Tossa Press

Tossa Press የመነን ዘር ነኝ ሲነኩኝ እንደ ንብ የምገነፍል ሲወዱኝ ያለኝን የምሰጥ❤

21/11/2025

ደሴ ላይ ሰልፍ አያስፈልግም ተረጋጉ። ክልል ያሉ አመራሮች ጉዳዩን ስለሚያውቁት በጅምላ የታሰሩ ንጹሃን ይፈታሉ ብለን እንጠብቃለን። ይኸ ትንኮሳ ግልጽ አይደለም።

🚩የደሴን "የልማት መጓተት እና ዉድቀት" የሚሞግቱ ጀግኖች ሲታሰሩ፤ የሙስና ጠበቃዎች ይጨፍራሉ!🎯 የደሴ ጉዳይ ወደ ቁልቁለት መንገድ እየሄደ ነው። በአንድ ወቅት የንግድ ማዕከል የነበረችው ከ...
20/11/2025

🚩የደሴን "የልማት መጓተት እና ዉድቀት" የሚሞግቱ ጀግኖች ሲታሰሩ፤ የሙስና ጠበቃዎች ይጨፍራሉ!

🎯 የደሴ ጉዳይ ወደ ቁልቁለት መንገድ እየሄደ ነው። በአንድ ወቅት የንግድ ማዕከል የነበረችው ከተማችን፣ ዛሬ በሙስና ተቦርቡራ፣ በመሬት ነጋዴዎች እጅ ወድቃ "የነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ" ትንቅንቅ ውስጥ ናት። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ውድቀቷን የተቃወሙና፣ የደሴ ዝርፊያ ይቁም" ያሉ የከተማዋ ልጆች ወደ ወህኒ ሲወርዱ፤ ሌላው ደስታውን መግለጹ ነው።
🎯 እውነታውን እንነጋገር!
በወንድማችን መታሰር ለምትጨፍሩ)፡
የሞዐ ተዋሕዶ ክንፎች ዛሬ "ወሐብያ ታሰረልን" እያላችሁ ፌሽታ የምታደርጉ አካላት፣ የታሰሩት ልጆች የጠየቁት ስለ መስጊድ ሳይሆን ስለ ከተማዋ መሬት እና ስለ ህዝብ ሃብት መሆኑን እያወቃችሁ ለምን ትክዳላችሁ?
የደሴ መሬት ሲሸጥ የንግድ ማዕከልነቷ እየደከመ ሲሄድ፣ የከተማዋ ገፅታ ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በተለየ ሁኔታ ወደ ኋላ ስትቀር፣ መንገድ ሲበላሽ እና ከተማዋ ወደ ኋላ ስትቀር እናንተን አይመለከታችሁምን? ወይስ እናንተ የምትኖሩት በሌላ ከተማ ነው? ሙስናን የሚቃወም ወገን ላይ የጥላቻ ጩኸት በማሰማት፣ ለዘራፊ አመራሮች "የጭብጨባ አጋር" መሆን፣ በታሪክ ፊት ተወቃሽ ያደርጋችኋል። ዛሬ በእነሱ እስር ብትጨፍሩም፣ ነገ የከተማዋ ውድቀት እናንተንም ይዞ መጥፋቱ አይቀርም። የምትጨፍሩት በራሳችሁ መቃብር ላይ ነው!

🎯 "ወሐብያ" የሚለውን የማሸማቀቂያ ካርድ ለምትመዙ: ይህ ያረጀ ስልት ነው። ከተማዋን እንደ ቅርጫ ስጋ የተከፋፈሉ ሙስኛ አመራሮች፣ ተጠያቂነት ሲመጣባቸው "ይህኮ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፣ ጠያቂዎቹ ወሐብያዎች ናቸው" ብለው የሚወረውሩትን አጥንት የምትቀበሉ ተላላኪዎች ናችሁ።
🎯 ሌባን "ሌባ" ማለት ወሐብያነት ነውን?
"የህዝብ ሀብት ለምን በሙስና ይዘረፋል?" ብሎ መጠየቅ ወሐብያነት ነውን?
እወቁት! ይህ ስም ለዘረፋው የተሰጠ "ሽፋን" (Cover-up) እንጂ እውነት አይደለም። የደሴ ህዝብ በሙስና እና በኑሮ ውድነት እየተቃጠለ፣ እናንተ በሃይማኖት ስም አቅጣጫ ልታስቀይሱ አትችሉም።
🎯 ለጥቅም ተጋሪ እና አሳሪ አመራሮች:
ስለ ልማት የጠየቀውን በማሰር፣ "ወሐቢያ" ብላችሁ ህዝቡን በማናከስ የስልጣን እድሜያችሁን ማራዘም ትችሉ ይሆናል፤ ግን ለጊዜው ነው። የደሴን ወጣቶች በማሰር የተዘረፈውን መሬት ህጋዊ ማድረግ፣ የከተማዋን ገመና መሸፈን አይቻልም። በእስር ቤት ብዛት እውነትን ማፈን አይቻልም።
🎯 ደሴ የወደቀችው በልጆቿ ጥያቄ ሳይሆን፣ በአመራሮቿ ዝርፊያ እና ያንን ዝርፊያ በሃይማኖት ካባ ለመሸፈን በሚሞክሩ ከፋፋዮች ሴራ ነው።
ዛሬ እውነትን ይዛችሁ የታሰራችሁ የደሴ ልጆች፣ ታሪክ ነጻ ያወጣችኋል! በወንድሞቻችሁ እስር የምትጨፍሩ ግን፣ የከተማችሁን ገዳዮች እያጀባችሁ መሆኑን ዘግይታችሁ ትረዱታላችሁ። ደሴ በሴራ አትፈርስም! እውነት ትዘገያለች እንጂ አትቀበርም!
©Amir Mohammed

