Neftegna Media

  • Home
  • Neftegna Media

Neftegna Media A media established to be the voice of the Amhara people!

ነፍጠኝነት ደማችን ነው
22/10/2023

ነፍጠኝነት ደማችን ነው

27/09/2023
ነካክተው ነካክተው የተኛውን  በሬ ! አደረጉት አውሬ ! በዚህ ሳምንት የተያዙትን ወረዳ እን ከተማ ሳይጨምር
23/08/2023

ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ ! አደረጉት አውሬ !
በዚህ ሳምንት የተያዙትን ወረዳ እን ከተማ ሳይጨምር

25/04/2023

የአማራን ሀይል ይቀላቀላሉ በሚል ጠመንጃ እንዳይዙ የአማራ ብሔር ተወላጅ ወታደሮች በአዲስ አበባ ተከለከሉ ።

የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ተወላጅ የፖሊስ አባላትን በማሠር ፣በማገድ አንዲሁም በሀሰት ክሴ እየተሰቃዩ እንደሆነ ምንጮቻችን መረጃ ሰጥተውናል ።
ልዩ ሀይሉን ከመበተን ጋር ተያይዞ ስጋት ያደረበት ኦሮሞ መራሹ ብልፅግና በአማራ ተወላጆች ሰበብ የአዲስ አበባ ፖሊስ በዱላ ምሽግ ውስጥ እንደሚያድር መረጃ ዎች እየወጡ ነው በዚህም የተነሳ ለስጋት ተጋልጠናል ብለውናል ።
የአማራ ተወላጆች የአፄ ቴድሮሶን ትሸርት ለብሰሀል በሚል ከስራ እየታገዱ እንዲሁም ውክቢያ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ በመግለፅ ለህዝብ ድምፅ እንድንሆናቸው ጠይቀዋል።

የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደየአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ባለሃብቶችን ለማሠርና ንብረታቸውንም ልክ እንደ ትጥቁ ለማስፈታት ...
25/04/2023

የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ

የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ባለሃብቶችን ለማሠርና ንብረታቸውንም ልክ እንደ ትጥቁ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ትናንት በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወቃል። በኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች የሚመራው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ ዘ-ሐበሻ እጅ ገብቷል። ይህም በኦሮሚያ ብልጽግና እና በአማራ ብልጽግና መካከል ያለውን ሽኩቻ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የብልጽግና ምንጮች ይናገራሉ። ደብዳቤውን ተመልከቱት፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እመጣለን።

በነገራችን ላይ የሞቱ ሰዎችም ጭምር በ እገዳው ስማቸው ተጠቅሷል።

የአማራ ልዩ ኃይል ቁልፍ እሴቶች***በአስተምህሮና በተግባርና የተደገፈው የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ እሴቶች በዘመን ሂደት የሚታደሱና የሚያድጉ እንጅ የሚፈርሱ አይደሉም። የአማራ ፖሊስ (በዋናነ...
09/04/2023

የአማራ ልዩ ኃይል ቁልፍ እሴቶች
***
በአስተምህሮና በተግባርና የተደገፈው የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ እሴቶች በዘመን ሂደት የሚታደሱና የሚያድጉ እንጅ የሚፈርሱ አይደሉም።

የአማራ ፖሊስ (በዋናነት ልዩ ኃይልና አድማ ብተና) የሚከተላቸው ከሙያው፣ ከተቋሙና ከአማራ ሕዝብ ታሪክና ባህል የሚመነጩ መርሆዎችና እሴቶች አሉት፡፡

በግዳጅም ሆነ በእረፍት ወቅት የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ የሚከተሉትን እሴቶች የዕለት ተዕለት ሕይወቱ አካል አድርጎ፣ አክብሮ ያስከብራል።

1) ታማኝነት (Loyalty)፡- ‹‹ተመልከት ዓላማህን ተከተል አለቃህን›› የሚለው አባታዊ ብሂል እንደሚያስገነዝበን የወታደር ተቀዳሚ ታማኝነት ለዓላማው ነው፡፡

ለአማራ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሀገሩ፣ ለሠራዊቱ፣ ለራሱ የጦር ክፍል፣ እንዲሁም አብረውት ለሚፋለሙት ጓዶቹ፣ ለአለቃው፣ ለሙያው የማያወላውል ታማኝነትና እውነተኛ እምነት ሊኖረው ይገባል፡፡ ለወገኑና ለእናት ሀገሩ የሚቆረቆር፣ ሕዝባዊ ወገንተኝነት የተላበሰ ነው።

2) ግዳጅ (Duty)፡- ግዳጅ ማለት ድርሻህን እንደ ቡድን/አሃድ አባል ተቀናጅህ ለመወጣት መቻል ነው፡፡ አንድ የሠራዊቱ አባል የተጣለበትን ሞያዊ፣ ህጋዊና ሞራላዊ ግዳጅ ያለ ማወላወል መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ማናቸውንም የተናጠልና የቡድን ግዳጅ ለመቀበል በሥነ-ሥርዓት የታረቀ፣ በአካልም በመንፈስም ብቁና ዝግጁ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል፡፡

3) ሥነ-ሥርዓት (Discipline)፡- ሥነ-ሥርዓት ወይም ዲሲፕሊን የወታደር ቁልፍ መለያ ባህሪ ነው፡፡ ሥነ-ሥርዓት በግልም ሆነ በቡድን ራስን መግዛት መቻል ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ከሁሉም በላይ ለሕግና ደንብ ተገዥ መሆን ያስፈልጋል፡፡ አዛዦችም ሆነ ወታደሮች በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ፣ በግዳጅ ላይም ሆነ ከግዳጅ ውጭ ለሠራዊቱ ደንቦች ፍጹም ተገዢ መሆንና በህጋዊ ትዕዛዞች መሰረት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ ውትድርና ከፍተኛና ጥብቅ የሥነ-ሥርዓት አክባሪነት ደረጃን ይጠይቃል፡፡

4) አክብሮት (Respect)፡- ወታደር ሕግን፣ የበላይ አለቆችን ፣ ጓዶችንና በአጠቃላይ የሰው ልጆችን ማክበር አለበት፡፡ ወታደራዊ አለቆችና የበላይ አዛዦችን ፍፁም አክብሮት መስጠት ወሳኝ ነው፡፡ በክፉም በደግም አብረው የተሰለፉትንና ህይወታቸውን የሚሰጡልህን ጓዶችህን በፍፁም ወንድምነት ፣ እህትነት በማክበርና እውቅና በመስጠት መተማመንን ለማጎልበትና ለቡድን ስራ አስፈላጊ ነው፡፡

5) መስዋዕትነት (Sacrifice)፡- መስዋዕትነት ማለት ራስን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ ከራስ የላቀ፣ ከግለሰብ በላይ የሆነ ግልጋሎት ነው፡፡ መስዋዕትነት የተልዕኮንና የቡድንን ፍላጎቶች ከግላዊ ፍላጎት ማስቀደም ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአማራ ፖሊስ መዋቅር /ልዩ ኃይልና አድማ ብተና/ ለማንኛውም መስዋትነት ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡

6) ክብር ጠባቂነት (Honor)፡- የታማኝነት፣ ግዳጅ፣ አክብሮት፣ መስዋዕትነት ፣ ጀግንነት የመሳሰሉትን የሠራዊቱን እሴቶች በምናደርገው ነገር ሁሉ መፈፀም ፣ መወጣትና መኖር ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ክብር ጠባቂነት የእሴቶች ሁሉ ማሰሪያ ነው፡፡

7) ጀግንነትና አርበኝነት (Courage & Patriotism)፡- ጀግንነት ማለት አካላዊ ወይም ሞራላዊ አደጋን፣ ችግርን ወይም ፈተናን ያለ ፍርሃት የመጋፈጥ ዝግጁነትና ብቃት ነው፡፡ አካላዊ ድፍረት በአካላችን ላይ ሊመጣ የሚችለውን እንደ ፍርሃትና ድካም ያለውን ጫና ለመጋፈጥና ለመቋቋም ያለ ዝግጁነት ነው፡፡ ሞራላዊ ድፍረት ደግሞ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ትክክለኛውን ነገር ለመፈፀም ያለ ቁርጠኝነት ነው፡፡ ሞራላዊና አካላዊ ድፍረት የውጊያ መንፈስ የሚገነባበትንና የግዳጅ ስኬት የሚወሰንበትን ጥንካሬ ይፈጥራል፡፡ የሞራል ፍርሃትን ወይም መከራን መጋፈጥ ከአካላዊ ድፍረት ላቅና ጠለቅ ያለ ወኔን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ጀግንነት ምሉዕ የሚሆነው ሁለቱም አካላዊና ሞራላዊ ድፍረቶች ሲደጋገፉና በሀገራዊ የአርበኝነት መንፈስ ሲታቀፉ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአማራ ፖሊስ መዋቅር (ልዩ ኃይልና አድማ ብተና) ለማንኛውም ግዳጅ በጀግንነትና በአርበኝነት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው።

8) ገለልተኝነት (Impartiality)፡- ሰራዊቱ እንደ ተቋም ከፖለቲካ ፣ ከእምነት፣ ከቡድናዊ ወገንተኝነትና ዝንባሌዎች ገለልተኛ የሆነና ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ ለሕግና ለሕዝብ ብቻ የቆመ መሆን አለበት፡፡ ለየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ለገዥውም ሆነ ለተቃዋሚው ጥቅም አስጠባቂ አለመሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

9) አንድነት (Unity)፡- የአማራ ልዩ ኃይል የአማራ ሕዝባዊ አንድነት ተምሳሌት መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በአስተሳሰቡም በድርጊቱም ከማናቸውም የአካባቢ፣ የእምነት፣ የባህልም ሆነ የዘውግ ልዩነት በላይና መላውን የአማራን ሕዝብ፣ በውስጡ ያቀፋቸውን ጨምሮ አካታችነት ባለው ሁኔታ የሚወክልና የክልሉን አንድነት በተግባር ያረጋገጣል።

10) የሀገር አድን ዘመቻ ቀዳሚ ተሰላፊነት፦ የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ፈተና ውስጥ በሚወድቅ ጊዜ ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፌዴራልና የክልል ልዩ ኃይሎች ጎን ተሰልፎ ሀገር የማዳን ሕዝባዊ አደራውን ይወጣል። በመታወቂያ ሥሙ የአማራ ልዩ ኃይል በግብሩ የኢትዮጵያ ዘብ፤ የመከላከያ ሠራዊት መከታ ጠባቂ ወንድም ሆኖ ሁልጊዜም ምንጊዜም ከጎኑ ይሰለፋል።

ትላንትም ዛሬም ነገም...
በሰብዓዊነት ማገልገል፤ በጀግንነት መጠበቅ!!

ሦስት ነገሮች፩. በዛው ሰሞን 'አፈነገጠ' እየተባለ ሲወራለት     የነበረው አብርሃ ድንኩል በሽራሮ ገጠራማ አካባቢዎች ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ ነው። ብ/ጀኔራል ምግበ ለከተማ ውጊያ ብቁ የ...
07/04/2023

ሦስት ነገሮች

፩. በዛው ሰሞን 'አፈነገጠ' እየተባለ ሲወራለት
የነበረው አብርሃ ድንኩል በሽራሮ ገጠራማ አካባቢዎች ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ ነው። ብ/ጀኔራል ምግበ ለከተማ ውጊያ ብቁ የሆኑ ኮማንዶዎችን 'ለልዩ ተልዕኮ' በሚል እያሰለጠነ ነው። ሎጀስቲክስ አሳላጩ ሌ/ጀኔራል ፍስሃ ኪዳነ (ማንጁስ) ነው። ሀሳብ አፍላቂዎቹ ታደሰና ፃድቃን ናቸው። ለነገሩ ጀኔራል ኃይለስላሴ (ወዲ እምበይተይ) ም ከዊልቸር ላይ ሆኖ ሀሳብ ከመሰንዘር እንዳልቦዘነ ነው የምንሰማው።

፪. በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በመወጠር ክልሉን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ማስገባት የሚፈልገው ኃይል ውጣሬውን ገፍቶበታል።

በአጭር አማርኛ፣ በፌዴራል-ኦሮሚያ በኩል ቀውሱን በማስፋት ክልሉን በወታደራዊ አመራር የመጠቅለል ብርቱ ፍላጎት አለ።

፫. የወልቃይት-ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ የቀድሞ ሲቪል ሰርባንቶችን የከረመ ደመወዝ በሚል ስም ለማማለል ከመቀሌ ሴራ እየተቀመረ እንደሆነ መረጃዎች አሉ። ይህ ሁነት አደገኛ ኃይል መበተኛ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። በአንድ ጎን በጀት ከልክሎ ለወንበዴው በመፍቀድ ወንበዴው ለአዲሱ የፖለቲካ ቁማር አቅም መፍጠር ዓላማው ግልጽ ነው።
***
ሲጠቃለል አማራ ክልልን ወደአደገኛ ቀውስ የማስገባት ግልጽ ፍላጎቶች አፍጥጠው መጥተዋል።

ሁኔታዎችን ለመቀልበስ በሳል የፖለቲካ አመራር ይጠይቃል። ታሪክ ቀያሪነት በድሎት ውስጥ እውን አይሆንም።

ምርጫ አንድ፦

የብልጽግና ሥራ አስፈፃሚ አሳለፈ የተባለውን ጊዜውን ያልጠበቀ የልዩ ኃይል ብተና ውሳኔ reconsider ማድረግ። ውሳኔውን መቀልበስ።

ምርጫ ሁለት፦

አሁን ያለው የፀጥታ ውጣሬ እየገፋ ሂዶ ወደለየለት ቀውስ ሲገባ ልዩ ኃይሉ ከአማራ ሕዝብና ሌሎች አጋር አካላት ጋር ሆኖ ለነፃነት ሲፋለም፤ የክልሉ አመራር በተቃራኒ በመቆም ክልሉን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም በወታደራዊ አመራር ስር እንዲወድቅ አልመው ለሚሰሩ ቁማርተኞች ቢሮውን ማስረከብ።

