የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ/Amhara people's Front in Armachiho

  • Home
  • የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ/Amhara people's Front in Armachiho

የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ/Amhara people's Front  in Armachiho Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ/Amhara people's Front in Armachiho, Digital creator, .

የብልጽግና ዋና አሻንጉሊት(አረጋ ከበደ) በአማራ ክልል
20/12/2023

የብልጽግና ዋና አሻንጉሊት(አረጋ ከበደ) በአማራ ክልል

20/12/2023

ሰላም ወዳጆች በኔትወርክ እና መሰል ችግሮች ምክንያት ከሚዲያ ርቀን ነበር አሁን ተመልሰናል
ድል ለአማራ ፋኖ

በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታግተው ከሚገኙ 29 ታጋቾች  የተላከ ደብዳቤ ለሚመለከተው ሀሉ ባሉበት                 ጉዳዩ:- የተጋረጠብንን በህይወት የመኖር አደጋ ስለማሳወቅ እኛሀ...
20/11/2023

በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታግተው ከሚገኙ 29 ታጋቾች የተላከ ደብዳቤ

ለሚመለከተው ሀሉ
ባሉበት

ጉዳዩ:- የተጋረጠብንን በህይወት የመኖር አደጋ ስለማሳወቅ

እኛሀ ስማችን ከታች የተዘረዘረው የአማራ ተወላጅ የግፍ ታጋቾች ከሶስት ወራት በላይ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ፍፁም ጭካኔ በተሞላበትና ኢ-ሰብአዊ በሆነ አያያዝ ከህግ ውጪ ታግተን እንደምንገኝ ይታወቃል።

ከዚህ በፊት ባሉት ጊዜያት የደረሰብንን አስከፊ የመብት ረገጣ አስመልክተን ለተለያዩ ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ተቋማት በዝርዝር አሳውቀናል።
የደረሰብንን ግፍና በደል በመቃወም ለቀናት የዘለቀ የረሀብ አድማ አድርገን ነበር። አልፎም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ሀላፊዎች የስራ ባልደረቦችና ለህዝብ ተወካዮች የአስቸኳይ ጊዜ አዋች መምሪያ ቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገን ነበር ።

ሆኖም ግን በቡድንና በተቋማት ደረጃ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እና የተደረጉ ግልፅ ውይይቶችና ጉብኝቶች ከንፈር ከመምጠጥና ሽንገላ ውጪ የሚፈፀምብንን ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግፍ ሊያስቆሙልን አልቻሉም። እንደውም ያነሳናቸውና ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እንደ ወንጀል ተቆጥረው ለተጨማሪ ለተራዘመ ግፍና በደል ዳርገውናል ።

በአሁኑ ሰዓትም በግፍ ታግተን በምንገኝበት የአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማለትም የህክምና እጦት ፣ የዘር ተኮር ጥቃትና መድሎ፣ ከፍተኛ የሆነ የአየር ንብረት አደጋ ተጋላጭነት ፣ የምግብና የንፁህ ውሃ እጥረት ፣ ብሎም ሆን ብሎና አስቦ በሁለተናዊ መንገድ ሰው መሆናችንን መቅጣትና ማሰቃየት እየተፈፀመብን ነው። በዋናነት መንግስት በተጠና ሁኔታ አቅዶ በታገትንበት ቦታ ስልታዊ ጥቃትና ስቃይ (systematic tourch) ማለትም አካላዊ ፣ ስነ ልቦናዊና ሞራላዊ ጥቃትና ስቃይ በተደራጀ አኳኋን እየተፈፀመብን ይገኛል።

በተጨማሪም ባለንበት ከባቢ እና ወታደራዊ ካምፕ ለህይወታችን አደጋ የሚፈጥሩ ማለትም ባሁኑ ሰዓት ለህይወታችን በመስጋት ልንገልፃቸው የማንችላቸው ግልፅና ተጨባጭ ስጋቶች ያሉ ሲሆን በማንነታችን መሰረት በአማራ ህዝብ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋና ግድያ ተቀፅላ የሆነው ድርጊት በእኛም ላይ በታገትንበት ካምፕ ውስጥ ይፈፀምብናል የሚል ግልፅ ስጋት አድሮብናል። ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችም ማስተዋል ችለናል።

ምንም እንኳን በአማራነታችን ከህዝባችንና ከወገናችን ተነጥለን በህዝባችን ላይ የሚፈፀመው ጅምላ ግድያ ፍጅና ማንነት ተኮር ጥቃት አካል መሆናችንን ብንረዳም ከዚህ አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ረገጣና በደል እንድንላቀቅ ህጋዊ ሞራላዊ እና ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ።

ግልባጭ
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ለተመድ የሰብዓዊ መብት ኮምሽን
ለአውሮፓ ህብረት
ለአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብት ኮምሽን
ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
ለሚድያ ተቋማት

ለትግራይ ተማሪዎች በእርዳታ የሄደላቸው ደብተር ነው ተብሏል።  በቅርብ እንደመሰረቱት ወዳጅነት በደንብ ለማያውቁት ህፃናት  "አፄ ዮሃንስ ነው" ሊሏቸው ይችላሉ።Getachew Shiferaw
12/10/2023

ለትግራይ ተማሪዎች በእርዳታ የሄደላቸው ደብተር ነው ተብሏል።

በቅርብ እንደመሰረቱት ወዳጅነት በደንብ ለማያውቁት ህፃናት "አፄ ዮሃንስ ነው" ሊሏቸው ይችላሉ።
Getachew Shiferaw

12/10/2023

ካለችው አንድ ምላስ በቀር አገዛዙ አልቆለታል ..‼️‼️

መስከረም 30🤣 ~ አሸባሪው አገዛዝ እስከ መስከረም 30 ቀን ፋኖን እደመስሳለሁ ብሎ ለአምስተኛ ጊዜ “ለመጨረሻ ጊዜ” ብሎ የሰየመው ዘመቻ ሙሉ በሙሉ ተቀልብሶ፣ ፋኖ ከፊል መልሶ ማጥቃት እያደረገ እያፈራረሰው ይገኛል፡፡

እንዲያውም ብአዴን ለሶስተኛ ጊዜ ባህርዳርን ለቆ እየተፈናቀለ ወደ አዲስ አበባ እየተሰደደ ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ለስድስተኛ ጊዜ የመጨረሻየ የሚል ዘመቻ ይከፍት እንደሆነ እናያለን፡፡

"ወግ ወጉስ ተይዟል" እንዲሉ ትግራይ ላይ '72 ሰአታት ሰጥቻለሁ፤ አንድ ሳምንት ሰጥቻለሁ' ምናምን እያለ የለመዳት ፉከራ አሁን አልሰራችም፡፡ ያኔ በማን ክንድ ነበር እንዲያ ጉልበታም መስሎ የነበረው? የበላበትን እጅ ነካሽ!

በነገራችን ላይ ደቃቃ ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች ለሆነ አላማ ብላችሁ ስታጅቧቸው ትልቅ ይሆናሉ፡፡ ትልቅ የሚሆኑት በእናንተ ድጋፍ ነው፡፡ እነሱ ግን ራሳቸው ትልቅ የሆኑ ይመስላቸውና ማበጥ ይጀምራሉ፡፡ የደገፋቸውን ሁሉ መራገጥም ይጀምራሉ፡፡ አይጧ ዝሆን ጀርባ ላይ ሆና ድልድይ ስትሻገር "ፓ አነቃነቅነው እኮ" እንዳለችው ነው፡፡ ብልጽግና ያጋጠማት ይሄው ነው!

በማን ትከሻ ላይ ሆና ነበር "ፓ ወያኔን እኮ አነቃነቅናት!" ያለችው? ታሪክ እና ጊዜ ፈርዷል፡፡

አሁንም እንላለን!

ብልጽግና ማን ስለሆነ ነው ከአማራ ጋር የሚገጥመው? ጅምር መንግስት ከግንድ መንግስት ጋር ገጥሞ ይተርፋል ወይ? ይሄ እኮ ራስን የማጥፋት ዘመቻ ነው።

ዝሆኑ ተሸክሞ ድልድይ ሲያሻግርህ ስለምን በጥፍርህ ጀርባውን ትቧጭራለህ? አሁንም ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ ውልቅ ብሎ አገራችንን ለህዝባችን ማስረከብ ብቸኛ ምርጫዋ ነው።

ህዝብ ያሸንፋል!

ወጥር ጀግናዬ💪💪🔥
ትግሉ እስከ ቀራኒዮ ነው‼️‼️🔥
እየጋለ የሚሄድ እንጂ ሚቀዝቀዝ ትግል አልተጀመረም🔥🔥

27/09/2023
የአጭበርባሪዎች የእነ አብይ አህመድ የማደንዘዣ ስልት(የምክክር ኮሚሽን) ምዕራፍ ሲገለፅ
22/09/2023

የአጭበርባሪዎች የእነ አብይ አህመድ የማደንዘዣ ስልት(የምክክር ኮሚሽን) ምዕራፍ ሲገለፅ

 #26/12/2015  ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ወጣት ወርቁ ይመር ይባላል። ተወልዶ ባደገበት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በአንድ ጽ/ቤት ባለሙያ ሆኖ ያስተማረውን ማህበ...
01/09/2023

#26/12/2015

ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ወጣት ወርቁ ይመር ይባላል።
ተወልዶ ባደገበት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በአንድ ጽ/ቤት ባለሙያ ሆኖ ያስተማረውን ማህበረሰብ በቅንነት እያገለገለ ይገኛል።
ነገር ግን ነሐሴ 26/2015 በኦህዴድ ሎሌ ካድሬዎች ፋኖን ትደግፋለህ በማለት አስረዉታል።
ለአብነት ያህል ይህን ወጣት ጠቀስን እንጅ እዚህ ወረዳ ላይ ብዙ ወጣቶች ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ፋኖ ናችሁ እየተባሉ በአገዛዙ ታጣቂዎች እየተደበደቡ ለእስር ተዳርገዋል ሲል የመረጃ ምንጫችን ከቦታው አድርሶናል።ገሚሶቹም በአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ወንበዴዎች እየተሳደዱ ይገኛሉ።
እነዚህን የወረዳው ከቶውንም የአማራነት ሽታ የሌላቸው መሃይም ካድሬዎችን ላልታወቁ ሀይሎች አደራ ተቀበሉን እንላለን።
#ድል ለአማራ ፋኖ

