Haylye L Abate View's

  • Home
  • Haylye L Abate View's

Haylye L Abate View's እውቀት ፈላጊዋን ትሻለች!!! Public Health Proffesional

23/09/2021

ሙከራ አንድ ሁለት ሦስት፣

september
22/09/2021

september

የበለሳ፣ የእብናት፣ የወረታ፣ የሐሙሲት፣ የአዲስ ዘመን፣ የእንፍራዝ፣ የከምከም፣ የቆላድባ፣ የወይና፣ የጎርጎራ፣ የአምባ ጊዮርጊስ፣ የገደብጌ፣ የወቅን፣ የደባርቅ ሰው በቆላውም በደጋው ያለህ ...
16/08/2021

የበለሳ፣ የእብናት፣ የወረታ፣ የሐሙሲት፣ የአዲስ ዘመን፣ የእንፍራዝ፣ የከምከም፣ የቆላድባ፣ የወይና፣ የጎርጎራ፣ የአምባ ጊዮርጊስ፣ የገደብጌ፣ የወቅን፣ የደባርቅ ሰው በቆላውም በደጋው ያለህ በውጭም በውስጥም ያለህ ወራሪው ማዕበል በጋይንት በጥጥራ የጨበጣ ውጊያ እያደረገ ነው፣ ወንድሞችህ ከጠላት ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው እየወደቁ ነው። ድረስላቸው! ጥሪውን ባልሰማ ብታልፈው ከመሞት አትድንም ጠላት ከቤትህ መጥቶ ያርድሃል። ትመምና አንድ ላይ ሆነህ ነጻነትህን አውጅ!

የጎብጎብ፣ የነፋስ መውጫ፣ የመኳቢያ፣ የታች ጋይንት፣ የጨጨሆ ሕዝብ ጠላት ሸሽቶ እንዳያመልጥ ፈጥርቀህ ያዘው! የተሽከርካሪውን ጎማ ኢላማህ አድርግ፣ በተናጠል የሚሸሸውን ጨክንበት! ባገኘኸው ነገር በሙሉ አስቀረው!

22/07/2021

መብራት ሰሞኑን ጠፍቷል!

እርሱም ወደ ግምባር ሄደ ይሆን?

22/07/2021
21/07/2021

የአማራ ብልፅግና ተገቢውን ቦታ ለፀጥታ ኃይሉ አስረክቧል። የአብን አመራሮች በሁሉም ግምባር ተገኝተው ለሰራዊቱ ድጋፍ እያደረጉ ነው።ታዲያ አማራን እንደ ሸንኮራ አገዳ መጦ የጣለው ታምራት ላይኔ እና ያሬድ ጥበቡ በምን ሒሳብ ነው አማራን ወክለው ሚደራደሩት። እንዲያውም አማራ ከነሱ የሚያወራርደው ሒሳብ አለው!

ምርጫው ካስገነዘበን ነገሮች አንዱ የአማራ ሕዝም ከአማራ ብልፅግና እና አብን ውጭ ትኩረት እንደ ማይሰጥ ነው!እናም አማራ ከፊት በሚሰሩት እንጂ ከኋላ በሚያሴሩት የሚመራበት ጊዜ አልፏል!

21/07/2021

ደረጀ እና ሐብቴ!

ከግብርና(እርሻ)መልስ፥የምታሳየው የድካም ፊት!
20/07/2021

ከግብርና(እርሻ)መልስ፥የምታሳየው የድካም ፊት!

19/07/2021

ለእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን
ለኢድ አል አድሐ/ አረፋ/ በአል አደረሳችሁ።

ትግል ለዘልዓለም ይኑር!***ከምርጫ በኋላ ከቢሮም ከባልደረቦቼም በተወሰነ መልኩ ርቄ ነበር።ለፅሞና እና ራስን ለመገምገም።እንዴት እንደሚደብር!ያ ዳገት መውጣት ቁልቁለት መውረዱ፤የሥራ ሰዓት ...
19/07/2021

ትግል ለዘልዓለም ይኑር!
***
ከምርጫ በኋላ ከቢሮም ከባልደረቦቼም በተወሰነ መልኩ ርቄ ነበር።ለፅሞና እና ራስን ለመገምገም።እንዴት እንደሚደብር!
ያ ዳገት መውጣት ቁልቁለት መውረዱ፤የሥራ ሰዓት አጣቦ ቢሮ ተገኝቶ ከባልደረቦች ጋር መመካከሩ፣ኃሳብ መስጠት መቀበሉ፣ለጋራ መጨነቅ መጠበቡ ኑሯል->ህልውናዬ!ደስታዬ!