ምርጫው የናንተ ነው።
***

የአማራ ልጆችና የአማራ ወዳጆች

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ወደሆኑ ቤተሰቦቻችሁና ወዳጆቻችሁ በእጅ ስልኮቻቸው በኩል አጫጭር መልዕክቶችን ላኩ፦

ለምሳሌ፦

"በሰሜን ዕዝ ሰማዕት ስም፣ አንድም የመከላከያ አባል ወደልዩ ኃይሉ አፈሙዝ እንዳያዞር። ጠባቂህ ወንድምህ ነው። ሰከን በል"

የሚል ይዘት ያለው የጽሑፍ መልዕክት ወደሰራዊቱ አባላት ላኩ። ይህ ወንድም ለወንድሙ ከሚያደርገው ምክርም ሆነ ራሮት እጅግ ጥቂቱ ነው። እናም ስልካችሁን አሁኑኑ አንሱ፤ መልዕክቱን ላኩ።

('ልዩ ኃይሉ ጀርባህን ልትሰጠው የሚገባ ጠባቂህ ወንድምህ ነው' የሚለው ኃይለ ቃል እንዳይዘነጋ!)

ፒላር የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ሊነኩ የሚችሉት በሀገራዊ ምክክሩ  ነው ብለን እናምናለን። ይህ ሳይሆን በፖለቲካ ውሳኔ ከባባድ ሀገራዊ ውሳኔዎችን በማን አለብኝነት ገዢው ፓርቲ እየወሰነ ከሆነ  ...
07/04/2023

ፒላር የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ሊነኩ የሚችሉት በሀገራዊ ምክክሩ ነው ብለን እናምናለን። ይህ ሳይሆን በፖለቲካ ውሳኔ ከባባድ ሀገራዊ ውሳኔዎችን በማን አለብኝነት ገዢው ፓርቲ እየወሰነ ከሆነ ሌሎች ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ለምሳሌ የማንነት ጥያቄ የተነሳባቸው አካባቢዎችንም ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ሊወሰንላቸው ይገባል።
ስለ ፍትህ የሚወሰድ እርምጃ ፅድቅ ነው!

"ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም"➕✳✳✳✳✳✳✳✳➕ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 23-2013 ዓ.ም ለጥቅምት 24 አጥቢያ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ሽበርተኛው ሕወሀት በክህደት ጥቃት ...
23/03/2023

"ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም"
➕✳✳✳✳✳✳✳✳➕
ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 23-2013 ዓ.ም ለጥቅምት 24 አጥቢያ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ሽበርተኛው ሕወሀት በክህደት ጥቃት መፈጸሙ ሁሌ የሚታወስና ፈፅሞ የማይዘነጋ እለት ነው።

እለቱን ስናስብ ለአመታት ቤት ንብረታቸውን ትተው የአገርን ዳር ድንበር እና ሉአላዊነት ለማስከበር ሐሩር እና ቁሩ ሳይበግራቸው በቀበሮ ጉድጓድ የቆዩት እና የትግራይ ሕዝብ ችግር ችግሬ ብለው ካላቸው እያካፈሉ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮቹን ከማንም ቀድመው ሲጋፈጡ የኖሩ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ጭካኔ በአሸባሪው ህዋሃት ባልጠበቁት እና ባላሰቡት ሰዓት የተካዱና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸውን ጀግኖች ሰማዕቶቻችንን በልባችን ታትመዋልና መቼም አንረሳቸውም! ትውልድም ሲዘክራቸው ይኖራል።

ዘንድር ለሁለተኛ ጊዜ እለቱን "ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል ስንዘክር ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የተዘረጋለትን የሰላም እጅ ገፍቶ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ ሕወሀትን ወረራ በመቀልበስና የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት እኒያ ክህደት የተፈጸመባቸውን ሰማዕታት አደራ በጀግንነት በወጣት ላይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ከፍ ብላለች!

ዛሬም በሀገር ወዳድ ልጆችዋ ሉዓላዊነትዋ መከበሩን ሰንደቅዋ ከፍ ብሎ መውለብለቡን ቀጥሏል! ጀግኖቻችንን እያመሰገንን እነሱ በደማቸው ያጸኗትን ሀገር ሌት ተቀን ሰርተን ድህነትን ተፋለመን በማሸነፍ የሀገራችንን ነጻትና ሉዓላዊነት እናጸናለን።

የኛ የነፍጠኞቹ በዓልእንኳን አደረሳችሁ !! ነፍጠኝነት የነፃነታችን ሚስጥር ነው ።
01/03/2023

የኛ የነፍጠኞቹ በዓል
እንኳን አደረሳችሁ !!
ነፍጠኝነት የነፃነታችን ሚስጥር ነው ።

ሸኽ ጦልሀ ጃዕፈርና አፄ ምኒልክ››››››››››››››››››››››››››የአጼ ዮሀንስን ስሁት የሀይማኖት ፖሊሲ በመቃወም ስለሀይማኖታቸዉ ክብርና ነጻነት ለመታገል በረሀ ከገቡት ሙስሊም ነፍጠ...
01/03/2023

ሸኽ ጦልሀ ጃዕፈርና አፄ ምኒልክ

››››››››››››››››››››››››››

የአጼ ዮሀንስን ስሁት የሀይማኖት ፖሊሲ በመቃወም ስለሀይማኖታቸዉ ክብርና ነጻነት ለመታገል በረሀ ከገቡት ሙስሊም ነፍጠኞች መካከል ሸኽ ጦልሀ ጃዕፈር አንዱ ሲሆኑ አፄ ዮሀንስ መተማ ላይ ተገድለዉ በምትካቸዉ አጼ ምኒሊክ ሲነግሱ እንዲህ ሆነ፣

አጼ ምኒሊክ የመስተዳድራቸዉ የማእዘን ዲንጋይ የሆነዉን የሀይማኖት ነጻነት ‹‹እስላምም ሆነ ክርስቲያን ያባቱን ሀይማኖት ይከተል›› በማለት ፈጥነዉ አወጁ። ሌሎች ጠቃሚ እርምጃዎችንም ወስደው ሀገር አረጉ፡፡ በአጼ ዮሀንስ ፖሊሲ ምክንያት ነፍጥ ያነሱ ሙስሊሞች ወደሰላማዊ ህይወታቸዉ መመለስ ጀመሩ፡፡ ሸኽ ጦልሀ ግን እንደሸፈቱ ናቸዉ፡፡ በአጼ ምኒሊክ ሠራዊት ላይ ዉስን የደፈጣ ጥቃቶች መፈፀማቸዉም ይነገራል፡፡ በመሀሉ ጣልያን ሀገራችንን በመዉረሩ የአድዋ ዘመቻ ሆነ፡፡ አጼዉ በድል እንደተመለሱ ሸኽ ጦልሀን ለመዉጋት 30 ሺ ህል ሠራዊት ሸኹ ወዳሉበት ሥፍራ አዘመቱ፡፡ ይህን የሰሙት ሸኹ የጦር አማካሪዎቻቸዉን ሰብስበዉ ምክክር ያዙ፡፡ ‹‹ምኒሊክ ጦር አዠምቶብናልና ምን እናዳርግ?›› በማለትም ጠየቁ፡፡ በወቅቱ የተሰጣቸዉ ምላሸ ‹‹ኢእላሙል አግቢያእ›› ከተሰኘዉ የሸኸ ሙሀመድ ታጁዲን ግሩም የታሪክ ድርሳን /ኪታብ/ ዉስጥ ገጽ 501 ላይ እንዲህ ሰፍሯል፡-

