Ethio World Wide

  • Home
  • Ethio World Wide

Ethio World Wide World Wide Daily News

ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት‼️ 🗣አቶ ጌታቸው ረዳበማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸ...
25/04/2024

ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት‼️

🗣አቶ ጌታቸው ረዳ

በማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ተናግረዋል።

ብልፅግና እና ህወሓት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው " እነዚህ ንግግሮች ከውህደት ጋር የተያያዙ አይደሉም " ብለዋል።

" የቅርብ ጊዜው ንግግራችን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ ነው። ውህደት አጀንዳም ሆኖ አያውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ስላላቸው የስራ ግኝኑት በተመለከተ ፥ " ጥሩ የሥራ ግንኙነት ነው ያለን። የራሳችን የሆነ ልዩነት አለን። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉን " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት አብረን እንድንሠራ ዕድል ስለሰጠን፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችን ምንም ይሁኑ ምን አብረን እንድንሠራ አስችሎናል። ይህም ወደፊት ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ በሙሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።

" ማንም ሰው ቢሆን፤ እኔን ጨምሮ መጠየቅ አለብን። ማንም ነጻ እንዲሆን መፈቀድ የለበትም። ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " ሲሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛዉ ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማእከላዊ ኢትዮጵያ በሚገኙ ምርጫ ክልሎች ምርጫ ለማከናወን የወጣ የምር...
25/04/2024

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛዉ ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማእከላዊ ኢትዮጵያ በሚገኙ ምርጫ ክልሎች ምርጫ ለማከናወን የወጣ የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ

24/04/2024

ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አስጀመረ!!!

ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡ የዲጂታል መታወቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኩባንያችን በወር በአማካይ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ለ32 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ ዕቅዱን 36% የሚያከናውን ይሆናል፡፡ ለዚህም ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላትን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን ስራውን አስጀምሯል፡፡ በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በሌሎች ከተሞች ማስፋፊያ የሚያከናውን ይሆናል፡፡

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ ከዜጎች በሚወሰዱ ውስን የባዮሜትሪክስ እና ዲሞግራፊክ መለያ አማካይነት የተረጋገጠ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ለቀልጣፋ ለአካታች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለቢዝነስ ትስስር፣ ለኢ-ጋቨርመንት አገልግሎት፣ በዳታ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርአት ለመገንባት፣ ለቀልጣፋ ማህበራዊ አገልግሎት፣ ለተሻለ የዜጎች ህይወት እንዲሁም የሳይበር ማጭበርበርን በመከላከል አስተማማኝ የዲጂታል ሥነምህዳር ለመፍጠር የላቀ ሀገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

በተጨማሪም አዳዲስ ምርትና አገልግሎት ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮ እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስ ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነት የሚጨምሩ የማይክሮ ብድር አገልግሎቶች ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡ በሀገራችን የተማከለ ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዳታቤዝ መገንባት ለቢዝነስ እና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈጣን እና አስተማማኝ የማንነት ማረጋገጫ (authentication) በመስጠት የተሻለ አሰራርን እንዲተገብሩ የሚያስችል ነው፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጋ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላቱን፣ ምርት እና አገልግሎቱን በአጋርነት የሚያቀርቡ ፍራንቻይዝ ማዕከላቱን፣ ወኪሎቹን እንዲሁም የገነባውን ግዙፍ የዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ሰርቪስ እና የዲጂታል መሰረተልማት አስቻይ ሁኔታ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያከናወኑ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያቸውን ባሉበት ሆነው ዳታ ብቻ በማብራት በነጻ በቴሌብር ሱፐርአፕ አማካይነት በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭ አመቻችቷል፡፡

እድሜያቸው ከአምስት አመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን በኩባንያችን ይፋ በተደረጉት የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ቀበሌ መታወቂያ፣ የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወዘተ ያሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ የሚችሉ ይሆናል፡፡ ከከተማ እና ገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና የብሔራዊ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ በተለያዩ የተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና ሌሎች በሀገ

24/04/2024

ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ ‼️

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

“የመሪዎች በእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ ተቀምጦ ቃሉን ማጥናት ባለንበት ዘመን እጅግ ወሳኝ የሆነ ልምድና ውሳኔ ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ከተሰሩ የሚመሯቸው ያድጋሉ፥ ማህበረሰብም ጤና ይሆናል” ሲ...
23/04/2024

