ዓባይ ሸንጎ - Nile Forum

  • Home
  • ዓባይ ሸንጎ - Nile Forum

ዓባይ ሸንጎ - Nile Forum ይህ ገጽ እንደ ጣና የሰፋ እንደ ዓባይ የረዘመ ሐሳበ ዓለም የሚጻፍበት ነውና ወዳችሁ አጋሩት !

06/11/2021
03/11/2021

ክብር ላንተ፣
ለእኔ መኖር ለተሰዋህ፣
ለእኔ ክብር ለተቀጣህ፣
ለእኔ ህይወት ሞት ለጠጣህ!

ክብር ላንተ፣
ላገር ክብር ስትትጋ፣ በባንዳ ለተወጋህ፣
ከእጅህ በልቶ ባደረ፣ ባጎረስኸው ለተከዳህ፣

ለዚህ ከሃዲ ወሮበላ፣ የዘራውን ባናሳጭድ፣
ደምህ ይፍረድ ለዘላለም፣ ከሰማያት ፍትህ ያውርድ።

***

02/11/2021

ያችን ቀን መቼም አንረሳትም።
ኢትዮጵያ ለትውልድ ሁሉ ትዘክረዋለች።
የትኛዋም ሀገር መከላካያ ኃይሏን አይደለምና የረሸነባትን ቀና ብሎ ያየባትን አካል ያለ ምህረት ትቀጣለች።
ይህን ካላደረገች ትዋረዳለች።
የሀገር መከላከያን ደም መመለስ የሀገር ህልውና እና የብሔራዊ ክብር ጉዳይ ነው!!!

21/10/2021

የአማራ መሆን ዕዳ!
አዲስ አበባ ተወልደህ ማደግህ ኢትዮጵያዊ ሆነህ መቆምህ ሁሉ ከዕዳ ያላዳነህ ለምን ነበር? ቤተሰቤችህ ዘራቸው ተጠንቶ አማራ መሆንህ አይደለምን? በእውነት ፊት መቆም የማይችሉ ድኩማን በሀሰት ምስክር ድርደራ ግፍህን ያበዙት ካንተ ሳይሆን ከአማራነትህ ላይ ጥል ስላለባቸው ነው። ለፍትሕ መቆምህ ለእውነት መታገልህ ዋጋ ያልኖረው አማራነትህ ነው። አማራ አዲስ አበባም ተወለደ የትም አደገ በግፍ ፍርድ እንደማይድን አየንብህ። ግን መች ተማርን? አማራን ጠላት ብለው የሚያሳድደት ሁሉ እየበረቱ እየሄዱ ግን አማራ እርስ በርስ ከመነታረክ መቼ ወጣ? አማራ ኢትዮጵያዊ በመሆን ከክልሉ ውጭ በመወለድ ነፃነት እንደማያገኝ ባንተ እያየን ግን መሃል አማራ ተወልደን አድገንም ለማንነታችን በአንድነት መቆም ተስኖናል። ለምን ይሆን? እንጃ!!!

አንተ ግን ሁሉንም አሸንፈሃል። ጀግና!
ሀሰተኞችን ማጋለት ብቻ ሳይሆን ለሚያሳድዱህ ይቅርታን ለምነህ ከፍታህን አሳይተሃል። አንበሳ!!!

07/09/2021
06/09/2021

አትውረድ!
ክብርህ ከፍታህ ነው! ዝቅ ስትል ትዋረዳለህ!

ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ወሎዬ፣ ሸዌ... ነኝ ብትል ክብርህ ማንነትህ አማራ መሆኑን ከዘነጋህ ወርደሃል። ከፍታህ አማራነት በኢትዮጵያዊነት ነው። የአማራነትም ክብር ሀገር ወዳድነቱ ለነፃነት ታጋይነቱ ዳር ድንበር አስከባሪነቱ ነው። ጠላት ሊከፋፍልህ ብዙ ሴራ ሲሰራ መኖሩንም አትዘንጋ። አንተም ክፍፍልን የሚያጠናክር ስራ ከሠራህ ታዲያ ጠላትስ ምን በደለን? ነጣጥሎ ከፋፍሎ አዳክሞ ሊመታን አይደለም እንዴ የዘመናት ሴራውና ድካሙ? ጠላት እንኳን ዛሬ ላይ በአንድ አማራነት ነው እየገደለን እያፈናቀለን ያለው። ኢትዮጵያንም ማፍረስ የሚፈልገው አማራ እንደሚወዳት ስለሚያውቅ አማራን የጎዳሁ መስሎት ነው። ኢትዮጵያም የምትድነው በአማራ አንድነት ኃይል መላውን ኢትዮጵያውያንን ማስተባበር ከቻልን ነው። የተከፋፈለ ኃይል ድል አያደርግም። የቁጥር ብዛት ብቻውን ትርጉም የለውም። አንድነት ምርጫ አይደለም። ግዴታ ነው። በተለይ አሁን ላይ ለድርድርም ለፉክክርም የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።

እርግጥ ነው አደረጃጀቶች በየአካባቢው መፈጠር አለባቸው። ግብና አላማቸው የአማራነት ክብርና መድረሻቸውም የኢትዮጵያ አንድነት እስከሆነ ድረስ በየቀበሌውም መደራጀቱ ችግር የለውም። ለአማራነት ክብር የሚዋደቁ ጀግኖች በየዞኑም በየወረዳውም ይደራጁ። ኢትዮጵያን የሚያድን ቡድን ከየትም ይምጣ። ችግሩ የሆነ ያልሆነ አጀንዳ በመፍጠር ከከፍታ የሚያወርዱን ጭቅጭቆች ላይ መግባታችን ነው። ይህ ነውር ነው። ትናንሽ ክፍተቶችን እየተጠቀሙ ትልቁን ሥዕል ለማበላሸት መሞከር ፈፅሞ ፀያፍ ነውር ነው። መደራጀታችንም ሆነ መሰልጠናችን አንዳችን ለሌላችን ለመሞት እንጅ እርስ በርስ ለመቀዋወም መሆን የለበትም፤ አይቻልምም። ይህ ወቅት መሰል እንቅፋቶችን ያለ ምህረት የምንታገልበት ነው። ምክንያት መፈለግ ያለብን ለአንድነት እንጅ ለልዩነት መሆን የለበትም። ለአንድነታችን መሠረት የሆኑ ብዙ ምክንያቶች እያሉን የልዩነት ሰበብ ፍለጋ አንድከም።

አንድ አማራ - ለአንዲት ኢትዮጵያ !