إننا كنا خرجنا لنقاتل لديننا والدفاع عنه، وهذا الملك قد أعلن بحرية الديانة فما لنا وللقتال

‹‹ቀያችንን ጥለን የወጣነዉ ስለሀይማኖታችን ለመፋለምና ለመከላከል ነበር፤ ሆኖም ይህ ንጉስ የሀይማኖት ነጻነትን ስላወጀ እምንዋጋበት ምክንያት የለም፡፡››

ሸኹ በዚህ ሀሳበ ተስማሙ፡፡ ጦራቸዉ እንዲያፈገፍግም አዘዙ፡፡ ዉጊያ ሳይደረግ ቀረ፡፡ ከዚህ በኋላ በሊቃዉንት አሸማጋይነት ከዳግማዊ ምኒሊክ ጋር ታረቁ፡፡ በመጀመሪያ ኢፋት፣ ቀጥሎም ጨርጨር የሚባል ቦታ በእርስትነ ከንጉሱ ተሰጣቸዉና ሞት እስኪለያያቸው ድረስ የአጼ ምኒሊክ ወዳጅና ባለሟል ሆነዉ ኖሩ፡፡

ይህ ታሪክና የነሸኽ ጦልሀ እጅግ ጠቃሚ ምስክርነት ሚከተሉትን ቁምነገሮች ያስጨብጠናል፡-

1) የሀይማኖት ነጻነት የዳግማዊ ምኒሊክ ሥርአተ መንግስት መሠረታዊ ፖሊሲ መሆኑን፣

2) ይህ ፖሊሲ የአንድ ሰሞን ፋሺን ሳይሆን ቀጣይነት ያለዉ ወይም ቋሚ እንደነበር፡፡ ምክንቱም እንደዚያ ባሆንማ ኖሮ ለሀይማኖታቸዉ እጅግ ቀናኢ የነበሩት የአርጎባዉ ነፍጠኛ ሸኽ ጦልሀና ባልንጀሮቻቸዉ ከአጼ ምኒሊክ ጋር በወዳጅነት ጸንተዉ አይቆዩም ነበር፡፡

3) ሸኽ ጦልሀ ጃዕፈርና ባልንጀሮቻቸዉ የዚያ ዘመን ሙስሊም ሊቃዉንት ኃይማኖታቸዉ እንደተነካ እርግጠኛ የሆኑበትን ሥርዓት ተፋለሙ፤ሁኔታዎች በጎ አቅጣጫ መያዛቸዉን ሲገነዘቡ ወደመደበኛ ሥራቸዉ ተመለሱ እንጅ ከታሪክ አሉታዊ ትዉስታዎች ላይ ተቸንክረዉ ‹‹በቆሞ ቀርነት›› ሲብከነከኑ አልተስተዋሉም፡፡ ከዚህም አልፈዉ የሀይማኖት ነጻነትን ያከበረላቸዉ ሥርዓት አካል በመሆን በአገር አስተዳደርና ግንባታ ሂደት የድርሻቸዉን ተወጡ፡፡ ሀገር የምትጸናዉና ማህበረሰብ ለደህንነቱና አብሮነቱ ዋስትና የሚያገኘዉ በእንዲህ ዓይነት ሚዛናዊ ንጻሬዎች ነዉ፡፡

4) የሙስሊም ሊቃዉንት እማኝነት የተቸረዉን የዳግማዊ ምኒሊክ የኃይማኖት ፖሊሲ ከርሳቸዉ በኋላ ከመጡት ሥርዓቶች የሀይማኖት አያያዝ፣ በተለይም የኢህአዴግና የብልጽግና መንግስታት ከሀይማኖቶች አኳያ ከተከተሏቸዉ አቅጣጫዎች ጋር ስናነጻጽረዉ ‹ጥቁሩ ሰዉ› በዚህ ረገድም ዘመን ቀደም እንደነበሩ እንገነዘባለን፡፡

ለማጠቃለል፣ የአድዋ ድል የአጼውን ወታደራዊ ስኬቶችና የዲፕሎማሲ ጥበቦች ብቻ ሳይሆን በሀገር ምሥረታ ረገድ የተከተሉትን አቅጣጫ በመመርመር ትምህርት ለመቅሰም ጥሩ አጋጣሚ ነዉ፡፡

የመረጃ ምንጭ፡- (ኢዕላሙል አግቢያእ፣አበልቃሲም ሙሀመድ ታጁዲን፣ዳረል ዲያእ አሳታሚ፣ኩዌት፣የመጀመሪያ ዕትም፣2022፣ ገጽ 498-504)
#በኡስታዝ ሃሰን ታጁ!

የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአፋጣኝ እንዲያስቆም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ይጠይቃል፣****...
03/12/2022

የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአፋጣኝ እንዲያስቆም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ይጠይቃል፣
********
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች የአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ የዘር ጭፍጨፋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየሰፋ ይገኛል:: የኦሮሚያ ክልል መንግስት በወለጋ እና ሌሎች አካባቢዎች በንፁሃን አማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ እገታ እና ንብረት ዝርፊያ ለማስቆም ፍላጎት እና አቅም እንደሌለው በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል፣ ቀላል የማይባለው የክልሉ መዋቅርም የጭፍጨፋው ተሳታፊና ሽፋን ሰጭ ሆኗል ። ጭፍጨፋው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ በዚህ ሳምንት እጅግ አደገኛ ወደ ሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል። የክልሉ መንግስት ክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ማንነት፣ ዘር እና ኃይማኖት ሳይለይ እኩል የመጠበቅ እና ከለላ የመስጠት መንግስታዊ ግዴታውን መወጣት ሳይችል ቀርቶ የአማራ ተወላጆች በተለይ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ይገኛል። ስለሆነ የፌድራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ማስቆም እና ጥፋተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ሲል አብን በጥብቅ ያሳስባል። የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል አመራሮች ላይ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ አብን እያሳሰበ የወገኖቻችንን ሕይወት ለመታደግ ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ባለባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት በፍጥነት ማሰማራት እንዳለበት አብን ያሳስባል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እና ዝርዝር መረጃ በማሰባሰብ ላይ ሲሆን፣ በቅርቡም ሰፋ እና ዘርዘር ያለ መግለጫ የሚያወጣ መሆኑን እያሳወቅን ችግሩ በፍጥነት እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚችለውን ሁሉ ማድረጉን የሚቀጥል ይሆናል።

ሰበር ዜና!በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ከተማ ከ50 በላይ የሚሆኑ እስረኞች በጅምላ መረሸናቸው ተሰማ!ነፍጠኛ ሚዲያህዳር 22/215 ዓ/ምበኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የጊዳ ኪረሙ ወረዳ መቀመጫ...
01/12/2022

ሰበር ዜና!

በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ከተማ ከ50 በላይ የሚሆኑ እስረኞች በጅምላ መረሸናቸው ተሰማ!

ነፍጠኛ ሚዲያ
ህዳር 22/215 ዓ/ም

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የጊዳ ኪረሙ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ኪረሙ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳያውሉ እንቅፋት ፈጥራችኋል በሚል ታስረው የነበሩ ከ50 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች በጅምላ መረሸናቸውን ከጅምላ ጭፍጨፋው አምልጠው የወጡ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

ከህዳር 09/2015 ዓ/ም ጀምሮ በከተማዋ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታስረው የነበሩ ከ50 በላይ የሚሆኑት እስረኞች በጅምላ እንደተረሸኑ የአማራ ድምፅ ከጅምላ ጭፍጨፋው አምልጠው ከወጡ የአይን እማኞች እና ከከተማው ነዋሪዎች አረጋግጧል።

ህዳር 09/2015 ዓ/ም የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች በከተማዋ የአማራ ተወላጆችን ያደራጃሉ፣ያሰለጥናሉ በሚል የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ፡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ለምን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው በዚህ መካከል በተፈጠረ አለመረጋጋት 32 ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ድምፅ መዘገቡ አይዘነጋም።

በእለቱ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳናውል አስተጓጉለውናል ያሏቸውን ከ50 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆችን በከተማዋ በሚገኘው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማሰራቸውን ነዋሪዎቹ ሲገልፁ ሰንብተዋል።

ከእስረኞቹ መካከልም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ህፃናት፣ሴቶችና አዛውንቶች መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ በእለቱ አመላክተው ነበረ።

በህግ ጥላ ስር የዋሉ ሰዎች እንዴት ይረሸናሉ በሚል ህዳር 20/2015 ዓ/ም ወደ አደባባይ የወጡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ተኩስ መክፈታቸው ተገልጿል።

ህዳር 20/2015 ዓ/ም አመሻሹን ጀምሮ ተጨማሪ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ወደ ከተማዋ የገቡ ቢሆንም፡ ነገር ግን አለመረጋጋቱ ተባብሶ ተጨማሪ ቁጥራቸው በውል የታወቀ 15 የአማራ ተወላጆች ሲገደሉ ከ26 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለው ህክምና አለማገኘታቸውንም የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

በከተማዋ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ በማስወጣት ተረሸኑ ከተባሉት 50 በላይ ሰዎች በተጨማሪ በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እና የአማራ ተወላጅ በሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ህዳር 09/2015 ዓ/ም 32 ሰዎች፡ በተመሳሳይ ህዳር 21/2015 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ 15 ሰዎች ተገድለዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፡ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ግዜ በድምሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን ነው ያመላከቱት።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተፈጠረው አለመረጋጋት አለመብረዱን የገለፁት የአይን እማኞቹ፡ በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ የአባይ በርሃን አቆራርጠው ወደ አማራ ክልል ምእራብ ጎጃም ዞን እየተጓዙ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

በመጨረሻም ነዋሪዎቹ፡ የአባይን ድልድይ ከተሻገሩ ቦኋላ መንገዱ ሰላም መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን በአማራ ክልል የሚገኙ የህዝብ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ ህይወቱን ለማትረፍ እየሸሸ ያለው ህዝብ አባይ ድልድይ ድረስ በመምጣት የትራንስፖርት ትብብር እንዲያደርጉላቸው ተማፅኖ አቅርበዋል።

ከስፍራው ያደረሰን ዘጋቢ ሁኔታው በጣም አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀውልናል

በወረዳው አመራሮች ትዕዛዝ በተከፈተ ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ተገደሉ!(የአማራ ድምፅ/ህዳር 13/2015 ዓ/ም)በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀሮ ቡሉቅ እና ጃር...
22/11/2022

በወረዳው አመራሮች ትዕዛዝ በተከፈተ ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ተገደሉ!

(የአማራ ድምፅ/ህዳር 13/2015 ዓ/ም)
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሀሮ ቡሉቅ እና ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ዛሬ ህዳር 13/2015 ዓ/ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በተከፈተ ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች የተገደሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ህይወታቸውን ለማትረፍ እግር ወዳመራቸው እየሸሹ መሆናቸውን ለአማራ ድምፅ ተናገሩ።

ጥቃቱ ዛሬ እንደሚጀመር የወረዳው አመራሮች የኦሮሞ ተወላጆችን ትናንት ህዳር 12/2015 ዓ/ም ለብቻ ሰብስበው "የአማራ ተወላጆችን ከነገ ጀምሮ ከአከባቢው ማፅዳት አለብን" የሚል መመሪያ ማስተላለፋቸውን የአማራ ድምፅ ምንጮች በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፈው አረጋግጠዋል።

የወረዳው አመራሮች ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት ጥቃቱ ዛሬ ህዳር 13/2015 ዓ/ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በሀሮ ቡሉቅ ወረዳ ልዩ ስሙ ሰንቀሌ በተባለ አከባቢ የተከፈተ ሲሆን ጥቃቱ ወደ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ መስፋፋቱንም የአማራ ድምፅ ምንጮች ገልፀዋል።

ጥቃቱ በሁለት አቅጣጫ እንደተከፈተባቸው የሚገልፁት የአይን እማኞቹ፡ በአንድ በኩል የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ ልዩ ኃይሎች የአማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ግድያ እየፈፀሙ መሆናቸውን አመላክተዋል።

በሁለቱ ኃይሎች በተከፈተው ጥቃት እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልተለየ በርካታ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ያሉት የአይን እማኞቹ፡ ከዚህ በተጨማሪ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውንም ጠቁመዋል።

ጥቃቱ በተከፈተባቸው ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ህይወታቸውን ለማትረፍ እግር ወዳመራቸው እየሸሹ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን የፌደራሉ መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ተማፅኖ አቅርበዋል።

ምንጭ ጌትነት አሻግሬ

የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለንግድ ባንክ ይህን ደብዳቤ ፅፏል‼️የፋይናንስ ተቋም ፖለቲካ ላይ ገብቶ መፈተፈት አልነበረበትም።ለማንኛውም መልሱን በጉጉት እየጠበቅን ነው።
14/11/2022

የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለንግድ ባንክ ይህን ደብዳቤ ፅፏል‼️የፋይናንስ ተቋም ፖለቲካ ላይ ገብቶ መፈተፈት አልነበረበትም።ለማንኛውም መልሱን በጉጉት እየጠበቅን ነው።

14/11/2022

እረፍት ያጣው አማራ እረፍት አግኝቷል።

"የይቱብ ጡረተኞች ተውን ስራችንን እንስራበት "

