Shewa Debreberhan Press

  • Home
  • Shewa Debreberhan Press

Shewa Debreberhan Press Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shewa Debreberhan Press, Media/News Company, .

01/09/2024
27/08/2024

"ትምህርት አገር ይገነባል ፤ ትውልድን ያስቀጥላል"

በእርግጥም በዘመነ ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ትምህርት የህልውና መሰረት ነው፡፡ ይህ እውነታ በዋነኝነት ዘመናችን ከተመሰረተበት የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ሥርዓት ባህሪ የሚመነጭ ነው፡፡ የአለም የኃይል አሰላለፍ የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎት፣ አስተሳሰብና ባህል በመፍጠር፤ ትምህርት መንግሥታት ለሚመኙት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና ዐብይ ሚና ይጫወታል:: በዚህ መነሻ የክልላችን መንግሥት ለትምህርት ጥራት ከፍ ያለ ትኩረት ይሰጣል። የነገ ሀገር ተረካቢዎች በትምህርት ዙሪያ ሊገነዘቧቸው ከሚገባቸው ወሳኝ እውነታዎች ውስጥ ቀዳሚው ትምህርት የዓለም ሥርዓት መቆጣጠሪያ ትልቁ መሳሪያ መሆኑን ነው።

በዚህ መነሻ የትምህርትን አስፈላጊነት እንዲህ እንቃኘዋለን:-

1. የኅብረተሰብ ዕድገት እና መሻሻል
ትምህርት የኅብረተሰብ ዕድገት እና መሻሻል ቁልፍ አካል ነው። ሰዎች ሲማሩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለህብረተሰቡ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስለሚያደርጉ የተረጋጋ እና አነቃቂ ማኅበረሰብ መፍጠር ይችላሉ።
በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የትምህርት አስፈላጊነት የሀገር ዕጣ ፈንታን ለመወሰን ትልቁ አቅም ሆኖ ያገለግላል። የአንዲት ሀገር ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በተማሩ ዜጎቿ ጥረት ነውና፡፡

2. ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት
ትምህርት በአገራት ልማት ውስጥ የጋራ ድጋፍ እና መረጋጋት ምንጭ ነው። የአንድ ሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚ ከትምህርት ጋር በቅርበት የተያያዘ ነው። በትምህርት ሥርዓቱና ዝማኔው ወደኋላ የቀረ አገር የዳበረ ኢኮኖሚ ሊገነባ አይችልም። ከተፈጥሮ ሀብት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ አቅም ቢኖረው እንኳ በተማረ የሰው ኃይል (በትምህርት በታነፀ ትውልድ) ካልተደገፈ ኢኮኖሚው ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው ሊሆን አይችልም።

3. ጥሩ ዜጎችን መፍጠር
ትምህርት በኅብረተሰቡ ውስጥ የሰለጠነ እና ትክክለኛ ስነ ምግባር ያላቸውን ሰዎች ብቁ አድርጎ ያፈራል። እነዚህ እውቀት ያላቸው ሰዎች ትክክለኛ ሀሳቦችን ይፀንሳሉ፣ መጨረሻም ለታላቅ ሕልውና ይጓዛሉ። የህግ ጥሰት ወይም የሥርዓት አልበኝነት ችግር በምንም መልኩ እውቀት ባላቸው ዜጎች ማኅበረሰብ ውስጥ አይገጥምም። በአንድ አገር ውስጥ ጤናማ የትውልድ ቅብብል ሊኖር የሚችለው ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ሥርዓት ሲፈጠር ነው።

4. የተሻሻለ ማኅበረሰብ
አሁን ባለንበት ዓለም፣ እንደ ኢትዮጵያም ሆነ እንደ አማራ ክልል በሕዝባችን ውስጥ ትምህርት ማግኘት በዙሪያችን ባሉ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ ሰፊያ የገበያ አቅም ባለው ቀጠና ውስጥ የበቃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ወሳኙ መንገድ በትምህርት ተሽሎ መገኘት ነው።