“የመሪዎች በእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ ተቀምጦ ቃሉን ማጥናት ባለንበት ዘመን እጅግ ወሳኝ የሆነ ልምድና ውሳኔ ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ከተሰሩ የሚመሯቸው ያድጋሉ፥ ማህበረሰብም ጤና ይሆናል” ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ገለጹ።

ከሚያዝያ 15 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የመሪዎች ሰሚናር የመክፈቻ ሥነሥርዓቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር የሰበክነውን እየኖርን በህይወታችን መገለጥ ስላለብን ቃሉን ሳናጓድል መፈጸም ለኢትዮጵያ ሰላምና በረከት ያደርገናል በማለት አስረድተዋል።

ይኸው ከ3 ሺ 500 በላይ ከሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የተወጣጡ የቤተ ክርስቲያንና የአገልግሎት መሪዎች በሚሳተፉበት ስብሰባ በሮሜ ምዕራፍ 14 ቁጥር 19 ላይ በመመስረት የወንጌል ተልዕኮና ሰላም በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያጠነጠነ ሰሚናር መሆኑ ታውቋል። መጋቢ ጻዲቁ አብዶ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የሰሚናሩን መጀመር ካበሰሩ በኋላ በጉባኤው ስለ እርቅ፥ ስለሰላም፥ ስለወንጌል ተልዕኮ እና ስለ አመራር ትኩረት ተሰጥቶ ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግርዋል። መጋቢ ደሳለኝ አበበ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ቦርድ ሰብሳቢም ይህ የወንጌላዊያን ህብረት እስከዛሬ ድረስ ጸንቶ የኖረው መከራ ስላላጋጠመው ሳይሆን የተጠራንበት መጠራት የተመሠረተው ጽኑ አለት በሆነው ክርስቶስ ላይ ስለሆነ ነው በማለት የህብረቱን የሃምሳ ዓመት ጉዞ አስታውሰዋል።

በስልጠናው መክፈቻ ዕለት መጋቢ ዶ/ር በድሉ ይርጋ በአሜሪካን ሀገር ዳላስ ከተማ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አማኞች ቤተ ክርስቲያን ዋና መጋቢ “መንፈሳዊ ስምሪት” በሚል ርዕስ የእግዚኦአብሔርን ቃል ያካፈሉ ሲሆን “እያንዳንዱ አማኝ ጥሪ የተሰጠው በህይወቱ ክርስቶስን እየመሰ፥ለ እንዲለወጥ ነው። መዳናችን በወስጥ ህይወት የሚከናውን ቢሆንም በወጫዊውም ህይወትም የሚታይ አዲሱን ህይወት ለብሶ መገኘት እንደሆነ አስገንዝበዋል። ለመንፈሳዊ ዕድገት ስምረት ከሚጠቅሙ መንፈሳዊ ልምምዶች ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግኑኝነትን፥ ጸጥታና ለብቻ መሆን፥ ነገርን አቅልሎ መኖርን፥ አገልጋይነትን፥ መሰዋዕትነትን፥ ወዳጅነትን፥ ወንጌል መመስከርን፥ ከጌታ መማርንና ደስታን ያካተተ ሊሆን እንደሚገባው ለመሪ አገልጋዮቹ አስረድተዋል።

ለሦስት ቀናት የሚቆየው ሰሚናር በወንጌል ስርጭት፥ በመሪነት፥ በሰላምና እርቅ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች በተለያዩ ዕውቀቱና ልምዱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚሰጥ ታውቋል።

የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️ በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክል...
23/04/2024

የካናዳ መንግሥት በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለባቸው ባላቸው የተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️

በዚህም በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው አስታውቋል።

ከኤርትራ ድንበር 10 ኪሎ ሜትር፣ ከሶማሊያና ኬኒያ የሚያዋስኑ ድንበሮች 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ ዜጎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲል የጉዞ መረጃዎችን በሚሰጥበት ድረገፅ አስፍሯል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ‼️በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የ...
23/04/2024

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ‼️

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።

23/04/2024

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ አቆሙ‼️

በሳውዲ አረቢያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በተለያዩ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

