Ethiopian News

  • Home
  • Ethiopian News

Ethiopian News political,economical and social issues more analysis in this page please like and follows!

25/03/2022
“በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ነው።“:-የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድ...
14/02/2022

“በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ነው።“:-የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

በዋናነት ለጥቃቱ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አንዱ የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን አገር ዉስጥ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እና ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት እንዲያንቀሳቅሱ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም አንዱ የፌስቡክ ኤዲተር የተላከለትን አጥፊ ተልዕኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የተጨማሪ 3 ሰዎች ሕይወት አለፈ***********************ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 187 የላብራቶሪ...
10/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የተጨማሪ 3 ሰዎች ሕይወት አለፈ
***********************

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 187 የላብራቶሪ ምርመራ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 506 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 93 ወንድ እና 77 ሴቶች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ዕድሜያቸውም ከ2 እስከ 115 ዓመት መሆኑን አስታውቋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በቦታ ሲለዩ፣

* ከአዲስ አበባ - 81 ሰዎች
* ከሶማሊ ክልል - 57 ሰዎች
* ከአማራ ክልል - 13 ሰዎች
* ከትግራይ ክልል - 7 ሰዎች
* ከኦሮሚያ ክልል - 7 ሰዎች
* ከሐረሪ ክልል - 3 ሰዎች እና
* ከደቡብ ክልል - 2 ሰዎች ናቸው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሦስት ኢትዮጵያውያን ሕይወት ማለፉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች፦

የ115 እና የ84 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና አንድ የ35 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ናቸው።

በኢትዮጵያ እስካሁን ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል።

ሕይወታቸው ያለፈው ሦስቱም ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 22 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 401 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,599 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር  2,336  ደ...
09/06/2020

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,599 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,336 ደርሷል። ተጨማሪ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 135 ወንድ እና 55 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 89 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉ። ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 153 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አስራ ስምንት (18) ሰዎች (11 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሱማሌ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 379 ደርሷል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ5 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሁለት (32) ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል ህክምና ላይ የነበረች።

2. የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤በህክምና ማዕከል ህክምና ላይ የነበረች።

3. የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

4. የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

5. የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ።

አሜሪካ በሁለት ወራት ውስጥ ዝቅተኛ የተባለውን የሞት ቁጥር መዘገበች↘️ በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 450 ሞት የመዘገበች ሲሆን ይህ ቁጥር በሁለት ወራት ጊዜ...
09/06/2020

አሜሪካ በሁለት ወራት ውስጥ ዝቅተኛ የተባለውን የሞት ቁጥር መዘገበች

↘️ በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 450 ሞት የመዘገበች ሲሆን ይህ ቁጥር በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው ተብሏል፡፡

↘️ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት ግንባር ቀደም በሆነችው አሜሪካ፤ እስካሁን 110ሺህ 990 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን 2 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

✅ BBC

09/06/2020

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች
• ጉለሌ - 10 ሰዎች
• ቦሌ - 42 ሰዎች
• ልደታ - 5 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 13 ሰዎች
• የካ - 5 ሰዎች
• ቂርቆስ - 9 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች
• አራዳ - 5 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 2 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,625 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 428 ሰዎች
• ጉለሌ - 211 ሰዎች
• ቦሌ - 202 ሰዎች
• ልደታ - 201 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 154 ሰዎች
• የካ - 90 ሰዎች
• ቂርቆስ - 76 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 72 ሰዎች
• አራዳ - 69 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 50 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 72 ሰዎች

#ሀረሪ

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰኣት ውስጥ የተደረገው 48 የላቦራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አሰራ ሰባት (17) ደርሷል፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች ተጋላጭነት ሁኔታ የታወቀ ንክኪ ያላቸው ሲሆን የ54 አመት ሴት የሀኪም ወራዳ ነዋሪ እና የ25 ወንድ ሲሆኑ የሽንኮር ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡

#ደቡብ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 476 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።

በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሀዋሳ ነዋሪ ነው። ግለሰቡ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠው ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) እንዳለው የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

#ትግራይ

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሰባ ዘጠኝ (79) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 207 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከሰባቱ (7) መካከል ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ ሶስቱ (3) ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው እንዲሁም የተቀሩት ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።



ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 519 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ።

ታማሚ 2 - የ10 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ።

ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ።

ታማሚ 4 - የ12 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ።

ታማሚ 5 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ቤኬ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም ፤ በለይቶ ማቆያ የሚገኝ።