06/09/2021

እንዴት ነህ ወታደር፣ እንዴት ነህ ወጥቶ አደር፤
እንቅልፍ አጥተህ ምትኖር፣ ለእኛ ሰላም ማደር።

ዳር ድንበር ሚጠበቅ በደምህ ነውና
ክብር ይገባሃል አንት የሀገር ጀግና።

04/09/2021

በልብ ትጥቅ ማስጣል!
# # #
ግፍ አንቀዥቅዦት እንደ እብድ ገብቶ
ሴት ማረከችው ቡሃቃ ደፍቶ :)
በወንዶች ምድር ጀግና መች ገዶ
ዲሽቃ ያስጥላል ሴት በማገዶ።

ምድሩ ጀግና እንጅ ባንዳ አያስጠጋም
ድሮም ልብ እንጅ ትጥቅ አይጋም።

በል ተነስ ወጣት ይጥፋ ጠላትህ
በልብ ትጥቅ ማስጣል ተማር ከእናትህ!

31/08/2021

ላይምርህ አትማረው፣ ላይተውልህ አትተወው... የምንለው ለዚህ ነው!

አመንህም አላመንህም ወደድህም ጠላህም የወረረህ ጠላት አንተንም ንብረትህንም የእምነት ተቋምና ቅርስህንም ሳያጠፋ ለምንም አይመለስን። ሊያጠፋህ ወስኖ ነው የተነሳው። እንግዲህ ለቤተ እምነት የማይመለስ ጠላት ምን ይሉታል? ይህን አረመኔ ጠላት ሳይውል ሳያድር ካላጠፉት ሁሉን ነገር ከማጥፋት አይመለስም።

ወራሪውና አሸባሪው ትህነግ በታሪካዊው የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የፈለገ ፀሐይ በቅሎ አግት ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሦስተኛው ክፍለዘመን የተመሠረተ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ነው። የቤተ ክርስቲያኑ አባቶች እንደገለፁት ትናንት ምሽት አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በከባድ መሳሪያ ጥቃት ይህንን ጥንታዊና ታሪካዊ ቤተክርስቲያኑን ማውደሙን አረጋግጠዋል።

አሸባሪው ቡድን ባደረሰው የከባድ መሳሪያ ጥቃት የቤተክርስቲያኑ 14 መስኮቶች፣ 5 በራፎች፣ ሕንጻውና ጣሪያው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። የገዳሙ ፍልፍል ዋሻም በአሸባሪ ቡድኑ መፍረሱ ተጠቁሟል።

የወረረን የትህነግ ኃይል አሸባሪነቱን ለማረጋገጥ ይህ ድርጊት በቂ ነው። ችግሬ ከመንግስት ጋር ነው እያለ ነገር ግን የሚዘርፈውም የሚያወድመውም የሕዝብን ንብረት ነው። እንኳን ከሕዝቡ ከእምነቱም የተጣላ መሆኑንም ቤተ ክርስቲያን በማፍረስ ከማሳየት ውጭ ሌላ ምን ሊያደርግ ይችላል? ይህን ወራሪ ለማጥፋት ከመረባረብ ውጭ ምንም አማራጭ የለም። ለዚህ ቡድን ጊዜ በሰጠነው ቁጥር ጥፋቱን እየጨመርን ነው የምንሄደው። የሕዝብ ጠላትነቱን ካወቅን እንደ ሕዝብ ለማጥፋት እንረባረብ።

https://www.facebook.com/1833317486886200/posts/2943334759217795/?app=fbl
19/08/2021

https://www.facebook.com/1833317486886200/posts/2943334759217795/?app=fbl

እነሆ ጀግና!
# # #
እንካ ወንድ የወንድ ልጅ ይኸው ተዋወቅ ጀግና
በክብር በነፃነት እንድትኖር እናት ሀገር አንድ ሁና
ሕይወት ሊሰጥ የወሰነ ባለ ጀብዱ ባለ ዝና
ልበ ሙሉ ነው ደፋር ሞትም ጠላትም የማይፈራ
በተግባር የተፈተነ ሳይገድል ማይፎክር ማያቅራራ
የእናት ጡት ነካሾችን አፈር ድንጋይ ያስነከሰ
ሀገሩን የከዷትን ገድሎ ደሟን የመለሰ
የጥቁር ብርሃን ፈገግታው ተስፋን ብቻ የሚዘራ
ድል አድራጊ ነፍጠኛ ኩሩ ልበ ተራራ
ሃሞተ መሉ ወታደር ኢትዮጵያዊ አማራ!!!!
# # # # #
በቴሌግራም ተከታተሉን!
https://t.me/nefitegnaeyita

17/08/2021

አማራ እንደአባቶችህ አኩሪ ገድል ፈፅመህ በታሪክ ተከብረህ የምትኖርበት እድል ወደ ቀየህ ዘልቋል። ለመልካሙ ገድል ተጋደል።

መልካሙ ከተባለለት በላይ ነው:: የሚመጥን እጩ!
04/06/2021

መልካሙ ከተባለለት በላይ ነው:: የሚመጥን እጩ!

"የአማራን ፖለቲካ በብዕራቸው የቀነበቡ ወጣት አመራር!"