5. የበለፀገ ሕይወት መስጠት
ትምህርት ሁል ጊዜ በኅብረተሰብ ውስጥ ከፍ ያለ ነው። ምቹ የአኗኗር ዘይቤን ለማረጋገጥ ሰዎች ራሳቸውን ማስተማር እና ስኬታማ እና እርካታ ለማግኘት ጥሩ ገቢ ያለው ሥራ ለማግኘት በትምህርት የበቁ መሆን አለባቸው።
ትምህርት የተሻለ ዝና ለማግኘት፣ በጎ ተፅዕኖ ለማምጣት አቅምና ጉልበት ይሆናል፤ በፍጥነት የስኬት መሰላልን የመውጣት ዕድልን ይጨምራል። ትምህርት የበለፀገ ሕይወት ለመምራት ተመራጭ መንገድ ነው።

6. ወደ ማህበረሰቡ መመለስ
የተማሩ ሰዎች በተረጋጋ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ማኅበረሰብ ውስጥ መኖር ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ይገነዘባሉ። አካባቢያቸውን ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡንም ለማሻሻል በሚረዱ ፕሮጀክቶች ላይ የመሳተፍ ዕድላቸው ሰፊ ነው። በአካባቢያቸው ያሉ አካባቢያዊ ችግሮችን በመፍታት የመሳተፍ ዕድላቸው ሰፊ ነው። ለአንድ ግለሰብ ጥሩ ትምህርት፣ ግለሰቡን በግል፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርገዋል። ትምህርት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችንን በተሻለ መንገድ እንድንሰራ ይረዳናል።

በተለይም፦
ሀ. የሞራል እና የሥነ-ምግባር እሴቶች
አንድን ግለሰብ እንዲያስብ እና እንዲያሰላስል የሚያደርግ በመሆኑ፣ ማንኛውም ነገር አንድ እርምጃ ወደ ተሻለ ውሳኔ እንዲመራ ያደርጋል (አቅም ይፈጥራል)

ለ. የመፍጠር እና የማሰብ ችሎታዎች
ትምህርት የአንድን ሰው የፈጠራ ክህሎት ያሻሽላል። አንድ ሰው ችሎታውን በፈጠራ አቀራረቦች እንዲጠቀም እና የበለጠ ከፍ እንዲል ዕድሉን ያቀርባል፡፡ ትምህርት ያላቸው ሰዎች በደንብ ማሰብ እና ማሰብ ይችላሉ፡፡ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲያንጸባርቁ እና እንዲተነትኑ አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡

ሐ. ምቹ ኑሮ መኖር
ሁሉም ሰው ምቹ ኑሮ መኖር ይመኛል ነገር ግን ይህ እንዲሆን ሰውየው የተማረ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ዘላቂ ሀብት ምንጩ ትምህርት ነውና። አንድ ሰው የተሻለ ኑሮን ለማግኘት እና የተደላደለ ኑሮ ለመኖር የትምህርትን ጥቅም ተረድቶ መማር አለበት።

መ. በሀገራት ዜጎች መካከል እኩልነት
የየትኛውም ሀገር ዜጋ እኩል እስከተማረ ድረስ በትምህርት ዓለም እኩል ዕድል ይኖረዋል፡፡ የዓለምን ሥርዓት (world order) የመቅረፅና የመምራት አቅም የገነቡ አገራት ትልቁ መሳሪያቸው ትምህርት ነው። በየትኛውም ዓለም የተሻለ የትምህርት አቅም ያላቸው ዜጎች በየትኛውም አገር ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ ነው።

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

26/08/2024

‹‹የትምህርት ለትውልድ›› ስራችን የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ እና የችግራችንን ሰንኮፍ ከመሰረቱ የመፍቻ ቁልፍ ነው !

ትምህርት የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት ፣ የምክንያታዊነት እና ግብረ ገብነት ፤ የተወዳዳሪነት እና ተባባሪነት ፣ የችግር ፈቺነት እና መፍትሔ አፍላቂነት ብቃት ያላቸው ዜጎች መቅረጫ መሳሪያ ነው፡፡ የአዳዲስ እይታዎች ምንጭ ፣ የሁለንተናዊ ህብረተሰባዊ ለውጥና ብልፅግናም ሞተር ነው፡፡

በክልላችን ህዝብ ዘንድም ትምህርትና እውቀት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ሀገር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ካለው የአጠቃላይ ትምህርት ማሻሻያ እንቅስቃሴ ባሻገር ለኛ ክልል ደግሞ በዚህ ዓመትና በቀጣይ ጊዜያት የምንሰራቸው ስራዎች ልዩ ትርጉም የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