አጀንዳችንን ሌሎች ባልተሰሩ የቤት ስራዎቻችን ላይ እንድናቶክር እድል ስጡን።

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አ...
10/11/2022

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መፍትሔ እንዲያገኙ:_

1) በግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም፣
2) ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም፣
3) ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም፣
4) ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም፣
5) ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም፣
6) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም፣
7) ጳጕሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም፣
8) መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም፤
9) መስከረም 20 ቀን 2005 ዓ.ም፣
10) መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም
11) ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በማውጣት የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲሰጡት ሲያሳስብ መቆየቱን አውስቷል።

ይሁን እንጅ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ዜጎች ለከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ዝርፊያና መውደም፣ ለእገታና መፈናቀል እየተዳረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡

1) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ ጽጌ ከተማ በጥቅምት ዐ8 እና 09 ቀን 205 ዓ.ም የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ንብረት ውድመት መድረሱን

2) በተመሳሳይ ጥቅምት 19 ቀን 205 ዓ.ም ከጊዳ አያና ወደ ነቀምት በሚወስደው መንገድ ላይ በህዝብ ትራንስፖርት ሲጓዙ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በአሁን ሰዓት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ከጥቅምት 2 ቀን 205 ዓ.ም ጀምሮ ከነቀምት ወደ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና አሶሳ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ቦታዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን መዘጋቱን እንዲሁም

የተዘጉ መንገዶችን እና በታጣቂ ቡድኑ የተያዙ አካባቢዎችን ለማስለቀቅ በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግስት የጸጥታ አካላት መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ ንጹሀን ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ከዓመታት በፊት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩና አንጻራዊ ሰላም አለ ብለው ወደ መኖሪያቸው በተመለሱ የጊዳ አያና ወረዳ ፊት በቆ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ በታጠቁ ቡድኖች ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑንም ገልጧል።

3) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሑሩታ ዶሬ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ/ም በሸኔ ታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም እንዳሉና የቀበሌው ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኙ፣

4) በተመሳሳይ በጀጁ ወረዳ አምሻራ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ 8 ሰዎች በሸኔ መገደላቸውን እንዲሁም

5) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ፣ አዲስ ህይወት፣ መንበረ ህይወት፣ ተስፋ ህይወት፣ መርቲ እና አጫሞ ቀበሌዎች የሚኖሩ _ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂ ቡድኑ ተከበው በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን፣

6) በተጨማሪም ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ 5 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂ ቡድኖች መገደላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡

7) በምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የሸኔ ታጣቂዎች በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ 4 ሰዎችን አግተው ከወሰዷቸው በኋላ እያንዳንዳቸው ሶስት መቶ ሺህ ብር (300.000) ካመጡ ከእገታው እንደሚለቀቁ ተገልጾላቸው የታጋቾች ቤተሰቦችም ገንዘቡን አሰባስበው ሲሄዱ የታገቱት ሰዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ወሊሶ ፖሊስ ጣቢያ አስከሬናቸው እንደተገኘና ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አስከሬናቸው ዘመዶቻቸው ወደሚገኙበት ተወስዶ የቀብር ስነ ስርዓታቸው መፈጸሙን ኢሰመጉ ለማወቅ ችሏል፡፡

8) በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሸኔ ታጣቂዎች ነቀምቴ ከተማ በመግባት ንጹሃን

ሰዎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዝርፊያና ሰዎችንም አግተው በመውሰድ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች

ለመረዳት ችሏል፡፡

9) ጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው የፍጥነት መንገድ ላይ ወደ መቂ ከተማ አካባቢ ታጣቂዎች በመንገዱ ሲጓዙ በነበሩ መኪናዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ጥቃት እንደፈጸሙ እና በዚሀም ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ አካል ጉዳት መድረሱን እና በመንገዱ ሲጓጓዚ የነበሩ አንዳንድ መኪናዎቸ መቃጠላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

10) በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊሚቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች ከሚኖሩበት አካባቢ ከ800 በላይ አባወራዎችን የሸኔ ታጣቂ ቡድን ወደ አካባቢው መጠጋቱን እና ከቦ መያዙን ተከትሎ መንግስት በፌደራል ፖሊስ በማጀብ ወደ ሌላ የጸጥታ ሁኔታው ወደሚሻልበት ቦታ ይዞአቸው መሄዱን ኢሰመጉ መረጃ መሰብሰቡን ገልጧል።

በመጨረሻም ኢሰመጉ ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ የአካባቢዎቹ የደህንነት ሁኔታ ምቹ ሲሆን ሰፋ ያለ የምርመራ ስራን በመስራት ዝርዝር ዘገባን እንደሚያዘጋጅ ገልጧል፡፡

ነፍጠኛ ሚዲያ
ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣ ********የኢትዮጵያ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ጋር...
09/11/2022

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣
********

የኢትዮጵያ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ጋር ሲያደርግ የነበረውን የሰላም ንግግር በተመለከተ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሂደቱን በንቃት እየተከታተለ እና አቋሙን በየጊዜው እያሳወቀ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአሸባሪው ትሕነግ መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገው የሰላም ሥምምነት ውል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተረጋገጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ያጋሩትን የሥምምነት ሰነድ ፓርቲያችን አብን ለመመልከት ችሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህን ባለ አስራ አምስት አንቀጽ ሆኖ የተዘጋጀውን የሰላም ሥምምነት ውል በጥንቃቄ እና ጊዜ ወስዶ የመረመረ ሲሆን ፣ ፓርቲያችን አቋም ለያዘባቸው ጉዳዮች በከፊል ምላሽ የሰጠ እና ሥምምነቱ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ያሉት መሆኑን ለመረዳት ችሏል፡፡ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር እያለ የሚጠራው ቡድን ከአምስት አስርት ዓመታት ጠመንጃ አንጋችነት ታሪክ በኋላ፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ትጥቅ ለመፍታት መፈረሙ እና በ30 ቀናት ውስጥ ትጥቁን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለማስረከብ ሥምምነት ላይ መደረሱ በሥምምነቱ መሰረት ከተፈጸመ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ የታሪክ እጥፋት መሆኑን እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክት እና በሽብር ቡድኑ እግታ ውስጥ ለቆየው እና ላለው የትግራይ ሕዝብም እፎይታ የሚሰጥ እንደሚሆን ፓርቲያችን አብን ያምናል፡፡

ሥምምነቱ በአፍሪካ ሕብረት ስር “ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” በሚል መርህ ፣ በአፉሪካ ለአፍሪካውያን የተሰራ መሆኑ እና በአፍሪካውያን ክትትል ስር ብቻ ተግባራዊ እንዲደረግ ሥምምነት የተደረሰበት አግባብ አጋጣሚውን ተጠቅመው ሀገራችን ኢትዮጵያን በማያቋርጥ ግጭት ውስጥ ለመዝፈቅ እና የቀውስ ማዕከል ለማድረግ የተሰለፉ ጠላቶቻችንን መመከት ያስቻለ እና መላው አፍሪካ ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ስርዓት (Neocolonialism)ነጻ ለመውጣት ለሚያደርገው ተጋድሎ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ ክስተት መሆኑን ፓርቲያችን ያምናል፡፡ ታጣቂ ቡድኑ የአፍሪካ የሕግ ማዕቀፎችን እና የኢትዮጵያ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ እውቅና ለመስጠት ሥምምነት ላይ መድረሱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ሀገራዊ ፈተና ሆኖ የዘለቀውን የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ለመመከት የሚያስችል በመሆኑ ፓርቲያችን አብን እውቅና የሚሰጠው ታላቅ ሀገራዊ ድል ነው፡፡