አቶ መልካሙ ተሾመ አለማየሁ ይባላሉ፡፡ ተወልው ያደጉት የውሆች ጋን፣ የግዮን አናት፣ ወላዲተ_ዓባይ በሆነችው ምድር ጎጃም_ሰከላ ነው።

እውነታን በማስረጃ እያስደግፉ ሲሞግቱ ለመረዳት የጠየቁት ብቻ ሳይሆኑ ለመርታት ያሠበ ባላንጣንም በቅፅበት የማሳመን አቅማቸው ድንቅ ነው፡፡ ላመኑበት ዓላማ የሚያካሂዱት ትግል፣ ቁርጠኝነታቸው፣ ፍትሃዊነት እንዲሠፍን ያላቸው የፀና ፍላጎትና ተግባር፣ ያላመኑበት የትህነግ መዋቅር እንዲገረሰስ የነበራቸው የሃሳብ ሙግት አይረሴ ነው፡፡ ልባዊ ሆነው የሚያዳምጡበት መንገድ ከአንባቢነታቸውና ከሠላው ብዕራቸው ጋር ተጣምረው ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕና እንዲላበሱም አስችሏቸዋል፡፡

አቶ መልካሙ ተሾመ አለማየሁ የኢትዮጵያ መዋቅርና ስርዓት በተሳሳተና አማራን በጠላትነት በሚከስ ትርክት ላይ የተገነባ መሆኑን በመረዳት ይህ ስርዓት እንዲወገድ በብዕራቸው ታግለዋል። ይህን ትርክት በመናድ በምትኩ እኩልነትን ለማረጋገጥ የአማራ ብሄርተኝነት እንደ ትህነግ ወይም እንደ ኦነግ (ሸኔ) ካለ እቡይነትና ተገንጣይነት እንዲርቅ መክረዋል።

የለውጡን አቅጣጫዎችም አመላክተዋል። ከፖለቲካ ዘይቤ እና ከአደረጃጀት አንጻር "...የኢትዮጵያን አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን የማይቀበል የብሄር ፖለቲካ እና ለብሄር ማንነት እውቅና የማይሰጥ የኢትዮጵያዊነት ብሄረተኝነት እኩል አደገኞች ናቸው" በማለት መፍትሄው አማካዩ መንገድ መሆኑን አስቀድው በረቀቀው ብዕራቸው አመላክተዋል፤ ተሟግተዋል።

የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን ቀንብበው (መፅሐፍ በመፃፍ) አስነብበዋል፤ ብዙዎቹን አንቅተዋል። ለውጡን ተከትሎ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ይዘው የዚያን ጊዜውን አዴፓን ተቀላቅለው ለጥያቄዎቹ አፈታትም ስትራቴጅዎችንና ስልቶችን በመንደፍ የበኩላቸውን ሚና ተወጥተዋል። በስራና በማህበራዊ ኑሮ የተወዳጇቸው ሠዎች አቶ አመልካሙ "የአማራን ፖለቲካ በብዕራቸው የቀነበቡ ወጣት አመራር" እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡

አቶ መልካሙ ተሾመ አለማየሁ በዳኝነት እና በጠበቃነት ሙያቸው በብቃት እና ከፍ ባለ ዲሲፕሊን ህዝብን አገልግለዋል። በ2011 ዓ.ም በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ፓርቲውን አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የጥናትና ምርምር ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

እኒህ እንደ ስማቸው መልካም የሆነ ስብዕናን የተላበሱ፣ የዕውቀትና የተግባር መሪ አቶ መልካሙ ተሾመ አለማየሁ በ6ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሰከላ ወረዳ ምርጫ ክልል፤ የክልል ም/ቤት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።

የግዮን ልጆች ሆይ ለህዝብ ጥቅም ሞጋች፣ ለውጡን ለማምጣት የታገሉና ለውጡ ያመጣቸው፣ በእውነትና በእውቀት የሚመሩ ወጣት ፖለቲከኛ የሰከላ ህዝብ ወኪል ይሆኑ ዘንድ በድምፃችሁ አጅቧቸው፡፡ የሰከላ ህዝብ ልጅህን ምረጥ!


ዕጩ ትውውቁ ይቀጥላል...

07/05/2021

(ኑ አብረን እንንቃ)
መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎችና የሚጋጩ ህልሞች በሚለው መጽሃፉ አማራዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ተጽዕኖ አንዱ ምንጭ የሚድያና የተግባቦት ብልጫቸው ነው ይላል። እውነቱን ነው፤ በሁሉም የተግባቦት ዘርፎች አማራዎች ምርጦች ነበሩ። ይህ ድምዳሜ ለድጅታል ዘመን ፖለቲካችን እውነት አይደለም።
የዛሬ አማራዎች በፕሮፖጋንዳው ሙሉ ብልጫ ተወስዶባቸዋል። ቀላል ምሳሌ ልስጥህ፤ ቀደም ሲል ጃዋር ሲራጅ ሞሃመድ የሚባል ልጅ ሲያንጫጫቸው ባጀ። ከሁለት ሚሊዮን በላይ የፌስቡክ ተከታይ ነበረው። አብዛኛው አማራው ነው። የተጽዕኖ መጠኑ የሚለካው በሚፈጥረው ስሜትና በሚነሱ ግብረ መልሶች ነው። አስተያየት ሰጭዎች በይበልጥ አማራዎች ነበሩ። ጃዋር ቤቱ ቁጭ ብሎ በእያንዳንዱ አማራ ቤት ውስጥ መግባት ቻለ። በውጤቱም ጃዋርን ከሆነው በላይ ያከበደ ግንዛቤ ተፈጠረ። የጃዋር የመደራደር አቅም በአመዛኙ ከዚህ የሚድያ ተጽዕኖው የሚመነጭ ነው። ጃዋር የሚያውቀውም የሚችለውም አንድ ነገር ብቻ ነው፤ መቃወም፣ ማመጽና ማሳመጽ። በእርግጥ የኦሮሞ ፖለቲካ ስሪት የአመጽ ነው። እውነቱ ይህ ቢሆንም የአማራ ፖለቲከኛና ልሂቅ ግን ጃዋርን የፖለቲካ መሃንዲስ እንደሆነ አመነ። ፖለቲካ ሌላ ምን መስሎሃል፤ ተጽዕኖ ነው።