17/08/2023

"ድመት አላይ ብትል አይጥ ቆነጠጠች" እንዲሉ አበዉ
#11/1272015
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ያሉ የብልጽግና ቅልብ ካድሬዎች እና አንዳንድ ፀረ አማራ ሚሊሻዎች የአካባቢውን ወጣቶች ባለፈው ታች አርማጭሆ ላይ በፋኖ እና በአገዛዙ ወንበር ጠባቂዎች(የኦህዴድ መከላከያ) መካከል በነበረው ዉጊያ ፋኖን ደግፋችኋል፣ፋኖ ናችሁ ወዘተ በማለት በከፍተኛ ሁኔታ እያዋከቡ ይገኛሉ።
ካድሬዎቹ ከሚያሳድዷቸዉ የከተማዋ ወጣቶች መካከል #ለአብነት ያህልም

1/መምህር አብራራው መንግስቴ
(ከዚህ በፊት በአማራነቱ ታስሮ ብዙ የተንገላታ እና ዋጋ እየከፈለ ያለ የአባቱ ልጅ ፋኖ)
2/አማኑኤል ክብረት
3/እንዳለው አዲሱ
4/ተመስገን እና
ሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ ይገኙበታል።

ከሌሎች የአማራ አካባቢዎች አንፃር ስንመለከተው ይህ አካባቢ የብዙ አቅመቢስ ካድሬዎች መሰብሰቢያ ነዉ።
ምክንያቱም የአከባቢው ወጣቶች ፋኖዊ እንቅስቃሴዎቻቸው እምብዛም ነዉ።

ስለሆነም "ድመት አላይ ብትል አይጥ ቆነጠጠች" እንደሚባለው አካባቢው ላይ የተደራጀ እና ፍፁም የአማራነት ስነ ልቦናን የታጠቀ ሀይል አለመኖሩን የተረዱት አቅመቢስ ካድሬዎች እንደፈለጉ ወጣቶች ላይ ይፈነጩ ጀምረዋል።

ይሁንእንጅ ወደፊት አካባቢው ላይ ትልቅ የካድሬ ፅዳት እና የአማራ ፋኖን የማደራጀት ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን።

ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩትን ካድሬዎችን አደራ ተቀበሉን እንላለን!

1/አቶ ነጋሽ ምስጋናው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ

2/አቶ ብሩክ መኮንን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ

3/ሻለቃ ናቃቸዉ አቸነፈ የወረዳው ጠረ ሽምቅ(ሚሊሺያ) አዛዥ እና ተላላኪ
ሌሎችም ፀረ አማራ ካድሬዎች ይገኙበታል።

15/08/2023

ፓርላማው በአማራ ሕዝብ ላይ የጀመረውን ሕዝባዊ ወ*ረ*ራ ለማስቀጠል የታለመለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጽድቋል።

12 ድምፅ ተዓቅቦ እና 16 ተቃውሞ ተመዝግቧል።

የድምፅ ተዓቅቦ እና ተቃውሞ ያሰማችሁ እንደራሴዎች እናመሰግናለን።

እጅ ያወጣችሁ አካላት ያልታወቁ ኃይሎች ሰላም እንዲሏችሁ፤ ስምና አድራሻችሁን እናደርሳለን።

ድል ለፋኖ‼️
እናሸንፋችኋለን‼️

  #29/11/2015በአርማጭሆዉ አብሪ ኮከብ ፋኖ ሲሳይ አሸብር የሚመራዉ የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ፋኖ መነሻውን አብርሃጅራ ከተማ በማድረግ በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ መዲና በሆነችዉ ማሰሮ ...
05/08/2023


#29/11/2015
በአርማጭሆዉ አብሪ ኮከብ ፋኖ ሲሳይ አሸብር የሚመራዉ የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ፋኖ መነሻውን አብርሃጅራ ከተማ በማድረግ በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ መዲና በሆነችዉ ማሰሮ ደንብ ከተማ አድርጎ ጎንደር ለመሔድ በጉዞ ላይ እያለ ማሰሮ ደንብ ከተማ ያሉት የብልጽግና ካድሬወች ሳንጃ ከተማ ለሚገኘው የኦነግ ሰራዊት ጥቆማ በመስጠት ከሳንጃ ከተማ በትንሽ ርቀት በምትገኝ ወይደንባሃ የምትባል ቦታ ላይ መንገድ የተዘጋባቸው መሆኑን የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰውናል
#ማሳሰቢያ እነዚህ ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸዉ አማራ አማራ የማይሸቱ የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ አሰተዳዳሪ ነጋሽ ምስጋናው እና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ ብሩክ መኮንን ዘመድ ካላቸዉ ይመከሩ ይረፉ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያቸው ነዉ አይ ካላችሁ እድሜ ላልታወቁ ሀይሎች ምድረ ሽንታም

04/08/2023

#የኦህዴድ አሽከሮች በአርማጭሆ
28/11/2015 ዓ/ም
አማራ በዚህ ወቅት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የፋሽስት ስርዓቱን(ጥቁር ጣሊያኖችን) ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን ትግሉን እንቅፋት ለመሆን የሚሞክሩ እንክርዳዶች መኖራቸውን አረጋግጠናል። ከወደ አርማጭሆ የተሰማዉ አሳፋሪ ክስተት ሁነኛ ምሳሌ ነዉ ነገሩ እንዲህ ነዉ በ27/11/2015 ጎንደር ላይ በአማራ ህዝባዊ ሀይል(ፋኖ) እና በስርዓቱ ወንበር ጠባቂ ሚሊሺያዎች(መከላከያ ሚሉት) መካከል በነበረው ዉጊያ መሠረት የአርማጭሆ ሹማምንቶች(ሆድ አደር አማሮች) ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ከማዕከላዊ አርማጭሆ፣ከታች አርማጭሆ እና ጠገዴ አርማጭሆ የተወጣጡ ሚሊሺያዎችን(ፀረአማራዎችን)ወደ ጎንደር ከተማ በፋኖ ወንድሞቻችን ላይ ጥቃት እንዲከፍቱ ልከዋል። ይሄው እኛ ደግሞ እነዚህን ሹማምንቶች አደራ ተቀበሉን እንላለን
የአርማጭሆ ወጣት ሰልጥን ታጠቅ ፋኖን ተቀላቀል

ፋኖ የነፃነታችን አርማ ነዉ

"አምቢ፤ለገዳዬ ግብር አልከፍልም" #ሼር ይደረግ!~ አማራን በጅምላ ለሚገድል~ የአማራ ገበሬን እንዳያርስ ጦር አዝምቶ ለሚጨፈጭፍ~ አርሶ አደሩን ማዳበሪያ ከልክሎ ከጥይት የተረፈውን የአማራ ...
05/07/2023

"አምቢ፤ለገዳዬ ግብር አልከፍልም" #ሼር ይደረግ!

~ አማራን በጅምላ ለሚገድል
~ የአማራ ገበሬን እንዳያርስ ጦር አዝምቶ ለሚጨፈጭፍ
~ አርሶ አደሩን ማዳበሪያ ከልክሎ ከጥይት የተረፈውን የአማራ ህዝብ በርሃብ ለሚጨርስ
~ አማራውን ከቀየው እያፈናቀለ፣ሀብት ንብረቱን እየዘረፈ፣እያዎደመ፣ቤቱን እያፈረሰ ጎዳና ለሚጥል
~ አብያተክርስትያናትን እና መስጅዶችን በከባድ መሳሪያ ለሚያወድም፣ምዕመናኑን ለሚጨፈጭፍ ስርዓት
~በአማራ ህዝብ ላይ በቀጥታ ጦር አዝምቶ፣ንፁሃንን ለሚጨፈጭፍ፣ሴቶችን ለሚደፍር፣እንስሳትን ለሚገድል እና ጀግኖቻችን ለሚያሳድድ
~የአማራውን ነገስታቶች አሻራ ያለባቸውን ቅርሶች ለሚያፈርስ፣ፊደሉን፣ቋንቋውን፣ማንነቱን እና ታሪኩን ለሚያጠፋ
~የአማራን ነጋዴዎች ባንክ አካውንት ለሚያግድ፣ድርጅቶቻቸውን ለሚወርስ፣ለሚያዋክብ ስርዓት
~አማራን ወደ አያቶቹ ከተማ አዲስ አበባ እና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይገባ ለሚከለክል፣በየመንገዱ እያገተ በሚሊየንስ ለሚዘርፍ
~ የአማራ ጋዜጠኞችን፣ሙሁራንን፣አክቲቪስቶችን፣ፈኖዎችን፣መሪዎችንና በአጠቃላይ ታጋዮችን በተለያዮ እስርቤቶች አጉሮ ለሚያሰቃይ
~የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረት እየዘረፉ"ታላቋ ኦሮምያን" ለሚያዋልድ ስርዓት
~ተፈናቃዮን ማስራቡ ሳያንስ፣ የዕርዳታ ንብረት ዘርፎ ለሚሸጥ ስርዓት፣ "እምቢ ለእኔ መግደያ ጥይት መግዣ ግብር አልከፍልም" የሚል ሰፊ ንቅናቄ በአማራ ነጋዴዎች እና ህዝብ በስፋት ሊጀምር መሆኑ ተነግሯል።

"እምቢ፤ግብር ለገዳዬ አልከፍልም" የሚለውን የአማራ ነጋዴዎች እና ህዝብ ንቅናቄ ሁሉም አካላት እኔዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል።

