08/10/2024
"ትውልድ የተቀራራቢ እሴት ተጋሪዎች ሰብሰብ ነው"
የፓራዳይም ለውጥ መነሻዎች ወይም ገፊ ምከንያቶች ውስጣዊና ውጫዊ ለውጦች ወይም ፈተናዎች ናቸው።
እነዚህ ሀገራዊ ፈተናዎችና ለውጦች፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችና ለውጦች፣ በነባሩ ፓራዳይም የእሳቤ ከፍተቶች ምክንያት መቋቋም ሳይቻል ሲቀር፣ የፓራዳይም ለውጥ ማምጣት የግድ ይላል።
ምክንያቱም በነባሩ ፓራዳይም ሀገር መምራት የማይቻለበት ደረጃ ሲደረስ፣ የአዲስ ፓራዳይም አስፈላጊነት ጎልቶ ይወጣል።
በዚህም አዲስ ፓራዳይም ይወለዳል፤ ይጠናከራል። ማኅበረሰብ አዲስ እሴትና የጋራ ጠባይ ወደ መቅረጽ ደረጃ ይደርሳል። ትውልድ የተቀራራቢ እሴት ተጋሪዎች ሰብሰብ ነው የሚባለውም ለዛ ነው ።