የትምህርት ዘመኑ ተልዕኳችንን ጥብቅና የሁላችንንም ቁጭት የተሞላ ትብብር አስፈላጊ የሚያደርጉ ምክንያቶችም አሉ፡፡
የክልላችን መንግስት የዘርፉን ችግሮች እና አቅሞች በመለየት ‘‘የትምህርት ለትውልድ’’ ንቅናቄ በማካሄድ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ማስተባበር ላይ የተመሰረቱ በርካታ ተግባራትን በክረምቱ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ባለፈው የትምህርት ዘመን በክልላችን ባጋጠመው የሰላም እጦት የተነሳ መማር ካለባቸው ህፃናትና ወጣቶች በርካቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ ያደረገ ሲሆን በርካታ ወደኋላ መላሽ ችግሮች አስተናግደናል፡፡

የዚህ የትምህር ዘመን ስራችን በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለፉንን እድሎች በቁጭት የሚያካክስ እና መሰረታዊ የሚባል ለውጥ በማድረግ ትውልዱን የሚታደግ መሆን ይኖርበታል፡፡

አሁን የተጀመረው የተማሪዎች ምዝገባንም ጨምሮ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ልዩ ትኩረታችንን እና የሁላችንን መተባበር ይፈልጋሉ፡፡ማናቸውም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትና ወጣቶችን ወደ ትምህርት ምዝገባ ከማምጣት ጀምሮ የትምህርት ተቋማትን ገፅታን በማሻሻል እንዲሁም ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ በማድረግ የህብረተሰባችን ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ አጠናክሮ እንዲቀጥል ይጠበቃል።

በትምህርት ላይ የምንሰራቸው የብቁና ንቁ፣ የምግባረ መልካምና ተወዳዳሪ ትውልድ ፈጠራ ስራችንን ማሳካት በዘላቂነት የችግሮቻችንን ሰንኮፍ ነቃይና ፀጋዎቻችን አስተባብሮ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና አሻጋሪ መሰረትን የማኖር ጉዳይም ጭምር ነው።

ያለፈው ስህተት እንዳይደገም እንማርበታለን እንጂ ተቀምጠን አንቆዝምበትም። የዛሬያችንን እድል በትብብር አሟጠን ለትውልዱ መልካም ሰርተንበት የነጋችንን መሰረት እናሳምር።

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

25/08/2024
26/06/2024
21/06/2023
21/05/2023

"ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን" በሚል መሪ ቃል በዓይነትና በይዘቱ ለየት ያለው ክልላዊ ኮንፍረንስ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተጠናቋል!

ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር)
በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ሲመክር የነበረው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ክልላዊ ኮንፍረንስ ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

የክልላዊ ኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በተለይም በውስጣዊ ችግሮቻችን ላይ ከመግባባት ባለፈ በዴሞክራሲያዊ መንገድና መርህን በተከተለ ትግል ላይ በመመስረት ችግሮቻችንን መፍታት እንዲሚገባ መተማመን ላይ መደረሱን ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ውጫዊ ጫናዎችን በቀላሉ ማለፍ የሚቻለው ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከርና ውስጣዊ ችግሮቻችንን በተገቢው መንገድ ማረም ሲቻል በመሆኑ ለዚሁ ተግባር ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

የክልሉን ህዝብ የበለጠ በማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን መስራት እንደሚገባም ኮንፍረንሱ መክሯል ያሉት ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) የህግ የበላይነት ለማስከበር፣ ሰላምን ለማስፈን፣ ሌብነትንና ብለሹ አሰራርን ለማስተካከል አመራሩ፣ አባሉና አጠቃላይ ህዝቡን በማሳተፍ መስራት እንደሚገባ መተማመን ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በጋራ ችግሮቻችንና የመፍተሔ አቅጣጫዎች ላይ አንድነትን የተላበሰና ወጥ አቋም እንዲያዝ መስራት እንደሚያስፈልግ ተሳታፊዎች በዝርዝር መክረዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የፓርቲው አመራርና አባላት እንዲሁም አጠቃላይ ህዝቡ የሚኖራቸው አንድነት የተገኙ ድሎችን የማፅናት አቅም እንደሚያላብስና በሂደት ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች መፍታትና መሻገር እንደሚያስችል ውይይት እንደተደረገበት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