የምርጫ ሂደት፥ውጤት እና ከምርጫ ወዲህ የተስተዋሉ ነገሮች እሳት ዳር ተቀምጦ የሚሰሙት ምርጥ"አጭር ትግል ወለድ ድርሰት!" ይሆናል።ሁላችንም፥ሁሉም በታሪክ መዝገብ ያልፋል።የዋሸ እንደፈራ! እውነት የያዘ እንደኮራ ይዘልቃል!
በጥቅሉ ድርብርብ ድሎችን በትግላችን አስመዝግበናል!

እናም፦ለህልውናችን-ልእልናችን ስንል ትግሉን በእጥፍ አሻሽለን እንቀጥላለን።በትምህርት ጎልብተን፥በጥሪት አፍርተን፥በሕዝባዊ መሰረት ሰፍተን ትግሉን እናፋጥነዋለን። ያለፍንም ያለንም እኛው ነን።ጠላት ይዘን ወዳጅ ደስ ይበለው!

19/07/2021

ራስታ!

19/07/2021

የተፈጥሮ የጀርባ ችግር(ጉብጠት,ጥመት,ዝንፈት) ላለባቸው ታካሚዎች ከሐምሌ 16-18 2013 ዓ/ም የአሜሪካን ጅውሽ ጆይንት ዲስትሪቢውሽን ኮሚቴ (JDC-Ethiopia') አስተባባርነት በደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የነፃ ህክምና አገልግሎት ስለሚሰጥ ደ/ብርሃንና አካባቢው እንዲሁም በዞን ውስጥ ያላችሁ ሁሉ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል!!!
©ደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

18/07/2021

ሰውን በሐሳብ ማሸነፍ እንጂ"ዝም በል!" ተብሎ ዝም አይልም። "እንዲህ አይባልም!" ስለተባለም የተባለውን ሊል አይችልም።ይልቅስ እስኪ ሐሳብ አምጡ፥አዋጡ! የተሻለውን እኖስዳለን! (ወንጋራዬን፥ንሱ ተቀበሉኝ!)

ለአቅመ ፖለቲካ ከደረስኩበት ጀምሮ፤መንግስት ቀውስን እንደ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተጠቅሞበታል።ለብዙ ጊዜ!
የተለየ ኃሳብ ያላቸው አብረውት እንዲቆሙ፥በሐሳብ ያልመሰሉትን ሲያሸማቅቅ፥ከፍተኛ ሐብት ሲያሰባስብ ቆይቷል።ለምሳሌ በባለፈው ህግ ማስከበር ዘመቻ ለአማራ ልዩ ኃይል ማጠናከርያ የአዲስ አበባዋ አዳነች አበቤ 300000000 ብር ከሌሎችም በጠቅላላ 1.5 ቢሊየን ተሰብስቧል።ኦዲት የሚያደርግ አካል የለም።ጎንደር ገንዳውኃ ለተፈናቀሉ ወገትች 600000000 ሚሊየን ብር ተሰብስቦ ለተግጂዎች ደርሷል?

ስለዚህ፣የጨነቀለት መንግስት ላይ ጫና ማድረግ"እኔን ያየ ይቀጣ!"ብሎ ክፉ ስራውን እንዲረግም ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ።ሁሌ ጉር ሲል ግርር ብሎ መደገፍ መንግስት ጉርታዋን እንደ አላርም ቀጥሮ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገፋ ሊያስጮኃት ይችላል።የተለዩ ኃሳቦችን ከመርገም መነጋገር።ሐሳብ ሰጥቶ መቀበል ይሻላል።እነ ልደቱን እና ይልቃልን ለማሸማቀቅ ጥረት ያደርግ የነበር መንጋ ዛሬ ተነስቶ"ታክቲካል፥ስትራቴጂካል!"ቢል ውኃ አያነሳም!

