Benishangul press

  • Home
  • Benishangul press

Benishangul press Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Benishangul press, Media/News Company, .

በርዕሰ መዲናችን ስም የተሰየመችው አሶሳ መርከብ የተሰኘችው የኢትዮጵያ መርከብ የኤርትራን ጭነት ለማንሳት ምጽዋ ወደብ መህልቋን ጥላለች
30/12/2023

በርዕሰ መዲናችን ስም የተሰየመችው አሶሳ መርከብ የተሰኘችው የኢትዮጵያ መርከብ የኤርትራን ጭነት ለማንሳት ምጽዋ ወደብ መህልቋን ጥላለች

28/12/2023
መተከል ሰላምሽ ይብዛ!!18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደረጃ በመተከል ዞን መዲና ግልገል በለስ ክተማ ይከበራል!!የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ...
28/11/2023

መተከል ሰላምሽ ይብዛ!!

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደረጃ በመተከል ዞን መዲና ግልገል በለስ ክተማ ይከበራል!!

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳና የክልሉ አፈ ጉባኤ ክቡር ዶ/ር ተመስጌን ዲሳሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የስራ ሀላፊዎችና የበዓሉ ዕንግዶች መተከል ዞን ግ/በለስ ከተማ አመሻሹን ገብተዋል።

መልካም በዓል!!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጥቅምት ወር ብቻ 32 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ*******************(አሶሳ፣ ጥቅምት 30/2016 ...
10/11/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጥቅምት ወር ብቻ 32 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ
*******************

(አሶሳ፣ ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጥቅምት ወር ብቻ 32 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን የክልሉ የጋራ ግብረ ሀይል አስታወቀ።

ግብረ ሀይሉ በክረምት ተጽዕኖ ወደ ስራ ያልገቡ ባህላዊ አምራቾች ወደ ስራ ለማስገባት ባደረገው እንቅስቃሴ የተመዘገቡ ውጤቶችን ገምግሟል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣ የወርቅ ግብረ ሀይሉ በጥቅምት ወር በባህላዊ መንገድ የተመረተውን የወርቅ ምርት አፈጻጸም እንቅስቃሴ በገመገመበት ወቅት፣ በጥቅምት ወር ብቻ 32 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ገልጸዋል።

በክልሉ በጥቅምት ወር የተገኘው የወረቅ ምርት አፈጻጸም ካለፉት ወራት ጋር ሲነጻጸር መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

የጋራ ግብረ ሀይሉ በቀጣይ ጊዜያት ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው ወርቅ የበለጠ ለመሻሻል የክትትልና ቁጥጥር ሥራውን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የቀጣይ አቅጣጫም አስቀምጧል።

በብዙ ድካምና መስዋእትነት የተገኘውን የመተከል ዞን ሰላም ዘላቂ የሚያደርግ በ3 አመታት  የሚተገበር የምክክርና እርቀ ሰላም ፕሮጅክት የክልሉ ፕረዚደንት የተከበሩ አቶ አሻደሊ ሐሰን በተገኙበ...
04/11/2023

በብዙ ድካምና መስዋእትነት የተገኘውን የመተከል ዞን ሰላም ዘላቂ የሚያደርግ በ3 አመታት የሚተገበር የምክክርና እርቀ ሰላም ፕሮጅክት የክልሉ ፕረዚደንት የተከበሩ አቶ አሻደሊ ሐሰን በተገኙበት ይፋ ሆነ!!
ሰላም ለኢትዮዽያ!!

ጋሪ ዎሮ የቦሮ ሺናሻ ህዝብ የዘመን መለወጫ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ይከበራል!!
15/09/2023

ጋሪ ዎሮ የቦሮ ሺናሻ ህዝብ የዘመን መለወጫ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ይከበራል!!

"ለተቸገሩት መድረስ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫችን በመሆኑ፣ ሁሌም ከተቸገሩት ጎን መቆም የሚፈጥረው ደስታ ልዩ ነው"፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ******************(አሶሳ፣ ጳጉ...
08/09/2023

"ለተቸገሩት መድረስ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫችን በመሆኑ፣ ሁሌም ከተቸገሩት ጎን መቆም የሚፈጥረው ደስታ ልዩ ነው"፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ
******************