በየደረጃው የገጠሙንን ችግሮች ለምፍታት በሚደረገው ጥረትም ህዝቡ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ባለቤትም ሆኖ እንደሚፈፅም የገለፁት ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) ክፍተቶቻችንን በውይይት ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ኮንፍረንሱ መምከሩን ተናግረዋል፡፡

በስምምነታችን መሰረት በቀጣይ ለክልሉ የሚመጥንና ክልሉ አገራዊ ድርሻውን በውጤታማነት እንዲፈፅም ማድረግ የሚያስችል አመራር ለመስጠት እንደሚሰራ የጠቀሱት ጋሻው አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) ኮንፍረሱ የመከረባቸውን አጀንዳዎች፣ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና የሚፈፀሙ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የስራ ስምሪት በመስጠት በድል ተጠናቋል፡፡

•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/

20/03/2023

ሁለንተናዊ ብልጽግና ያለ ጠንካራ ፓርቲ አይረጋገጥም፤
***************************************
አገር የማጽናት ከትውልድ ወደ ትውልድ የማሻገር ትልማችን ሊሳካ የሚችለው ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በጽኑ ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ በመትከል እንደሆነ አምነን ከዚህ በመነሳት የምንገኝበትን ሁኔታ በአግባቡ ተረድተን መስራት አለብን፡፡

ምንም እንኳን ከሰላም እና ጸጥታ መደፍረስ ከዜጎች መፈናቀል እና ሞት ጋር በተያያዘ ያጋጠሙን ጉድለቶች ቀላል ተደርገው የሚወሰዱ ባይሆንም በአንጻሩ አገር ወዳድ ዜጎች በመፍጠር ለዜጎች ሁለንተናዊ ክብር እና ዘላቂ ሰላም የሚተጋ መንግስታዊ መዋቅር እና ተቋማዊ ሪፎርም ለማረጋገጥ የሰራነው ስራ ከፍ ያለ ትርጉም የሚሰጠው ነው፡፡

እንደ አገርም ሆነ እንደ አማራ ክልል ስኬቶቻችን በርካታ እና ስፋት ያላቸው ቢሆኑም ያጋጠሙን በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ በፖለቲካው ውስጥ ባሉ ጽንፈኛ አመለካከት አራማጆች እየደረሰ ያለው ወከባ እና ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች የክልሉ መንግስት እና ህዝብ ሙሉ ጊዜው በልማት እና በኢኮኖሚ ግንባታው ላይ እንዳያውል እንቅፋት ሆነውበታል፤ምንም እንኳ በልማቱ እና በኢኮኖሚ ግንባታው በኩል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ቢቻልም፡፡

ይህ ደግሞ የህዝባችንን ፈተና በእጅጉ ከማወሳሰቡም በላይ እንደ አገር የምንፈልገውን የወንድማማችነት እና እህትማማችነት ስኬት ዳር እንዳይደርስ ከማድረጉም ባሻገር በአገረ መንግስቱ ቀጣይነት ላይ የህልውና ስጋት እስከመሆን ሊደርስ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ መላውን የአማራ ህዝብ ከሌሎች ክልሎች ወንድም እህቶቹ ጋር ሆኖ ዋነኛ አቅም አድርገን በመጠቀም የፅንፈኝነት አስተሳሰብን እና ተግባርን በአጭሩ መቅጨት ይገባል፡፡

ጽንፈኝነት የወለደው አገራዊ ፈተናም ቢሆን ፖለቲካው እንዳይሰክን በማድረግ በኩል ከፍተኛ አሉታዊ ጫና አሳድሯል፤እያሳደረም ይገኛል፡፡

በእርግጥ እንዲህ አይነቱ ተግዳሮት ለአገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ሁሉም አምኖ በትኩረት ከተሰራ እና የውስጠ ፓርቲ ፖለቲካዊ ጤንነታችንን በቅጡ መመልከት ከተቻለ መፍትሔ የማይመጣበት አንዳች ምክንያት የለም፡፡

