26/10/2020
1. 1. የክፍሉ የመጀመሪያ መልዕክት
ሙስና የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንቅፋት ነው፡፡ ሙስና የሀገራችን ልማት እንዲቀጭጭ፣ እንዲቀነስና እንዳይፋጠን በማድረግ ህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚያደርግ ማህበራዊ ችግር ነው፡፡ ሙስና በመንግስት ለልማትና ለህዝባዊ አገልግሎት የተመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዳይውል በማድረግ የተቋማት ተልዕኮ ውጤታማ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ በኮሌጃችንም ሙስናና ብልሹ አሠራርየሚከሰት ከሀነ አድሎአዊነት እንዲሰፍን፤ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት እንዲኖርና ህብረተሰቡ የሚጠብቀውን አገልግሎት በተዘረጋዉ (በወጣዉ) ስታንዳርድ መሠረት እንዳያገኝ ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይከሰቱ አስቀድሞ መከላከል ያስፈልጋል፡፡
ሙስና በማንኛውም ጊዜና አጋጣሚ ሊከሰት የሚችል ችግር በመሆኑ በኮሌጃችንን ውጤታማነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በመሆኑም በቢሯችንን ሊከሰት የሚችለውን ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ተቋማዊ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ በማዘጋጀት ችግሩን ለመቅረፍ ብርቱ ጥረት ማድረግ የግድ ይላል፡፡ የተዘጋጀውንም ተግባራዊ ማድረግጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም በቢሯችን የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች፣ሠራተኞችና ተገልጋዩ ማህበረሰብ ይህንን ስትራቴጂ በመገንዘብ ተግባራዊ በማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል ይጠበቅባቸዋል፡፡