Moges Eriso Bilate

  • Home
  • Moges Eriso Bilate

Moges Eriso Bilate information is the power

What's on your mind?
14/12/2023

What's on your mind?

25/11/2023

💢የብልጽግና_ታላቁ_ትርክት 💪💪💪
********************************
👉🅰በ2018 ይሆናል፣
👉🅱በ2023 -በኢትየዮጽያ፣
👉🆎በ2040 ይባላል(ብልጽግና-የኢትዮጵያ ከፍታ፤ሀገራችን አለም አቀፍ የብልጽግና ምሳሌ ትሆናለች)...✍

የመውጫ ፈተና ናሙና መሆኑ ነው?
22/11/2023

የመውጫ ፈተና ናሙና መሆኑ ነው?

  መሣሪያዎች አንዱ የሆነው ትምህርት ቤቶች ተዘግቷል።👉ሀዲያ ዞን ባደዋቾ✍
21/11/2023

መሣሪያዎች አንዱ የሆነው
ትምህርት ቤቶች ተዘግቷል።
👉ሀዲያ ዞን ባደዋቾ✍

20/11/2023

የብልጽግና
'ከዕዳ ወደ ምንዳ' ሥልጠና ምን ይጠበቃል?

19/11/2023

አንድ ሰዉ እራሱን አውቋል የሚባለው መቼ ነው?

13/11/2023

💢ምንዳህ ምንድነው❓
**********************
ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን❓ምንዳህ ምንድነው❓👇👇👇👇👇

የውሸት እየኖራ የእውነት የሚሞት .....
24/09/2023

የውሸት እየኖራ የእውነት የሚሞት .....

06/09/2023

አገልጋይነት ከሞራልና ከሥነ ልቦና ከፍታ ይመነጫል፤ ሀሴትንም ያጎናጽፋል !

Loading...
04/09/2023

Loading...

03/09/2023


1.አቶ ዘሪሁን እሸቱ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
2.ዶ/ር አባስ መሐመድ ኢንቨ/ኢ/ ቢሮ ኃላፊ ፣
3.ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም ፋይ/ቢሮ ኃላፊ ፣
4.አቶ ሺመልስ ዋንጎሮ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፣
5.አቶ ይረጋ ሀንዲሶ ቴክ/ሙ/ት/ት ስ/ቢሮ ኃላፊ
6.አቶ ተመስገን ካሳ ሠላመና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ፣
7.ገብሬ ጋጌ ፐብሊክ/ሰ/ሰ/ሀ/ልማት ቢሮ ኃላፊ
8.አቶ ማቲዮስ አንዮ ደን/አካ/ጥ/ ቢሮ ኃላፊ
9.አቶ ዘይኔ ብልካ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
10.አቶ ተዉፊቅ ጁሃር ሥራ/እ/ፈ/ ኢ/ል/ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ አክመል አህመዲን ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
12.ዶ/ር ባዩሽ ተስፋዬ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
13.አቶ ዳንኤል ዳምጠው ንግ/ገ/ል/ቢሮ ኃላፊ
14.አቶ ሠላሙ አማዶ ሳይን/ቴክ/ቢሮ ኃላፊ
15.አቶ ሉምባ ደምሴ ሠ/ማ/ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
16.ወ/ሮ ባይዳ ሙንዲኖ ሴቶች/ህ ቢሮ ኃላፊ
17.አቶ ዳዊት ኃይሉ ዉኃ/ማዕ ቢሮ ኃላፊ
18.አቶ ሣሙኤል መንገሻ ባህ/ቱር ቢሮ ኃላፊ
19. ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ መን/ኮሙ/ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የሥራ ጊዜ!