(አሶሳ፣ ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም) "ለተቸገሩት በጎ ማድረግ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫችን በመሆኑ፣ ሁሌም ከተቸገሩት ጎን መቆም የሚፈጥረው ደስታ ልዩ ነው" ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የከተማውን ባለሀብት በማስተባበር ለአረጋዊያን እና አቅመ-ደካሞች የማዕድ ማጋራት ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለአቅመ-ደካሞችና አረጋዊያን ማዕድ አጋርተዋል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በጎነት በፈጣሪ ዘንድ ዋጋ የሚያሰጥ ተግባር በመሆኑ፣ የህይወታችን አንዱ አካል አድርገን ማስቀጠል ይጠበቅብናል ብለዋል።

ለተቸገሩት በጎ ማድረግ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ልዩ መገለጫችን ነው ያሉት አቶ አሻድሊ፣ ሁሌም ከተቸገሩት ጎን መቆም የሚፈጥረው ደስታ ልዩ መሆኑን ገልጸዋል።

በእኛ በጎ ማድረግ ውስጥ ተስፋ እና ደስታ የሚፈጠርላቸውን ዜጎች እያሠብን የበጎ አድራጎት ሥራችንን ሁሌም አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል ብለዋል።

በክልሉ የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ወ/ሪት ሚስኪያ አብደላ፣ በአስቸገሪ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉትን ዜጎች ማዕድ ማጋራት የህልውና እርካታን እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በየጎዳናው የሚገኙትን ወላጅ አልባ እና አረጋዊያንን ከጎዳና በማንሳት የበጎነት ተግባርን መፈፀም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህል አድርጎ መያዝ እንደሚገባውም ወ/ሪት ሚስኪያ ተናግረዋል።

ለሀገር በርካታ ዉለታ የዋሉ አረጋዊያዊያንን መንከባከብ ታሪክ የማይረሳው አሻራ መሆኑን የተናገሩት የቢሮ ሀላፊዋ፣ ይህንን ፕሮግራም ላስተባበሩት ባንቡ ሆቴል፣ ሰምሀል ሆቴል እና ቤንስ አይንከን ሆቴል ምስጋና አቅርበዋል።

"ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር በምትከፍሉት ውድ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ትቀጥላለች" ፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን******************(አሶሳ፣ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም...
07/09/2023

"ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር በምትከፍሉት ውድ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ትቀጥላለች" ፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
******************

(አሶሳ፣ ጳጉሜ 02/2015 ዓ.ም) "ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር በምትከፍሉት ውድ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ትቀጥላለች" ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጳጉሜን 2 - የመሥዋዕትነት ቀን
"በመሥዋዕትነት የምትጸና ሀገር" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

ቀኑ ስለሀገርና ሕዝብ መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን በማስታወስና ክብር በሚሰጡ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን ማለዳ ላይ በተካሄደ የእግር ጉዞ፣ ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ለማፅናት መስዋዕትነት ለከፈሉ የሃገር ጀግኖች ክብር በመስጠትና ቃልም በመግባት ተከብሯል።

በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ ዕለቱን ስናከብር ለዛሬ መኖራችን መስዋዕትነት ለከፈሉ እና ወደፊትም ዋስትና ለሆኑት የመከላከያ ሠራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስና ሚሊሻ ምስጋና በማቅረብ እና ሁሌም ከጎናችሁ መሆናችንን በማረጋገጥ ነው ብለዋል።

አባቶቻችን ያስረከቡንን ሉዓላዊት ሀገር አንድነቷ ሳይሸረሸር ከነሙሉ ክብሯ ለትውልድ የማሻገር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ያሉት አቶ አሻድሊ፣ ይህ የሚሆነው ደግሞ የዘመነና ጠንካራ ሠራዊት ሲኖር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ለሀገር ሉዓላዊነትና ክብር እየተከፈለ ባለው ውድ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ በሚገባት ከፍታ ልክ ሆና እንደምትቀጥልም አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናግረዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶች ረግበው የክልሉ ሕዝብ የሠላም አየር እንዲተነፍስ ለከፈላችሁት መስዋዕትነት የክልሉ መንግስትና ሕዝብ ሁሌም በጀግንነት ያስታውሳችኋል ብለዋል።

በተለይ ወጣቱ ትውልድ በጀግንነቱንና አይደፈሬነቱ ከሚታወቀው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ ለሀገርና ለሕዝብ ክብር መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ምስጋናና ዕውቅና መስጠታቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

የዘንድሮው “ጓንዷዋ” በዓል አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች መከበር መጀመሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ********************...
06/09/2023

የዘንድሮው “ጓንዷዋ” በዓል አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች መከበር መጀመሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ
********************************