 #መርጃ!                                                                     አገሪቱን እያመሰ ያለው መንግስት ተብየው ብልጽግናም በሉት ኦህዴድ/ብአዴ...
05/07/2023

#መርጃ! አገሪቱን እያመሰ ያለው መንግስት ተብየው ብልጽግናም በሉት ኦህዴድ/ብአዴን የሽብር ተግባሩን ለማፋጠን የሚጠቀምባቸው የሚዲያ አካላት ወይም አክትቪስት በየ ማህበራዊ ሚዲያ ፕላት ፎርሞች እርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ:: እነዚህ ስማቸውን ከዚህ በታች የምዘረዝራቸው አክቲቪስት ባንዳወች በተለያየ ጊዚያት አማራ እንዲጠፋ በነሽመልስ አብዲሳ በየወሩ በሚሊዮን ብር እየተከፈላቸው የሚሰሩ የአማራ ጠላቶች መሆናቸውን ማንኛውም የአማራ ተወላጅ እውቅና እንዲወስድ ያወቀ ደግሞ ላላወቁት በማጋራት እንድታደርሱልን ሲል የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ ጥሪውን ያስተላልፋል:: 1) ባንዳ ብሩክ አበጋዝ ከወሎ 2) ባንዳ ቶማስ ጀጃው ከጎንደር 3) ጌትነት አልማው ከጎጃም ስለሆነም ማንኛውም የአማራ ህዝብም ይሁን የአማራ መከራ መከራየ ነው የምትሉና ከእውነት ጎን የቆማችሁ ዜጎች እነዚህ ከላይ በስም የተጠቀሱት ባንዳወች በፌስ ቡክ፡ በትዊተር፡ በዋትሰአብ ይሁን በማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ የሚያስተላልፉትን የጠላት አጀንዳና ፕሮፖጋንዳ ከመቀበል እንድትቆጠቡ እናሳስባለን:: የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም ድል ለአማራ ህዝብ! ሰላም ለሀገራችን!

የኢትዮጵያ ወይስ የኦሮሞ መከላከያ ሰራዊት???                                                                                           ...
04/07/2023

የኢትዮጵያ ወይስ የኦሮሞ መከላከያ ሰራዊት??? በአንድ ወቅት ጠሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ስብሰባ ቀርበው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊ የአወቃቀር ሹመት ስብጥር የተናገሩትን ንግግር ማንም ሰው ያስታውሰዋል ብየ አስባለሁ:: =============================== ጠሚሩ በንግግራቸው 60% የሚሆኑት የአኢትዮጵያ መከላከያ መኮንኖች የትግራይ ብሔር ተወላጆች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል:: ይሁን እንጅ ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግስት ይባስ ብሎ ነገሩን ከድጥ ወደ ማጡ አድርሶታል:: ይህ ማለት የሀገሪቱን የመከላከያ የጦር መኮንኖች ከ90% በላይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ማድረግ ፍትሐዊነት አለውን? ውድ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በታች ያለውን መረጃ አንብባችሁ የተሰማችሁን አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ምላሻችሁን በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ላይ አስቀምጡ:: ሸር በማድረግም ይህን እውነታ ለሁሉም አዳርሱ!

04/07/2023

የአማራ ህዝብ ጉዞህን ወደ ቀይ ባህር ሳይሆን ቀይ ደም ወደ ሚጠጣው ነብሰ በላ ቡድን አራት ኪሎ አድርግ!

በጭራሽ አልፀፀትም!ከአማራ ህዝብ ጎን በመቆሜ በጭራሽ ፀፀት አይሰማኝም፣ ከአማራ ህዝብ ጎን መቆም አድርባይነት አይደለም ለእውነት መቆም እንጂ! ልጆቼ ከዚህ በላይ መከራ ቢደርስብኝ ስለ እውነ...
04/07/2023

በጭራሽ አልፀፀትም!

ከአማራ ህዝብ ጎን በመቆሜ በጭራሽ ፀፀት አይሰማኝም፣ ከአማራ ህዝብ ጎን መቆም አድርባይነት አይደለም ለእውነት መቆም እንጂ! ልጆቼ ከዚህ በላይ መከራ ቢደርስብኝ ስለ እውነት እንጂ ስለ አማራ አይደለም። ይልቅስ እውነትን ችላ ብዬ ለሆዴ ብሰለፍ ያኔ ይፀፅተኝ ነበር። ስጋዬ ነፃ ቢሆንም መንፈሴ እስረኛ ነበር። አሁን በሚገርም ሁኔታ ውስጤ ሰላም ነው።

የታሪክ ፀሀፊ እና ጋዜጠኛ ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ

03/07/2023



በምስራቅ ጎጃም ደጀን ከተማ ገልገሌ ደንበዛ ተብላ በምትጠራ ቦታ ላይ በአሁን ሰአት የፖሊስ አዛዡ ዘውዱ ታደለ እና ምክትል አዛዡ ሳጅን ወርቁ የተባሉ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።
ሹፌራቸው ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷልም ተብሏል።
ፅናት ሚዲያ -Tsinat media

የአማራ ድምጽ

03/07/2023

"የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ ጉዳይ በዝርዝር!...
ክልሎች የራሳቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ የመማር፣ የማሳደግ መብት እንዳላቸው ደንግጓል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አመራር ግን ይህንን መብት የደፈጠጠው በምን ስልጣኑ ነው?"

አቴና ቱማ አሳምነው

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሰኔ 26/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት “ተዘጋ”;
አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት “ተዘጋ”
የባህል ጥናት ማዕከል “ተዘጋ”

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ:- The first and only university in Ethiopia and the world to officially close Amharic Language and Literature department!

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከቋንቋ፣ ከማንነት፣ ከታሪክ፣ ከባህልና ከአገር በቀል ዕውቀቶች ጋር የተያያዙ የትምህርት መስኮች እንዲዘጉ መወሰኑ

1. መነሻ:_

ዩኒቨርሲቲው ማስተማር የጀመረው በማኅበራዊ ሳይንስ፣ በተፈጥሮ ሳይንስና በሥነ ትምህርት ክፍች ነበር፡፡

በዚህም ብዙ ሺህ ተማሪዎች አስተምሮ አስተምሮ አስመርቋል፡፡ የአካባቢው ማኅበረሰብም ብዙ ርቀው ሳይሄዱ በመረጡት የሙያና የትምህርት መስክ ለመማር እድል አግኝቶ ቆይቷል፡፡

ዛሬ ግን ይህ መብት ባልታወቀ ምክንያት ተጥሶ የአካባቢው ወጣቶችና ጎልማሶች በመረጡት የትምህርት መስክ እንዳይማሩ እንዳይሰለጥኑ፣ እውቀትና ክህሎቶች እንዳይኖራቸው ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተወስኖባቸዋል፡፡

ሌሎች የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበራዊ ሳይንስን ማለትም ታሪክ፣ አማርኛ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ፣ ጂኦግራፊ፣ ሶሲዮሎጂ፣ ሳይኮሎጂ፣ ጋዜጠኝነት፣ ፖለቲካ ሳንስ ወዘተ እያሰፋ በማስተማር በፒ.ኤች.ዲ ደረጃ እያሰለጠኑ ባለበት ሁኔታ፤ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የሚማሩ በርካታ ተማሪዎች እያሉ፣ ተመራጭ ሆኖም ሳለ፣ የሚያስተምሩ በርካታ መምህራንም እያሉ፣ የማኅበረሰቡም የመማር ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እያለ ለምን እንዲዘጉ ተደረገ?

የሸዋ ታሪክ፣ ባህል፣ መልክዓ ምድር፣ የአማርኛ ቋንቋን፣ ሀገር በቀል እውቀትን፣ ኪነ ጥበቡን ማን ያጥናቸው? የአካባቢው ወጣቶችና ተማሪዎች እንዲዘጉ በተወሰነባቸው በእነዚህ የትምህርት መስኮች ለመማርና ለመሰልጠን ለምን ይከለከላሉ?

ክልሎች የራሳቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ የመማር፣ የማሳደግ መብት እንዳላቸው ደንግጓል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አመራር ግን ይህንን መብት የደፈጠጠው በምን ስልጣኑ ነው?

ሸዋ በኢትዮጵያ ታሪክ ፖለቲካ ባህልና ኪነጥበብ በርካታ ፋና ወጊ ሊቃውንት የፈለቁበት፤ ሃገር ያጸኑ፣ ሕይወታቸውን ለሃገር እድገትና አንድነት የሰጡ ናቸው፤ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ፣ አጼ ምኒልክ፣ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም፣ መኮንን እንዳልካቸው እና ሌሎች አያሌ ይጠቀሳሉ፡፡

ይህም አካባቢው ቋንቋ፣ ዲፕሎማሲ፣ ታሪኩ በተለይ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ፣ ማኅበረሰባዊ ጥናት፣ ሃገር በቀል እውቀቱ፣ ኪነ ጥበቡ፣ የትውልድ ቅብብሎሹ ይጠና ዘንድ ትልቅ መነሻ ሃብት ነው፡፡

ከዚህ የታሪክ ቁርኝት በግድ ተነጥሎ ከቋንቋ፣ ባህልና መሰረታዊ ሳይንስ ጋር የተያያዙ ትምህርቶችን መዝጋት ከእውነትና ከሕዝብ ጋር መጋጨት ከመሆኑም በላይ ተጠያቂ የሚያደርግ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ነገር የሚደረገው ይህ ነው የሚባል መሰረታዊ ጥናት ሳይደረግ በጥቂት አመራች ፍላጎትና ግላዊ ውሳኔ መሆኑ ሲጨመርበት ድርጊቱን ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ሳይንሳዊ ያደርገዋል፡፡

መምህራን አልተወያዩም፣ ተማሪዎች አልተወያዩም፣ ማኅበረሰቡ እንደባለድርሻ አካል ሃሳቡ አልተጠየቀም፣ ይፋዊ ጥናትም አልተደረገም፡፡