በሳውዲ አረቢያ እየታየ ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሥልጠና ማዕከላት ስራ ማቆማቸው ተጠቁሟል።

በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል ሪያድ፣ ዲሪያህ፣ ሁረይማላ ከዱርማ እና አል ቁዋይያህ ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀው ለጥንቃቄ ሲባል በአሲር፣ ናጅራን እና በሌሎች የተጎዱ አከባቢዎች የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል።

ኪንግ ካሊድ ዩኒቨርሲቲ እና ናጃራን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲሁም የቢሻ ዩኒቨርሲቲ ፋኩልቲዎች በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ የተነሳ ስራቸውን ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል በአየር ሁኔታ ዘገባው በምስራቅ እና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክልሎች በቀጣይ ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚጥል ተንብዮአል።

ከመካከለኛ እስከ ከባድ ነጎድጓዳማ ንፋስና በረዶ የታጀበ የአየር ሁኔታ በሪያድ ክልል እስከ ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ማዕከሉ ገልጿል።

በተጨማሪም ማዕከሉ በቀይ ባህር እና በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ያለው የባህር ላይ የንፋስ ፍጥነት በሰአት እስከ 50 ኪ.ሜ እንደሆነና እና በነጎድጓድ ጊዜ ከፍታው ከሁለት ሜትር ሊበልጥ እንደሚችል ማስታወቁን ገልፍ ኒዊስ ዘግቧል።


23/04/2024
የሀገራት የብድር ማዕቀፍ ማሻሻያ እና የብድር እፎይታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ****************የሀገራት የብድር ማዕቀፍ ማሻሻያ እና የብድር እፎይታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ...
20/04/2024

የሀገራት የብድር ማዕቀፍ ማሻሻያ እና የብድር እፎይታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ
****************

የሀገራት የብድር ማዕቀፍ ማሻሻያ እና የብድር እፎይታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄዷል፡፡

መድረኩ በዓለም ባንክ፣ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እንዲሁም የቡድን 20 የወቅቱ ፕሬዚዳንት በሆነችው ብራዚል የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

በመድረክ ላይ የዓለም የብድር ስርዓት ማዕቀፍ በፍጥነት መሻሻል በሚችልበት እና የብድር እፎይታ በሚሰጥበት አግባብ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ አበዳሪዎች የብድር አከፋፈል ስርዓቱን ለማሻሻል እያደረጉ ያለውን ጥረት አድንቀው የብድር አከፋፈል ማሻሻያ ማዕቀፉ እና የብድር እፎይታው ያላቸውን ጠቀሜታ መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች‼️እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው፡፡...
19/04/2024

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች‼️

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯን አለማቀፍ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው፡፡

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ...
19/04/2024

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡

የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር ሰፋን እና ኤርሚያስ መስፍን በተጋጣሚዎቻቸው መሸነፋቸውን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

18/04/2024

𝖨RАN 𝖨Ѕ ОN F𝖨RЕ! Ⅼаrɡеѕt Ѕаⅼvо of 𝖴Ѕ ТОMА𝖧А𝖶K M𝗂ѕѕ𝗂ⅼеѕ 𝖧𝗂t Аⅼⅼ 𝖧оutһ𝗂 Ѕесrеt Bаѕеѕ and 𝖶еароnѕ Сасһе.Nice

GRACIAS POR SU DIFUSIÓN OFICINA DE COMUNICACIONES, PDE
MASA/.

ክፍለ ጦሩ በሰበታ ሃዋስ ወረዳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን አሸባሪ የሸኔ ቡድን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቱን ገለፀ፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ...
17/04/2024

ክፍለ ጦሩ በሰበታ ሃዋስ ወረዳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን አሸባሪ የሸኔ ቡድን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋቱን ገለፀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አያሌው ታደሰ ወረዳው የሚሊሺያ ኃይል ባስመረቀበት ዕለት እንደተናገሩት ሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች በተፈተነች ጊዜ አጋጣሚውን በመጠቀም አሸባሪው ሸኔ ማህበረሰቡን ሲዘርፍ እና ሲያሰቃይ ነበር።

ክፍለ ጦሩ በአሸባሪው ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ አካባቢው ወደ ነበረበት ሰላም መመለሱንም ምክትል አዛዡ አረጋግጠዋል፡፡