20/11/2025

በውሸት ያከማቸኸውን የደሴ ልማት ልማት ጠያቂ በማሰር አታቆመውም‼️

❝ውሃብያ❞ ጮኸብን አሉ፣ እሺ አልናቸው ህዝቡ ❝አንድ ከተማ ላይ አንድ ሌባ ጌጥ ነው፣ ሁለትም ያለ ነው እንዴት ሙሉ ከተማው ሌባ ይሆናል❞ ብሎ ጮኸባቸው 🎯 ክራር ቀየሩና ጲም ጲሪሪም እያደረ...
20/11/2025

❝ውሃብያ❞ ጮኸብን አሉ፣ እሺ አልናቸው ህዝቡ ❝አንድ ከተማ ላይ አንድ ሌባ ጌጥ ነው፣ ሁለትም ያለ ነው እንዴት ሙሉ ከተማው ሌባ ይሆናል❞ ብሎ ጮኸባቸው

🎯 ክራር ቀየሩና ጲም ጲሪሪም እያደረጉ ❝ግብር የማይከፍሉ ነጋዴዎች ናቸው፣ ስለዚህ ግብር እንጥልባችኋለን፣ እስከ አሁን ዝም ያልናችሁ ስላልነካችሁን ተካፍለን ስንበላ ቆይተናል፣ አሁን ግን ከነጋችሁን በግብር አርጩሜ እንገርፋችኋለን❞ አሉ፣ እሺ አልናቸው ፣ ህዝቡ ደግሞ አሁንም ❝አንድ ከተማ ላይ አንድ ሌባ ጌጥ ነው፣ ሁለትም ያለ ነው እንዴት ሙሉ ከተማው ሌባ ይሆናል፣ ኧረ ጫዎታ ቀይሩ ደሴያችንን የሰነፍ ተማሪ ደብተር አስመሰላችኋታ፣ መሬቱ ተሽጦ ሲያልቅ ከውስጥ ምን አለ ተብላችሁ ነው ከተማውን ያረሳችሁት፣ ቢያንስ ወደነበረበት መልሱት አለ❞ ህዝብ ያየውን ነዋ የሚናገረው

🎯 አሁን ደግሞ ❝ከሌላ መንደር፣ ሰፈር፣ ጎጥ ስለመጣን ነው❞ ብለው ደሴ የማይከሰስበትን የማይታሰበውን የማይታማበትን፣ የወሎ ህዝብ ሰውን በሰውነቱ የሚያከብርበትን ክደው ለቅሶ ተቀምጠው ቆሎ እየቆረጠሙ ነው። በተለይ ደግሞ ብልፅግና ያለችው ሴትዮ እያኜከችው ነው። 🙄🤔

ለማንኛውም ህዝቡ ምንም ማዟዟር የሌለው የመልማት ጥያቄ ጠይቋል፣ ጥያቄውን ሳታጣምሙበት መልሱለት፣ ደሴን የሚያክል ግዝፍ ጥንታዊ ከተማው ላይ የተፈጠረውን ችግር ፍቱለት

#አከሲ
Mohammed Jewad

ዛሬ ሰኞ አይደለ !! እስኪ ስለ ባቲ ገበያ እናውራ ፣   _ባቲ......!!!"ኧረ ባቲ ባቲ ባቲ ገንደልዩ ሀድራው የሚሞቀው ደራርበው ሲታዩ"ባቲ በኢትዬጵያ በቋንቋና ባህል ልዩነት ያልተገደበ...
17/11/2025

ዛሬ ሰኞ አይደለ !! እስኪ ስለ ባቲ ገበያ እናውራ ፣ _ባቲ......!!!