2. ‹ዲፈረንሼሽን›

‹ዲፈረንሼሽን›፣ ‹ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ›ና ‹አፕላይድ ዩኒቨርሲቲ› በአሁኑ ወቅት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያለአግባብና ምንነታቸውን በውል ባለመረዳት ወይም እነሱን ሰበብ በማድረግ አደገኛና ድብቅ ዓላማን ለማስፈጸም ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡

ከዚሁ ከ‹ዲፈረንሼሽን› (የትኩረት መስክ ልየታ) ጋር በተያያዘ ያለበቂ ጥናት፣ ያለአሳማኝ ምክንያት እና የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞችም ሆነ ባለድርሻ የሆነው የአካባቢው ማኅበረሰብና የማኅበረሰብ መሪዎች ሳይመክሩበት በጥቂት የከፍተኛ አመራር አባላት የተሸፋፈነ ውይይትና ውሳኔ ሰጭነት ምክንያት በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከማንነት፣ ከታሪክ፣ ከባህል፣ ከቋንቋና ከአገርበቀል ዕውቀቶች ጋር የተያያዙ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች እንዲዘጉ መወሰኑ አግባብ ካለመሆኑም በላይ ከፍተኛ ትምህርታዊ፣ ማንነታዊ፣ አብርሆታዊና ማኅበራዊ ቀውስን የሚጋብዝ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

አንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አገልግሎቱን ከሌሎች ተፎካካሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሻለና በተለየ ሁኔታ ሳቢ አድርጎ በማቅረብ ላይ የሚያተኩረውን ‹ዲፈረንሼሽን› ወይም ‹ልየታ› የተባለውን ሃሳብ አሳስቶ በመረዳት ወይም ሆነ ብሎ የግልንና የቡድንን ጥቅም ለማስፈጸም አስቦ በመንቀሳቀስ የትምህርት ክፍሎችንና ኮሌጆችን መዝጋት በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተያዘ እንቅስቃሴ ሆኗል፡፡

ከዓለም የከፍተኛ ትምህርት ልምድ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በዕቅድና ስትራቴጂያዊ አካሄድ የሚከተል መሆን ሲገባው ተቋሙ ከ‹ዲፈረንሼሽን› ዓላማ በተሳሳተ አቅጣጫ ርቆ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ሲቋቋም ጀምሮ ለ16 ዓመታት በስራ ላይ ያሉትን የማህበራዊ ሳይንስና ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ከነ መምህራናቸው፣ ከነአስተዳደር ሰራተኞቻቸው፣ ከነ ቤተሙከራቸው፣ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ እስከደረሱ መርሐግብሮቻቸው ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ ለማፈራረስ እየተሄደበት ያለው የተሰላ ዕቅድ ካለፈው ስህተታችን አለመማራችንን የሚያሳይ ሲሆን በቀደመው ሥርዓት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተባረሩ 42 ምሁራንና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሯዊ ሞቱን ይሙት በሚል የተፈጸሙትን ደባዎች በአስር እጥፍ አባዝቶ መተግበር አጥፊነቱ እንጂ አልሚነቱ አይታየንም፡፡

ለረጅም ጊዜ የፈሰሰውን ሃብት (በየዓመቱ በቢሊዮን ብር እንደሚመደብ ልብ ይሏል)፣ ጉልበትና ዕውቀት መና የሚያስቀርም ይሆናል፡፡

3. የልዬታ/`differenciation` ወይም የልህቀት ማዕከል መነሾ?

በዓለማቀፍ ዓውድ እንደምንረዳው ልዬታ/`differenciation` ወይም የልህቀት ማዕከል/`centre of excellence` አንድ ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመበትን ዓላማ ወይም የተቋቋመበትን አካባቢ እምቅ ሃብት (potential) ማለትም የተፈጥሮ ሃብት፣ በሳይንሳዊ ጥናት ቢለማ እምቅ የሆነ ያልለማ ሃብት፣ አገር በቀል እውቀት ሃብት፣ ባህል፣ የታሪክና አርኬኦሎጂ እምቅ ሃብት፣ የአየር ንብረትና የማኅበረሰብ አኗነዋርና ፍልስፍና ወዘተ ግምት ውስጥ ይገባል፡፡

በመሆኑም ትምህርት ሚኒስር ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢያቸውንና የተቋማቸውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የትምህርት መስኮችን ለይተው እንዲልኩ ለዩኒቨርሲቲዎች በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች መርተው በሚልኩበት ወቅት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዓላማው ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ለልህቀት ማዕከልነት የሚያበቃ ተግባራዊ መሰረት የሌላቸው መስኮች ለይቶ ባካተተበት ሁኔታ የአካባቢውን እምቅ የባህልና የቋንቋ ጥናት፣ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታክና አርኬኦሎጂ ጥናት፣ የአገርበቀል እውቀትና ማንነት ጥናት መስኮች ያሉባቸው የማኅበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ጥናት መስኮችን የልህቀት ማዕከል አድርጎ ካለመምረጡም ባሻገር መስኮቹ “ይዘጋሉ”፣ መምህራኑንም “ትባረራላችሁ” በማለት ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በየአደባባዩ በየስብሰባው አመራሩ በተደጋጋሚ ንግግር ሲያደርግ ተሰምቷል፤ ይህም አልበቃ ብሎ በይፋ የጥናት መስኮችን ለመዝጋት የሚረዳ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ነድፈው ለመዝጋት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡

በነገራችን ላይ አንድ የትምህርት ተቋም የተወሰኑ የተመረጡ መስኮችን የልህቀት ማዕከል አደርጋለሁ የሚል ውሳኔ ይዞም ሆነ ተቋሙ ሲመሰረት ጀምሮ በተመረጡ መስኮች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ለመላቅ ሲያልም ሌሎች የትምህርት መስኮችን ይዘጋል ወይም አይሰጥም ማለት አይደለም፡፡

በመረጣቸው መስኮች ላይ ከሌሎች በተለዬ የአካባቢንና የተቋሙን እምቅ ዳራ፣ የሰው ሃብትና አመቺነት በመጠቀም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እሰራ ነገር ግን በሌሎች መስኮችም መማር ማስተማሩን ያስቀጥላል፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራር ድርጊት ግን በዓለማቀፍ አውድም ሆነ በአገራችን ባልተለመደ መልኩ “አልፈለኳቸውም” ያላቸውን መስኮች የልህቀት ማዕከላት ባይሆኑ እንኳ መማር ማስተማር ላይ እንዲቀጥሉ ማድረግ የሚቻልበት አሰራር እያለ በአስደንጋጭ ሁኔታ ለመዝጋት ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ተመሳሳይ መመሪያ የተሰጣቸው የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ከአካባቢያቸው ባህልና እምቅ ሃብት እንዲሁም የተቋማቸው ሁኔታ አንጻር የልህቀት ማዕከላቸውን የመረጡ ቢሆንም ሌሎች መስኮችን ለመዝጋት የሄዱበት የጥድፊያ መንገድ እንደሌለ ለማጣራት ችለናል፡፡

በአገራችን ያለውን ልምድ ብንወስድ፣ የልህቀት ማዕከል ልየታ የሚለው ሃሳብ ከመምጣቱ በፊት ጀምሮ ሃሳቡ ተፈጻሚ የሆነባቸው ተቋማትን እናገኛለን፡፡

ለምሳሌ፡- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሚታወቀው በውሃ ቴክኖሎጂ ነው፤ ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርና፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ (በውሃ፣ በመርከበኝነት/ማሪን ትክኖሎጂ) የሚታወቁ ሲሆን ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡

አንዳንዶቹ ሲመሰረቱ ጀምሮ ለዚሁ ዓላማ ታስቦ የተቋቋሙ አሉ፣ ለምሳሌ አርባምንጭን መውሰድ ይቻላል፡፡

ይህን የልህቀት ልየታ መተግበር ከጀመሩም በጣም ረዥም ጊዜ ማለትም ለአስርተ ዓመታት የዘለቀ ነው፡፡

ነገር ግን አንዳቸውም ሌሎች የትምህት መስኮችን አልዘጉም፣ እንደውም አዳዲስ መስኮችን፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ እስከ ተፈጥሮ ሳይንስ በመክፈት እያስፋፉ ነው፡፡

ብዙ የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች በተቋቋሙባቸው ጊዜያት የነበሩ የጥናት መስቻቸውን የሚታወቁባቸው የልህቀት ማዕከላቸው ያደርጋሉ፡፡

የደብረ ብርሃ ዩኒቨርሲቲ ከነባራዊ ሃቅ፣ ከሳይንሳዊ አመክንዮም ሆነ ከሃገር ዓቀፍና ከዓለማቀፍ ተሞክሮዎች ባፈነገጠ መልኩ በጥቂት የአመራር አካላት ፍላጎትና የግል አተያይ በመነሳት ተሞክሮዎችን ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሳያመሳክሩ ዓላማው ግልጽ ባልሆነና ለተጨማሪ መጠራጠር በሚገፋፋ መልኩ የቋንቋ (ቃል በቃል ፕሬዚዳንቱ `አማርኛን ይዤ አልቀጥልም` ማለቱን ልብ ይሏል)፣ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ፣ የባህል፣ የአካባቢው እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና አገር በቀል እውቀት ጥናት መስኮችን ለመዝጋት በሚያሳፍር ሁኔታ ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ሌላው፤ እነዚህ የትምህርት መስኮች ዩኒቨርሲቲው ሲከፈት ማስተማር የመጀረባቸው መስኮች በመሆናቸው ብዙ የሰው ሃይል፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሃብት የፈሰሰባቸው ከመሆኑም በላይ አንዳንዶቹ መስኮች በ3ኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ደረጃ ማስተማር የጀመሩ ነበሩ፡፡