(አሶሳ፣ ጳጉሜ 01/2015 ዓ.ም) የ2016 የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጓንዷዋ” በዓል አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች መከበር መጀመሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ።

በዓሉ "ጓንዷዋ ለዘላቂ ሠላም እና ልማት" በሚል መሪ-ቃል በአሶሳ ከተማ በአካባቢ ጽዳት ዘመቻ እና በባህላዊ ክዋኔዎች ዛሬ መከበር ጀምሯል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የጓንዷዋ በዓል የአዲስ ዓመት መሸጋገሪያ መሆኑን ገልጸው፣ አዲስ ተስፋ፣ ብርሃን፣ መተሣሰብና መልካም ነገር የሚንጸባረቅበት በዓል መሆኑን ጠቁመዋል።

የዘንድሮው የ"ጓንዷዋ" በዓል አብሮነትን፣ ሠላምንና ልማትን በሚያጠናክር መልኩ መከበር መጀመሩን ተናግረዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች እንደሚከናወኑ የገለጹት አቶ ጌታሁን፣ ዛሬ የአገልጋይነት ቀን በመሆኑ የጓንዷዋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በጋራ የአካባቢ ጽዳት መካሄዱን ገልጸዋል።

በዓሉ በቀጣዮቹ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ መርሃ-ግብሮች የሚከበር ሲሆን የደም ልገሳ፣ ለተቸገሩና ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ፣ ከዚህ ቀደም የተተከሉ የችግኞችን በመንከባከብ፣ በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቪሽን እና በባህላዊ ትዕይንቶች እንደሚከበር አስታውቀዋል።

የጓንዷዋ በዓልን ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍና የበዓሉን መልካም እሴት ለማስተዋወቅ የተለዬ ትኩረት መሠጠቱን ጠቅሰዋል።

በጽዳት ዘመቻው ላይ የተሳተፉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው፣ የጓንዷዋ በዓል የሠላም፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቅሰው፣ የበለጠ እንዲተዋወቅመሥራት ይገባል ብለዋል።

በዓሉ የሁላችንም ነው ያሉት አመራሮቹ፣ ከባህላዊ ይዘቱ ባሻገር በበጎ አድራጎት ተግባራት እየተከበረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በጉሙዝ ብሔረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበረው ይህ የዘመን መለወጫ በዓል በማህበረሰቡ ዘንድ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ከመከበሩም ባሻገር ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች የሚገናኙበትና ወቅቱ አዲስ ምርት የሚደርስበት በመሆኑ ማህበረሰቡ በጋራ ተሰባስበው የሚቋደሱበት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ልባም እና በሳል መሪ!
28/08/2023

ልባም እና በሳል መሪ!

ኩሶ ኢንተርናሽናል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ****...
24/08/2023

ኩሶ ኢንተርናሽናል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ
****

(አሶሳ፣ ነሀሴ 18/2015 ዓ.ም) ኩሶ ኢንተርናሽናል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አወቀ አይሸሹም ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ኩሳ ኢንተርናሽናል በትምህርቱ ዘርፍ ያከናወናቸውን ተግባራት በተመረጡ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ ኩሶ ኢንተርናሽናል የክልሉን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅና የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማረጋገጥ አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኩሶ ኢንተርናሽናል በክልሉ የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ እና ብቁ ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር እየሰሩ ያለውን ስራ የክልሉ መንግስት እንደሚደግፍ አቶ ጌታሁን ገልጸው፣ የጀመራቸውን አበረታች ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አወቀ አይሸሹም (ዶ/ር)፣ ኩሶ እንተርናሽናል ዘላቂ የትምህርት የልማት ግቦችን ለማሳካት ከቢሮው ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው ብለዋል።

ድርጅቱ በሠራቸው ሥራዎች ሴት ተማሪዎች በስነ ልቦና ዝግጁ ከማድረግ አልፎ የራስ መተማመናቸውን እየጨመረ መምጣቱን ዶ/ር አወቀ ተናግረዋል።

የሴት ተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ፣ መጠነ መድገም ለመቀነስ እንዲሁም የትምህርት ብክነት ለማስቀረት ድርጅቱ ትልቅ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ድርጅቱ በቀጣይ ካቀፋቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር ለመጨመር እየተሠራበት መሆኑን ዶ/ር አወቀ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የኩሶ ኢንተርናሽናል ተወካይ አቶ ወንደሰን ከበደ፣ አካታች የስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ ለሴት ተማሪዎችን አጋዥ መፅሀፍቶችን በማዘጋጀት ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በፕሮጀክቱ ለሚደገፉ ሴት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ ዩኒፎርም እና ሌሎች ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ወንደሰን ተናግረዋል።