ትህነግ የህልውና ሥጋት መሆኑን ሁሉም ይናገራል። ምክንያቱም እውነት ነው።ደግሞ ትህነግ በሩቅ ስለሆነ ፈሪውም ይህ አይከብደውም።ከዚያ ውጭ አማራ የሕልውና ሥጋት የለበትም?…ጊዜው አይደለም።የመርዝ ብልቃጡ ላይ እናተኩር።ትህነግ!…ወደዚያ ስንቀጥል የጦር መኃንዲሶችን፥ የአማራ ልዩ ኃይሎችን እና ጋዜጠኛን ማሰር ተገቢ ነው?ይህም የህልውና ትግሉ አካል ነው?ከጠላት ጋር ጦርነት ገጥሞ ወዳጅ ይታሰራል?ወይስ እኒህን ያሰራቸው እንደ ህወኃት የህልውና ሥጋቶች ናቸው ብሎ ነው?ለአማራ ሕዝብ የሕልውና ሥጋቶች አይደሉም።እናም የሕልውና ትግል እንዳታስብ አያደርግህም!
Haylye Ethiopia

18/07/2021

ባለሥልጣን ከሆንክ፣

በማናቸውም ጉዳዎች፥በማንኛውም ጊዜ ያሻህን ተናገር።ከፈፅሞ ይህን አይልም እስከ ይህን ያለው ከዚህ አንፃር ነው ይጋርዱኃል። ከለላ ይሆኑኃል።ለሚቃወሙህ ግን"ጊዜው አሁን አይደለም!"ይባላል።አንተ ከጊዜ በላይ ነህና!

17/07/2021

ኃይለ ሥላሴ፤ለተከበረው ምክር ቤታቸው!

17/07/2021

ፋኖን እያሰርክ፥የህልውና ትግል አታደርግም!!!

17/07/2021

ያረረበት ያማስላል!!!

14/07/2021

መፍትሔው የአባቶቻችን መንገድ መከተል ነው!
(ረዘም ያለ የድርጊት ማመላከቻ ፣ ከዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ)
*****

የአማራ ሕዝብ ደመኛ ጠላት የሆነው ትህነግ በወታደራዊ ድል ተሸንፎ፣ ተዋጊው ተበትኖ፣ አመራሩ ህይዎቱን ለማትረፍ ሲቅበዘበዝበት ከነበረበት ነባራዊ ሁኔታ ወጥቶ እንደገና እንዲሰባሰብ፣ ወታደር እንዲመለምልና እንዲያሰለጥን፣ በየቦታው የቀበረውን መሳሪያ አውጥቶ እንዲታጠቅና የትግሬን ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አደራጅቶ አማራን እንዲወርና እልቂት እንዲፈጽም መንገዱ ተከፍቶለት እየተግተለተለ ነው።

በዚህ ሂደት ውስጥ የአገሪቱ የፓለቲካና ወታደራዊ መሪዎች ወይም ከፍተኛ ወታደራዊና ፓለቲካዊ አመራሮች ወይ ከፍተኛ የአመራር ድክመት አሳይተው ለዚህ ሁናቴ ዳርገውናል፤ አልያም ደግሞ በታቀደና በተጠና መንገድ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ለመደለል ሲባል የፓለቲካዊ ውሳኔ ተወስኖ ወልቃይትና ራያን ለትህነግ ዳግም ቅኝ ግዛት ለመመለስ ከመጋረጃ ጀርባ ስምምነት ተፈጽሞ ሊሆን ይችላል። የፌደራል መንግስትም ሆነ የወታደራዊ፣ የጸጽታና ደህንነት ተቋማት ይሄን ጉዳይ በተመለከተ ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ መግለጫ እንኳን አልሰጡም።