01/09/2023
01/09/2023

‼️
**********************************
በማዕ/ኢትዮጵያ ክልል ባደዋቾ ሀዲያ:-
➡️የሥር አመራሮች ሆነዋል‼️
✅ት/ቤቶች ታሽጓል
✅ጤና ተቋማት ተሽጓል
✅የምሁራን አፍ ታሽጓል🙊
✅የመን/ ሠራተኞች የረሃብ ስሳይ ሆነዋል
✅ሌብነትና የውሸት ሪፖርት ተጠናክሯል
✅የዜጎች ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት ቀልድ ሆነዋል
✅ሌሎች የመንግስት ተቋማት አገ/ት ተቋርጧል(except ፖሊስና ፍርድ ቤቶች)
👉የኔትወርክ ቡድን ሥር ስለሰደደ የህግ የበላይነት የግለሰቦች ቂም መበቀያ ሆነዋል።
✅የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት አቤቱታውን ባልሰማ ዝም ያለው ይሁን⁉️
✅ህዝቡ ደሞ ይግባኝ ለፈጣሪ ብለዋል።
መድረሻው በተመለከተ :-
የባደዋቾ_ሀዲያን ጉዳይ #ጠምጥመው የያዘው(ጭቆናው) በጭንቅላታችን ላይ ያሳደግነው (የኔትወርክ ቡድኑ) እንጂ የውጪ ሀይል አይደለም ። ይህ ቡድን: በመቀማት እንደ እስስት መልክ በመቀያየር አንዴ ሕዝቡን በመምሰል ሲያሻው ደግሞ አጀንዳ ቆልምመው በቅጥረኞቻቸው በኩል ሕዝብ ውስጥ በመወርወር፤ የህግ የበላይነት በሚል ሽፋን በሠላማዊ መንገድ አቤቱታ የሚያቀርቡ ምሁራንን በማሳደድና በማሠር የራሳቸውን አጀንዳ በማሣካት ከደርግ ጀምሮ ለብዙ አመታት ቆይተዋል። ፍትህ ለህዝባችን‼️

የሁሉም የሀዲያ ህዝብ በሀገሪቱ ብልጽግና ጉዞ ለሚኖረው አሻራ ትልቅ እንቅፋት ልሆን ስለሚችል ጉዳዩ ያሳስበናል።👇👇👇👇👇

29/08/2023

‼️
************************************
በማዕከ/ኢትዮ/ክልል እና የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ከመቸገራቸው የተነሳ የቤት እቃዎቻቸውን ለመሽጣት ተገደዱ።‼️👇👇👇👇👇👇
!

  ለመንግሥት ቅርበት ካላቸው አካላት  ፦✅  ላይ አንድም የኢኮኖሚ ወይም ማህበራዊ ልማት ቢሮ ለምን አልተመደበም?" ለሚለው፦በየትኛው ከተማ ምን እንደሚመደብ ሳይታወቅ መጀመሪያ የተመረጡ ከተ...
13/08/2023