ምክትል አዛዡ ለምረቃ የበቁ የሚሊሺያ አባላት የተገኘውን ሰላም አስጠብቀው ለመቆየት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመው ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የአካባቢው ማህበረሰብም በቀጠናው ለተመደቡ የፀጥታ ሃይሎች ተባባሪ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በሰበታ ክፍለከተማ የሰበታ ሃዋስ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው ወረዳው በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለበት በመግለፅ ለዚህ ያበቃን የመከላከያ ሠራዊቱ በመሆኑ በወረዳው ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ዘጋቢ አብራራው ፈንቴ
ፎቶ ግራፍ አብራራው ፈንቴ

17/04/2024

አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ኢራን ላይ ማዕቀብ ለመጣል ዝግጅት ጀመሩ‼️

ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኅብረት፤ እስራኤል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተሰናዱ ነው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት የለን “በሚቀጥሉት ቀናት” እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ደግሞ ኅብረቱ ማዕቅብ ለመጣል እየሠራ መሆኑን ገልጠዋል።እስራኤል አጋሮቿ የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።

የተባበሩት መንግሥታት የኢራን የሚሳዔል ፕሮግራም ላይ የጣለው ማዕቀብ ባለፈው ጥቅምት ጊዜው አብቅቷል።እኒህ ማዕቀቦች የሚጣሉት የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመግታት ነው የሚሉ ሐሳቦች ከፖለቲካ ተንታተኖች ዘንድ ይሰማሉ።አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ኢራን ላይ የተለያዩ ማዕቀቦች ከዚህ ቀደም መጣላቸው አይዘነጋም።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ሄርዚ ሀሌቪ ባለፈው ሰኞ በሰጡት አስተያየት ኢራን ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ሳያገኝ አያልፍም የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ባደረሰችበት ወቅት 300 ሚሳዔሎችና ድሮኖች ከራሷ ክልል፣ ከኢራቅ፣ ሶሪያ እና የመን አስወንጭፋለች።አብዛኛዎቹ ሚሳዔሎች እና ድሮኖች በእስራኤል እና አጋሮቿ ዒላማቸውን ሳይመቱ እንዲከሽፉ ተደርገዋል።ቴህራን እንዳለችው ጥቃቱን የሰነዘረችው እስራኤል፤ ሶሪያ በሚገኘው ቆንስላዋ ላይ ጥቃት አድርሳ 13 ሰዎችን ለገደለችበት ጥቃት አፀፋውን ለመመለስ ነው።

እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት እስካሁን ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠችም። በምትኩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢራንን ለማሽመድመድ እየሠራች ትገኛለች።እስራኤል 30 የሚሆኑ አጋር ሀገሮች የኢራን የሚሳዔል ፕሮገራም ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጠይቃለች።አልፎም እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኢስላሚክ ሪቮሎሺናሪ ጋርድ ኮር የተባለው የኢራን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኃይል ሽብርተኛ ተብሎ እንዲፈረጅ ጠይቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ቡድኑን ሽብርተኛ ብትልም ዩኬ ይህን ከማድረግ ተቆጥባለች።

ማክሰኞ ዕለት ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትር የለን “በሚቀጥሉት ቀናት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንደምንጥል ይጠበቃል” ብለዋል።ሚኒስትሯ አክለው ኢራን ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ “ምናልባት የምናየው ይሆናል” ካሉ በኋላ “ኢራንም አሁንም በግልፅ ነዳጅ እየሸጠች ነው፤ ስለዚህ ጉዳይ የምናደርገው ነገር ይኖራል” ሲሉ ማዕቀቡ ምን ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል።


የማስተር አብነት ከበደ ፋዉንዴሽን ተመሰረተ😮👏ከእናንተ ደጋግ ወገኖቼ ጋር የጀመርነው በጎ ስራ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ወደ ህጋዊ ተቋም/ፋውንዴሽን ያደገ ስለሆነ እንኳን ደስ አለን እያልኩይህን...
16/04/2024

የማስተር አብነት ከበደ ፋዉንዴሽን ተመሰረተ😮👏

ከእናንተ ደጋግ ወገኖቼ ጋር የጀመርነው በጎ ስራ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ወደ ህጋዊ ተቋም/ፋውንዴሽን ያደገ ስለሆነ እንኳን ደስ አለን እያልኩ