የተፈፀመው የፓለቲካ ሴራም ይሁን የአመራር ድክመት ትህነግ ወደራያና ወልቃይት፣ ጠገዴ ጠለምት የሚያደርገው እንቅስቃሴ እስከ አላማጣና ማይ–ጠምሪ እስክትድረስ ድረስ የአገር መከላከያ ሰራዊት ምንም አይነት የመከላከልና መልሶ የማጥቃት ርምጃ ካለመውሰዱም በላይ በሁለቱም ግንባሮች የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ እንደተደረገ ከአካባቢው የሚወጡ ሪፓርቶች አመላክተዋል።

በዚህም ሆነ በዚያ የትህነግን ፋሽስታዊ ወረራና የትግሬን ወደ አማራ ርስቶች እያደረገ ያለውን መስፋፋት የመከላከልና የመመከት ሸክም ለጊዜውም ቢሆን በአማራ ህዝብ ላይ ወድቋል። የአማራ ክልል መንግስት «የህልውና ዘመቻ» ብሎ በሰየመው ጥሪ ሚሊሻና ልዩ ሀይሉን ያንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የሀብትና የቁሳቁስ ማሰባሰብ ዘመቻም ጀምሯል።

የአማራ የፓለቲካ ድርጅቶችም ለህዝባቸው ታሪካዊ የክተት ጥሪ አስተላልፈዋል። ስለዚህ በመላው ኢትዮጵያ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚከተሉትን የተግባር እንቅስቃሴ ያለአንዳች መዘግየትና ማመንታት መፈጸም ይገባዋል፦

1) በመጀመሪያ ወጣቱ በየአካባቢው የቀበሌና የወረዳ መስተዳድሮች እንዲያደራጁትና ወደ ሰሜን አማራ በተደራጀ መንገድ ለመዝመት አጭር ስልጠና እንዲሰጡትና እንዲያዘምቱት መጠየቅ አለበት። ስልጠናው ያለአንዳች መጓተት በአስቸኳይ በየቀበሌው መሰጠት አለበት።

የግል ትጥቅ ያለው የራሱን ትጥቅና ስንቅ አዘጋጅቶ በመያዝ መዘጋጀት፣ የግል ትጥቅ የሌለው ደግሞ ከአካባቢው መስተዳድር መጠየቅ፤ በዚህ ሂደት ትጥቅ ማግኜት ያልቻለ ደግሞ እንደ ገጀራ፣ ጩቤ፣ ሳንጃ፣ ጊሌ፣ ቆንጨራ፣ ጦርና ሌሎች የባህልና በአካባቢው የሚያገኛቸውና በቀላሉ ሊያሰራቸው የሚችሉ የነፍስ ወከፍ የጨበጣ መሳሪያዎችን አዘጋጅቶ፣ የጦር መሳሪያ ካለው ጓደኛና ወዳጅ ዘመድ ጋር ራሱን አደራጅቶ ወደ ሰሜን ለመዝመት መዘጋጀት አለበት። መሳሪያ ያለውና ለመዝመት የማይችል ግለሰብ ካለ በአካባቢው መዝመት ለሚችሉ ወጣቶች መሳሪያውን በውሰት መስጠት አለበት።

መሳሪያ የሌለው ለዘማቾች የአቅሙን ስንቅና አልባሳት አዘጋጅቶ መስጠት አለበት። የአካባቢ ጀግኖችን መሪና የጎበዝ አለቃ አድርጎ መሰየምና በየአካባቢው በየደረጃው የሚመሩ የእዝ ሰንሰለቶች ያሉት የህዝባዊ ሰራዊት/የአርበኛ ጦር ማዘጋጀትና መዘጋጀት ያስፈልጋል።

አሁን በየወረዳው ካለው ወጣት የህዝብ ቁጥር አንፃር ከእያንዳንዱ ወረዳ ቢያንስ ከ500 እስከ 1000 ወጣትና ጎልማሳ መልምሎ ማዘጋጀት ይቻላል። በትንሹ ከአማራ ክልል ብቻ ከ100 ሺ እስከ 150 ሺህ ህዝባዊ ሰራዊት መመልመል፣ የአጭር ጊዜ ወታደራዊ ስልጠና መስጠትና ለአርበኝነት ትግል ማዘጋጀት ይቻላል።