በሰላም ሥምምነቱ ላይ ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ሕዳር 3 ቀን 2020 ዓ.ም) ስለመሆኑ እውቅና ማግኝቱ ፤ የሽብር ቡድኑ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ መሰል የሽብር ቡድኖች ስምሪት ላለመስጠት ፣ ላለማገዝ እና ላለመተባበር ግዴታ የገባበት መሆኑ ፤ ሥምምነቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሕግ አግባብ በሽብርተኝነት በተፈረጀ አንድ ታጣቂ ቡድን መካከል የተደገረ ስለመሆኑ የተረጋገጠበት መሆኑ ፤ የሽብር ቡድኑ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱ እና የሰላም ንግግር መድረኩን ወደ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ለመቀየር የተደረገው ጥረት የከሸፈበት መሆኑ ከሚጠቀሱ የሥምምነቱ ጠንካራ ጎኖች ውስጥ ናቸው፡፡ ይሁንና የሰላም ሥምምነቱ እጥረቶች ያሉበት ስለመሆኑም ፓርቲያችን ለማስተዋል ችሏል፡፡

ፓርቲያችን አብን የሀገር አንድነትን ለማጽናት እና ለዘላቂ ሰላም ሲባል በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚችሉ አንዳንድ እርምጃዎች ላይ ተቃውሞ የማይኖረው ቢሆንም፣ ከምስረታ ሰነዱ ጀምሮ አማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ኁልቆ መሳፍርት የሌለው መከራ በሕዝባችን ላይ ያደረሰን ፣ ፋሽስታዊ የፖለቲካ ፕሮግራምን እና ሽብርን የፖለቲካ ግብ ማስፈጸሚያ አድርጎ የቀረጸን “ነጻ አውጭ” ድርጅት የፖለቲካ ኅልውና ለማስቀጠል የተደረሰው ሥምምነት ፣ ሥምምነቱ የታለመለትን “የሀገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት የማክበር” መርህ የሚጣረስ እና ለሀገራችን ሰላም እና አንድነት ቀጣይ ስጋት እና አደጋን የሚጋርጥ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ስህተት ነው፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክም ሆነ በሌሎች ሀገሮች የፖለቲካ ታሪክ እንደሚታወቀው “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ሽብርን እንደ ሁነኛ የፖለቲካ ትግል መሳሪያ አድርገው የሚጠቀሙ በመሆናቸው ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ቁሚያለሁ በሚል ማንም ሀገር እና መንግስት ሕጋዊ እውቅና የማይሰጣቸው እና በሕገወጥነት ተፈርጀው ኅልውናቸውን ለማክሰም እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም አሁን ትጥቅ ለመፍታት የተስማማውን ትሕነግ ጨምሮ ሌሎች “ነጻ አውጭ ግንባሮች” በሀገራችን የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ከተከሰቱበት ያለፉት አምስት ዓስርት አመታት ወዲህ በሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸው የሩቅ እና የቅርብ ትዝታችን ብቻ ሳይሆን ፣ አሁንም እየኖርንበት ያለ ሃቅ ነው፡፡

ሌላው የሥምምነቱ እጥረት ሆኖ ሊቆጠር የሚችለው የሽብር ቡድኑ የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሳባቸው የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና አማራዊ ማንነታቸውን ለማስጠበቅ ብርቱ ትግል በማድረጋቸው ለዘር-ማጥፋት ድርጊት ተጋልጠው የቆዩትን የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች በሚመለከት የሰፈረው የስምምነት ቃል ነው፡፡ አካባቢዎቹ በስምምነቱ የመሸጋገሪያ ተግባራት ድንጋጌ (Transitional Measures) አንቀጽ 10(4) ስር ራሳቸውን ችለው የሚታዩ ስለመሆኑ የሥምምነት ቃል መስፈሩ ለጊዜው እፎይታ የሚሰጥ ፣ በትግራይ (Tigray Proper) ከሚቋቋመው አስተዳደር በተለየ ሁኔታ የሚስተናገድ ስለመሆኑ የሚያመላክት እና ፓርቲያችን አብን በዚሁ አግባብ ግንዛቤ የያዘበት ቢሆንም ፣ አካባቢዎቹ በአማራ ክልል ስር እንደሚቀጥሉ በግልጽ በስምምነቱ ላይ አለመስፈሩ የስምምነቱን ክሽፈት እንዳያስከትል ስጋት ላይ የሚጥል ነው፡፡

የአማራ ሕዝብም ሆነ የጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ሳያገኝ ከትሕነግ የፖለቲካ ፕሮግራም ገጽ በገጽ ተገልብጦ በሥራ ላይ በዋለ ሕገ-መንግስት እና ሕገ-መንግስቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት በኃይል ወደ ትግራይ የተካለሉትን የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎችን በሕገ-መንግስቱ አግባብ ውሳኔ ያገኛሉ በሚል በዚሁ የሥምምነቱ ክፍል ሥምምነት የተደረሰበት አግባብ ለሶስት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ግፍ እና እንግልት ሥር ለኖረው የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሕዝባችን ከወዲሁ ዋስትና የማይሰጥ በመሆኑ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን አሳስቦታል፡፡የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ውድ ዋጋ የተከፈለበት የማንነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያለው እና የሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት የሚረጋገጥበት ጉዳይ መሆኑን ግንዛቤ እንዲያዝበት ፓርቲያችን ያሳስባል፡፡

ስለሆነም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል:-

፩. በሰላም ሥምምነቱ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ቡድኑ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት በሙሉ አቅሙ እና ትኩረት እንዲሰራ፤

፪. የ “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ፖለቲካዊ ኅልውና ሕጋዊ እውቅና በሚያገኝበት ሀገር ፣ የሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ፤ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ እያለ የሚጠራው ቡድን እና መሰል “ነጻ አውጭ” ቡድኖች የፖለቲካ ኅልውናቸው እንዲከስም እንዲሰራ እና የሕግ ክልከላ ስራ ላይ እንዲያውል፤

፫. የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና ከ30 ዓመት በላይ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች አሁን ባሉበት አማራ ክልል ሥር ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉ መንግስት በአፋጣኝ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ እና

፬. በአሸባሪው ትሕነግ ጀማሪነት በሶስት ተከታታይ ዙር በተካሄደው የወራራ ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ፣ አፋር እና ትግራይ አካባቢዎች መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም ሥራ የፌደራል መንግሥቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲመራና እንዲያስተባብር፣ መላው ኢትዮጵያውያንም ለመልሶ ግንባታው እና መቋቋሙ ሥራ ድጋፍ እንዲያደርጉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም.

