Hano siyadii

Hano siyadii Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hano siyadii, News & Media Website, .

26/04/2024
10/04/2024

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ 1445ኛውን የዒድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

"መላው የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በወላይታ ዞን አስተዳደር ስም እንኳን አደረሳችሁ/እንኳን አብሮ አደረሰን ለማለት እፈልጋለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነትና የአብሮነት ዕሴቶቻችን ጎልተውና ደምቀው የምናከበርበት በዓል እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን ለመግለፅ እወዳለሁ።

ብዝሀነታችንን እንደፀጋ ተጠቅመን ያለ ልዩነት አንዳችን ከሌላችን ጋር የመተጋገዝ ኢትዮጵያዊ ባህላችን አብሮነትንና መቻቻልን የሚያሰፍን አርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን።

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ወር ያሳየው የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመረዳዳትና የመቻቻል ተምሳሌትነት ትምህርት የተወሰደበት ስለሆነ በሌሎች ከነቶችም ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል።

ልዩነቶቻችንን በመቻቻልና በመተሳሰብ ስናስኬድ ውበታችንና አቅማችን በመሆኑ ያለንን የመቻቻልና የመደጋገፍ ዕሴቶቻችን ቀጣይ እንዲሆኑ ትውልድን በጋራ ዕሴቶቻችን ፋይዳዎች ዙሪያ ከቤተሰብ ጀምሮ ተከታታይነት ባለው መንገድ መቅረጽና መገንባት ኃላፊነት በብቃት መወጣት ይገባናል።

በዚህም አጋጣሚ ህዝባችንን ለማስገንዘብ የምፈልገው እንደ ዞናችን የበልግ ዝናብ በሁሉም አካባቢ በተሻለ ሁኔታ እየጣለ ስለሆነ ውሃ በመያዝ እና እርጥበት ተጠቅመን ትርፍ በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሙሉ አቅም ርብርብ ማድረግ ላፍታም መዘንጋት ያለብን ስላልሆነ አንድነታችንን አጠናክረን ሠርቶ መቀየር እንደሚቻል ካሳለፍናቸው ድሎች ተምረን ቃልን በተግባር መርህ ተከትለን የበለጠ በየደረጃው ሁላችንም ተቀናጅተን የመፍጠን እና መፍጠር እሳቤን በመጠቀም መሥራት ተገቢ ይሆናል።

በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች የጀመርናቸው ኢንሸቲቮች ለአብነት የርግብ አተር፣ የእንሰት፣ የካሳቫ እና የሙዝ ልማት ሥራ በውጤታማነት በማልማት ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት አለብን።

በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንንና ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች እገዛችን እንዳይለያቸው አሳስባለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ /እንኳን አብሮ አደረሰን።"

ኢድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ሳሙኤል ፎላ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ሚያዝያ 2/2016 ዓ.ም

10/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፦ አቶ አሳምነው አይዛ
ኢድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታ ሲል የሰጠውን የዒድ በዓል መላው ሕዝበ ሙስሊም በሐሴት የሚያከብሩበት ለታላቁ የኢድ- አልፈጥር በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ኢድ አልፈጥር በዓል ሕዝበ ሙስሊሙ ወሩን ሙሉ በጾምና በስግደት፣ እንዲሁም በመልካም ተግባራት አሳልፎ ከፈጣሪ የመጨረሻውን ምንዳ የሚቀበልበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ ያሉትን መልካም ነገሮች ይዞ እርስ በእርሱ እየተጠያየቀ፣ አብሮነቱንና አንድነቱን የሚያሳይበት፣ ያለው ከሌለው የሚረዳዳበት፣ ያገኘው ካላገኘው ምግብንና ፍቅርን ተጋርቶ የሚያሳልፍበት ዕለት ነው። እነዚህ እሴቶችና የበዓሉ ትሩፋቶች ከእምነቱ ተከታዮች ባለፈ ለሌሎችም መትረፍ የሚችሉ ናቸው።