ይህን ማድረግ ሲቻል የክልላችንን ብሎም የአገራችንን መጻዒ እድል በሚወስኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ያስችለናል፡፡ እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግስት የተቀመጡ አውራ አቅጣጫዎችን በኃላፊነት እና በተጠያቂነት ስሜት መያዝ እና ለተፈጻሚነታቸው መትጋት ያስችለናል፡፡

ስለሆነም የህዝባችንን ሁለንተናዊ ደህንነት እና ጥቅም አክብሮ ማስከበር ከላይ እስከታች የሚገኘው የፓርቲያችን መዋቅር ግዴታ መሆኑን በአግባቡ መረዳት ይገባል፡፡

የክልላችንን አንድነት እና የህዝባችንን ሰላም በጽኑ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ ወቅቱ የሚጠይቀውን እና አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ ሲሰራ ቆይቷል፤እየሰራም ይገኛል፡፡

ለዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ለህዝቦች አንድነት ተጠናክሮ መውጣት፣ለዜጎች ክብር እና ነጻነት እንዲሁም በህይወት የመኖር መብት መረጋገጥ እና የአካል እና የንብረት ደህንነት መከበር በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መስራት እንዳለበት በአማራ ክልል የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች መተማመን ላይ በመድረስ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

ያለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ እቅዶችን ማሳካትም ሆነ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲሁም የተቀመጡ የፓርቲ አቅጣጫዎችን ማስፈጸም እንደማይቻል በማመን ለዚህ ዘርፍ የተለየ ትኩረት አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡


"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/

09/03/2023

አማራ ክልል ምንም መሰረተ ልማት ሳንሰራ፤ አባካኝ በሆነ መንገድ ውሃ አጠጥተን፣ መስኖ ሳንገድብ እንኳ አሁን ባለን ውሃ ብቻ 1 ሚሊዮን ሄክታር ማልማት እንችላለን፤

ክቡር አቶ ግርማ የሽጥላ
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ አባል


"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/

21/02/2023

ሀሳብ ሀብት ነው፤በሀሳብ ውስጥ ሰላም፣መተሳሰብ፤መከባበር፣አንድነት፣አጋርነት እንዲሁም ብልጽግና አለ፤ይህ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡የሁሉም ነገር መነሻዎች የሰዎች ሀሳብ ነው፡፡

ሰዎች ፈጣሪ በሰጣቸው አዕምሮ ተጠቅመው መልካም ነገሮችን ማፍለቅና ማምረት ሲጀምሩ ከእነሱ አልፈው ለህዝብና ለሀገር ጠቃሚ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ይቀይራሉ፤በተቃራኒው ከፈጣሪው የተቸረውን አዕምሮ መጠቀም ያልቻለ ደግሞ ለተንኮልና ከሰውነት ዝቅ ላሉ ማንነቶችና ይዘዋቸው ለሚመጡ ድርጊቶች ይጋለጣሉ፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በመሰረታዊነት ከሚታገልባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ መሰረታዊ የሆነው ነገር ደግሞ አንዱ የሃሳብ ልዩነቶችን በመቻቻል ማስተናገድ ነው፡፡

ብልፅግና በሀሳብ ልዕልና የሚያምን ፓርቲ ስለሆነ ብቻ አይደለም ለዲሞክራሲ ትኩረት የሚሰጠው፤ይልቁንም በሀሳብ ፍጭት ውስጥ የዳበረና ለሀገር ብልጽግና የሚጠቅም ውጤት ስለሚገኝ እንዲሁም ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለመንግሥት ቁመና የሚመጥን አስተሳሰብ ማዳበር ላይ ክፍተት መኖሩን ስለሚረዳ እንጂ፡፡

በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሃሳብ ልዩነቶች ፀጋ እንጂ እክል እንዳልሆኑ ብልጽግና ፓርቲ ከልብ ይረዳል፡፡ ለመሆኑ ምን ያህሎቻችን የሃሳብ ልዩነቶችን ባለማክበራችን የተነሳ በዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ላይ መግባባት እንዳይፈጠር እንቅፋት እንደሆነ እንረዳ ይሆን?