ይሄ ሃሳብ የቀደመው አገዛዝ ማኅበራዊ መሰረቶችን ለመናድ የማኅበራዊ ሳይንስ ጥናቶችን `ተፈጥሯዊ ሞታቸውን እንዲሞቱ` የሄደበትን መንገድና በአገረ-መንግስት እሳቤ ላይ የጣለውን ትውልድ ማይረሳው ጠባሳ ለመድገም የሚደረግ መፍጨርጨር እንዳይሆን ያሰጋል፡፡

4. የሸዋ አካባቢ ታሪካዊ ዳራ, የልዬታ ሃሳብ & የአማርኛና ታሪክ መዘጋት
ከላይ እንደተገለጸው ከአሁን በፊት በዓለማቀፍ ዓውድ እንደምንረዳው ልዬታ/`differenciation` ወይም የልህቀት ማዕከል/`centre of excellence` አንድ ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመበትን ዓላማ ወይም የተቋቋመበትን አካባቢ እምቅ ሃብት (potential) ማለትም የተፈጥሮ ሃብት፣ በሳይንሳዊ ጥናት ቢለማ እምቅ የሆነ ያልለማ ሃብት እና መሰል ነባራዊ ሃቆችን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም ነው፡፡

ለዚህም ጥናት የሚያስፈልገው ሲሆን ከጥናት መነሻዎች ውስጥ አንዱ የአካባቢውን ተፈጥሯዊና ማኅበራዊ መሰረትን መመርመር ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ አካባቢው ምን አለው ተብሎ ሲጠየቅ በጥና የተደገፈ የመካከለኛው ታሪክ ጥናት፣ የአማርኛ ቋንቋና ማንነት ጥናት፣ በተፈጥሮ ሳይንስ መስኮች የሚበለጽጉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት፣ አገር በቀል እውቀት፣ የአካባቢ ማዕከላዊነት፣ የኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ግንባታ እሳቤ የዳበረበት እንደመሆኑ `ይዘጉ` የተባሉት የማህበራና የተፈጥሮ ሳይንስ መስኮች እጅጉን አስፈላጊ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥናት መስኮች፤ የአካባቢውን እምቅ ሃብት ለሳይንሳዊ ግብዓት ለመጠቀም፣ ማኅበረሰቡንም ተፈጥሮና ታሪክ ከቸረው ጸጋው የምርምር ተቋዳሽ እንዲሆን ከሁሉም በላይ ቋንቋውን የማበልጸግ፣ ታኩንና ተፈጥሯዊ ሃበቱን የማበልጸግ፣ ማንነቱን የማስጠናት፣ በሃገር በቀል እውቀቱ ሳይንሳዊ ድጋፍ አግኝቶ የመጠቀም ከመንግስት የተፈቀደለትን ህጋዊና በተፈጥሮ ጣገኘውን ፀጋዊ መብቶቹን የሚገፍ ነው፡፡

በጀርመን ሃገር የሚገኘው ሃምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ከሚታወቅባቸው የጥናት መስኮች ውስጥ አንደኛው `የኢዮብ ሉዶልፍ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል/Hiob Ludolf center for Ethiopian Studies` አንዱ ሲሆን የምርምር ትኩረቱን የኢትዮጵያ ጥናት ሆኖ በዋናነት የመካከለኛው ዘመን ላይ ያደረገ ነው፡፡

ለምርምሩ ግብዓት ደግሞ በብዛት የመካከለኛው ዘመን አስኳል ከሆነው ከሸዋ አካባቢ የታሪክ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የግእዝ ቋንቋ፣ የአርኬኦሎጂ፣ የመዛግብት፣ የአገር በቀል እውቀት፣ ባህላዊ ጥበባት እና መሰል ሃብቶችን ይዋሳል፡፡

በዚህ ስራው ጀርመኑ ሃምቡርግ ዩኒቨርሲቲ በዓለም ይታወቃል፡፡ በሸዋ እምብርት ላይ የሚገኘው ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ግን የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተፈጥሯዊ መብት በሚገፍና ክብርን በሚነካ መልኩ የመካከለኛው ዘመን ጥናት ያለበትን የአማርና ቋንቋ፣ የማንነት፣ የባህላዊ ጥበባት፣ የታሪክ፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የግእዝ ቋንቋ፣ የአርኬኦሎጂ፣ የመዛግብት፣ የአገር በቀል እውቀት እና ሌሎች የኢትዮጵያዊነት አስኳር የሆነ የጥናት መስኮችን ያቀፉ የማኅበራዊ ሳይንስና የተፈጥሮ ሳይንስ መስኮችን በጥቂት አመራች የግል ተነሳሽነት `ለመዝጋት` ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

ሸዋ በተስፋ ገብረስላሴ አማካኝነት የፊደል ገበታ ቀርፆ አማርኛ ቋንቋን በዘመናዊ መንገድ ለማስተማር ግንባር ቀደም ነው፡፡

አማርኛ ቋንቋ የውቀት ብርሃን ሆኖ በመላው ኢትዮጵያ እንዲሰራጭ ታሪካዊ ድርሻውን ተወጥቷል፡፡

ሸዋ የደራሲያን መንደር ነች፡፡ የጥበብ ጥማት ያለበት ሁሉ ያሻውን ያህል የሚቋደስባት የሥነጽሁፍ ጓደ ናት፡፡

ይህም ሲባል:- ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን፣ ተስፋ ገብረስላሴን፣ ተክለጻድቅ መኩሪያን፤ መርስኤ ኃዘን ወልደ ቂርቆስን፣ ደጃዝማች ወልደሰማዕት፣ ተክለሐዋሪያት ተክለማርያምን፤ ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤልን፣ ዳኛቸው ወርቁን፣ ሌሎች አያሌ የሥነ ሰብዕ ታላላቅ ልሂቃንን መጥቀስ ይቻላል፡፡

እነ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ `የአማርኛ ሥነ ትሑፍ አባት` የተባሉትን ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ ብላቴን ጌታ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሐንስ፣ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፣ አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ፣ ደስታ ተክለ ወልድን፣ አክሊሉ ኃብተ ወልድ፣ መኮንን እንዳልካቸው፣ እንዳልካቸው መኮንን፣ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ፣ ይድነቃቸው ተሰማ እና ሌሎች በርካታ ደራስያን፣ የቋንቋ ልሂቃንን የዲፕሎማሲና አስተዳደር ሰዎችን፣ አርበኞችን፣ የታሪክ ባለሙያዎችን የአገር በቀል እውቀት ተመራማሪዎችን፣ የኢትዮጵያ መሰረቶችና ባለውለታዎችን፣ የስልጣኔ ፋናወጊ ሰዎችን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ስለሆነም አማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሲከፈትም አንዱ ዓላማው ይህን ታሪካዊ እና ትምህርታዊ እሴት ማስቀጠል፤ የእነዚያን እንቁ የኪነጠበብ ሰዎች የአእምሮ ውጤት ማጥናት እና መዘከር ነበር፡፡

ነገር ግን ይህ እረፍት የነሣቸው ባለሥልጣናት በትውልድ ቀየው ላይ እንኳን መጠጊያ አንፈቅድለት ስለምን ይላሉ?

ከጅምሩ ኮሌጆቹ ሲደራጁም ሆነ በስሩ ያሉ በርካታ ትምህርት ክፍሎች ሲከፈቱ በጥናት ላይ ተመስርተው፣ የአካባቢውንና የሀገርን ፍላጎትን ያገናዘቡ፣ ታሪክን የሚያስጠብቁ፣ ስነ-ልቦናንና ማህበራዊ እሴትን የሚያዳብሩ እንዲሁም የመልማት ጸጋን መሠረት በማድረግ ነበር።

ስለሆነም ለእነዚህ ትምህርት ክፍሎች መዘጋት ያበቃቸውን ምክንያት ለመረዳት ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የሚቀርብ ጥያቄ ነው፡፡ ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ አንዱ ዓላማ የአካባቢውን ማህበረሰብ በቅርበት ለማገልገል፣ በእውቀት ለማበልጸግ፣ ወጉን፣ ደንቡን፣ ፍላጎቱን በምርምር ለማገዝና ጥያቄዎቹን ለመመለስ ነው።

5. ምን ይጠበቃል?

በግልጽ አነጋገር አማርኛ ቋንቋ የሀገሪቱ ልሳን ነው፡፡ የ120 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መግባቢያ ነው፡፡

እውነታው ይህ ከሆነ፣ ይህን ሀገራዊ ፋይዳ የማደግፍ የፌደራል ተቋም አስተዋጽኦው ምን ሊሆን ነው? በመሆኑም አማርና ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ሃገር በቀል እውቀት ጥናት እና መሰል ከአካባቢው ማኅበረሰብ ተጨባጭ ሁኔታም ሆነ ከዓለምዓቀፍ አውድ እውነታ ጋር በሚጻረር መልኩ ለመዝጋት የዩኒቨርሲቲው አመራር የወሰነው ውሳኔ የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርግና በአስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ነው፡፡

የትምህርት መስኮቹ መዘጋት ለዩኒቨርሲቲውም፣ ለአካባቢው ማኅበረሰብም ሆነ ለሀገር ብክነት ነው፡፡

በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከተውና የሚገደው ማንናው ሰው የሚከተሉትን ነጥቦች ሊያጤናቸው ይገባል፡፡

ከሚዘጉት የትምህርት ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነው አማርኛ የሃገሪቱ የሥራ ቋንቋ ከመሆኑም ባሻገር በመላ ሃገሪቱ የንግድ፣ የባህል፣ የትምህርት ቋንቋ መሆኑ፤

በአማርኛ ትምህርት ክፍል ከሚጠቀሱት የጥናት መስኮች ውስጥ የግእዝ ጥናት አንዱ ነው፡፡ ይህ የግእዝ ቋንቋ ደግሞ ከጥንት ዘመን በተለይ መካከለኛው ዘመን ጀምሮ የሃገሪቱ ፖለቲካ፣ የባህል፣ የሥራ፣ የሥነ ጽሑፍ እና ኪነ ጥበብ ቋንቋ ሆኖ የዘለቀ መሆኑና መዘጋቱ የራሱ የሆነ ትውልዳዊ ክፍተት የሚፈጥር መሆኑ፤

ከሚዘጉት የትምህርት ክፍሎች ውስጥ አንዱ ታሪክ በተለይ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ከሚጠናባቸው ሃሳባዊ ቦታዎች አንዱ የሸዋ አካባቢ መሆኑ ይታወቃ፡፡ የኢትዮጵያ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ዋነኛ ሁነቶች የተከናወኑበትና ከፍተኛ የጥናት ግብዓትና ሪሶርስ ያለበት አካባቢ ላይ ዩኒቨርሲቲው እንደመመስረቱ ይህን የጥናት መስክ ዋነኛ ትኩረቱ ሊያደርገው በተገባ ነበር፡፡

ምንጭ_አቴና ቱማ አሳምነው

03/07/2023

ኦነግ ደግሞ አጀንዳ ፈጥራ ሙታ ቀይ ባህር ምናምን ትላለች እንደ አማራ መጀመሪያ የሚፈሰውን ቀይ የሰው ልጅ ደም ማስቆም አለብን!