ይህንኑ ስራ በተደራጀ እና በተጠናከረ መልኩ ለመስራት በህጋዊ ተቋም ደረጃ የተመሠረተው ማስተር አብነት ከበደ ፋዉንዴሽን በሁሉም የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በመገኘት አቅመ ደካማና ጧሪ የሌላቸውን እናቶችና አባቶች ከጎዳና ህይወት በማንሳት በቋሚነት ድጋፍ እንዲያገኙ በጽናት ይሰራል።

ይህ ድል የሁላችንም ነዉና በሁሉም ነገር ራሳችሁን ሰጥታችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ዉድ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ ፈጣሪ ይስጥልን።

አመሠግናለሁ 🙏
ማስተር አብነት ከበደ

Top 10 African countries with the most   handsome men according to GREAT AFRICA 1)- Somalia  🇸🇴2)- Ethiopia  🇪🇹3)-Rwanda...
16/04/2024

Top 10 African countries with the most handsome men according to GREAT AFRICA

1)- Somalia 🇸🇴
2)- Ethiopia 🇪🇹
3)-Rwanda 🇷🇼
4)- Eritrea 🇪🇷
5)- Algeria 🇩🇿
6)- Nigeria 🇳🇬
7)-Morocco 🇲🇦
8)- South Africa 🇿🇦
9)-Egypt 🇾🇪
10)- Tunisia 🇹🇳

16/04/2024

Top 30 Countries with the highest Christian population in the world

1)- United States 🇺🇸
No of Christians: 230,000,000
Percentage of Christians: 71%

2)- Brazil 🇧🇷
No of Christians: 180,770,000
Percentage of Christians: 90%

3)- Mexico 🇲🇽
No of Christians: 107,780,000
Percentage of Christians: 92.4%

4)- Nigeria 🇳🇬
No of Christians: 88,400,000
Percentage of Christians: 49%

5)- Philippines 🇵🇭
No of Christians: 86,500,000
Percentage of Christians: 85%

6)-Russia 🇷🇺
No of Christians: 80,000,000
Percentage of Christians: 65%

7)- Democratic Republic of the Congo 🇨🇩
No of Christians: 63,150,000
Percentage of Christians: 92%

8)- Italy 🇮🇹
No of Christians: 53,230,000
Percentage of Christians: 83%

9)-Ethiopia 🇪🇹
No of Christians: 52,580,000
Percentage of Christians: 64%

10)- China 🇨🇳
No of Christians: 48,220,000
Percentage of Christians: 3%

11)- Germany 🇩🇪
No of Christians: 46,600,000
Percentage of Christians: 56.1%

12)- Columbia
No of Christians: 43,560,000
Percentage of Christians: 92%

13)- South Africa 🇿🇦
No of Christians: 43,090,000
Percentage of Christians: 79.8%

14)- France 🇫🇷
No of Christians: 40,000,000
Percentage of Christians: 63%

15)- Argentina 🇦🇷
No of Christians: 37,561,000
Percentage of Christians: 88%

16)- Poland 🇵🇱
No of Christians: 36,090,000
Percentage of Christians: 94.3%

17)- Ukraine 🇺🇦
No of Christians: 34,830,000
Percentage of Christians: 81.9%

18)- Kenya 🇰🇪
No of Christians: 34,774,000
Percentage of Christians: 85.1%

19)- United Kingdom 🇬🇧
No of Christians: 33,200,000
Percentage of Christians: 59.3%

20)- Spain 🇪🇸
No of Christians: 33,000,000
Percentage of Christians: 71%

21)- Tanzania 🇹🇿
No of Christians: 31,342,000
Percentage of Christians: 61.4%

22)- India 🇮🇳
No of Christians: 30,000,000
Percentage of Christians: 2.3%

23)- Uganda 🇺🇬
No of Christians: 29,943,000
Percentage of Christians: 88.6%

24)- Venezuela 🇻🇪
No of Christians: 28,340,000
Percentage of Chri

16/04/2024

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የተሰጠ መግለጫ‼️

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ የማይማረው ህወሐት ለአራተኛ ዙር በህዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል። የፌዴራልና የአማራ ክልል ክልሉ መንግስታትም በህዝብ ላይ የተቃጣውን የጥፋት ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ ህወሐት በህዝብ ትግል ተገፍትሮ ወደ ትግራይ ከተሰበሰበ በኋላ በተደጋጋሚ ወረራ በመፈፀም በህዝባችን ላይ ለጆሮ የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ ፈፅሟል። ምንም እንኳን ህወሐት በተደጋጋሚ ጊዜ በቆሰቆሰው ጦርነት የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቀጥታ የገፈቱ ቀማሽ ይሁኑ እንጅ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያ ሐገራችንን መበታተን እና የፈራረሰች ሐገር መፍጠር መሆኑን በአፈ ቀላጤው በኩል በተደጋጋሚ ተናግሯል።

