መወሰኑ ይታወሳል። የአማራ ክልል በአጠቃላይ በተወካዮች ምክር ቤት 138 የፓርላማ ወንበሮች አሉት።

የአፋር ክልል ካሉት ስምንት የፓርላማ መቀመጫዎች መካከል ሁለቱ በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ አልተካሄደባቸውም። በፓርላማ 178 መቀመጫዎች ባሉት የኦሮሚያ ክልል፤ በተመሳሳይ የጸጥታ ችግር ምክንያት በሰባት የምርጫ ክልሎች ምርጫ አልተደረገም። የምርጫ አካባቢዎቹን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ እስካሁን ለምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ያልሰጠው የኦሮሚያ ክልል መሆኑን ብርቱካን በትላንቱ መግለጫቸው ተናግረዋል።

የቦርድ ሰብሳቢዋ የኦሮሚያ ክልል ለቦርዱ ማብራሪያ አለመስጠቱን ቢያነሱም “ኦሮሚያ ላይ ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች፤ አሁን ለምርጫ አስቻይ ሁኔታ ያለ አይመስለንም” ሲሉ ምርጫ ባልተደረገባቸው የክልሉ አካባቢዎች አሁንም የጸጥታ ችግር መኖሩን ጠቁመዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምርጫ ያልተደረገባቸው አካባቢዎች መኖራቸውንም የቦርድ ሰብሳቢዋ አስታውሰዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካሉት ዘጠኝ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ ምርጫ የተከናወነው በሶስቱ ብቻ ነው። በተመሳሳይ ከ99 የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ ምርጫ ተካሄዶ በተወካዮች የተያዙት ሃያ ስምንቱ ብቻ ናቸው። እነዚህን መቀመጫዎች ያሸነፈው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ነው።

በክልሉ ህገ መንግስት መሰረት ሃያ ስምንት የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች መንግስት ለመመስረት ስለማያስችሉ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ የሚገኘው ከስምንት አመት በፊት በ2007 ዓ.ም የተመሰረተው መንግስት ነው። በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በክልሉ በዚህ ዓመት ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ቦዴፓ ምርጫ ያልተደረገባቸው አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት “ለምርጫ አስቻይ የሆነ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ” የሚል እምነት እንዳለው በዚሁ መግለጫው አስታውቋል። ፓርቲው ይህን ቢልም የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ግን “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እኛም ራሳችን ቡድን ልከን በደንብ መገምገም ያለብን ይመስለናል” ሲሉ የጸጥታ ሁኔታው ተጨማሪ ዳሰሳ እንደሚያስፈልገው በትላንቱ መግለጫቸው አመልክተዋል። ቦርዱ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ የሚገመግም የመረጃ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ማካሄዱ አይዘነጋም።

ምርጫ ቦርድ ይህን የግምገማ መርሃ ግብር ከማካሄዱ አምስት ወራት አስቀድሞ፤ በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ማድረግ ጀምሮ ነበር። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታህሳስ 2014 ሊካሄድ ታቅዶ ለነበረው ምርጫ ይደረግ የነበረው ዝግጅት፤ የድምጽ መስጪያ ጊዜው ከመድረሱ ሁለት ወራት አስቀድሞ ተቋርጧል። ቦርዱ ጊዜያዊ የምርጫ ሰሌዳ ካወጣ በኋላ ዝግጅቱን ያቋረጠው፤ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በመላው ኢትዮጵያ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ነው።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ ካልተካሄደባቸው አካባቢዎች በተጨማሪ ድጋሚ ምርጫ የሚያከናውንባቸው አካባቢዎች መኖራቸውንም ትላንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ከእነዚህ አካባቢዎች መካከል አንዱ የሆነው በደቡብ ክልል የሚገኘው የቡሌ ምርጫ ክልል ነው። ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው የድጋሚ ምርጫ በመጪው ጥር 29 እንደሚካሄድ የቦርዱ ሰብሳቢ ገልጸዋል።

የድጋሚ ምርጫውን በዚህ ቀን ለማድረግ የተወሰነው፤ የቡሌ ምርጫ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ከሚካሄድባቸው ዞኖች አንዱ በሆነው ጌዴኦ የሚገኝ በመሆኑ የድምጽ አሰጣጡን አንድ ላይ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ብርቱካን አስረድተዋል። ለድጋሚ ምርጫ አዲስ ምዝገባ እንደማይኖር የጠቀሱት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ “ቀኑ በሚደርስበት ጊዜ እዚያ አካባቢ ያሉ መራጮች ይሄንኑ እንዲያውቁ እናደርጋለን” ብለዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abyssinia News Source አቢሲኒያ የዜና ምንጭ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share