03/07/2023

ጋዜጠኝነት ምን ማለት እንደሆነ የእውነት ቋሚ ሀውልት ነው። ደፋር፣ አሰላሳይ፣ ትሁት እና ለሄደው ለመጣው የማያሸረግድ የእውነት እና የሀቅ አምድ ነው።

ጋዜጠኝነት

ጋዜጠኝነት ከዕለት ተዕለት የሕይወት ገጠመኝ፣ ከጠመንጃ አፈሙዝ ከሚንቦገቦግ የእሳት ላንቃ፣ ከተወሳሰበ የመንግሥትም ሆነ የድርጅት ሚስጥር አንዳች ጠቃሚ የፕሬስ ውጤትን ፈልቅቆ ለማውጣት ጥረት የሚደረግበት የሕይወት መስክ ወይም ሙያ ነው፡፡

ለጋዜጠኛነት ሥራ፣ የሙያ ብቃት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ምናልባት፣ «ጋዜጠኛው በአንሸራታች ቀለም ወይም ጭቃ በተሞላ ጎዳና በፍፁም ጥንቃቄ እንደሚጓዝ ወይም በበረዶ በተሸፈነ መሬት ላይ ባለተሽከርካሪ ጫማ እንደሚከንፈው ሰው የሚቆጠር ነው፤» በሚል ቢገለጥ ምናልባት ይቀል ይሆናል፡፡ ጋዜጠኛነት፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ክህሎት በትምህርት ቤት ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡

ነገር ግን የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ ሌት ተቀን የማንበብ፣... የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ ሌት ተቀን የመጻፍ፣... የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ ሌት ተቀን የማረም ውስጣዊ ፍላጎት ነው፡፡

የጋዜጠኝነት ሙያ ምግብ ሳይበላ የሚሠራበት፣ ወይም በሆነ አጋጣሚ ረዥም መንገድ በእግር የሚኬድበት፣ የጋዜጠኝነት መሣሪያዎችን ተሸክሞ የሚጓዝበት፣ ያለረዳትና አይዞህ ባይ የሚዋትቱበት በመሆኑ ጋዜጠኛ ሆኖ ለመቀጠል ፍላጐት ብቻ ሳይሆን አካላዊ ብቃት፣ አዕምሯዊ ብቃትና የባህርይ ብቃት እንዲኖረው ያስፈልገዋል፡፡

ጋዜጠኛው ለማወቅ፣ አውቆም ለማሳወቅ የተዘጋጀ ዜጋ እንደመሆኑ መጠን ሊቀ ሊቃውንቱን እንኳን ባይሆን መካከለኛዎቹን ከመካከለኞቹም የተሻሉትን መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ይህንንም ደረጃ ለመያዝ ፍላጐት ወይም ምኞች ወይም ዝንባሌ ብቻ አይበቃም፡፡ ራስን በንባብ ማነፅንና ከሌሎች በመማር ለማደራጀት ጥረት ማድረግን ይጠይቃል፡፡ በጥቅሉ ጋዜጠኝነት የተራራቀን ዓለም በሴኮንዶች ጊዜ ውስጥ የማገናኘት ሙያ ነው ልንለው እንችላለን፡፡

ጋዜጠኝነት በየብስ ላይ ሳይወሰን ዕድገቱን ከሳይንስ ጋር አጣምሮ በመጓዝ ስለህዋውና ስለባህር ውስጥ ጥበባት መረጃዎችን፣ ትምህርቶችን እየሰጠ በዚያው ልክም እያዝናና እንደሚገኝም ከዕድገት ታሪኩ እንገነዘባለን፡፡

የሩቅ አገር መልካም ወሬ በሚል ርዕስ የጻፉት ቤን ጀንስን፣ «ጋዜጠኛው በከፊልም ቢሆን የተቀደሰ ነው፣ ካለበለዚያም ጠቢቡ ሰለሞን 'ከሩቅ አገር የሚመጣ ወሬ (ዜና) ጥማትን እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውኃ ነው' እንዳለው መሆን ይኖርበታል፤» በማለት፣ የጋዜጠኛው የሙያ ብቃት ብዙ ሰዎች ከሚገምቱት በላይ ከፍተኛ ተልዕኮ ያለው መሆኑን ሲጠቅሱ፣

ሒንሪ ማርቲን የተባለው እንግሊዛዊ «የማወቅ ፍላጐቱ አነሳስቶት ያኔ ምንም ዓይነት መገናኛ ወዳልነበረውና ጫካ ወደበዛበት ምሥራቅ አፍሪካ በመጓዝ የዶክተር ዴቪድ ሊቪንግስተንን መገኘት ሥፍራው ሄዶ በማየት ባያበስር ኖሮ፣ ሚስጥሩ የጥቂት ሰዎች ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር፤» በማለት በምሳሌ ይገልጡልናል፡፡

እንደ ቤን ጆንሰን አገላለጥ አንድ ጋዜጠኛ ማንም ሰው በቀላሉ የማያገኘውንና ተቀብሮ ይቀር የነበረውን በእግሩ በመጓዝ ጭምር ፈልፍሎ የማውጣት ከፍተኛ ችሎታ ያለው ነው፡፡

በዚህም ሒደት ሕይወትን ያህል ትልቅ ቁምነገር ለደን አራዊትና አደገኛ ሕመም አሳልፎ መስጠትን የሚጠይቅ ሙያም ነው፡፡

ጋዜጠኝነት ሙያ ፣ እውቀት፣ ሚዛናዊነት፣ አርቆ አሳቢነት ፣ ኃላፊነት መሸከም ፣ ተሰጥኦና ፍላጎትም ነው፡፡
የዚህ ሁሉ አምሳል ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነው።

03/07/2023

እነ ሽመልስ አብዲሳ "የእኛ ሰው በባህርዳር" ብለው የሚጠሩት እና የሚተማመኑበት ሰማ ጥሩነህ!

ሰማ ጥሩነህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መንግስት መዋቅር የተመለመለው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር ይላሉ ምንጮች። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ የግርግሩ ትክክለኛ ምክንያት ባይታወስም ግርግር የነበረነት ወቅት ነበር።

ሰማ ጥሩነህ ያኔ ነው የተመለመለው። ምልመላውም የተከናወነው በአቶ በረከት ሰምዖን ነበር። ሰውየው የመንግስት መዋቅር ውስጥ ከመግባቱ በፊት በአዲስ አበባ ወዛደር/ጫኝ አውራጅ/ ነበር የሚሰራው። (ለስራው ትልቅ ክብር ያለኝ መሆኑ ይሰመርበት) ይለናል ምንጫችን።

በወቅቱ የተነሳውን ግር ግር ለማብረድና ወጣቶችን ለማሳሰር በወቅቱ በበረከት ሰምዖን አይን የገባው ሰማ ጥሩነህ ነበር። ሰማ በበረከት ሰምዖን ሲመለመል በስርዓት መጻፍም ሆነ ማንበብ አይችልም ነበር ብሎኛል የቅርብ ጓደኛው።

ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ስልጠና ተስጥቶት ማንበብና መጻፍ ሲጀምር የስለላ ስልጠና/ደህንነት/ እየተከታተለ እዛው አዲስ አበባ ከቆየ በኋላ ወደ ሶማሌ ተልኮ እዛው ሶማሌ ሲሰራ ቆይቶ በኋላ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲላክ ተደረገ።

ቤንሻንጉል እያለም እያንዳንዷ ግጭትና ጸረ አማራ ዘመቻ ይካሄድ የነበረው በዚሁ ሰውዬ አስተባባሪነት ነበረ ከዛም ከመተከል አምጥተው አዊ ዞን ተመድቦ እየሰራ በአማራና አገው መካከል ግጭት ፈጥሮ እንጅባራን የደም ማዕበል እንዲበላት በተለያየ ጊዜ ሞክሮ ሲከሽፍበት ከርሟል።

ይህን ማድረግ ባለመቻሉ በአለቃዎቹ ቂም የተያዘበት ሰማ ከአዊ ዞን ተነስቶ ወደ አሶሳ ተላከ ከዛ በኋላ በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች ጸረ አማራ አስተምሮዎችን በሚገባ ፈጽሟል። የመተከል እልቂት የሰማ ጥሩነህ ስራ ውጤት ነውም ብለዋል።

ከዛ በኋላ ገዱ ለትህነግ ጀርባውን መስጠት ሲጀምር የአገው ሸንጎን እንዲያደራጅና ገዱን እንዲሰልል ወደ አማራ ክልል መለሱት። በሚገባ ስራውን ሲሰራላቸው ቆይቶ ለአገው ሸንጎ ጥንካሬ ሲባል ወደ አዊ ዞን እንዲመጣ ተደረገ።