ይህ የእናት ጡት ነካሽ ቡድን የሐገራችን ደጀን የሆነውን የሰሜን እዝ የመከለከያ ሰራዊት በማጥቃቱ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያጋጠመውን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ለሶስተኛ ጊዜ እየተመላለሰ ያደረገው የሐገር ማፍረስ ሙከራ ባይሳካለትም እንኳን አድፍጦ ለጦርነት ከመዘጋጀት ግን ቦዝኖ አያውቅም።

ህወሐት ከጦርነት ውጭ መኖር የማይችል፣ በጦርነት አድጎ በጦርነት ያረጀ ቡድን በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አማፂያንን ከማስታጠቅ አልፎ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመወገን ሐገራችንን የጦር ቀጠና ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ነበር የከረመው። በቀጥታ ከሚደግፋቸው የጥፋት ኃይሎች በተጨማሪ የራሱን ኃይል በማደራጀት የሰርጎ ገብ ኃይል እየላከ ህዝባችንን ሲረብሽ መክረሙ ሳያንሰው በአሁኑ ሰዓት በራያ በኩል ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ከፍቶ ይገኛል።

ኋላ ቀርነት እና ግትርናት ዋና መገለጫው የሆነው የጥፋት ቡድን የሚሊዮኖችን ህይዎት በቀጠፈውና ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር ዛሬም ለሌላ ዙር እልቂት ተዘጋጅቶ በህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በህዝቦች እኩልነት እና በብሔረሰቦች መብት ፈፅሞ የማያምነው ህወሐት እኔ የማልገዛት ኢትዮጵያ ተረጋግታ መኖር የለባትም የሚል ያልተገራ ክፉ አመሉን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በዚህም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እኩልነትን ፈፅሞ እንደማይሻ አረጋግጧል።

ለህዝባችን የሚከተሉትን መልዕክቶች እናስተላልፋለን

1. ምንም እንኳን አሸባሪው እና ተስፋፊው ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ከታሪካዊ ጠላቱ የሚሰነዘርበትን ወረራ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት እንዲመክት፣

2. ህዝባችን ከወያኔ ትጥቅ አስፈች ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ እና ከዚህ ታሪካዊ ጠላት የሚመጣን ማንኛውንም ውዥንብር ጆሮ እንዳይሰጥ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የወገን ኃይሎች ለወያኔ የሚያሳዩትን የተለሳለሰ የባንዳነት መንገድ ህዝባችን ፈፅሞ እንዳያዳምጥ እና እንዲህ ያሉትን ቡድኖች አጥብቆ እንዲታገል፣

3. የአማራ እና የአፋር ህዝብ የጦርነቱ ዋና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኃይሎች የሚፈልጉትን ሁሉ በማቅረብ ከሐገሩ ጎን እንዲቆም

4. ህዝባችን ይህን ታሪካዊ ጠላት በመቅጣት የተለመደ ጀግንነቱን እንዲወጣ ስንል ጥሪ እያቀረብን፤ በተለይ መንግስት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በዝምታ የሚመለከት ከሆነ፤ ህዝባችን ስርአትን አምኖ ችግሮች ሁሉ በህግ አግባብ ይፈታሉ የሚል ቀናኢነቱ ማታለያ ሆኖ ከዋለ፤ ይህ በራያ ብቻ የማይቆም ይልቁንም የሁሉ

አሳዛኝ ዜና - የፀሎትም ጥሪ!በጣም የምንወዳቸው የወንጌል አርበኛ የምስራቅ  ቤተክርስቲያን (Eastern Assyrian Church) አባት ናቸው ፣ ዛሬ በአገልግሎት መድረክ ላይ እያሉ ከባድ...
15/04/2024

አሳዛኝ ዜና - የፀሎትም ጥሪ!