ታማሚ 6 - የ3 ዓመት ህፃን ኢትዮጵያዊ የጉጂ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 7 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጉጂ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 8 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 9 - የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪ (ምርመራው የተደረገው ነቀምቴ ላብራቶሪ ነው)

136 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,775 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይ...
08/06/2020

136 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,775 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,156 ደርሷል።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ወንድ እና 51 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 97 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 124 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 12 የውጭ ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 115 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እና 1 ሰው ከደቡብ ክልል ናቸው።

በተጨማሪም በትላንትናው ዕለት አስራ ሰባት (17) ሰዎች (8 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከአማራ ክልል፣ 2 ከአፋር ክልል እና 2 ከቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 361 ደርሷል።

ሁለት አዳዲስ የቅሪተ አካል ዝርያዎች በኢትዮጵያ ተገኙ4.8 እስከ 4.3 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠሩ ሁለት አዳዲስ የቅሪተ አካል ዝርያዎች በኢትዮጵያ አፋር ክልል ጎና በተባለ ሥፍራ ተገኝተዋል።...
04/06/2020

ሁለት አዳዲስ የቅሪተ አካል ዝርያዎች በኢትዮጵያ ተገኙ

4.8 እስከ 4.3 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠሩ ሁለት አዳዲስ የቅሪተ አካል ዝርያዎች በኢትዮጵያ አፋር ክልል ጎና በተባለ ሥፍራ ተገኝተዋል። ከጎና እና ከመካከለኛው አዋሽ ብቻ የሚታወቁት ሁለቱ አዳዲስ ዝርያዎች በኢትዮጵያ መገኘታቸውን ከሳይንስ ኤክስ ኤ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

ጎና በአፍሪካ ከሚገኙት ፓሊዎ አንትሮፖሎጂካል ቦታዎች መካከል አንዱ ሲሆን አርዲ-ፒቲከስ ራሚደስ በመባል የሚታወቁት የሆሚኒድ ዝርያዎች ተገኝተውበታል። የቅሪተ አካሉ ግኝቶች ከጎና በስተደቡብ በሚገኘው መካከለኛው አዋሽ ጥናት አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለዩትን የአርዲፒቲከስ ራሚደስ ዝርያዎች የሚመስል የላይኛው መንጋጋ ፣ መንጋጭላ እና ከራስ ቅል ውጪ የሚገኙ አጥንቶች (postcrania) ያካተተ መሆኑን ተገልፅዋል።

እነዚህ ቅሪተ አካላት ስለ ጦጣዎች ባዮሎጂያዊ ለውጥ ጠቃሚ መረጃ ከማቅረባቸው በተጨማሪ አርዲፒቲከስ ራሚደስ ስለሚኖርበት ጥንታዊ አካባቢ ወሳኝ መረጃ ይሰጣሉ ። እነዚህ ቅሪተ አካላት በብዛት የሚገኙት ቦታ ሲታይ አርዲፒቲከስ ራሚደስ የኖረበት በደን የተሸፈነ መኖሪያ ከነበረው የመካከለኛው አዋሽ የተለየ ሆኖ ተገኝቷል ።

አርዲ ፒቲከስ ራሚደስ በምሥራቅ አፍሪካ በሁለት እግሮች ከሚሄድ የሆሚኒድ ዝርያዎች መካከል አንዱ ነው።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪ አንድ ሰው ህይወት አልፏል።ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150)...
04/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪ አንድ ሰው ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 56 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 147 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሶስቱ (3) የውጭ ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 123 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 13 ሰዎች ከአማራ ክልል እና 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው 4 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 250 ደርሰዋል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 18 ደረሰ!

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት የነበረ ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበትና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላትናው ዕለት ህይወቱ አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል።

የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ። 🇪🇹👉የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን  እንዳሉት ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉ 1 ሺህ ...
02/06/2020

የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ። 🇪🇹

👉የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን እንዳሉት ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉ 1 ሺህ 200 ታማሚዎችን መያዝ እንዲችል ተደርጎ ተደራጅቷል።

👉ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።

👉ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።

👉በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።

👉በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠናም ተሰጥቷል።

👉በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ሐሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል ለኢዜአ ተናግረዋል።

👉በማዕከሉ ሕሙማን አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ፤ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሠራተኞችም ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ትኩረት መሰጠቱንም አክለዋል።

👉በተለይም የአየር ሥርዓት ፍሰቱን ለማስተካከል የሚረዱ መሣሪያዎች መገጠማቸው ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል።