ኩሶ ኢንተርናሽናል በክልሉ በ7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ190 በላይ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቡራሞ ወረዳ በ2015/16 እየለማ የሚገኝ የመኸር የቦቆሎ ኩታ-ገጠም ማሣ!
23/08/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቡራሞ ወረዳ በ2015/16 እየለማ የሚገኝ የመኸር የቦቆሎ ኩታ-ገጠም ማሣ!

“በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኩታ-ገጠም እርሻን በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው” ፡- አቶ አሻድሊ ሀሰን***************************(አሶሳ፣ ነሐሴ 12/...
18/08/2023

“በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኩታ-ገጠም እርሻን በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው” ፡- አቶ አሻድሊ ሀሰን
***************************

(አሶሳ፣ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርናውን ከተበጣጠሰ አሠራር በማውጣት እና የኩታ-ገጠም ልማትን በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ አቡራሞ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች የግብርና ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በሌማት ትሩፋት የተሠሩ የዶሮ፣ የእንቁላል፣ የቀይ ሥጋ ምርት መንደሮችን፣ የክላስተር ሠብሎችን የጎበኙ ሲሆን የመኽር ስንዴ ዘርን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በ2015/16 የመኸር ወቅት 937 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን የታቀደ ሲሆን፣ ከዕድቅ በላይ ለማሳካት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በምርት ዘመኑ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው መሬት ውስጥ እስካሁን ከ900 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የሚሆነው በተለያዩ ሠብሎች በዘር መሸፈኑን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ለግብርና ምቹ ሠፊ የመሬት ሀብት ቢኖርም እስካሁን ማልማት የተቻለው ግን 20 በመቶውን ብቻ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አሻድሊ፣ ግብርናውን ከተበጣጠሰ አሠራር በማውጣት እና የክላስተር አሠራርን በማስፋት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተያዘው የምርት ዘመን ብቻ ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሆነው በኩታ ገጠም መልማቱን አስረድተው፣ እየታ ላለው ለውጥ የዘርፉን አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል።

በአቡራሞ ወረዳ ቡልድግሉ ቀበሌ ብቻ ከ7 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የኩታገጠም የበቆሎ ሠብል መልማቱንም ለአብነት አንስተው፣ በቀጣይ መሠል ውጤታማ ተሞክሮዎችን ወደሌሎች አካባቢዎች የማስፋት ሥራ ይከናወናል ብለዋል፡፡

የክልሉ የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ አበረታች ነው ያሉት ርዕሰ-መስተዳድሩ፣ በምርት ዘመኑ ከ29 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቀዋል።

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር በእርሻ ትራክተር ድጋፍ፣ በመሠረተ-ልማት ግንባታ፣ በመስኖ ዘርፍ ለክልሉ እያደገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆቸውን በጉብታቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በሌማት ትሩፋት የዶሮ እርባታ፣ የእንቁላል፣ የቀይ ስጋ ምርት፣ የአሳ፣ የወተት መንደሮችን ለመፍጠር እና ተሞክሮውን በእያንዳንዱ ቤተሰብ ደረጃ ለመተግበር እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ ለክላስተር የተሰጠውን ትኩረት በለሙት ሠፋፊ መሬቶች መረጋገጥ ይቻላል ያሉት ኢንጂነር አይሻ፣ የተጀመረውን የእርሻ ሜካናይዜሽን በማጠናከር በክልሉ ያለውን የመልማት አቅም ሙሉ በሙሉ ወደውጤት መቀየር እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ለግብርና ሜካናይዜሽን መጠናከር እና በክልሉ ያሉት የውኃ ሃብቶች ወደልማት እንዲቀየሩ ትልልቅ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ኢንጂነር አይሻ፣ በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አርሶ-አደሮች ሽልማት አበርክተዋል።

በክረምት በጎ ፍቃድ የሚከናወኑ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ**************(አሶሳ፣ ነሐሴ 05/201...
11/08/2023

በክረምት በጎ ፍቃድ የሚከናወኑ አበረታች ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ
**************