ለመንግሥት ቅርበት ካላቸው አካላት ፦
✅ ላይ አንድም የኢኮኖሚ ወይም ማህበራዊ ልማት ቢሮ ለምን አልተመደበም?" ለሚለው፦
በየትኛው ከተማ ምን እንደሚመደብ ሳይታወቅ መጀመሪያ የተመረጡ ከተሞችን በማወዳደር ነጥብ ተሰጥቷቸዋል። አንደኛ የሚወጣ ከተማ የአስተዳደርና የፖለቲካ ክላስተር እንደሚሆን ተቀምጦ የነበረ በመሆኑ ሆሳዕና 1ኛ ስለወጣች የአስተዳደርና የፖለቲካ ማዕከል እንድትሆን ተመርጣለች። በመሆኑም ሆሳዕና የተመደቡ ቢሮዎች ቀድሞውኑ ከቢሮዎቹ የሥራ ባህርይ አንፃር በአስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል ላይ እንዲሆኑ ተለይተው የነበሩ ናቸው። በአስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል የኢኮኖሚ ወይም የማህበራዊ ልማት ቢሮ አምጥቶ መቀላቀል አይቻልም፤ ሁለት ወዶ የለም፤ የአስተዳደርና የፖለቲካ ማዕከል መሆን ከሌላው ቢሻል እንጂ አያንስም የሚል ነው!!
✅ ር/መስተዳድር መቀመጫ ከሆነችው ወላይታ ሶዶ አንፃር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ር/መስተዳድር መቀመጫ ለሆነችው ሆሳዕና እንዴት በቁጥር ያነሰ ቢሮ ተመደበ?" ለሚለው፦
ከክልሉ ህዝብ ብዛትና ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች የተነሳ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አጠቃላይ ቢሮዎች ብዛት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮች ቁጥር ይበልጣል። ወጪን ለመቀነስ ሲባል በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉት ቢሮዎች አንዳንዱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሙሉ በሙሉ የለም፤ አንዳንዶቹ ደግሞ አንድ ላይ የተጣመረ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከቢሮ ወደ ኮሚሽን፣ ኢንስቲትዩት ወዘተ ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል።
ለምሳሌ፦
የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አለ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የለም።
ኢንዱስትሪ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አለ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ተብሎ merged ነው።
ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አለ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል፣ ቱሪዝም እና ወጣቶችና ስፖርት ተብሎ አንድ ላይ የተጣመረ ሆኗል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አለ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግን ወደ ኢንስቲትዩት ዝቅ ተደርጓል።
ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አለ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግን ወደ ኮሚሽን ዝቅ ተደርጓል።
ሌላው የወላይታ ዞን ህዝብ ብዛት ከሀዲያ ዞን ስለሚበልጥ ይህም በድልድሉ ወቅት ታሳቢ የተደረገ በመሆኑ ለሆሳዕና ከተማ የተደለደለው የቢሮ ብዛት ከወላይታ ሶዶ ከተማ ሊያንስ ችሏል፤ የሆሳዕና ብቻ ሳይሆን የዲላ ከዱራሜው፣ የጂንካ ከወራቤው የሚበልጠው በነዚህ ምክንያቶች ነው የሚል ነው።
✅ ? ለሚባለው፦
ከአንድ ዞን ክልሉ ሁለት ማዕከል መርጦ ሳይሆን ከዞኑ ፖለቲካና ነባራዊ ሁኔታዎች የተነሳ ዞኑን ሰላማዊ ለማድረግ ለጉራጌ ዞን የሚደርሰው ድርሻ ለሁለት ተከፍሎ በወልቂጤ እና በቡታጅራ ከተሞች እንዲደለደል ዞኑ በጠየቀው መሠረት የተሰራ ነው፤ የቢሮዎቹ ብዛትም ከዞኑ ህዝብ ብዛት አንፃር ነው የሚል ነው።
✅ ?" ለሚባለው
ግብርና አንድ ቢሮ ቢባልም በጣም ከፍተኛ ሀብት የሚመደብባቸው ተጠሪ ተቋማትን የያዘ ነው። ለምሳሌ የመስኖ ልማትና ተቋማት አስተዳደር ብቻውን እንኳን ከአንዳንድ 3 ወይም 4 ቢሮዎች የሚበልጥ ሀብት የሚመደብለት ነው።
በተመሳሳይ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የአደጋ መከላከልና ኮሚሽን የመሳሰሉ ተቋማትም ብዙ ሀብት የሚይዙ ተቋማት ናቸው።
በተጨማሪም ዱራሜ የተመደቡት እንደ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ፣ ደን ልማትና አከባቢ ጥበቃ፣ የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥርና ኳራንታይን ባለስልጣን፣ ምርጥ ዘር ድርጅት እና የአከባቢ ጥበቃ ቁጥጥር ባለስልጣን የመሳሰሉ ተቋማትም ብዙ ሠራተኛ የሚይዙና ለከተማውና ለአካባቢው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚችሉ ናቸው።
በመሆኑም ግብርናና ተጠሪ ተቋማትን እና እያንዳንዳቸው የሚያንቀሳቅሱትን ሀብትና የሠራተኞቻቸው ብዛት ስታይ ከዞኑ ህዝብ ብዛት አንፃር ዱራሜ የተመደበው ከሌላው ያነሰ አይደለም የሚል ነው።
✅ የተመደበው ቢሮ ያንሳል ለተባለው፦
የህዝብ ብዛት ስታይ ለምሳሌ የጉራጌ ዞን ከሀላባ ዞን 7 ጊዜ ይበልጣል። ይህ በቢሮዎች ድልድልም ከፍተኛ ልዩነት አምጥቷል የሚል ነው።
በአጠቃላይ አገልግሎትን በቅርበት ከማግኘት በተጨማሪ ቢሮዎቹ የሚገኙባቸው ከተሞች በዋናነት የሚጠቀሙት ከቢሮዎቹ ሠራተኞችና ተገልጋዮች ገሚገኝ ገቢ ሲሆን የቢሮዎቹ ፕሮጄክቶችና ሀብቶች ግን ለርዕሰ መስተዳድር ቀርበው በክልሉ ም/ቤት እየፀደቁ ለሁሉም የክልሉ ህዝብ እኩል የሚያገለግል ናቸው የሚል ነው።
===========================
ይሄ የኛ አቋም ሳይሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ለመንግሥት አካላት ቅርበት ካላቸው ሰዎች በኩል የተሰጠ ምላሽ ነው። በበኩሌ አምኜ የተቀበልኩትም አለ፤ ያልተቀበልኩትም አለ። ማብራሪያውን እንዴት አያችሁት? ምክንያታዊ ሆነን ማየት ነው። (Via Dr.Dembelo T) ?