በጣም የምንወዳቸው የወንጌል አርበኛ የምስራቅ ቤተክርስቲያን (Eastern Assyrian Church) አባት ናቸው ፣ ዛሬ በአገልግሎት መድረክ ላይ እያሉ ከባድ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

ተሽሏቸው ዳግም ያለማመቻመች የሚሰብኩትን የማዳን እና የመንግስት ወንጌል እንዲሰብኩ ሁላችንም አጥብቀን እንድንፀልይላቸው ጥሪ እናቀርባለን።

በሽብር ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በቀጠናው የሚገ...
15/04/2024

በሽብር ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2016 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰሞኑን በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በወሠደው እርምጃ በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት በማዕከላዊ ዕዝ የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አባይነህ አስማማው ተናግረዋል።

ኮሎኔል አባይነህ ሰሞኑን ክፍለ ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ማለትም በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ባሉ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የተሰማራው የክፍለ ጦሩ ሰራዊት አባላት በታጣቂው የሸኔ ቡድን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

መከላከያ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሞራልና ወኔ ተልዕኮውን እየፈጸመ እንደሚገኝ የተናገሩት ኮሎኔል አባይነህ አስማማው በግዳጅ ቀጠናችን በምስራቅ ወለጋ ዞን ጅማ አርጆ እና አገሎ እንዲሁም ጉዳያ ቢላ በተባሉ ቦታዎች በተደረገው ስምሪት በውጊያው ስምንት የሽብር ቡድን አባላት መማረካቸውንና አሥራ ሁለቱ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለሰራዊቱ የሰጡ መሆኑን ገልፀዋል።

በዘመቻው 01መትረየስ ፣08 ክላሽ እና በርከት ያሉ ተተኳሾችን ከሽብር ቡድኑ ማስቀረት መቻሉንም ገልፀዋል።

የክፍለጦሩ ሠራዊት ጥንቃቄ በተሞላበት አካሄድ የሽብር ቡድኑን ከቀጠናው ጠራርጎ የማውጣት እና በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለሚሰጡ ታጣቂዎች በአግባቡ እየተቀበለ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

ዘጋቢ ደረጀ ኤልያስ
ፎቶ ግራፍ ደረጀ ኤልያስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

15/04/2024

እስራኤል “ትክክለኛው ሰዓት ላይ” ለኢራን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እሰጣለሁ አለች‼️

እስራኤል ልክ እንደ ኢራን ሁሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎችን በመተኮስ ‘ትክክለኛው ሰዓት ላይ’ የበቀል እርምጃ እውስዳለሁ አለች።ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ከሚያባብስ እርምጃ እንዲቆጠቡ አገራት ቢያሳስቡም እስራኤል ግን ትክክል ሆኖ ሳገኘው የአጸፋ እርምጃ እውስዳለሁ ብላለች።

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ቀጥተኛ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከ300 በላይ ሚሳኤል እና ድሮኖች ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል።ከ300 በላይ የሚሆኑት ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ከኢራን፣ ኢራቅ እና ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ጉዳት ሳያደርሱ በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በወዳጆቿ አማካይነት እንዲከሽፉ ተደርገዋል።

ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በማምከን ድጋፍ ስታደርግ የነበረችው አሜሪካ እስራኤል የበቀል እርምጃ ብትወስድ ተሳታፊ አልሆንም ስትል አስታውቃለች።አምስት አባላት ያሉት የእስራኤል የጦር ካቢኔ እና የአገሪቱ ፓርላማ አባል ቤኒ ጋንትዝ ትክክለኛው ሰዓት ላይ ኢራን ለፈጸመችው ተግባር እስራኤል ዋጋ ታስከፍላታለች ብለዋል።

World 🌎 Biggest Economies
15/04/2024

World 🌎 Biggest Economies

15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ኔቫቲም ስትራቴጂያዊ መሰረት ማጥቃታቸው ተገለጸ********************የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት ቢያንስ 15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ስትራቴ...
15/04/2024

15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ኔቫቲም ስትራቴጂያዊ መሰረት ማጥቃታቸው ተገለጸ
********************

የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት ቢያንስ 15 የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ስትራቴጂያዊ አየር ማረፊያን መትተዋል።