👉ከማዕከሉ የሚወገዱ ፍሳሾች ለብቻ እንደሚወገዱና ደረቅ ቆሻሻዎችም በዘመናዊ መሣሪያ በመታገዝ የሚወገዱ መሆኑንም ዶክተር እስማኤል ተናግረዋል።

👉በማኅበረሰቡ ዘንድ የኮቪድ-19 ማዕከላትን የመፍራት ሁኔታዎች መኖሩን የጠቆሙት ዶክተር እስማኤል ይህ አመለካከት ሊቀየር እንደሚገባም አሳስበዋል።

👉በዚህ ረገድ በማዕከሉ ለሕሙማን የጤና ትምህርቶችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ለመሥጠት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
ምንጭ ፋና

02/06/2020

የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ። 🇪🇹

👉የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን እንዳሉት ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉ 1 ሺህ 200 ታማሚዎችን መያዝ እንዲችል ተደርጎ ተደራጅቷል።

👉ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።

👉ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።

👉በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።

👉በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠናም ተሰጥቷል።

👉በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ሐሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል ለኢዜአ ተናግረዋል።

👉በማዕከሉ ሕሙማን አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ፤ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሠራተኞችም ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ትኩረት መሰጠቱንም አክለዋል።

👉በተለይም የአየር ሥርዓት ፍሰቱን ለማስተካከል የሚረዱ መሣሪያዎች መገጠማቸው ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል።

👉ከማዕከሉ የሚወገዱ ፍሳሾች ለብቻ እንደሚወገዱና ደረቅ ቆሻሻዎችም በዘመናዊ መሣሪያ በመታገዝ የሚወገዱ መሆኑንም ዶክተር እስማኤል ተናግረዋል።

👉በማኅበረሰቡ ዘንድ የኮቪድ-19 ማዕከላትን የመፍራት ሁኔታዎች መኖሩን የጠቆሙት ዶክተር እስማኤል ይህ አመለካከት ሊቀየር እንደሚገባም አሳስበዋል።

👉በዚህ ረገድ በማዕከሉ ለሕሙማን የጤና ትምህርቶችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ለመሥጠት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ተጨማሪ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎ...
02/06/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ተጨማሪ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 59 ወንድ እና 28 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ10 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እና 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 28

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 18

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 41

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው 14 ሰዎች (6 ከኦሮሚያ ክልል እና 8 ከሶማሌ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 231 ደርሰዋል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 14 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመሪያው የ30 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን ሁለተኛዋ የ56 ዓመት በአዲስ አበባ የተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።

ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈና ለእስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመጡበት ጊዜ በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ናቸው። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል።

02/06/2020
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደረሰ*******************************በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ሰባ...
02/06/2020

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደረሰ

*******************************

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ሰባ ሁለት (72) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ በከተማው ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ (889) ደርሷል፡፡

በ 24 ሰዓታት ውስጥ የቫይረሱ የተገኘባቸው 72 ሰዎች በክ/ከተማ ደረጃ ሲታይ አዲስ ከተማ 28፣ ልደታ 7፣ ጉለሌ 3፣ ኮልፌ ቀራንዮ 0፣ ቦሌ 12፣ አራዳ 8፣ የካ 5፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 2፣ ቂርቆስ 3፣ አቃቂ ቃሊቲ 4 መሆናቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡ — sharing a COVID-19 Update.

በአለም ሀገራት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ሪፖርት:--እንግሊዝ----- 556 ሰዎች(111)-ህንድ     ------ 200 ሰዎች-ሜክሲኮ----...
02/06/2020

በአለም ሀገራት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ሪፖርት:-

-እንግሊዝ----- 556 ሰዎች(111)
-ህንድ ------ 200 ሰዎች
-ሜክሲኮ------ 151 ሰዎች
-ኢራን ------ 81 ሰዎች
-ጣልያን ------ 60 ሰዎች
-ቺሊ ------ 59 ሰዎች
-ፈረንሳይ ------ 31 ሰዎች
-ካናዳ ------ 30 ሰዎች
-ደቡብአፍሪካ-- 22 ሰዎች
-ስፔን ------ ዛሬ ምንም በቫይረሱ የሞተ ሰው የለም።

እስካሁኗ ሰአት ድረስ የተመዘገበ ሞት
24 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ
-አሜሪካ ----- 297 ሰዎች
-ብራዚል ------ 220 ሰዎች
-ሩሲያ ------- 162 ሰዎች