13/08/2023

የሰብአዊ መብት መከበር ትልቅ መንግስት ያስፈልገዋል ?

13/08/2023

of Human Rights
ክብር, ነፃነት, እኩልነት እና ወንድማማችነት

08/08/2023

Mati mati woshi macceessiminnami shigiggaa'oolla.

05/08/2023

የመንግስት ሠራተኞች #ደመወዝ ነው እንዴ ሁልጊዜ በልመና የሚከፈለው❓
(Badawacho Hadiya)

03/08/2023

Haatto'aare liirrammaa
Hanaqqalitto'aarre mugummo.
Kasheemmaatta mahi wixxaa'immahe❓

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ🇪🇹የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፷፬🅰 #አንቀፅ፱(፪)_የደመወዝ_ክፍያ_በሚለው_ርዕስየማንኛው...
24/04/2023

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ
🇪🇹የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፷፬
🅰 #አንቀፅ፱(፪)_የደመወዝ_ክፍያ_በሚለው_ርዕስ
የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣
✅ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ ሲገልጽ፣
✅ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
✅ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት፣
ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም፡፡
🅱
✅ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ለሥራው ማከናወኛ
በተሰጡት መሣሪያዎችና መገልገያዎች ላይ በሚደርስ
ጉዳት ወይም ጥፋት በዕዳ ተጠያቂ የሚሆነው ጉዳቱ
ወይም ጥፋቱ በሠራተኛው ቸልተኝነት ወይም ሆነ ተብሎ
በተፈፀመ ድርጊት ምክንያት የደረሰ እንደሆነ ነው፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
"የደመወዝ ብድር ዕዳ" እንደተጠበቀ ሆነው፤
በተመለከታ:-
የመን/ሠራተኞች በፍ/ቤት ባልተወሰነበት የወር ደመወዝ ልያዝ/ልቆረጥ የሚችልበት ህግ/መመሪያ/አዋጅ ያለ አይመስለኝም።

ምናልባት ውስን የመን/ሠራተኛ
1⃣ ፣
2⃣ ፣
3⃣ ፣
4⃣ እና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ከየአስተዳደር እርከኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሚመለከታቸው አካላት ወጪ አድርገው ያልከፈሉ እንደሆነ መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት በእዳ ተጠይቀው የመክፈል ግዴታ መኖሩ አያጠራጥርም። ምክንያቱም የትኛውም ተቋም ስቋቋም እውቅና ተሰጥቶት ወደ ስራ ሲገባ ተቋማዊ መተዳደሪያ መመሪያ/አዋጅ መሠረት የወጪ፣ገቢና ሚዛን(Balance) ሰነድ ይኖረዋል።
ከላይ የተገለፀው በክልል ደረጃ ያሉ (ኦሞ.ማ.ፋ፣ኅ.ሥራ..፣የመን.ፋ.ኢ.ል)ተቋማትን ላያካትት ይችል ይሁን?