(አሶሳ፣ ነሐሴ 05/2015 ዓ.ም) ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ አበረታች የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ከኢፌዴሪ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ጋር በመሆን በሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት በክልሉ የሚከናወኑ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በይፋ አስጀምረዋል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

እነዚህን ባለፉት ዓመታት የተሰሩ አበረታች የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

በተያዘው ክረምትም የአረጋዊያንን ቤት የማደስ፣ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የመጠገንና እና ወላጅ አልባ ህፃናትንም መደገፍ፣ የችግኝ ተከላ ትኩረት ተሰጥቶ በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ቱሪዚም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ ክልሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኛ ክልል በመሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በተያዘው ክረምት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተጠሪ ተቋማትና ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ፣ የአረጋዊያን ቤት ጥገና የቤተ-መፅሀፍት እድሣት እና የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚከናወኑ ሚንስትሯ ተናግረዋል።

በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ15ሺ በላይ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል።

በመርሃ-ግብሩም ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ምግብ ነክ የሆኑ ድጋፎችን ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ የአቅመ-ደካማ ቤቶችን ዕድሳት አስጀምረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ*****************(አሶሳ፣ ነሐሴ 04/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳ...
10/08/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
*****************

(አሶሳ፣ ነሐሴ 04/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

የክልሉ ካቢኔ ዛሬ ባደረገው መደበኛ ስብሰባው ጥራት ያለው የግብርና ግብአት አቅርቦት እና የጥራት ቁጥጥር አገልግሎት ስርአት በመዘርጋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

በመቀጠልም፣ በተከለሰው የጤና አገልግሎት ክፊያ ስርዓት ላይ እንዲሁም በክልሉ ስራ አመራር ተቋም የአዳራሽ ዋጋ ማሻሻያ ላይ ውይይት ያካሄደው መስተዳድር ምክር ቤቱ፣ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ማሻሻያ በማድረግ ወደሥራ አንዲገባ ውሣኔ አሣልፏል።

 #የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቀረበ‼️******************(አሶሳ፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም) ...
04/08/2023

#የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቀረበ‼️
******************

(አሶሳ፣ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሠላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርቧል‼️

የቢሮው ኃላፊ አወቀ አይሸሽም (ዶ/ር) ፈተናው በሠላም መጠናቀቁን ጠቁመው፣ ለዚህም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል‼️

ጸጥታ አካላት ተፈታኝ ተማሪዎችን ከሩቅ ቦታ ወደ ፈተና ማዕከል አጅበው በመምጣት ላደረጉት አስተዋጽኦ በልዩ ሁኔታ ሊመሠገኑ ይገባል ብለዋል‼️

የክልሉ የፈተና ኮማንድ ፖስት አባላት የፈተናውን ሁኔታ በየዕለቱ በመከታተልና ችግሮች ሲፈጠሩ ወዲያው መፍትሔ በመስጠት ያደረጉት ርብርብ ለቀጣይ ስራ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል‼️

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ******************(አሶሳ፣ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ...
26/07/2023

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ
******************

(አሶሳ፣ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በዛሬው ዕለት ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሠረት፦

1. አቶ ፀሐይ ጉዮ - በሰላም ግንባታናና ጸጥታ ቢሮ የሰላም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
2. አቶ በሽር አብዱራሂም - በክልሉ ትምህርት ቢሮ የፕላን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
3. አቶ አብዱልሙኒዮም አደም - በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
4. አቶ ታሪኩ ኩመራ - የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
5. አቶ ናስር መሀመድ - በመሬትና ማህበራት ማደራጃ ቢሮ የመሬት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
6.አቶ ሀብታሙ አለነ - በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ መሀመድ ሀመደኒል - የውሀና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
8. አቶ መሀመድ አኑዌሪ - በፋይናንስ ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ምክትል ቢሮ ሃላፊ
9. አቶ ሙሳ አብዱረሂም - በመንገድና ትራንስፓርት ቢሮ የመንገድ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
10. አቶ ዑመር መሀመድ - በፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
11. አቶ ገርቢ ሎላሳ - በክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
12. አቶ ፀጋዬ ተሰማ - የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
13. አቶ ሞሲሳ መሸሻ - የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
14. አቶ አትንኩት ሽቱ - በክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
15. አቶ ኢዶሳ ጎሹ - በሥራ እና ክህሎት ቢሮ የስራ ዕድል ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ ኑረዲን ሙክታር - የመሬት እና ህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ ቢሮ የህብረት ስራ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
17. ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ - በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ
18. አቶ አብዱልሙንየም አብዱልዋሂድ - በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ምክትል ቢሮ ሀላፊ