ይህን ሀይል ስልጠናውን ካጠናቀቀ በኋላ ከልዩ ሀይሉና ሚሊሻው ጋር አደራጅቶ የአማራን ህዝብ ህልውና ማስከበር ይቻላል። አዲስ አበባን ጨምሮ ከክልሉ ውጪ የሚኖረው በሚሊየን የሚቆጠር የአማራ ወጣትም በተደራጀ መንገድ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ የህልውና ትግሉ አካል ሊሆንና ሊቀላቀል ይገባል።

2) የአካባቢ መስተዳድሮች ከተለያዩ የፓለቲካና የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት ወጣቱን የመመልመል፣ የማደራጀትና በተገኘው ትጥቅና ስንቅ እንዲዘጋጅ በማድረግ በአካባቢው ከሚገኘው ማህበረሰብ ሀብት በማሰባሰብና ተሽከርካሪ በመመደብ ለግዳጅ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ስራን በተቀናጀ መንገድ መከወን ያስፈልጋል።

3) በየደረጃው ለአማራ ህዝብና ለኢትዮጵያ እየታገላችሁ ያላችሁ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በሙሉ ደግሞ ልክ የትግሬ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከገዢው ትህነግ ጋር የነበራቸውን ልዮነት ለጊዜው ወደ ጎን አድርገው አብረው እንደተሰለፉት ሁሉ ከአማራ ክልል ከገዢ ፓርቲ ጋር ያለንን ግንኙነት ወደጎን በመተው በየደረጃው ከሚገኙ የአማራ ብልጽግና አመራሮች ጋር ተባብሮ በመቆምና መላ ህዝባችን በማስተባበር ህልውናውን እንዲያስከብር ተቀናጅተን መስራትና ህዝባችን የገጠመውን የህልውና አደጋ እስኪከበር ድረስ ልዩነታችን በይደር ይዘን በትብብር ህዝባችን ለማዳን መነሳት አለብን።

የአብን አመራርና አባላት ድርጅታችን ባቀረበልን ጥሪ መሰረት ከነገ ጀምሮ ከቀበሌ፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የመንግስት መስተዳድር ሀላፊዎች ጋር በመቀናጀት ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን።

4) የዞንና የክልሉ መስተዳድሮች በተመሳሳይ መንገድ ከየቀበሌውና ከየወረዳው የተደራጀውን ሀይል ስምሪት ለመስጠት ከልዩ ሀይሉና ከሚሊሻው ጋር በደጀንነትና ጎን ለጎን ሆኖ እንዲዋጋ ለማድረግ በሚያሰችል መልኩ ማዘጋጀት፣ ህዝቡን ከጫፍ ጫፍ በአጭር ጊዜ በማነቃነቅ ህልውናውን እንዲያስከብር ማድረግ ያስፈልጋል።

5) የአማራ የሀይማኖት መሪዎች፣ ሽማግሌዎችና የተለያዪ የሲቪክ አደረጃጀቶችም ህዝቡን በመቀስቀስና በማንቀሳቀስ ነፃነቱን እንዲያስከብር የሚጠበቅባችሁን በመወጣት፣ የምትችሉም ግንባር ድረስ በመዝመት ለነፃነታችሁ ሰማዕት ለመሆን መዘጋጀት ያስፈልጋል።

6) የከተማ ከንቲባዎችና የወረዳ አስተዳደሮች ከማህበረሰቡ ለዘመቻው የሚሆን ሀብት ከማሰባሰብ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊከናወኑ የሚችሉ የሀብት ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከህዝባችን በአንድ ጊዜ በቢሊየን ብሮች የሚደርስ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደሚቻል በመገንዘብ ወደስራ መግባት አለባችሁ።