ጃዋር እጅግ ዘግይቶ ቢታሰርም ተተኪ ጃዋሮችን ግን እየተመለከትን ነው። ታዬ ደንድአ የሚባለው ልጅ በትምህርቱም፣ በእድሜውም፣ በልምዱም፣ በብስለት ደረጃውም ገና ልጅ ነው። እንኳን ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በራሱ ዙሪያ ያለውን የኃይል አሰላለፍም አይገነዘበውም። በኦሮሞ ፖለቲከኞችም ዘንድ እንኳን ሚዛኑ የቀለለ ከአንድ ተራ አክቲቪስት የተሻለ ግምት የማይሰጠው ሰው ነው። በአማራው ዘንድ እየገነባው ያለው ምስል ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው። ታዬ ቁጭ ብሎ መደመርን እያነበበ (ሌላ ያነበበው መጽሃፍ ስላለመኖሩ በአስር ጣቴ እፈርማለሁ) በእያንዳንዱ የአማራ ቤት ውስጥ ይገባል። ልጁ ከሆነው በላይ ምስል እየተፈጠረለት ያለው በዋናነት በአማራዎች ነው። አጀንዳ ተቀብለህ በዚያው ነጥብ ስትሽከረከር ከዋልክ የእሱ ምርኮኛ ነህ። እነዚህን ልጆች መከታተል ያለብህ ለማወቅ እንጅ ለመከተል መሆን የለበትም። ዓለም እና ፖለቲካ ደግሞ በይበልጥ የፕሮፖጋንዳ ውጤት ናት። በፕሮፖጋንዳው ብልጫ ከተወሰደብህ ፖለቲካህን እተተቀማህ ነው፤ ቆም ብለህ አስብ። በጥናት ያልተረጋገጠ ቢሆንም ማህበራዊ ሚድያ ላይ የአማራው ተሳትፎ ከፍተኛ ነው። የሚጽፈውም በአማርኛ መሆኑ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የመድረስ እድል አለው። ተወደደም ተጠላም ዛሬም ቢሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የስበት ማዕከል አማራው ስለሆነ በሁሉም ባለጉዳዮች የመጎብኘት እድል አለው። ይህን አንጻራዊ እድል ተጠቅሞ እንደ ጃዋር እንደ እነ ታዬ ደንድአ ብዙ ተጽዕኖ ለመፍጠር ያልቻለው ለምንድን ነው?
እነ ክርስቲያን ታደለ፣ ምስጋናው አንዷለም፣ ውብሸት ሙላት ፣ በለጠ ሞላ፣ ጌታቸው ሽፈራው፣ አንሙት አብርሃም፣ የሺሀሳብ አበራ ወዘተ ያላቸው ተከታይ ተደምሮ የታዬ ደንደአን አይበልጥም፤ የጃዋርን አያክልም። ከእነዚህ አንዱ ግን ሁለት ጃዋርን እና አስራ አምስት ታዬ ደንድአን ያህላል።

እና ምክንያቱ ምንድን ነው? ብዙ ነው ሰበቡ። ዋናውን ብቻ ልንገርህ፤ ሌላው ሁሉ በየብሄሩ ሲደራጅና የኢትዮጵያን ፖለቲካ በእጁ ሲያስገባ የአማራ ልጆች ምን እየሰሩ ነበር፤ በ1960ዎቹ ጀምሮ? ዘመኑን መዋጀት ዙሪያቸውን ማንበብ ተስኗቸው እንቅልፍ ላይ ነበሩ። ይኸው ነው።

የዛሬም የአማራ ልጆች የድጅታል ዘመን ፖለቲካንና ፕሮፖጋንዳን መረዳት አቅቷቸው መለስተኛ እንቅልፍ ላይ ናቸው። ኑ አብረን እንንቃ!!!
(Tewaney Belay)

07/05/2021

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ አልነበርንም። ከዛሬ ጀምሮ ትንታኔዎች፣ ዜናዎችና መረጃዎችን የምናቀርብ ይሆናል።

የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ተመስገን ጥሩነህ፤ ህወሃቶች ሁለት ምርጫ ብቻ አላቸው ብለዋል። እጃቸውን ይስጡ ካልሆነ ሞትን ይጎነጫሉ። በእርግጥም ጦርነት ውስጥ የገባነው ለሽርሽር አይደለም። አሸባ...
07/11/2020

የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ተመስገን ጥሩነህ፤ ህወሃቶች ሁለት ምርጫ ብቻ አላቸው ብለዋል። እጃቸውን ይስጡ ካልሆነ ሞትን ይጎነጫሉ። በእርግጥም ጦርነት ውስጥ የገባነው ለሽርሽር አይደለም። አሸባሪዎችን ለመግደል ከበቂ በላይ ምክንያት አለ።
ሁሉም አማራ ከጎንዎ መሆኑን እናረጋግጣለን፤ ክቡር ፕሬዚደንት።

የጆይ ባይደን መመረጥ ከፍተኛ ስትራቴጂካዉ ጠቀሜታ ባለው የአፍሪካ ቀንድ በጠቅላላ እና በኢትዮጵያ ላይ ደግሞ በተለይ ከፍ ያለ ትርጉም ይኖረዋል። በሁሉም መመዘኛዎች ለእኛ ኢትዮጵያውያን ከፍ ...
07/11/2020

የጆይ ባይደን መመረጥ ከፍተኛ ስትራቴጂካዉ ጠቀሜታ ባለው የአፍሪካ ቀንድ በጠቅላላ እና በኢትዮጵያ ላይ ደግሞ በተለይ ከፍ ያለ ትርጉም ይኖረዋል። በሁሉም መመዘኛዎች ለእኛ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ የምስራች ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
ምስሉን ከቢቢሲ አማርኛ የፌስቡክ ገጽ የወሰድነው ነው።