09/11/2022

ይኸው ነው ከዚህ ውጭ የመሀል ሀገር የትህነግ አጋሮች አርፋችሁ ቁጭ በሉ።

ይህን ነው የወደድኩት! DDR!*****Article 6 – Disarmament, Demobilization, and Reintegration (DDR)The Parties:a. Agree and recogni...
03/11/2022

ይህን ነው የወደድኩት! DDR!
*****
Article 6 – Disarmament, Demobilization, and Reintegration (DDR)

The Parties:

a. Agree and recognize that the Federal Democratic Republic of Ethiopia has only one defence force;

b. Shall design and implement a comprehensive DDR program for TPLF Combatants consistent with the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia;

c. Agree that within 24 hours of the signing of this Agreement, an open channel of communication between senior commanders of both sides will be established;

d. Agree to organize a meeting of senior commanders within 5 days from the signing of this Agreement to discuss and work out detailed modalities for disarmament for the TPLF combatants, taking into account the security situation on the ground;

e. Agree to undertake the disarmament of the heavy armaments of the TPLF combatants as a matter of priority based on a detailed schedule to be agreed upon between the senior commanders of the Parties. The disarmament activities in the schedule should be completed within ten days from the conclusion of the meeting of the senior commanders. The ten-day period could be extended based on the recommendation of the senior commanders, to be endorsed by the Parties.

f. Agree to finalize the overall disarmament of the TPLF combatants, including light weapons within 30 days from the signing of this Agreement;

g. Agree that the demobilization and reintegration plan will consider the Tigray Region's law-and-order needs.

(Gentu )

ሙሉ የስምምነት ሰነድ(English version)‼️Joint Statement between the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia an...
02/11/2022

ሙሉ የስምምነት ሰነድ(English version)‼️
Joint Statement between the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and
the Tigray Peoples’ Liberation Front (TPLF)

1. As per Article 3 of the Agreement for Lasting Peace and Permanent Cessation of Hostilities, the Representatives of the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the TPLF have agreed to announce to the people of Ethiopia and the rest of the world that after 10 days of intensive negotiations have concluded a peace agreement.

2. We have agreed to permanently silence the guns and end the two years of conflict in northern Ethiopia.

3. The conflict has brought a tragic degree of loss of lives and livelihoods and it is in the interest of the entire people of Ethiopia to leave this chapter of conflict behind and live in peace and harmony.

4. It is fundamental that we reaffirmed our commitment to safeguarding the sovereignty and territorial integrity of Ethiopia and to upholding the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia. Thus, Ethiopia has only one national defense force. We have also agreed on a detailed program of disarmament, demobilization, and reintegration for the TPLF combatants, taking into account the security situation on the ground.

5. We have agreed that the Government of Ethiopia will further enhance its collaboration with humanitarian agencies to continue expediting aid to all those in need of assistance.

6. We have agreed to implement transitional measures that include the restoration of Constitutional order in the Tigray region, a framework for the settlement of political differences, and a Transitional Justice Policy framework to ensure accountability, truth, reconciliation, and healing.

7. To start implementing these undertakings without delay, we have agreed to stop all forms of conflicts, and hostile propaganda. We will only make statements that support the expeditious implementation of the Agreement. We urge Ethiopians in the country and abroad, to support this Agreement, stop voices of division and hate, and mobilize their resources for economic recovery and rehabilitation of social bonds.

8. The Government of Ethiopia will continue the efforts to restore public services and rebuild the infrastructures of all communities affected by the conflict. Students must go to school, farmers, and pastoralists to their fields, and public servants to their offices. The Agreement requires the support of the public for its smooth implementation. This is a new and hopeful chapter in the history of the country.

9. We express our gratitude to all actors contributing to the success of this endeavor. In particular, the African Union Commission Chairperson, the African High-Level Panel led by His Excellency former President Olusegun Obasanjo, supported by His Excellency former President Uhuru Kenyatta, and Her Excellency Dr. Phumuzile Mlalmbo, former Deputy President of the Republic of South Africa. We thank the Chairperson of the African Union Commission, His Excellency Mr. Moussa Faki Mahamat, Commissioner Bankole Adeoye and his colleagues for their tireless work during these talks. We rely on their continued support as we implement the Agreement.

10. We thank His Excellency President Cyril Ramaphosa, the President of the Republic of South Africa, and Her Excellency Dr. Naledi Pandor, the Minister for the Department of International Relations and Cooperation of South Africa for the excellent facilities they put at the disposal of these talks and their words of encouragement to the parties towards these successful results. We are indebted for the hospitality accorded to us by the People and Government of the Republic of South Africa.

11. We are grateful to the people of Ethiopia for encouraging these talks and patiently waiting for the outcome. We are confident that they will embrace the results of these talks and ensure their timely implementation.

12. Finally, we are confident that friends of Ethiopia and members of the diplomatic community will lend their support in rebuilding infrastructures in affected communities and the economic recovery of the country. We call on all types of media outlets to support peace, reconciliation, unity, and prosperity in Ethiopia.
Jointly Delivered at Pretoria, the Republic of South Africa, on 2nd November 2022.

"አብን ወልቃይት እና ራያ በደም ወደ ቀድሞ  ማንነቱ  በመስዋትነት የተመለሰን   ለመደራደሪያነት ማስቀመጥ በህዝባችን ላይ መሳለቅ ነው አለ "@@@@@@@@ # # # # # # #@@@@@@@@...
02/11/2022

"አብን ወልቃይት እና ራያ በደም ወደ ቀድሞ ማንነቱ በመስዋትነት የተመለሰን ለመደራደሪያነት ማስቀመጥ በህዝባችን ላይ መሳለቅ ነው አለ "

@@@@@@@@ # # # # # # #@@@@@@@@

የአብን መግለጫ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የተሰጠውን መግለጫ ወደ ራሳቸው ፍላጎት በመጎተት ላልተገባ ትሩጓሜ ተደርጓል ስለዚህ ይህንን ጋዜጣዊ ማብራርያ ተጠርቷል ብለዋል የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ ።

በአሸባሪነት የተፈረጀውን ትህነግ ከመንግስት ጋር የሚደረገውን የሰላም ንግግር እንደ ድርድር አድርጎ ማቅረብ በራሱ ስህተት ነው በሚል ንግግራቸውን የጀመሩት የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዋናነት ይህ አሸባሪ ቡድን ትጥቅ ፈትቶ ከየትኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ታግዶ የሚከስምበት እና ወንጀለኞች ለፍትህ ቀርበው የአማራ ህዝብ እንባ እስኪታበስ አበክረን የምንታገል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል። ቀጣይ ዝርዝር ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን

ነፍጠኛ ሚዲያ
22/2/15
አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጵያ

03/05/2022

እስልምና እና ፀጉር ማሳደግ ? ወዳጄ ከሚሴ ላይ ማን እንደሚበጠብጥህ እይ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Neftegna Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share