"ኧረ ባቲ ባቲ ባቲ ገንደልዩ
ሀድራው የሚሞቀው ደራርበው ሲታዩ"

ባቲ በኢትዬጵያ በቋንቋና ባህል ልዩነት ያልተገደበ፣ በጋራ መኖርና መከባበር መገለጫ ሁና ዘልቃለች፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ደግሞ ይህ ጠንካራ እሴቷ ጎልቶ ይታያል፡፡ የባቲ ሰኞ ገበያ ከተለያዩ የሀገር ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ያስተናግዳል፡፡ ባቲ የሚለው ስም ከቦታ መጠሪያነት ባሻገር ከውበትና የሙዚያ ቅኝት ጋር ተያይዞ በድፍን ኢትዬጵያ ይታወቃል፡፡ ባቲ ከኢትዬጵያ የባህል ሙዚቃ ቅኝቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ባቲ የውበትና የፍቅር ቦታ ነው፡፡ "ውበት ሲለካ ባቲ ነው ለካ" ይባላል፡፡

የባቲ ገበያ ዘወትር ሰኞ ይውላል፡፡ ገበያው በሀገራቺን ካሉ ገበያዎች ሁሉ ሰፊና ህብረ ብሄራዊ ስለመሆኑ ብዙ መፅሀፍት መስክረውለታል፡፡ በተለይ በግመል ገበያነት ተወዳዳሪ የለውም፡፡ ግብይቱ ሰፊ ሜዳ ላይ ነው የሚከወነው፡፡ በገባያው በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን መንግስት ወንጀለኞችን በስቅላት ለመቅጣት የሚያስችል የተተከለ ብረት ለታሪክ ምስክርነት ቁሟል ያኔ ገባያተኛው እያየ ነበር ወንጀለኞች በስቅላት የሚቀጡት፡፡ የሰኞ ገበያ በባቲ ልዩ ነው፡፡

በገበያው ለሽያጭ የማይቀርብ የለም፡፡ ጌጣጌጥ፣ ዘመናዊና ባህላዊ አልባሳት፣ የቀንድና የጋማ ከብት፣ ፍራፍሬ፣ ቅመማቅመም፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ወ.ዘ.ተ በሰፊው ገበያ በገፍ ይቀርባሉ፡፡ ውበትና ፍቅር በተሞላው ገበያ ተፈልጎ የሚታጣ ነገር የለም፡፡

ባቲ ገበያ በውጭና ሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በጣም ተወዳጅ እና ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ አርጎባ፣ አፋር እና ትግራይ ህዝቦች መገኛ መሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ህዝቦች በባህላዊ አልባሳቶቻቸው ተውበውና አጊጠው ያላቸውን በመያዝ በፍቅር ሲገበያዩ ይውላሉ፡፡ በባቲ ገበያ ማነህ ከየት ነህ ብሎ ጥያቄ የለም፡፡

ሁሉም ያለውን ይዞ በመቅረብ ይገበያያል፡፡ ከአፋር :- ፍየል፣ በግ፣ ግመል፣ አህያና የወተት ተዋፅኦ የሆነው ቅቤ ይመጣል፡፡ ከአርጎባ አከባቢ የባህል እቃዎች፣ ጌጣጌጦች፣ አልባሳት በተለይ የሽመና ውጤቶች ይመጣሉ፡፡ ከአማራ ደግሞ የተለያዩ ዘመናዊና ባህላዊ አልባሳት፣ ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ እና ሸንኮራ አገዳ የመሳሰሉት ይመጣሉ፡፡ ከኦሮሞ በአብዛሀኛው የአገዳ እህሎች በዋናነት ማሽላና በቆሎ፣ ፍራፍሬ ይቀርባሉ፡፡

የባቲ ገበያ ከገበያነት ባሻገርም የማህበራዊ መገናኛ መድረክም ነው፡፡ በማራኪ አለባበስና አጋጊያጥ ገበያ የሚመጡበት ጎረምሳዎችና ሳዱላዎች ለፍቅር የሚፈላለጉበትና የሚተጫጩበት ቦታ ነው፡፡ በገበያው ልቡ የከጀላትን ቆንጆ ፈልጎ ያጣ ኮበሌም እንዲህ እያለ ያዜማል፡፡

"ባቲ ገበያ ላይ ቅል ይዤ እንደለማኝ
አንቺን አላገኘሁ ገበያው አልቀናኝ፡፡"
በባቲ ገበያ በመታደም ውበት፣ ፍቅርና አብሮነትን ይጎብኙ፡፡

👑💪👍

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tossa Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share