1) በሰሜን እዝ የጦር መኮንኖች ላይ የተፈጸመው ክህደትና ግፍ የሚያደርሰውን ንዴትና ብስጭት እጅጉን ስሜት ይፈታተናል። ጥርሳችን ነክሰን ትግላችን እንቀጥል። 2)  ልብ አድርጉ አሁን ሁሉም ...
07/11/2020

1) በሰሜን እዝ የጦር መኮንኖች ላይ የተፈጸመው ክህደትና ግፍ የሚያደርሰውን ንዴትና ብስጭት እጅጉን ስሜት ይፈታተናል። ጥርሳችን ነክሰን ትግላችን እንቀጥል።
2) ልብ አድርጉ አሁን ሁሉም ጉዳያችን ህወሃትን መደምሰስን ታሳቢ ያደረገ ነው። ስትራቴጅክ ጉዳያችያችን ስትራቴጅክ ጠላታችን መደምሰስ ነው።
3) አንድነታችንና ትብብራችን ካስቀጠልን ምንም ጉዳይ ከአቅማችን በታች ነው።
4) The sky is the limit!!!

የጀመርነው ጦርነት የጸሃይ ግባት (Sun set) ወይም ጸሃይ  መውጣት (Sun rise) ለመሆን የሚችል በሁለት ገጹ የተሳለ ሰይፍ  ነው።  የምንወስነው እኛ ነን። አያያዛችን ነው ውጤቱን የ...
07/11/2020

የጀመርነው ጦርነት የጸሃይ ግባት (Sun set) ወይም ጸሃይ መውጣት (Sun rise) ለመሆን የሚችል በሁለት ገጹ የተሳለ ሰይፍ ነው። የምንወስነው እኛ ነን። አያያዛችን ነው ውጤቱን የሚወስነው።

06/11/2020

1) በጅምላ ማሰብና በስማ በለው መነዳት መቼ ወደ አማራ ፖለቲካ እንደገባ አላውቅም። ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው።
2) ማዕከላዊ መንግስቱ በህወሃት ላይ ጦርነት አውጇል። ይህ ጦርነት በማናቸውም መለኪያ ተገቢነትና ተቀባይነት ያለው ነው። እጅግ ሲያንስ ፍትሃዊ ፤ ሲበዛ ቅዱስ ጦርነት ነው። አንዱን ምክንያት ብቻ እንጥቀስ፤ ህወሃት በሚከተለው የፖለቲካ አስተሳሰብም ይሁን በተግባራዊ እንቅስቃሴው አሸባሪ ድርጅት ነው። በዓለም ፖለቲካ ውስጥ ከአገር አንድነትና ከህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚበልጥ ምንም ጉዳይ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የአገር አንድነት በእጅጉ ተጠቅቷል። ከዚህ አልፎ በኢትዮጵያ ጦር ላይ የተፈጸመው ክህደት ህወሃትን ከአይ ኤስ አይ ኤስ የሚብስ አሸባሪ ያደርገዋል። በመሆኑም ጦርነቱ ከመዘግየቱ በቀር የሚነቀፍበት ቅንጣት ምክንያት የለም። ወንድማማቾች ምንትስ ቅብጥርስ የሚሉ ፖለቲካን በባዮሎጅ የሚተነትኑ የቤት ልጆች ናቸው።
3) ለህወሃት የአሸባሪነት ደረጃ የሚመጥን ወታደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው ወይ? ህወሃት የኢትዮጵያን ጦር የሚገዳደር አቅም አላት ወይ?
4) የጦርነቱ ዓላማ ምንድር ነው? ህወሃትን መደምሰስ ወይስ በህወሃት ውስጥ ያሉ ጥቂት አመራሮችን መማረክ? የህግ ማስከበር እርምጃ ማለት ምንድን ነው? እነ ጌታቸው አሰፋን ልደታ ወደተሰየመው ችሎት ለማቅረብ ነው ወይ? ይህ ምን የሚሉት ማሳነስ ነው? ህወሃትን መደምሰስ ማለት የህወሃትን አባላት በሙሉ መረሸን ማለት የሚመስለው ዘገምተኛ ካልሆነ በቀር የቀበሌ ግብርና ሰራተኛ የህወሃት አባል ነጻ ሰው ነው ምናምን የሚባል ፕሮፖጋንዳ አይሰራም።
5) የማእከላዊ መንግስቱ ግራ የሚያጋባ አሰራርና እርምጃ ወታደራዊ ጉዳዮች በአደባባይ የሚገለጡ ባለመሆናቸው የሚሰጠውን ግምትስ benefit of the doubt እንኳን የዘለለ ነው።
6) የአማራ ፖለቲካ በዚህ ጦርነት ውስጥ ያለው ድርሻ፣ ኃላፊነት፣ ዓላማና ግብ እንዲሁም ተጠባቂ ውጤት ምንድን ነው? ምን ማድረግ አለበት? ምንስ ማድረግ የለበትም? በእነዚህ ነጥቦች ላይ በቂ ግልጽነትና ግንዛቤ ተፈጥሯል ወይ?
---
-----
-------
እጅግ በአነስተኛ ኪሳራ እና በአጭር ጊዜ ለማለቅ የሚችለውን ጦርነት በተዝረከረከ አመራር የማያባራና የተራዘመ እንዳይሆን ስጋት አለን። ማናቸውም የጉዳዩ የአመራር ጉድለትና መዛነፍ ግን የጦሩን ልክነት አያስቀረውም፤ የህወሃትን አሸባሪነት አይለውጠውም። ስለሆነም የሚቀርቡ ማናቸውም ትችቶችና ጥያቄዎች ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ ከማሳሰብ በቀር ሌላ ዓላማ የላቸውም። በእነዚህ ትችቶች በኩል ለህወሃት የለዘበ አቋም መያዝ ህወሃትነት ነው።