በእስልምና ዕምነት ፆም ለምዕመኑን ትዕግሥት፣ ትህትና እና መንፈሣዊ ትምህርት ይሰጠዋል ተብሎ ይታመናል። ረመዳን ለ"አላህ" ሲባል የሚፆም ፆም እንደሆነና ሙስሊሙ ምዕመን ለሠራው ኃጢያት ምህረትን የሚጠይቅበት፣ ዕለት ተዕለት ለሚሠራቸው ኃጢያቱና ከሠይጣን ፈጣሪው ይጠብቀው ዘንድ የሚፀልይበት እንዲሁም የዕምነቱ ተከታዮች ራሳቸውን ከኃጢያት የሚያነፁበት ወቅት መሆኑን የእምነቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ።

ሕዝበ ሙስሊሙ “በረመዳን የሰራቸውን መልካም ተግባራት ሁሉ ከበዓሉ በኋላም ከማሕበራዊ ሕይወታችን ጋር ተቀናጅተውና ኢስላማዊ ስብእናን አድምቀው ማሳየት ይገባቸዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በርስ በመተሳሰብ ምስኪኖች በዒድ ዕለት ከመለመን እንዲዱኑና የዕለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ለዚህም ነው ነብዩ ሙሃመድ "አንተ የምትወደውን ለሌላው ወንድምህ እስካልወደድክለት ድረስ በትክክል አላመንክም" ሲሉ ያስተማሩት።

በተሰማራንበት መስክ ወደኋላ የሚጎትቱ እንቅፋቶችን በወንድማማችነት እሴት አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለን ፈተናዎችን በፅናት መሻገር ያስፈልጋል፡፡ ብሩህ ተስፋ እና አዲስ ዘመን ከፊታችን አለ! ስለዚህ አንዳችን ለሌላችን ድርና ማግ፤ ዋልታና ማገር ሆነን ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም አለብን፡፡

በዞናችን የሚትገኙ ውድ የሙስሊም ወንድምና እህቶቼ፣ በተቀደሰው የረመዳኑ ወር ለሀገራችን ብሎም ለአከባቢያችን ጸጋና በረከት፣ ሰላምና ፍቅር እንደ ጾማችሁና እንደ ጸለያችሁ ሁሉ፥ በክብረ በዓሉም፣ ከዚያ ወዲያ ባሉት ቀናትም ለሀገራችንና ለሕዝባችን ዱዐ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በትሕትና እጠይቃለሁ።

በዚህ ጊዜ ክፋትን አርቀን መልካምነትን፣ ጠብና ጥላቻን ንቀን በምትኩ እርቅና እዝነትን በሀገራችን ብናነግሥ ምድራዊ ረድኤቶች ብቻ ሳይሆን ሰማያዊ ምንዳዎች በዝተው እንደሚጠብቁን አልጠራጠርም።

ሰሞኑን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን ወደ ልህቀት ማዕከል ለማሳደግ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ህዝቡ እያሳየ ያለው ድጋፍና አጋርነት እጅግ የሚመሰገን በመሆኑ በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ከተባበረንና ከተጋገዝን ከሰራን ታሪክ መስራት እንደሚቻል አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ዘላቂ ሠላም ሲናስብ ልማት፣ ዕድገት፣ ለውጥ፣ ብልፅግና እና ዴሞክራሲ ግንባታ ማሰብ ነዉና ሠላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክት በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የተስፋና የበረከት ዒድ እንዲሆን እመኛለሁ።

ዒድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

አሳምነው አይዛ
የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

10/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!፡- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር እንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዝበ መስሊሙ በረመዳን ወር ያዳበራቸውን መልካም ስራዎች ሁሉ ከረመዳን ውጪም የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት ለወገን አለኝታነቱን ማሳዬት ይኖርበታል።

በየጊዜው እና በየወቅቱ የሚገጥሙንን ፈተናዎችን በጥበብ ለመሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም ያስፈልጋል፡፡

በወንድማማችነት ጥላ ስር ተሰባስበን አንድነታችንን ይበልጥ የሚያጠብቁ እና የሚያደምቁ መርሃ-ግብሮችን ሃገራዊ መሠረት እና ይዘት እንዲኖራቸው የበለጠ መስራት የሚይቅበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

በክልላችን የሚትገኙ ውድ የሙስሊም ወገኖቼ፣ ከኢድ በዓል ያገኘናቸውን ዕሴቶች በሁሉም ዘርፎች እንደምንተገብራቸው እተማመናለሁ።

የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ ዒድ አልፈጥር በዓልን እርስ በርስ በመተሳሰብና በመረዳዳት የቆዬ የኢትዮጵያዊነት መገለጫን ዳግም በአደባባይ ማሳዬት ይገባቸዋል ብዬ አምናለሁ።