ለምሳሌ፦ 15ቱ የዞንና ሜትሮፓሊቲያን ከተሞች 50 ቦታዎች በአንድ ጊዜ መቶ ፐርሰንት ክፍያ የሚፈፀም የሊዝ ጨረታ ቢያዘጋጁና አሁን ባለው አማካይ የሊዝ ዋጋ ቢሸጡ፦ 15×50×1,500,000 ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ይችላሉ። በተመሳሳይ ከ140 አካባቢ ወረዳ ከተሞችና ንዑስ ከተሞች እያንዳንዳቸው 50 ቦታዎች በ500 ሺህ ብር ሊዝ ቢሸጥ ወደ 140*50*500,000 = 3.5 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ይቻላል። በጥቅሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወዲያውኑ ካሽ መክፈል ለሚችሉ ሰዎች ቦታውን በማስተላለፍ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል። በተጨማሪም ከክልሉ መንግስትና ከልማት ድርጅቶች ተጨማሪ በጀት ማሰባሰብ ይቻላል።

7) ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ከጦር የተቀነሱ የአማራ የጦር መኮንኖችን፣ መስመራዊ መኮንኖችንና ባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ወደ አማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ህዝባዊ ሀይል እንዲመለሱ በቀረበው ጥሪ መሰረት እያንዳንዱ የአማራ ወታደራዊ አመራርና ተመላሽ ሰራዊት የክልሉን መንግስት ጥሪ በቀናነት ተመልክቶ መመለስና ህዝባዊ ሀይሉን ወደመምራት መምጣትና ህዝባችን ከፈጽሞ ጥፋት መታደግ የሚገባን ጊዜ ላይ መድረሱን መረዳት ያስፈልጋል።

8) የአማራው ዳያስፖራ በተደራጀና እና በተቀናጀ መንገድ የፋይናንስ፣ የአድቮኬሲና የውጭ ግንኙነት ስራዎችን መስራትና የአገር ቤቱን ትግል ማገዝ ይችላል። እያንዳንዱ የአማራ ዳያስፓራ በየአካባቢው የአማራ ኮሚኒቲዎችን በመቀላቀልና በቋሚነት በወር በአማካይ $100 ማዋጣት ይችላል። 10 ሺ የአማራ ዳያስፖራ እንኳ ይህን ማድረግ ቢችል በወር 1000000 ሚሊየን ዶላር ማበርከት ይችላል። በዚህም ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ እንደ ሳታላይት ስልኮችና የህክምና ቁሳቁሶች ለታጋዩ ወገናቸው ማድረስ ይችላሉ።

9) የአማራ ባለሀብቶች ካላቸው ገንዘብ ጥቂቱን እንኳ ለህልውና ትግሉ እንዲሰጡ ማሳመንና ማግባባት ያስፈልጋል።

10) የአማራ ሴቶች የሚችሉ መዝመት፣ መዝመት የማይችሉት ደግሞ የኋላ ደጀን በመሆን ስንቅ ማዘጋጀት፣ ስንቅ በማቅረብ፣ የደከመውን በማበረታትና የቆሰለውን በማከም ከወንዶች እኩል ለህልውና ትግሉ ግዴታቸውን ለመወጣት ከአሁኑ ጀምሮ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው።

11) የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቱ በዚህ ሰአት የአማራን ህዝብ የሚከፋፍል፣ የክልሉን መሪዎች ከነድከመታቸውም ተቀብሎ ከጎናቸው ሆኖ ከማገዝና የአማራን ህልውና ለማስከበር ከመዘጋጀት በዘለለ በምንም አይነት መንገድ እጣት መቀሳሰር፣ መውቀስ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽ፣ የጎሪጥ መተያየት ወዘተ እንደማያዋጣ ተገንዝቦ፣ ተባብረን መቆም አማራጭ የሌለው መሆኑን በመረዳት በሀላፊነት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።

12) በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የተለያዩ ተቋማት ያላችሁ ፊደል የቆጠራችሁ የአማራ ልጆችም በህልውና ትግሉ በቀጥታ ከመሳተፍ በተጨማሪ እንደ ትዊተር ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም፣ እንዲሁም የአለም አቀፍ ሚዲያና ተቋማትን ያለመሰልቸት በማስረዳትና በመጎትጎት ለህዝባችን በተናበበ ዘመቻ መልክ ድምጽ የምትሆኑበት ጊዜው አሁን ነው።