በመሆን በርዕሰ መስተዳድሩ ተሹመዋል።

18/07/2023

ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የትምህርት ቤቶች መሰረተ_ልማት ማሻሻያ ህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ ር ብርሃኑ ነጋ እና ክቡር ር/ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን በተገኙበት በአሶሳ ዪኒቨርሲቲ አዳራሽ ተጀመረ።

"ነገን ዛሬ እንትከል" በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላው ቀጥሏል።ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በሆሞሻ ወረዳ ጾሬ የስደተኞች ካምፕ ተገኝተው ከክልሉ አመራሮች፣ ...
17/07/2023

"ነገን ዛሬ እንትከል" በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላው ቀጥሏል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በሆሞሻ ወረዳ ጾሬ የስደተኞች ካምፕ ተገኝተው ከክልሉ አመራሮች፣ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ስደተኞች ጋር ችግኞችን መትከላቸውን ቀጥለዋል።

ተጀመረነገን ዛሬ እንትከል!!!  **************ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት እለት ነው!!በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ...
17/07/2023

ተጀመረ
ነገን ዛሬ እንትከል!!!
**************

ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት እለት ነው!!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዛሬው ዕለት ብቻ 10 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።

መላው ኢትዮጵያውያንም በያሉበት ስፍራ ጀንበር ወጥታ እስከምትገባ የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ነገን ዛሬ ይተክላሉ።

ድምፃችንን ማህፀነ ለምለሟ ቤጉ ላፈራችው አማኑኤል ተርፋ እንስጥ!ቤንሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን  ያፈራው  የጉሙዝ ተወላጅ  የሆነ  ባለ ልዩ ተሰጦ  አማኑኤል ተርፋ ብዙ  ውጣውረዶችን አልፎ በ...
05/07/2023

ድምፃችንን ማህፀነ ለምለሟ ቤጉ ላፈራችው አማኑኤል ተርፋ እንስጥ!

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን ያፈራው የጉሙዝ ተወላጅ የሆነ ባለ ልዩ ተሰጦ አማኑኤል ተርፋ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል ።
ይህ ባለ ራይ ተጫዋች የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2015 ዓ.ም ኮከብ ተስፈኛ ተጫዋች እጩ ሆኖ ቀርቧል ።
እንዲህ ዓይነት ታታሪ ሰው ሕልሙ እንዲሳካ ማገዝ በተዘዋዋሪ ብዙዎች የእሱን አርዓያ እንዲከተሉ መነሳሳት ስለሆነ ድምፃችሁንን ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ላይ በመስጠት የራሳችንን ሚና እንወጣ ።

የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የርስዎ የአመቱ ተስፈኛ ተጫዋችን ከቀረቡት እጩዎች ውስጥ ይምረጡ! እስከ ሰኔ 29/2015 ብቻ የሚቆይ ዮሴፍ ታረቀኝ / አማኑኤል ተርፉ / አበ....

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በይፋ አስጀመሩ**********************(አሶሳ፣ ሰኔ 24/2015 ዓ.ም) ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ...
01/07/2023

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በይፋ አስጀመሩ
**********************

(አሶሳ፣ ሰኔ 24/2015 ዓ.ም) ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ እና የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2015 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እና የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት "ዛሬን ነገ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የፌዴራል፣ የክልል፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አመራሮችና አባላት በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና መ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች በአሶሳ ዞን አቡራሞ ወረዳ አጤጦ ቀበሌ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያ በሆነው በተያዘው ክረምት 55 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስደናቂ ውጤት እያስመዘገበች ነው ያሉት ርዕሰ-መስተዳድሩ፣ ይህንን ስኬት ለማስቀጠል በሁለተኛው ምዕራፍም የህብረተሰቡ ተሣትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ክልል መሆኑን ጠቁመው፣ የችግኝ ተከላ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳን በመረዳት ይህንን የተፈጥሮ ሀብት ጠብቆ ለትውልድ ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከሚተከሉት ችግኞች ውስጥ 70 በመቶውን የሚይዙት የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

በመጀመሪያ ምዕራፍ ያለፉት አራት ዓመታት በክልሉ 120 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፣ የመጽደቅ ምጣኔያቸውም ከ80 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀጣይም በአንድ ጀምበር 10 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ይካሄዳል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ወጣት አቶ አክሊሉ ታደሰ፣ አንድነትና አብሮነት እየተተከለ እንዲሄድ አየተደረገ ነው፣ ፍሬውንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ እናየዋለን ብለዋል።