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በሀሳብ ልዕልና ወይም በዴምክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ለማለት ቢከብድም ሁሉም ሰው የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት፣ ልማትና ዕድገት፣ብልጽግና አንድነቷ የጠነከረ ሀገር ይፈልጋል፤ነገር ግን የጋራ ሃሳብ ከሌለና ሁሉም በየግሉ የሚሮጥ ከሆነ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባት የሚኖረው አበርክቶ ቅንጣት ይሆናል፡፡


"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/

16/02/2023

ተላላፊ በሆኑ በሽታዎች ምክንያት የሚደርሰውን ሞት ለመከላከል እና ለመቀነስ እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎችን መጠን ለመቀነስ ፣ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ስርጭት እና ሞት ለመቀነስ እንዲሁም የጸረ-ኤች አይ ቪ/ኤድስ ህክምና አገልግሎት ያገኙ ሰዎች ሽፋን ለማሳደግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጦት እየሰራ ይገኛል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶውን ባስተዋወቀበት ሰነዱ በግልጽ እንዳስቀመጠው ከኤች አይ ቪ ቫይረስ በተጨማሪም ቲቢ፣የስጋ ደዌ እና ወባ በሽታዎች ስርጭትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ለህዝብ ቃል የገባ ሲሆን የክልሉ መንግስት ቃሉን በተግባር መወጣት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ አንጻር በወባ በሽታ ሳቢያ የሚደርሰውን የሞት መጠን በጥቂት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በልዩ ትኩረት እና ስምሪት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

የጤናው ዘርፍ ስኬታማ ለማድረግ የሰው ሃይል ልማት እና አስተዳደር በማሻሻል ጥራትን ማዕከል ያደረገ የጤና ባለሙያ እና ሐኪም ተደራሽነት እንዲጨምር የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተሰጠውን ስምሪት እና አቅጣጫ የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም ክልሉ በጤናው ዘርፍ ለሌሎች ክልሎች አርዓያ መሆን የሚያስችለውን አመርቂ ውጤት ለማምጣት አበክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡


•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01

27/01/2023

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ ውሳኔዎች ላይ ውይይት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል- ወጣት ተስፋሁን ተሰማ

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ "ለኢትዮጵያና አፍሪካዊ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት!" በሚል መሪ ቃል በአዳማ ከተማ መካሄዱን የጠቀሱት በአማራ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ተስፋሁን ተሰማ የጉባኤ ውሳኔዎችን በተመለከተ ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ለሚገኘው የሊግ መዋቅር ለማወያዬት የቅድመ ዝግጅት ተግባር መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን በየደረጃው ለሚገኙ የወጣቶች ሊግ አባላት ጋር በመወያየትና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ የውሳኔዎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማስቻል ከጥር 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እስከ ቀበሌ ያለው የሊግ መዋቅር ውይይት እንደሚያካሂድ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወጣት ተስፋሁን ተሰማ ተናግረዋል፡፡

የውይይት መድረኩ ጠንካራ የሊግ መዋቅር ለመፍጠር፣ ለዘላቂ ሰላምና አገራዊ አንድነት ግንባታ፣ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጎልበት ድርሻው የጎላ እንደሚሆን የገለፁት ወጣት ተስፋሁን ተሰማ በየደረጃው ያለው የሊግ መዋቅር አመራርና አባላት ለመድረኩ ግብ ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

ወጣት ተስፋሁን በመልዕክታቸው በውይይቱ በጉባኤ ውሳኔዎች ላይ በአዳዲስ ሃሳቦች ማዳበርና መተግበር ከታች እስከ ላይ ለሚገኘው የሊግ መዋቅር መጠናከር ወሳኝነቱ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ከውይይት ባሻገር በየመድረኮቹ ውሳኔዎቹ መተግበር የሚችሉብት እንዲሆን ማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነፃነት የነበራትን ጉልህ ድርሻ በዘመነ ሉላለዊነት የሚያስቀጥል ወጣት ያስፈልገናል በማለት የገለፁት ወጣት ተስፋሁን ዘር፣ ቀለም፣ ማንነትና ወሰን ሳይገድበው ለሰው ልጆች ሰላም፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት አዎንታዊ ሚና የሚጫዎት የወጣት ሊግ አደረጃጀት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት አጠናክረን እንሰራለንም ብለዋል፡፡


•~•~•
"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ ፤ ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
~~~
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም ፡-https://t.me/appamhara01

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shewa Debreberhan Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share