ከዒድ እስከ ዒድ፣ ሁላችንንም የሚመለከት የህዝብ በዓል፣ የሀገር በዓል ይሆንልናል። የዚህ በዓል በደመቀ ሁኔታ መከበር፣ የሁላችንም ድምቀት፣ የሁላችንም ክብር እንደሆነ ማወቅ ይገባናል።

በድጋሚ፣ እንኳን ለታላቁ የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ዒድ ሙባረክ!

01/04/2024

እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰባስቧል

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 21/2016 ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር የተጀመረው ድጋፍ እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል።

በገንዘብ ብር 1,674,251.82 ሲሆን ጠቅላላ የዓይነት ገቢ በብር ሲገመት 1,278,650.00 መሆኑን ታውቋል።

ጠቅላላ የገንዘብና የዓይነት ገቢ በብር 2,952,901.82 መሆኑን እናሳውቃለን።

በድጋፉ የተሳተፋችሁትን በሙሉ ምስጋና እያቀረብን የተጀመረው ድጋፍ ግቡ እስከሚሳካ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ እናቀርባለን።

Oottiidi Wolaytta Worqaa Mayzzana!

01/04/2024

ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰባስቧል

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 21/2016 ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር የተጀመረው ድጋፍ እስካሁን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል።

በገንዘብ ብር 1,780,251.82 ሲሆን ጠቅላላ የዓይነት ገቢ በብር ሲገመት 1,278,650.00 መሆኑን ታውቋል።

ጠቅላላ የገንዘብና የዓይነት ገቢ በብር 3,058,901.82 መሆኑን እናሳውቃለን።

እስካሁን በድጋፉ የተሳተፋችሁ በሙሉ ምስጋና እያቀረብን የተጀመረው ድጋፍ ግቡ እስከሚሳካ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ እናቀርባለን።

Oottiidi Wolaytta Worqaa Mayzzana!

01/04/2024

"መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ልብና መንፈስ ተሳስረን፤ ሁሉንም የምንጠቅም፣ ሁሉንም ምናገለግል፣ ሁሉን የምንወድና ለሁሉም የምንቆም መሆን ይጠበቅብናል።"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

01/04/2024

ሊቃን መደገፍና ማስተባበር ከሁላችን የሚጠብቅ የወል ኃላፊነት ነው፦ አቶ አሳምነው አይዛ

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 22/2016 ሊቃን መደገፍና ማስተባበር ከሁላችን የሚጠብቅ የወል ኃላፊነት መሆኑን የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛ አሳሰቡ።

"ሊቃን ወደ የልህቀት ማዕከል" ለማሳደግ የተጀመረው ንቅናቄ እጅግ ትልቅ ውጤት እያስገኘ ይገኛል ብለዋል አቶ አሳምነው።

ለአንድ ማህበረሰብ ዕድገትና ለውጥ ትምህርት መሠረት ነው ያሉት አቶ አሳምነው እንደሀገር በትምህርት ስርዓት ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

እንደዞን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ልዩ ትኩረት እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።

በሀገር ደረጃ ገናና ስም ያለው፣ የኩራታችን ምንጭና የምሁራን መፍለቂያ የሆነውን የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤትን "የልህቀት ማዕከል" ለማድረግ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በጥሩ ሁኔታ እንደቀጠለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ጥሪን ተቀብለው በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ የወልማ አባላት፣ ደጋፊዎች እና አጋሮች እያደረጉ ላለው ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናን አቅርበዋል።

የተጀመረውን ንቅናቄ ከግብ እስኪደርስ ድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት አቶ አሳምነው ሊቃን መደገፍና ማስተባበር ከሁላችን የሚጠብቅ የወል ኃላፊነት ነው ብለዋል።

25/03/2024

ኢትዮጵያ 4ኛ ወርቋን አገኘች🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በ10ሺ ሜትር ወንዶች ንብረት መላክ እና ገመቹ ዲዳ ተከታትለው በመግባት ኢትዮጵያን የወርቅ እና ብር ሜዳልያ አሸናፊ አድርገዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hano siyadii posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share