ሠላምና ሀገርን በጋራ እንጠብቅ! እንንከባከባቸው!

የብልጽግና ጉዞ በደቡብ ክልል ወዴት ይጠቁም ይሆን❓የክልሉ መንግስት ለሚታዩ ልማቶች እንደሚወደስ ሁሉ ለሚከሰት ቀውስም መፍትሄ በማፈላለግ ሚናው የጎላ ሊሆን ይገባል።  መንግስት ተግባራዊ እያ...
18/04/2023

የብልጽግና ጉዞ በደቡብ ክልል ወዴት ይጠቁም ይሆን❓
የክልሉ መንግስት ለሚታዩ ልማቶች እንደሚወደስ ሁሉ ለሚከሰት ቀውስም መፍትሄ በማፈላለግ ሚናው የጎላ ሊሆን ይገባል።

መንግስት ተግባራዊ እያደረገ ካለው በርካታ የሪፎርም ስራዎች አንዱ የሆነው “መዋቅራዊ አደረጃጀትና አመራር ቦታዎች ምደባ" የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት ብቻ መሆን እንዳለበት ይታመናል፡፡ ነገር ግን

እንደ ዞናችን ወደታችም ወደላይም የተዘረጋ የኔትወርክ ቡድኑ በአዲሱ የክልል አደረጃጀቶች የተሻላ ቦታወችን እያማተረ መቆያቱ ጉድለት ነው ባይባልም የህዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች አፍኖ ከማቆየት ይልቅ Proactive ሆነው ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ከመፍታት ረገድም ኃላፊነት እንዳለው ግልጽ ነው።
ጎልተው ከሚታዩ ኢ-ፍትሐዊነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለአብነት:- የመንግስት ሠራተኞች ከ፪-፫ወራት የወር ደመወዝ ካለመከፈሉም በላይ ሰሚ ያጣው ህዝብ በሚያዝያ 10/2015ዓ/ም የፌደራል መንግስት እንዲደርስ ከአ/አበባአርባ ምንጭ የፌደራል መንገድ በመዝጋት ቅሬታቸውን አሰምቷል። ✍

  @ሀድያከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢ-ፍትሐዊነትናየመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ የሚያቀርቡ ምሁራንን ማሰርና ማስፈራራት ከወንጀል የማይቆጠርበት ሁኔታዎች ሆነዉ እየተመለከትን ነው...
15/04/2023

@ሀድያ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢ-ፍትሐዊነትናየመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ የሚያቀርቡ ምሁራንን ማሰርና ማስፈራራት ከወንጀል የማይቆጠርበት ሁኔታዎች ሆነዉ እየተመለከትን ነው።
ምሁራን ቅሬታዎችን በሠላማዊ መንገድ መጠየቅ ምንድነው ስህተቱ? ይህን እኩይ ተግባር የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ አካላት ውስጥ አንዳንድ የመንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት ጭምር ተሳታፊ እየሆኑ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ሆኗል። እነዚህ የኔትወርክ ሃይሎች ለማንም የሚበጁ አይደሉም። ህዝብን እርስ በርስ የሚያጫርሱ በመሆናቸው ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ የማድረግ ጥረት የፌዴራል መንግስት ስራ ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ዲሞክራሲና ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ ስኬት የሚመዘገበው የመንግስት ጥረት በህዝብ ተሳትፎ ሲታጀብ ብቻ በመሆኑ ሁሉም ሠላም ወዳድ ዜጋ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ በህዝብና መንግስት መካከል የግምብ አጥር ሆነዉ ለህዝባችን እንቅፋት የሆኑ አካላትን ትግል ማድረግ በቀጣይ ጊዜያትም ቁርጠኝነትና የጋራ ትብብር እንደሚያስፈል የህዝብ ዓይንና ጆሮ ታዝቧል::
❤መልካም የትንሳኤ በዓል!