ለትህነግ ያለው ፍቅር የትየለሌ ነው ያለው ምንጫችን አሁንም ቢሆን የአገው ሸንጎ ዋና አንቀሳቃሽና የኦህዴድ በተለይም የትህነግ ሰላይ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ባንዳ ነው። ታስታውሱ እንደሆነ አለን ምንጫችን "የክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ እያለ እያንዳንዱን የጦርነት ዝግጅት በመግለጫ መልክ ነበረ ሚዲያ ላይ እንዲወጣ የሚያደርገው"

ሰውየው ቀጥታ የሚገናኘው ከእነ አብይ/ ሽመልስ/ ብርሃኑ ጁላ አሁን ደግሞ ከእነ ደብረፂዮን ጋር ነው የሚሉት ምንጮች በአማራ ክልል የተከፈተውን ጦርነት በበላይነት እያስተባበረ እና መረጃ እየሰጠ ያለው እሱ ነውም ብለዋል። ያው የእነ ይልቃል ከፋለ የድውይ ስብስቦች የሚሰሩት አድርባይነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

በመከላከያም ይሁን በክልሉ ፀጥታ መዋቅር እንዲሁም ከአመራሩ ለህዝብ ውግንና ያላቸውን መረጃ በመሰብሰብ እንዲመቱ ወይም እንዲሸማቀቁ አለያም እንዲባረሩ እና ከቦታው እንዲቀየሩ ይሰራል።

በስብሰባም ላይ እና ለአንዳንዶቹም ስልክ እየደወለ " ውሎ አዳራችሁ፤ ውይይታችሁ ከፋኖ ጋር ነው፤ እንወያይ እያላችሁ ፋኖን ልቡን ታሳብጣላችሁ" እያለ ለማሸማቀቅ ሙከራ ሁሉ አድርጓል።

ሌላው የዚህ ሰውዬ አደገኛነት አማራውን እረፍት ለመንሳት እና አጀንዳውን ለማሳት ጎንደር አካባቢ በደረቅ ወንጀል የሚፈለጉትን የቅማንት ታጣቂ እያደራጀ እና በውይይት፤ በእርቅ የተዘጋን ፋይል ለመቀስቀስ ጥረት እያደረገ መሆኑ ነው።

ለዚህ ደግሞ በከተማችን በወንጀል የሚጠረጠሩ አንዳንድ አመራሮችን: በህዝብ የተነጠሉ እና የማይፈለጉ አመራሮችን: በዘመድ አዝማድ ተደራጅተው ከህዝቡ ላይ ተጣብቀው ጎንደርን ከሚግጧት ጋር ተናበው ነው እየሰሩ ያሉት።

ለአብነት ያህል ወደፊት በዝርዝር እመጣለሁ (ብሏል ምንጫችን) ለአሁኑ የአዘዞ እና አካባቢው ፖሊስ አዛዥን ኮማንደር ብርሃኑን መጥቀስ እችላለሁ። ከዚህ ሰውዬ ጋር በመገናኘት ጎንደር ውስጥ ደም አፋሳሽ ነገር ለመፍጠር ሰሞኑን ሞክሮ ከሽፏል። ይህንንም እመጣበታለሁ። ሌላው ሰማ ጥሩነህ በቋራ መተማ ሱዳን አዋሳኝ ያለውን የሰዎች እገታና ዘረፋ ታጣቂዎችን አደራጅቶ የሚመራው ፤ ከመተከል አማራ እንዲፀዳ እየሰራ ያለው እሱ ነው።

"ክልል ብሎ ለማዋለድ ከጎንደር ቋራ ጀምሮ ቤኒሻንጉልን በከፊል እነ ሽመልስ አብዲሳ የቀረውን በመያዝ ተጎራባች ክልል ለመሆን ያቀደ ነው። ያው ቅዠት ቢሆንም ቅሉ!

በምስሉ ላይ ከሰማ ጋር አብሮ የሚታየው ኮማንደር ብርሃኑ ይባላል በጎንደር የአዘዞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ሲሆን ከሰማ ጥሩነህ ጋር በጎንደር ደባ እየፈጸመ ያለ ባንዳ ነው በማለት መረጃውን ከምስሎቹ ጋር አያይዞ አድርሶናል ምንጫችን

02/07/2023

መነሻችን ታች አርማጭሆ ወረዳ አቸሬ ከተማ አድርገን የቤት ዕቃ ቁሳቁሶችን በመኪና ጭነን ወደ ጎንደር ስንጓዝ ሳንጃ ከተማ ከሚገኘው የመከላከያ ኬላ ፍተሻ በአገዛዙ የሰራዊት አባላት ግፍና በደል ደረሰብን ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል:: ====================== የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ ሰኔ 25/2015 ዓ.ም አርማጭሆ ======================= ታች አርማጭሆ ወረዳ አቸሬ ከተማ ተነስተን የቤት ቁሳቁስ በጭነት አይሲውዝ መኪና ጭነን ወደ ጎንደር ከተማ ስንጓዝ ሳንጃ ከተማ መግቢያው በር ላይ ከሚገኘው የመከላከያ ኬላ ፍተሻ በአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ግፍና በደል እንግልት ደርሶብናል ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ህጋዊ ዜጎች አቤቱታቸውን ለሚዲያችን በውስጥ መስመር አድርሰውናል:: ቀኑ ሐሙስ ሰኔ 22/2015 ዓ.ም ከቀኑ 1፡30 ሰዓት አካባቢ የተወሰኑ የቤት እቃወችን ማለትም ፍሪጅ፡ቁም ሳጥንና አልጋ በጭነት መኪና ጭነን ከአቸሬ ወደ ጎንደር በምንጓዝበት ጊዜ ነበር ሳንጃ ከተማ የሚገኘውና በኮሎኔል መከተ የሚመራውና ኬላ ፍተሻ የሚገኘው የሰራዊት አባላት ህጋዊና ማንነታችን የሚገልጽ መታወቂያ እያለን ዛቻና ማስፈራሪያ ቃላቶችን በመጠቀም የትም መሔድ አትችሉም በማለት ከጉዟችን አስተጓጉለውናል ሲሉ ተበዳይ አጋርተውናል:: እኛ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ዋስ ጠበቃ ሲሆንና የህዝብ ደህንነትን ሲያስጠብቅ፥የሀገር ሉአላዊነት እንዳይደፈርና ሀገርን ከውጭ ወራሪ ጠላት ሲከላከል እንጅ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስን ሰላማዊና ህጋዊ ዜጋን ሲያንገላታ አይተንም ሰምተንም አናውቅም ሲሉ ምሬታቸውን የገለጹት ከዚህም በላይ ያገቱትን መኪና አንለቅም ብለው በገንዘብ የተደራደሩን መሆናቸውን መላው የአርማጭሆ ህዝብ እንዲያውቅልን ሲሉ ምሬታቸውን አሰምተዋል:: ልብ በሉ መከላከያ ተቋም የኪራይ መሰብሰቢያም እስከመሆን ደርሷል ሲሉ ተበዳይ በደላቸውን አጋርተውናል::በመጨረሻም የዚህን ቀጠና የመከላከያ ሰራዊት የሚመራው የመከላከያ መኮንን ኮሎኔል መከተ እንዲህ አይነት ጸያፍ ድርጊትና ከሚሊታሪ ህግ አፈንግጠው የተቋሙን ስም የሚያጠለሹትን አባላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና በህግ እንዲቀጡ ያድርግልን ሲሉ ተበዳይ አሳስበዋል::

ለመላው የአርማጭሆ ህዝብ! ፋኖን ተቀላቀሉ!
02/07/2023

ለመላው የአርማጭሆ ህዝብ! ፋኖን ተቀላቀሉ!

02/07/2023

ጎበዜ ደመወዝህ ስንት ነው?
[በጋዜጠኛ አዲሱ ደርቤ]

በአንድ ወቅት አንድ ወዳጃችን በወሬ መሐል "ጎበዜ ኢሳት ውስጥ ቀንም ሌትም ጭምር ከሚሰሩት ጋዜጠኞች መካካል አንዱ ነህ፤ ደመወዝህ ግን ስንት ነው?" የሚል ጥያቄ ያነሳል፤ እኛም ቀጥሎ የጎበዜን መልስ መጠበቅ ጀመርን።

ጎበዜም እንዲህ ሲል መለሰ፦ እኔ ኢሳት ውስጥ የምሰራው በኢትዮጵያን ዘንድ ታማኝ ሚዲያ ስለሆነ ነው። ኢሳት ውስጥ ስሰራ የሚከፈለኝ ደመወዝን ሳይሆን የማስበው ኢትዮጵያን በሚከታተሉት ሚዲያ የአማራን ከኢትዮጵያ መገለል እና ሰቆቃ በተለይም ደግሞ የጽንፈኛውን ኀይል ሴራ ማጋለጥ ነው ሲል መለሰልን።

ይህን የጠየቀው ጋዜጠኛ አመሰግናለሁ የሚል ምላሽ ሰጥቶ ለሰፊ ሰዓት የያዝነውን ቀጠሮ አቋርጦት ተነስቶ ሄደ።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከኢሳትም እውነትን ስላጋለጠ ብቻ በግፍ ተባረረ። በኋላም የአማራ ድምፅ ሚዲያን በመመሥረት የግፉአን ድምፅነቱን አጠናክሮ ቀጠለ። የግፉ አስፈጻሚ እና ፈፃሚ የሆነው የፋሽስቱ ዐቢይ አህመድ አገዛዝ ለበርካታ ጊዜ ወደ አፈናና እስር ዳረገው በቅርቡ የአማራ ምልክቶችን "አሸባሪ" በማለት ወደ እስር ቤት ሲያግዝም ጎበዜ ሲሳይም አንዱ ሰለባ ሆነ።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ለሕዝብ ታማኝ የሆነ፤ ንዋይ የማይገዛው ጀግና ጋዜጠኛ ስለመሆኑ እኔ ምስክር ነኝ፤ ምክንያቴ ደግሞ ብዙ የቀረበለትን አማራጮች ስለማውቅ ነው።