13) ከፌደራል መንግስቱም ጋር ግልጽ ዘለፋና ፍጥጫ ውስጥ ከመግባትና ያማያስፈልግ መጓተት ውስጥ ከመጠለፍ ይልቅ የህልውና ትግላችን እያካሄድን ጎን ለጎን ደግሞ ፌደራል መንግስቱ አገርን ከአሸባሪዎች የመጠበቅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጫና የማድረግ ስራ እንስራ። ፌደራል መንግስቱ ይህን ማድረግ ባይችል እንኳ በአማራ ህዝብ ላይ ግልጽ ትንኮሳና ጣልቃ ገብነት እስካልተፈመ ድረስ ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር ግጭት ውስጥ ላለመግባት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ማጠቃለያ፦

የአማራ ህዝብ ስማ፣ እንደ አባቶችህ የአርበኝነት ታሪክ የምትጽፍበት የመጨረሻው ደወል ተደውሏል! አንድም አማራ ሳትቀር ተነስ፣ ለህልውናህ እስከመጨረሻው ታገል፣ ህልውናህን በክንድህ አስከብር!

አማራ በጠንካራ ክንዱ ህልውናውን ያስከብራል!

13/07/2021

ስሰማቸው ቋቅ ከሚሉኝ ቃላት"ክልላችን፥ሕዝቦች!"

13/07/2021

ለመላው የአማራ ህዝብ የቀረበ ህዝባዊ የትግል ጥሪ!

አማራ ህዝብ ከባድ ዋጋ ከፍሎ ያስወገደው የትህነግ ሀይል ዳግም እንዲያንሰራራና ህዝባችን በመስዋእትነት ያስከበረውን ማንነት በፖለቲካ አሻጥር እንዲገፈፍ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም።

በአሁኑ ሰዓት የአማራ ህዝብ አፅመ ርስት የሆኑት የኮረምና አለማጣ አካባቢዎች በትህነግ እጅ ስር እንዲወድቁ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቋም የወሰደ መንግስታዊ ክፍል ስለመኖሩ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል።

ከመነሻው ህዝባችን የፖለቲካ ቁማር ማስያዥያ እንዳይሆን በሚል ያልተቋረጠ ጥሪ ስናቀርብ ብንቆይም የተለያዩ አካላት በፈጠሩት ውዥንብርና የአመራር ክፍተት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዳግም ለህልውና አደጋ ተጋልጦ ይገኛል። ትህነግ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በርካታ ህዝብ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መፈፀሙም ታውቋል።

ስለሆነም:-
1/ መላው የአማራ ህዝብ ይህ ጉዳይ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ፣
2/ የአማራ ወጣቶች በየአካባቢያችሁ በመምከርና በመደራጀት፣ ራሳችሁን በማስታጠቅ ለሁለንተናዊ ዘመቻ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣
3/ በሁሉም አካባቢዎች ያላችሁ የአማራ ፋኖዎች በአሁኑ ሰአት ህዝባችን ያጋጠመውን የህልውና ትግል ለመቀልበስ በግንባር ለመንቀሳቀስ ፈጣን ዝግጅት እንድታደርጉ፣
4/ መላው የአማራ ህዝብ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና በተለይም በመካከላችን ሆነው ሴራና ጥቃት የሚያቀናብሩ፣ በሰርጎ ገብነት መረጃ ለጠላት የሚያቀብሉ አካላትን በንቃት በመከታተል የማክሸፍና የመቆጣጠር ስራ እንዲያከናውን፣
5/ በተለያየ የአመራር ጥፋትና ጥሰት ያላግባብ ተገፍታችሁ ከፀጥታና ከወታደራዊ አመራርነታችሁና ሙያችሁ ውጭ የተደረጋችሁ የአማራ ልጆች በሙሉ ህዝባችሁን ለመታደግ የሚደረገውን ታሪካዊ እንቅስቃሴ ለመቀላቀል ዝግጅት እንድታደርጉ፣
6/ ሂደቶችን በአስተውሎት እየተከታተልንና መረጃ እየሰበሰብን በመቆየት ነገሮች ይሻሻላሉ በማለት ብንጠብቅም ችግሮቹ በፍጥነት ሲወሳሰቡ በማየታችን ለህዝባችን ህልውና ይህንን ጥሪ ለማድረግ ተገደናል።
ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ በዚህ አግባብ በፖለቲካ ሸፍጥና በአመራር ክፍተት ምክንያት የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ለሚደረገው ሁለንተናዊ ዘመቻ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በደጀንነት ርብርብ እንዲደረግ ንቅናቄያችን ይሄን ታሪካዊ ጥሪ እያስተላለፈ፣ የህልውና ዘመቻውን በሙሉ እንዲቀላቀሉ እና እንዲያሰረተባብሩ ለሁሉም የንቅናቄያችን አባላትና አመራሮች ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