ወጣቶችም የችግኝ ተከላን ጨምሮ በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ሲሳተፉ ይህንን ዓላማ ለማሣካት መሆን እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል።

8 ሚሊዮን የሚሣተፉበት የወጣቶች የክረምት መርሃ-ግብር ዛሬ መጀመሩን ጠቅሰው፣ በተለያዩ የበጎ ሥራዎች ተሣትፎው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች አንዱ የችግኝ ተከላ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተያዘው ክረምት ብቻ 400 ሚሊዮን ችግኞችን ይተክላሉ ብለዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ ብዙ የተራቆቱ አካባቢዎችን አረንጓዴ የማድረግ እና አረንጓዴ የሆኑትን ደግሞ ባሉበት መጠበቅ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ አረንጓዴ መሆን ይጠበቅባታል፤ ይገባታልም ያሉት አቶ ዛዲግ፣ ለዚህም መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ስላለፈውና ስለዛሬው ብቻ በቂ አለመሆኑን ተረድተን ችግኝ ከተመትከል ባለፈ አብሮነታችንን በማጠናከር ስለነገ የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅነው የተናገሩት።

የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኻሊፋ፣ በሁለተኛው ምዕራፍ በተለይም ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚታወቅበትን የማንጎ እና የቀርቀሃ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

 #የሰላም ጉባኤ በደማቋ  #ቻግኒ ከተማየአማራ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች ወረዳዎች የሰላምና ጸጥታ መድረክ በቻግኒ ከተማ ተካሄደ።ውይይቱን የመሩት የሁለቱ ክልል ከፍተኛ የ...
30/06/2023

#የሰላም ጉባኤ በደማቋ #ቻግኒ ከተማ

የአማራ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች ወረዳዎች የሰላምና ጸጥታ መድረክ በቻግኒ ከተማ ተካሄደ።

ውይይቱን የመሩት የሁለቱ ክልል ከፍተኛ የሰላምና የፀጥታ አመራሮች ሲሆኑ በመድረኩም የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የዞን እና የወረዳ የፀጥታ መዋቅር አመራሮች፣ የመተከል ዞን አመራሮች፣ የምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ አብዮት አልቦሮ ዞን ከዞን ጋር፤ ወረዳ ከወረዳ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ለምንፈልገው ዘላቂ ሰላም ተስፋ ሰጪ ለውጥ አምጥተዋል፤ አሁን የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማፅናት የሁለቱ ክልልሎች የጋራ ርብርብ፣ መደማመጥና መተባበር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊው አክለው እንደገለጹት በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ እና በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳዎች አካባቢ አልፎ አልፎ ለሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የተለየ ትኩረት በመስጠት፣ ለመፍታት በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

የአማራ ክልል ሰላምና ደሕንነት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በበኩላቸው የአማራ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ በየጊዜው መወያየታችን በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የጎላ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ተናግረዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ መኾኑንም አክለው ገልጸዋል።

ውይይቱ ላይ የሁሉም ዞን አመራሮች አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡ ሲኾን በቀረቡት ሃሳቦች ምክክር ተደርጎ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዙ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች  እንኳን ለ 1444ኛ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን
27/06/2023

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1444ኛ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለተኛ ዙር ስልጠና ላይ የሚገኙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ችግኝ ተከሉ**********************************(አሶሳ፣ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም) በ...
26/06/2023

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለተኛ ዙር ስልጠና ላይ የሚገኙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ችግኝ ተከሉ
**********************************

(አሶሳ፣ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለተኛ ዙር ስልጠና ላይ የሚገኙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በክልሉ በሶስቱም ዞኖች በየደረጃው የሚገኙ 657 የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች "በመፍጠንና በመፍጠር የወል እውነቶችን የማጽናትና ቀጣይ የትግል ምዕራፍ" በሚል መሪ-ቃል 2ኛ ዙር ሁለተኛ ዙር ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሶስተኛ ቀኑን ከያዘው የስልጠና መድረኩ ጎን ለጎን በአሶሳ ማዕከል ስልጠና ላይ የሚገኙት አመራሮቹ ዛሬ በኢንዚ ተራራ ተገኝተው የችግኝ ተካላ አካሂደዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሣትፈዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share