10/11/2022

🙊አዋላጅና አዋቂ
ያየውንና የታዘበውን
#ሁሉ አይናገርም
ብዬ እንጂ...✍

ከደራሲያን አለም
31/08/2022

ከደራሲያን አለም

Praise be to the God and Father of our Lord Jesus Christ! In his great mercy he has given us new birth into a living hop...
23/04/2022

Praise be to the God and Father of our Lord Jesus Christ! In his great mercy he has given us new birth into a living hope through the resurrection of Jesus Christ from the dead,
(1 Peter 1:3). Happy Easter!

02/04/2022
18/03/2022

ጨለማን የሚገፈው ብርሀን ነው፡፡ ድካምን የሚያቀለው እረፍት ነው፡፡ ጥላቻን የሚያስወግደው ፍቅር ነው፡፡ ቂምንና ቁርሾን ማስወገድ የሚቻለው በይቅር ባይነት ነው፡፡

ግጭትን መፍታትም የሚቻለው በሰላም ነው፡፡ ከዚህ ውጭ የሚሆን ነገር የለም፡፡ አለመግባባት ወይም የማይታረቅ ተቃርኖ የሚፈታው ላለመግባባት ወይም ቋሚ ለሆነው ተቃርኖ መነሻ የሆነውን ቋጠሮ በውይይትና በቅን ልቦና ተነጋግሮ መቋጫ ማበጀት ሲቻል ነው፡፡

የለውጥ እይታ ሁልጊዜም የሚከተለው ተቃራኒ መንገድ ነው፡፡ የችግሩን ተቃራኒ ገፅታ ሳይመለከቱ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ የድህነት ተቃራኒ ገፅታ ብልፅግና ነው፡፡ በድህነት ምህዋር ላይ በመሽከርከር ድህነትን መቅረፍም ማስወገድም አይቻልም።

ድህነትን ለማሸነፍ መጀመሪያ በድህነት ላይ የመረረ አቋም መያዝ ያስፈልጋል። አንድን ነገር ስለጠላነው ብቻ አይወገድም፡፡

ያንኑ የጠላነውን ነገር ለመለወጥ ተኪ አመለካከት መገንባትና ለያዝነው ተኪ አመለካከት ተግባራዊ መሆን አቅደን መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ለውጥ የብዙ እይታና ድካም ውጤት ነው፡፡ በፍላጎት ብቻ የሚረጋገጥ ለውጥ የለም፡፡

ጨለማ የሚገፈፈው በብርሃን ነው ስንል ሰው ብርሀንን ለመውለድ ደጋግሞ ማርገዝ፣ ደጋግሞ ማማጥ፣ ደጋግሞ መውለድ፣ ደጋግሞ ማሳደግና ለፍሬ ማብቃት ይጠይቃል፡፡ የቶማስ ኤድሰን የብርሃን መሻት ጉዞ በአንድ ለሊት የተገኘ ውጤት አይደለም፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ውስጥ የምትገኝ አገር ናት፡፡

ድህረ ኢህአዴግ የተጀመረው አገራዊ ለውጥ በፈታኝ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈ ያለ የለውጥ ጉዞ ይሁን እንጂ በርካታ አመርቂ ውጤቶች የተመዘገበበት መሆኑ አይካድም፡፡

እንደ አገር የተጫነንን ሰው ሰራሽ ጨለማ ለመግፈፍ ደጋግመን የመሞከራችንን ያህል ሳንታክት ጨለማው እስኪገፈፍ ድረስ ጥረት የምናደርግ ከሆነ ያለምንም ጥርጥር ጨለማውን ማሸነፍ እንችላለን፡፡ በተጨባጭም እየሆነ ያለው ይኸው ነው፡፡

10/03/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Moges Eriso Bilate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Moges Eriso Bilate:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share