13/07/2021

ህወኃትም ሆነ ኦሮሙማው አላማቸው ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው።ያለ አማራ ብልፅግና ትብብር ግን ይህ አይሳካም። የሚተባበራቸው ጀርባውን በማከራየት እና አማራውን በማፈን ነው!…ከነቃ መታደግም ይችላል።ንቃ! ዶሮው ሦስት ጊዜ ጮኋል!

>318 000 በላይ ሰዎች የምፅፈውን እንደሚመለከቱት ስለማውቅ ሁሉንም በኃላፊነት አደርጋለሁ።ይህ ሁሉ ሐሳቤ ይዋጥለታል ማለት አይደለም።
13/07/2021

>318 000 በላይ ሰዎች የምፅፈውን እንደሚመለከቱት ስለማውቅ ሁሉንም በኃላፊነት አደርጋለሁ።ይህ ሁሉ ሐሳቤ ይዋጥለታል ማለት አይደለም።

13/07/2021

የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻ፦
***
ከፊትለፊት ሕወኃት፤ከጀርባው ክህደት ተጋርጦበታል። ተፈፅሞበታል። ነገሮችን ማሽሞንሞንም ይሁን ማጓጓን የኔ ኃላፊነት አይደለም።እውነታው ይህ ነው! እሱ ነው ሥራዬ!

13/07/2021

የአማራ ብልፅግና አመራሮች መቼ ከፍርሐት ድደን እንደሚወጡ አላውቅም።በቲዊተር"ድረሱልኝ!" ከማለት ከአማራ ፖለቲካ ኃይሎች ጋር ቁጭ ብሎ ቤት ዘግቶ መምከር ለራሳቸውም ይበጃል።ይህ ባይሆን ቀዳሚ ተጎጂዎቹ ራሳቸው ናቸው።በህሊናም በታሪክም ለብቻ ተጠያቂ ከመሆን ተጠያቂ-ተጋሪ ማብዛቱ በራሱ ምክንያታዊ ነው።አሁንም ብትመክሩ ይሻላል!

12/07/2021

አሜሪካን በሰደድ እሳት እየተቀጣች ነው፣ ኢትዮጵያን መንካት ወደዚህ ይወስዳል።ታላቁ እስክንድርም ሞክሮ አልተሳካለትም። ደርቡሽም በሉት ግብፅ፤ጣሊያንም የዚያድ ባሬ ጦርም፣ትህነግም ይኸው ተቅበዝባዥ ሁናለች።

ኦሮሙማውንም ያሳየኝ!

12/07/2021

እግዚአብሔር ተዋጊ ነው!

አንዷለም አራጌን ይቅርታ መጠየቅ ይገባኛል! ይቅርታ!
12/07/2021

አንዷለም አራጌን ይቅርታ መጠየቅ ይገባኛል! ይቅርታ!

11/07/2021

ክፉዎች የሚጠፉበትን ጊዜ እንጂ እንደሚጠፉ እናውቃለን!

Samri!

11/07/2021

+ ከቀብር መልስ +

ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?

እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው:: ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው::

ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዞአል::

ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24

ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል:: ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል:: በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም::
ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን:: ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ:: በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል:: በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል:: ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1 ቆሮ 15:42-43)

ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል:: አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው:: "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል:: የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል:: ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገር

ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ:: በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ::

እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም:: የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው:: ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው:: የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው:: የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው:: የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን:: እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን:: ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱንምና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን::

"የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 5 2013 ዓ ም
አዲሳባ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haylye L Abate View's posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share