04/11/2020

1) አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ጦርነት ውስጥ ነን። ጦርነቱ የሚመራው በጦርነት ህግ ነው። ዝርዝሩ በሜዳው ግንባር ላይ የሚፈጸም ነው።
2) በመጨረሻው ጣዕረ_ሞቷ በመሃል አገር ሽብር ለመፈጸም መሞከሯ አይቀርም። አካባቢያችን በንቃት እንከታተል፤ እንጠብቅ።
3) በመጨረሻም ድል ከእኛ ጋር ናት።

03/11/2020

1) ህወሃትን ለመደምሰስ በማናቸውም ኃይል እና ጊዜ የሚወሰድ እርምጃ በሁሉም መለኪያዎች ተገቢነትና ተቀባይነት አለው።
2) የአማራ ኃይሎች ሁሉ ማናቸውንም ልዩነቶች ወደጎን በመተው አብረው መቆም አለባቸው።
3) የሁሉም ግፎችና በደሎች ምንጩ ህወሃት ነው።

02/11/2020
02/11/2020

1) ኦነግ ሸኔ የሚሉት አሸባሪ ድርጅት በመንግስት የሚደገፍ መጠባበቂያና ሴራ ማስፈጸሚያ ቡድን ነው።
2) በመጀመሪያ ከነትጥቁ የገባው በአጋጣሚ አይደለም። ላለፉት ሁለት ዓመታት ተከታታይ የሽብር ድርጊቶችን እየፈጸመ በዝምታ የታለፈው ከአቅም በላይ ሆኖ አይደለም።
3) መፍትሄው የመግለጫ ጋጋታ አይደለም። ቁርጠኛ አቋም ይዞ እውነቱን ፊት ለፊት መግጠም። ወደፊት የሚሆነው እስካሁን ከሆነውም የከፋ ነው።

የባህርዳር ዓለማቀፍ  ኤርፖርት ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለማቀፍ አየር ማሪፊያ  መባል አለበት። በስህተት እንኳን ከዚህ ውጭ ሊሆን አይገባም። ይህን የማይቀበሉትን ስማቸውን በባንዳነት መዝግበን...
01/11/2020

የባህርዳር ዓለማቀፍ ኤርፖርት ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለማቀፍ አየር ማሪፊያ መባል አለበት። በስህተት እንኳን ከዚህ ውጭ ሊሆን አይገባም። ይህን የማይቀበሉትን ስማቸውን በባንዳነት መዝግበን እንይዛለን፤ ነገ እኛው ራሳችን እንሰይመዋለን።

ዓባይ ሸንጎ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ይመኛል፤ እንኳን አደረሳችሁ።
29/10/2020

ዓባይ ሸንጎ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ይመኛል፤ እንኳን አደረሳችሁ።

27/10/2020

የባህር ዳር አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ስያሜ "በላይ ዘለቀ" ብቻና ብቻ ነው መሆን የሚችለው። ከዚህ ውጭ የሚሰጥ ምንም አይነት ስያሜ ተቀባይነት የለውም። "ለምን?" ከተባለ፦

አንደኛ፦
የቀድሞ ስሙ በላይ ዘለቀ ስለነበር። በኃይለ ሥላሴም በደርግም ዘመን የባህር ዳር አየር ማረፊያ ስም "ደጃዝማች በላይ ዘለቀ" ነበር። ኢህአዴግ ነው የቀየረው። ስለዚህ በፖለቲካ ፍላጎት የተቀየረውን ስያሜውን ወደ ቀድሞ ስሙ መቀየር ከምንም በላይ ትክክል ነው።

ሁለተኛ፦
ሀገርን ከውጭ ወራሪ ከፋሽስት ቅኝ ግዛት ነፃ በማውጣት ሂደት ወደር የማይገኝለት ጀግና በላይ ዘለቀ እያለ ሌላ ስያሜ ስለማያስፈልግ። የቦታውም የወንዙም የሐይቁም ስም (ባሕር ዳር፣ ዓባይ፣ ጣና) አለ ሁሌም ይኖራል። ኤርፖርት ተሰየመለትም አልተሰየመለትም ሕያው ሆኖ ይኖራል። ለእነዚህ ስሞች መታሰቢያ የግድ አያስፈልጋቸውም። ሕያው ሆነው የሚኖሩ ናቸውና። ይልቁንስ በጊዜው ትልቅ ታሪክ ሰርቶ ያለፈው ጀግና ነው ስያሜው የሚገባው። ለመሆኑ "በላይ ዘለቀ" የምንለው የ የባህር ዳሩን አየር ማረፊያ አይደል እንዴ!? ይኸውም በዓባይና ጣና ዳር ነው የሚገኘውን እንጅ ሌላ አይደለምና የግድ በቦታው መሰየም የለበትም። በላይን ለመሰለ ጀግና ግን ይገባዋል። ለኢትዮጵያ ደም መላሽ ሲያሰው ነው። ይህን የሚቃወም ከኢትዮጵያ ጋር የተጣላ ባንዳ ብቻ ነው።

ሦስተኛ፦

"በላይ ዘለቀ" የሚለው ስያሜ በአማርኛ ትርጉሙ ለአየር መንገድ እጅግ ስምሙ የሆነ ስም ነው። "በላይ ዘለቀ" ማለት "በላይ ሄደ፣ በሰማይ በረረ" ለማለት የምንጠቀምበት ስያሜም ስለሆነ። ይህ ስም ጀግናውን ከማስታወስም ባሻገር በአማርኛ ለአየር ማረፊያ ስያሜ ወደር የማይገኝለት ስያሜ ነው። እናም ለአማራ ክልሉ መዲና ለባህር ዳሩ አየር ማረፊያ ከዚህ ስም ውጭ አይታሰብም። ይህን የሚቃረን ከታሪክም ከሕዝብም ከራሱ ቋንቋም የተጣላ ነው።

"በላይ ዘለቀ" ብቻ!!!