በእንግሊዝ ከዚ በፊት ሪፖርት ያልተደረገ 445ሰው ሞት እና የዛሬ 24 ሰአታት 111ሞት ጨምሮ አንድ ላይ የ556ሰዎች ሞት በዛሬው እለት ሪፖርት ተደርጓል። በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6,328,177 ደርሷል። ከ375,942 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። ከ2,883,363 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።
መልካም ምሽት✋

✍️''ኢትዮ-መረጃ''

በዚህ ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ*******************************በተያዘው ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ...
02/06/2020

በዚህ ዓመት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ

*******************************

በተያዘው ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ገንዘቡ የተሰበሰበው በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እና በቦንድ ሽያጭ ሣምንት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል።

ለግድቡ ግንባታ 1.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ድረስ 605 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

ይሁን እና በወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ ባለመቻሉ ገቢው ሊቀንስ መቻሉ ተነግሯል፡፡

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን 13.54 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ላይብራሪ እንዲጠቀሙ ተወሰነ******************የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በ...
01/06/2020

የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ላይብራሪ እንዲጠቀሙ ተወሰነ
******************

የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ተማሪዎች እና መምህራን ያለክፍያ በዲጂታል ላይብራሪ እንዲጠቀሙ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኮቪድ-19 ወደ አገራችን መግባቱን ተከትሎ የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና (የዩኒቨርስቲዎች እና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና) መቋረጡ እና ትምህርትን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በኦንላይን የማስቀጠል ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርትን በኦንላይን ሲያቀርብ የተማሪዎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በመገንዘብ በነፃ መጠቀም ለማስቻል ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በተሠራው ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያዘጋጀውን የዲጂታል ላይብራሪ ተማሪዎች እና መምህራን ገብተው ሲጎበኙ ከከፍያ ነፃ ወይም ዜሮ ሬቲንግ እንዲሆን መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና ማኅበረሰቡ በ http://ndl.ethernet.edu.et/ ገብቶ የነፃ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ጠቁሞ፣ ተማሪዎች እና መምህራን የኦንላይን መማር ማስተማር ሂደቱን በዚሁ አግባቡ እንድትቀጥሉ አሳስቧል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮ-ቴሌኮም ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።
source EBC

01/06/2020


✅በ24 ሰዓት 2,926 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ
✅ባለፉት 24 ሰዓት 85 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል
✅በሀገራችን ዛሬ 1 ተጨማሪ ሞት ተመዝግቧል
✅8 ተጨማሪ ታማሚዎችም ከቫይረሱ አገግመዋል

✅ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ዕድሜያቸው ከ1 ወር እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ሲሆን 51ዱ ወንድ 34ቱ ሴቶች እንዲሁም በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው
✅ዛሬ ከበሽታው ያገገሙት 8 ከኦሮሚያ 5 ከአዲስ አበባ ነው

✅72 ከአዲስ አበባ
✅5 ከኦሮሚያ ክልል
✅4 ከትግራይ ክልል
✅3 ከሶማሌ ክልል
✅1 ከአማራ ክልል

✔️ 48ቱ የውጭ ጉዞም ሆነ ንክኪ የሌላቸው
✔️ 19ኙ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው
✔️ 18ቱ በቫይረሱ ከተያዙት ጋር ንክኪ ያላቸው

* በዛሬው ዕለት የሞተው የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወንድ ሲሆን ቫይረሱ ተገኝቶበት በየካ ኬተቤ በፅኑ ህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዴቹ መፅናናትን እንመኛለን

📌 ጠቅላላ 112,377 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል
📌 በሀገራችን የተረጋገጠ ጠቅላላ ኬዝ 1,257 ደርሷል
📌 ከታማሚዎች ውስጥ 12 ታማሚዎችን በሞት አጥተናል
📌 ዛሬ ያገገሙትን ጨምሮ ጠቅላላ 217 ደርሰዋል
📌 2 ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል
📌 1,026 ታማሚዎች የህክምና ክትትል እያደረጉ ሲሆን 4 ታማሚዎች ፅኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ ይገኛሉ

ምንጭ:- ጤና ሚኒስትር

√ ለሟቾቹ ቤተሰቦችና ወዳጆች መፅናናትን እንመኛለን


ሼር ማድረግም አይርሱ

ሮበርት ሙጋቤ እንዲህ ብለው ነበር1 ለነጫጭ መኪኖች ጥቁር ጎማ መጠቀም እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነትአይጠፋም2 ከሌሎች ቀለማት በፊት ነጫጭ ልብሶችን አስቀድሞ ማጠብ እስካልቆመድረስ ዘረኝነት አይ...
01/06/2020