ኢራን ቅዳሜ ለሊት በእስራኤል የሚገኘውን ኔቫቲም አየር ሰፈርን በ15 ሚሳኤሎች ኢላማ አድርጋለች ሲሉ ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን እያስነበቡ ይገኛሉ።

መህር የተሰኘው የኢራን ዜና ወኪል ጥቃቱን ተከትሎ ጣቢያው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት እና ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነ ቢገልጽም የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ግን የተተኮሱት ሚሳኤሎች በስፍራው ቀላል ጉዳት ካማድረስ ውጭ በአየር ማረፊያው ላይ የደረሰ የጎላ ጉዳት የለም ብለዋል ።

የኔቫቲም አየር ማረፊያ በኔጌቭ በረሃ ክልል ውስጥ በእስራኤል ከተያዙት ግዛቶች በስተደቡብ እና በቢየር ሸቫ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን የእስራኤል መንግስት የኤፍ-35 ተዋጊዎች ዋና ጣቢያ ነው።

ጥቃቱ የደረሰባት እስራኤል እና አጋሮቹ ከኢራን የተተኮሱ ሚሳኤሎች ቀጥር በርካታ መሆኑን በማንሳት ከ300 በላይ የሚሆኑትን ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን አደጋ ሳያደርሱ ማክሸፋቸውን አስታውቀዋል።

ቅዳሜ ለሊት ላይ ኢራን በእስራኤል ላይ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የተኮሰቻቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከሞላ ጎደል ያልተሳኩ ነበሩ ሲሉ የእስራኤል እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ገልፀዋል።

ከኢራን ግዛት የተተኮሱት ከ300 በላይ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች አብዛኛዎቹ እስራኤል ከመድረሳቸው በፊት ተጠልፈዋል ሲል ሲኤንኤን አስነብቧል።

የእስራኤል ጦር እንዳስታወቀው በኢራን የተተኮሰ "99 በመቶ" ሚሳኤሎች በእስራኤል እና በአጋሮቿ የከሸፉ ሲሆን "ጥቂት" የባለስቲክ ሚሳኤሎች ብቻ ወደ እስራኤል ደርሰው ጉዳት አድርሷል።

በአጠቃላይ 170 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ ከ30 በላይ ክሩዝ ሚሳኤሎች እና ከ120 በላይ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ኢራን በአንድ ሌሊት ወደ እስራኤል መተኮሷንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ በስልክ ተናገሩት በተባለው መልዕክት እስራኤል ግብ የሌለውን የኢራን ጥቃት መከላከል በመቻሏ ድል ነው ሲሉ መናገራቸውን አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ለሲኤንኤን ተናግረዋል ።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ሚሳኤሎቹን ለመምታት ምን አይነት መከላከያ እንደተጠቀሙበ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ከ70 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሶስት ባለስቲክ ሚሳኤሎች በአሜሪካ ባህር ሃይል መርከቦች እና ወታደራዊ አውሮፕላኖች መምከናቸውን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ በኋላ መግለጫ ያወጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ አሜሪካ እስራኤልን ከኢራን ጥቃት ለመከላከል ጥሩ ዝግጅት እንዳደረገች ገልፀዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ የእስራኤልን መከላከያ ለመደገፍ ባለፈው ሳምንት ውስጥ የአሜሪካ ጦር አውሮፕላን እና የባላስቲክ ሚሳኤል መከላከያ አውዳሚዎችን ወደ ክልሉ አንቀሳቅሳለች።

ብሪታንያም ብትሆን በክልሉ ያላትን የንጉሳውያን አየር ሃይል አውሮፕላኖችን በመጠቀም ጣልቃ ለመግባት መዘጋጀቷን ተናግራለች።

የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይም ፈረንሳይ የኢራንን ጥቃት በመከላከል ላይ ተሳታፊ መሆኗን ተናግረዋል።

በእስራኤል ላይ ከተተኮሰው የጦር መሳሪያዎች መካከል የተወሰኑት የተተኮሱት ከኢራቅ እና የመን መሆኑንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

እስራኤል ሀማስን ለመዋጋት በሚል በጋዛ የጀመረችው ጥቃትን ተከትሎ የአለም ሀገራት በጎራ ተከፍለው ሲቃወሙና ሲደግፉ ተስተውሏል ።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio World Wide posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share