25/10/2020

ለማናቸውም አንድ ነገር በእርግጥ መታወቅ አለበት። የአማራ ትግል ያሸንፋል። በመሃል የሚከፈለው ዋጋ ዓይነትና መጠን ነው ናላችን እያዞረው ያለው፤ ከዚህ በቀር የኢትዮጵያን ፖለቲካ በመሰረቱ እንደምንቀይረውና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ሆኖ እንደምንተክለው እግዜርም ሴጣንም፣ ህወሃትም ኦነግም እኩል ያውቁታል።
የምንከፍለውን ዋጋ ለመቀነስ አንድነታችንን እናሳድግ። በአማራነት የተጠቃን ህዝብ በጎንደሬነት፣ ጎጃሜነት፣ ወሎየነት፣ ሸዌነት፣ አገውነት ለመታደግ መሞከር የ21ኛው መቶ ክፍለ_ዘመን የአላዋቂነት ጣሪያ ይሆናል።

የኦሮሞ ተረኝነት ምንም አዲስ ነገር የለውም። ከተረኝነት ፍላጎቶች ውስጥ አንደኛው አዲስ አበባን የመዋጥ እንቅስቃሴ ነው። አንዱ የዚህ ውጠት ማስፈጸሚያ ስልት አፋን ኦሮሞን የከተማዋ የስራ ቋ...
25/10/2020

የኦሮሞ ተረኝነት ምንም አዲስ ነገር የለውም። ከተረኝነት ፍላጎቶች ውስጥ አንደኛው አዲስ አበባን የመዋጥ እንቅስቃሴ ነው። አንዱ የዚህ ውጠት ማስፈጸሚያ ስልት አፋን ኦሮሞን የከተማዋ የስራ ቋንቋ ማድረግ ነው። ይህን ለመተግበር እና ህግም ባይኖር በተግባር ለማስለመድ ብዙ እንቅስቃሴዎች አሉ። እንዲህ ያለው ስግብግብነት የሚገታው በትግል ብቻ ነው። ምክትል ከንቲባው ዣንጥራር ዓባይ ሁለተኛ ቋንቋን የሚጠይቅ ህግም ሆነ አሰራር የለም፤ የስራ ቋንቋችን አማርኛ ነው፤ ይህን የሚተላለፉ ካሉ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።
በእርግጥ አዳነች አቤቤ ወይም አብይ አህመድ አሊ ይህን የሚያስተባብል መግለጫ ሊሰጡ ይችላሉ። በተለይም ጠሚው ብዙ ቋንቋ ስለ መቻል ጥቅም የሚሰብክ ጽሁፍ እንደሚያጋራን ይጠበቃል።
በዓባይ ሸንጎ እምነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ የተመሰረተ ነው። የፖለቲካል ኢኮኖሚያችን መካና መዲና (ማስመስከሪያ) ናት አዲስ አበባችን። ስለሆነም በአዲስ አበባ ጉዳይ እጅግ ልዩ በሆነ ብቃትና ንቃት መከታተልና መልክ ማስያዝ ይገባል። ዣንጥራር አባይ የሰጡት መግለጫ በይዘቱም ሆነ በቀረበበት ጊዜ ተገቢ ነው። ስለሆነም ምክትል ከንቲባው እንዲበረቱ ማገዝ፣ መረዳትና መተባበር ያስፈልጋል።

1) የአባይ ጉዳይ የተበላሸው በአብይ አህመድ አሊ ስህተት ነው ።  ይህ በምንም ዓይነት የስኬት ንግግር ለመሸፈን አይችልም። 2) እሱ ከመጣ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ እና አማራዎች ደግሞ...
24/10/2020

1) የአባይ ጉዳይ የተበላሸው በአብይ አህመድ አሊ ስህተት ነው ። ይህ በምንም ዓይነት የስኬት ንግግር ለመሸፈን አይችልም።
2) እሱ ከመጣ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ እና አማራዎች ደግሞ በተለይ እየታረዱ ናቸው። ግልጽ የዘር ፍጅት ተደርጓል፤ በተደጋጋሚ። አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ማስከበር አልቻለም። ይህ የአንድ መንግስት የመጨረሻው ዝቅተኛው ግዴታ ነው። በዚህ የመንግስት ልፍስፍስነት ውስጥ አብይ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል። እየመረጡ ኃላፊነት ለመውሰድ አይቻልም።
3) ይህ ሁሉ ሆኖ አብይ ሊቀመንበር ሆኖ ከቀጠለ እውነትም የብልጽግና አመራር እንቅልፋሞች ናቸው።

23/10/2020

መተከልም ሆነ ጉራፈርዳ የሚታረደው አማራ መዋቅር እና ስርዓት አቁሞ በከረመው የመጤ_ነባር ፖለቲካ የተነሳ ነው። የተሳሳተውን የፖለቲካ ትርክት እጅግ ቢያንስ በገዥው ፓርቲ በብልጽግና ውስጥ ውድቅ በማድረግ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ዘይቤና አደረጃጀት ተተግብሮ ነበር። አሁን እየደረሰ ላለው እልቂት የየአካባቢው የብልጽግና አመራር ድርሻ ከፍተኛ ሆኖ ይታያል።
ትግሉን ከማራዘምና የሚከፈለውን ዋጋ ከማብዛት በቀር መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ እና እኩልነትንና ፍትሃዊነትን በተረጋገጠ አኳኋን ከማስፈን የሚያስቀር ኃይል የለም።

የኢትዮጵያ እና የዓለም ሙዚቀኛ በሁለት ይከፈላል፤ ጂጂ እና ሌላው። በእርግጥ ጂጂን ሙዚቀኛ ብቻ ብሎ ማለፍ  ፍርደ_ገምድልነት ነው። አሰላሳይ፣ ባለቅኔ፣ ፈላስማ፣ አብዮተኛ፣ ገጣሚ እና ከያኒ...
21/10/2020