ሮበርት ሙጋቤ እንዲህ ብለው ነበር
1 ለነጫጭ መኪኖች ጥቁር ጎማ መጠቀም እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት
አይጠፋም
2 ከሌሎች ቀለማት በፊት ነጫጭ ልብሶችን አስቀድሞ ማጠብ እስካልቆመ
ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም
3 ጥቁር ቀለምን ለመጥፎ ገድ፣ ነጭን ደግሞ ለሠላም ምልክት መጠቀም
እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም
4 ጥቁር ቀለምን ለሐዘን፣ ነጭን ግን ለሠርግ መጠቀም እስካልቆመ ድረስ
ዘረኝነት አይጠፋም
5 ዕዳቸውን ያልከፈሉ ሰዎችን ከነጭ መዝገብ ይልቅ ጥቁር መዝገብ ላይ
መመዝገብ እስካልቆመ ድረስ ዘረኝነት አይጠፋም
6 በፑል (ስኑከር) ጨዋታ ላይ ጥቁሩ ድንጋይ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ነጩ
ድንጋይ በሜዳው ውስጥ ብቻውን በድል መንከባለሉ እስካልቀረ ድረስ ዘረኝነት
አይጠፋም
• እኔ በበኩሌ ችግር የለብኝም ሽንት ቤት ስገባ የምጠርገው በነጭ ወረቀት
( ሶፍት) እስከሆነ ድረስ ብዙ ቅር አይለኝም። "
-----------------------

♨️ ሼር ያድርጉ ♨️
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ

01/06/2020

ሁለት የራያ ቆቦ ወረዳ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ህግ በማስከበር ላይ እያሉ ሕይወታቸው አለፈ።

በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ አስተዳዳሪ እና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ሕይወታቸው አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍን እና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ ሞላ ዛሬ ሕይወታቸው ያለፈው ሕግ ለማስከበር ጥረት በማድረግ ላይ በነበሩበት ጊዜ መሆኑን ሰምተናል።

ድርጊቱ የተከሰተው ዛሬ ግንቦት 23/2012 ዓ.ም ከሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኝ መንጀሎ በተባለ ቦታ እንደሆነም አብመድ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኃላፊዎቹ ለሥራ ከቆዩበት ወልድያ ወደ ቆቦ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍና ለኮሮና ወረርሽኝ በሚያጋልጥ መልኩ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲያጓጉዝ ተመልክተው ሕግ ለማስከበር ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የወረዳው መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው አምባው ተናግረዋል። ባጃጇ ታርጋ እንደሌላትና አሽከርካሪውም ለመቆም ፈቃደኛ እንዳልነበረ መረጃ ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።

የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ነጋ ድንበሩ ለአብመድ እንደገለጹትም ከሮቢት ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው መንጀሎ ላይ አሽከርካሪው ባጃጇን በማቆም ከአካባቢው ወዳለ ሰርግ ቤት ከተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀላቸውን፣ ቀጥሎም ወደ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በመተኮስ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት።

ተሽከርካሪዋ በቁጥጥር ሥረ መዋሏ እና ተጠርጣሪዎችም መታወቃቸው ተገልጿል። በቁጥጥር ሥር ለማዋልም ክትትል እየተደረገ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ሕይወታቸውን ላጡት የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለኅብረተሰቡ መጽናናትን እንመኛል።

በአሜሪካ የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ወደ አመጽ እየተቀየሩ ነው።በጆርጅ ፍሎይድ ሞቱ ምክንያት በአሜሪካ የተጀመረው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለስድስተኛ ተከታታይ ቀን በመላ ሀገሪቱ ተዛምቶ ቀጥሏ...
01/06/2020

በአሜሪካ የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ወደ አመጽ እየተቀየሩ ነው።

በጆርጅ ፍሎይድ ሞቱ ምክንያት በአሜሪካ የተጀመረው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለስድስተኛ ተከታታይ ቀን በመላ ሀገሪቱ ተዛምቶ ቀጥሏል፡፡ በትንሹ በ40 ከተሞች ሰዓት እላፊ ገደብ ቢታወጅም ህዝቡ ገደቡን ወደ ጎን በመተው ሰልፉን የቀጠለ ሲሆን ይሄም በሀገሪቱ ዉጥረት አንግሷል።