የኢትዮጵያ እና የዓለም ሙዚቀኛ በሁለት ይከፈላል፤ ጂጂ እና ሌላው። በእርግጥ ጂጂን ሙዚቀኛ ብቻ ብሎ ማለፍ ፍርደ_ገምድልነት ነው። አሰላሳይ፣ ባለቅኔ፣ ፈላስማ፣ አብዮተኛ፣ ገጣሚ እና ከያኒም እና ሌላም ብዙ ነገር ናት፤ እጅጋየሁ ሽባባው የኔአባት። ሰውነትን የበየነች፣ ኢትዮጵያዊነትን እስከ ሰባተኛው ሰማይ አርቃ የሰቀለች፣ ግጥምና ዜማን ሰዉ ከማይደርስበት ከፍታ ያኖረች፣ ሚዛን የሆነችው እሷ።
ዓባይ ሸንጎ ከጂጂ ጀርባ ያለው ማንና ምንድን ነው? ብላ ጠይቃለች። የተጠየቁ ገመድ ወደ የቤተሰቡ የመቻል ጓዳ፤ ወደ የቻግኒ አገው ምድር ታሪክና የቅኔ ገምቦነት፣ ወደ ጎጃም ያልተገለጡ ምስጢሮች ወስዶናል። በሌላ ጊዜ የምንዳስሰው ይሆናል።

1) ኢትዮጵያውያንን መጤ/ነባር፣ ጨቋኝ/ተጨቋኝ፣ ሴም/ኩሽ ወዘተርፈ እያለ የሚከፋፍለው የፖለቲካ አስተሳሰብ በማናቸውም መለኪያ ተቀባይነት የለውም። በዚህ ላይ የቤንሻንጉልጉሙዝ  ፖለቲከኞችን ...
18/10/2020

1) ኢትዮጵያውያንን መጤ/ነባር፣ ጨቋኝ/ተጨቋኝ፣ ሴም/ኩሽ ወዘተርፈ እያለ የሚከፋፍለው የፖለቲካ አስተሳሰብ በማናቸውም መለኪያ ተቀባይነት የለውም። በዚህ ላይ የቤንሻንጉልጉሙዝ ፖለቲከኞችን ጨምሮ ሁሉም ተስማምቶ ነው ብልጽግና የተመሰረተው። ይሁንም እንጅ የክልሉ መንግስት ከስር ባያያዝነው መግለጫው ወደ ቀደመ እሱነቱ መመለሱን ገልጦ ጽፏል። ይህ እጅግ አደገኛ ምልክት ነው። የክልሉ አመራር ወደ ቀደመ ትፋቱ መመለሱ በመደበኛ የፓርቲ ዲሲፕሊን የሚታይ አይሆንም። እጅግ ጥብቅ በሆነ መንገድ ተገምግሞ አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ይህን በተገቢው አጭር ጊዜ ማስተካከል ካልተቻለ፤ ሲያንስ ክልሉን ወደ ህወሃት ጉያ የሚከትት ሲሆን ሲበዛ ደግሞ ብልጽግናን የማፍረስ አደጋን አዝሏል። የሚመለከተው የፓርቲው አካል ነገሩን በክብደቱ እና በአደገኝነቱ ልክ እንዲመለከተውና እንዲያርመው ለማሳሰብ እንወድዳለን።
2) ይህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ከክልሉ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እና ከፌዴራላዊው የመንግስት አወቃቀር ጋር የሚጣረስ አይደለም። የተሳሳተውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ማስቀረት የክልሉን የራሱን የማስተዳደር መብትና ነጻነት እንደመጋፋት አድርጎ ማቅረብ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም ሁለቱን ጭብጦች ለያይቶና በየአንጣራቸው መረዳት አስፈላጊ ይሆናል።
3) ከለውጥ በፊት የነበረው መዋቅራዊና ስርዓታዊ ችግር ምንጩ (The original Sin) ይህ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰውና የክልሉ መንግስት የያዘው አቋም ነው።
4) ዓባይ ሸንጎ የጉዳዩን አሳሳቢነት ትገነዘባለች፤ በመሆኑም ትኩረት ተሰጥቶት እንዲፈታ ጥሪ ታቀርባለች።

1) ደራሲው፣ አርበኛው፣ አምባሳደሩ፣ ፖለቲከኛው፣ ብርቱው ሰው ሃዲስ አለማዬሁ የሚታወስበት  ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በስሙ ተሰይሞ ማስተማር ጀምሯል። የህንጻ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ በዛ...
17/10/2020

1) ደራሲው፣ አርበኛው፣ አምባሳደሩ፣ ፖለቲከኛው፣ ብርቱው ሰው ሃዲስ አለማዬሁ የሚታወስበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በስሙ ተሰይሞ ማስተማር ጀምሯል። የህንጻ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ በዛሬው እለት ተቀምጧል። ይህን ላደረጉ ሁሉ ዓባይ ሸንጎ ታመሰግናለች።
2) ሃዲስ አለማየሁ ራሳቸው አባል የሆኑበትን ንጉሳዊ ስርዓት በሰላ ብዕራቸው የተቹ ፣ ቀጥሎ የመጣውን ሁሉ አስቀድመው የተነበዩና የመከሩ ፖለቲከኛም ናቸው። ፖለቲካን ከፍቅር እኩል ተራቅቀውበታል።

1) ዶር ድረስ ሳህሉ ጎሹ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመው ቃለ_መኃላ ፈጽመዋል። 2) ባህርዳር ከተማ  ተራማጅ አመራር ከመራት በአጭር ጊዜ መሰረታዊ መሻሻሎችን እና በመካከለኛ ጊዜ ...
16/10/2020

1) ዶር ድረስ ሳህሉ ጎሹ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመው ቃለ_መኃላ ፈጽመዋል።
2) ባህርዳር ከተማ ተራማጅ አመራር ከመራት በአጭር ጊዜ መሰረታዊ መሻሻሎችን እና በመካከለኛ ጊዜ ደግሞ የተሟላ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሏትን እድሎች ይዛለች።
3) ዓባይ ሸንጎ ለከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶር) መልካም የስራ ዘመን ትመኛለች።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዓባይ ሸንጎ - Nile Forum posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share