በአንዳንድ ከተሞች ሀይል የተቀላቀለበት የአመጽ ድርጊት እንደነገሰም ተዘግቧል፡፡ በተለይም የኒውዮርክ ፣ ቺካጎ ፣ የፊላደልፊያ እና የሎስ አንጀለስ ሰልፈኞችን ለመበተን አድማ በታኝ ፖሊሶች ከፍተኛ ፈተና እንደገጠማቸው ያሳያል፡፡ ብዙ የፖሊስ መኪናዎች በእሳት ተቃጥለዋል፣ በብዙ የቢዝነስ ተቋማትም ዘረፋ ተፈጽሟል፡፡ በዋይት ሀውስ አቅራቢያ ባሉት ንብረቶች ላይ እሳት በለኮሱ ሰልፈኞች ላይ የዋሽንግተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭሽ በመተኮስ ለመበተን ሙከራ አድርጓል፡፡ አርብ ማታ በነበረው አለመረጋጋት ፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለደህንነታቸው ሲባል በዋይት ሀውስ ከመሬት በታች ወዳለ ማረፊያ ተወስደው ነበር ተብሏል፡፡

#ሮይተርስ

ፎርብስ ኢትዮጵያን ከኮቪድ19 በኋላ የዓለም ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን አቅም ካላቸው 7 አገሮች አንዱ ብሎ አስቀምጧል ።የኢትዮጵያን እጅግ ማራኪ ታሪካዊ ዳራ፤ የአውሮፓን ኃያልነት በጦር...
01/06/2020

ፎርብስ ኢትዮጵያን ከኮቪድ19 በኋላ የዓለም ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን አቅም ካላቸው 7 አገሮች አንዱ ብሎ አስቀምጧል ።

የኢትዮጵያን እጅግ ማራኪ ታሪካዊ ዳራ፤ የአውሮፓን ኃያልነት በጦርነት አሸንፋ ከቅኝ ግዛት የተቋቋመች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗን ፤ ቀደምት የሰው ዘር አባቶቻችንም ከዚህ ለምለም አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣታቸውን ጠቅሶ ፎርብስ ኢትዮጵያን ከኮሮና ወረርሽኝ ማግስት አብዝተው ሊጎበኙ ከሚችሉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ አካትቷል።

ቱሪስቶች ወደዚህች ታሪካዊ ሃገር ጎራ ቢሉ ከታሪካዊ እሴቶቿ በተጨማሪ ከዓይነተ ብዙ ተፈጥሯዊ ሃብቶቿ ብዙ ሊያተርፉ ይችላሉም ብሏል። ኢራን፣ ሚያንማር (በርማ)፣ ጆርጂያ፣ ፊሊፒንስ፣ ስሎቬንያ እና ቱኒዚያ ኢትዮጵያን ተከትለው በመጽሄቱ ከተጠቀሱት ሃገራት ውስጥ ይካተታሉ።

አሜሪካ ለብራዚል 2ሚሊዮን ዶዝ ሀይድሮክሲክሎሮኪውን የተሰኘውን መድሃኒት መላኳ ተሰማ ፡፡ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ለወላጅ እናቴ መድሃኒቱን ገዝቼ ሳጥን ውስጥ አስቀምጫለው አሉ የዓለም የጤና ድር...
01/06/2020

አሜሪካ ለብራዚል 2ሚሊዮን ዶዝ ሀይድሮክሲክሎሮኪውን የተሰኘውን መድሃኒት መላኳ ተሰማ ፡፡ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ለወላጅ እናቴ መድሃኒቱን ገዝቼ ሳጥን ውስጥ አስቀምጫለው አሉ የዓለም የጤና ድርጅት ለኮቪድ-19 ህሙማን ይህንን የፀረ ወባ መድሃኒት ሀገራት ከመጠቀም እንዲያቆሙ ቢያደርጉም አንዳንድ ሀገራት ግን ክልከላውን በመጣስ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡

የዩኤስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን የፀረ ወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ይጠቀሙ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ የብራዚሉ አቻቸው ጄር ቦልሴናሮ በበኩላቸው የ 93 ዓመት እድሜ ያላት ወላጅ እናቴ የፀረ ወባ መድሃኒቱ ካስፈለጋት ብዬ በሳጥን ውስጥ ገዝቼ አስቀምጫለው ብለዋል የፀረ ወባ መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ስለመቻሉ ሣይንሳዊ ማስረጃ የለም፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share