ጋዜጠኝነት ምን ማለት እንደሆነ ጎበዜ ሲሳይ የእውነት ቋሚ ሀውልት ነው። ደፋር፣ አሰላሳይ፣ ትሁት እና ለሄደው ለመጣው የማያሸረግድ የእውነት እና የሀቅ አምድ ነው።

"የህይወት ተልዕኮህ ዓለምን መለወጥ ከሆነ ለዓላማህ ከግብ መድረስ አቋራጭ መንገድና የላቀው መሣሪያ ጋዜጠኝነት ነው።" ቶም ሰቶፓርድ ( እንግሊዛዊ ጸሐፊ ተውኔት)

#ጋዜጠኝነት ከባድ ኃላፊነት ነው ፥ ለተለያዩ መከራዎችና አደጋዎች የሚያጋልጥ ሙያ ስለሆነ አደገኛነቱ ከመዓድን ቆፋሪነት ተርታ ያሰልፈዋል።

#ጋዜጠኝነት

ጋዜጠኝነት ከዕለት ተዕለት የሕይወት ገጠመኝ፣ ከጠመንጃ አፈሙዝ ከሚንቦገቦግ የእሳት ላንቃ፣ ከተወሳሰበ የመንግሥትም ሆነ የድርጅት ሚስጥር አንዳች ጠቃሚ የፕሬስ ውጤትን ፈልቅቆ ለማውጣት ጥረት የሚደረግበት የሕይወት መስክ ወይም ሙያ ነው፡፡

ለጋዜጠኛነት ሥራ፣ የሙያ ብቃት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ምናልባት፣ «ጋዜጠኛው በአንሸራታች ቀለም ወይም ጭቃ በተሞላ ጎዳና በፍፁም ጥንቃቄ እንደሚጓዝ ወይም በበረዶ በተሸፈነ መሬት ላይ ባለተሽከርካሪ ጫማ እንደሚከንፈው ሰው የሚቆጠር ነው፤» በሚል ቢገለጥ ምናልባት ይቀል ይሆናል፡፡ ጋዜጠኛነት፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ክህሎት በትምህርት ቤት ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡

ነገር ግን የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ የማንበብ፣ ሌት ተቀን የማንበብ፣... የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ የመጻፍ፣ ሌት ተቀን የመጻፍ፣... የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ የማረም፣ ሌት ተቀን የማረም ውስጣዊ ፍላጎት ነው፡፡

የጋዜጠኝነት ሙያ ምግብ ሳይበላ የሚሠራበት፣ ወይም በሆነ አጋጣሚ ረዥም መንገድ በእግር የሚኬድበት፣ የጋዜጠኝነት መሣሪያዎችን ተሸክሞ የሚጓዝበት፣ ያለረዳትና አይዞህ ባይ የሚዋትቱበት በመሆኑ ጋዜጠኛ ሆኖ ለመቀጠል ፍላጐት ብቻ ሳይሆን አካላዊ ብቃት፣ አዕምሯዊ ብቃትና የባህርይ ብቃት እንዲኖረው ያስፈልገዋል፡፡

ጋዜጠኛው ለማወቅ፣ አውቆም ለማሳወቅ የተዘጋጀ ዜጋ እንደመሆኑ መጠን ሊቀ ሊቃውንቱን እንኳን ባይሆን መካከለኛዎቹን ከመካከለኞቹም የተሻሉትን መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ይህንንም ደረጃ ለመያዝ ፍላጐት ወይም ምኞች ወይም ዝንባሌ ብቻ አይበቃም፡፡ ራስን በንባብ ማነፅንና ከሌሎች በመማር ለማደራጀት ጥረት ማድረግን ይጠይቃል፡፡ በጥቅሉ ጋዜጠኝነት የተራራቀን ዓለም በሴኮንዶች ጊዜ ውስጥ የማገናኘት ሙያ ነው ልንለው እንችላለን፡፡

ጋዜጠኝነት በየብስ ላይ ሳይወሰን ዕድገቱን ከሳይንስ ጋር አጣምሮ በመጓዝ ስለህዋውና ስለባህር ውስጥ ጥበባት መረጃዎችን፣ ትምህርቶችን እየሰጠ በዚያው ልክም እያዝናና እንደሚገኝም ከዕድገት ታሪኩ እንገነዘባለን፡፡

የሩቅ አገር መልካም ወሬ በሚል ርዕስ የጻፉት ቤን ጀንስን፣ «ጋዜጠኛው በከፊልም ቢሆን የተቀደሰ ነው፣ ካለበለዚያም ጠቢቡ ሰለሞን 'ከሩቅ አገር የሚመጣ ወሬ (ዜና) ጥማትን እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውኃ ነው' እንዳለው መሆን ይኖርበታል፤» በማለት፣ የጋዜጠኛው የሙያ ብቃት ብዙ ሰዎች ከሚገምቱት በላይ ከፍተኛ ተልዕኮ ያለው መሆኑን ሲጠቅሱ፣

ሒንሪ ማርቲን የተባለው እንግሊዛዊ «የማወቅ ፍላጐቱ አነሳስቶት ያኔ ምንም ዓይነት መገናኛ ወዳልነበረውና ጫካ ወደበዛበት ምሥራቅ አፍሪካ በመጓዝ የዶክተር ዴቪድ ሊቪንግስተንን መገኘት ሥፍራው ሄዶ በማየት ባያበስር ኖሮ፣ ሚስጥሩ የጥቂት ሰዎች ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር፤» በማለት በምሳሌ ይገልጡልናል፡፡

እንደ ቤን ጆንሰን አገላለጥ አንድ ጋዜጠኛ ማንም ሰው በቀላሉ የማያገኘውንና ተቀብሮ ይቀር የነበረውን በእግሩ በመጓዝ ጭምር ፈልፍሎ የማውጣት ከፍተኛ ችሎታ ያለው ነው፡፡

በዚህም ሒደት ሕይወትን ያህል ትልቅ ቁምነገር ለደን አራዊትና አደገኛ ሕመም አሳልፎ መስጠትን የሚጠይቅ ሙያም ነው፡፡

ጋዜጠኝነት ሙያ ነው፡፡
ጋዜጠኝነት እውቀት ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ሚዛናዊነት ነው፡፡
ጋዜጠኝነት አርቆ አሳቢነት ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ኃላፊነት መሸከም ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ተሰጥኦና ፍላጎትም ነው፡፡

የዚህ ሁሉ አምሳል ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነው።

02/07/2023

#ሊጠፋ የተፈረደበት ህዝብ "ባደርገውም እሞታለሁ ባላደርግርውም አልድንም" ህይን ንግግር የተናገረችው በመጻህፍ ቅዱስ ትንቢተ ዳንኤል ላይ የምትታወቀዋ ሴት ሶስና ነች::በአንድ ወቅት ሶስና በምትኖርበት ሀገር ህዝቦችን የሚያስተዳድሩና የሚያገለግሉ ሁለት ሀሰተኛ መምህራን ነበሩ:: ታዲያ እነዚህ መምህራን በማህበረሰቡ ዘንድ ቅቡልነትና ተሰሚነት ያላቸው፥ እነርሱ ያሉት ብቻ የሚፈጸም መሪ ሆነው ግን አስመሳዮች ነበሩ::ከለዕታት አንድ ቀን እነዚህ ሰወች ይህችን እግዚአብሔርን የምትፈራና ባሏን የምታከብር ሴት ለስጋዊ ፍላጎት ለወሲብ ተመኟት:: መመኘትም ብቻ ሳይሆን ባሏ ነገዴ ስለነበር ከሀገር ወጥቷል:: እነዚህ ሀሰተኛ መምህራን የባሏን የኢዮአቄምን ከቤት መውጣት ተከትለው ፥ሶስና ከቤታቸው የአጥር ግቢ በአትክልት ቦታ ሰውነቷን ለመታጠብ ብቻዋን በነበረችበት ጊዜ እነዚህ ሁለት ሰወች ፍላጎታቸውን ለመፈጸም ከተደበቁበት ቦታ ወጥተው መጡና ከእኛ ጋር ትተኛለሽ አለበለዚያ ግን ከወንድ ጋር ተኝታ ስትማግጥ አገኘናት ብለን እንናገራለን አሏት:: በዚህ ሁኔታ ሶስና ተጨነቀች ያላት አማራጭ ሁለት ነው አንደኛው ሰወች ያሏትን መፈጸም አለበለዚያ ደግሞ መጮህና ሰውን መጥራት፥ በሀገሪቱ ህግ መሰረት አንዲት ሴት ከባሏ በላይ ወይም ትዳር ሳትፈጽም ከወንድ ጋር ብትገኝ በድንጋይ ተወግራ ትሞታለች:: ልብ በሉ! ሶስና ከነዚህ ሀሰተኛ መምህራን ጋር ግንኙነት ብትፈጽም እግዚአብሔር ይፈርድባታል እምብኝ ብላ ብትጮህ ደግሞ እነዚህ ሰወች ከሰው ጋር ስትማግጥ አገኘናት ብለው በድንጋይ አስወግረው ያስገድሏታል፥ ምክኒያቱም ደግሞ እነዚህ ሰወች በህዝቡ ዘንድ ተሰሚነት አላቸው :: ሶስና በጣም ተጨነቀች!እናንተ በሶስና ቦታ ብትሆኑ ምን ትመርጣላችሁ? ምንስ ታደርጋላችሁ? ------------------------------------ ውድ ጓደኞቸ በዚህ ጽሁፍ ላስተላልፈው የፈለኩት ሀሳብ ወይም መልእክት የአማራ ህዝብ በገዥወችና በሀሰተኛ መሪወች ከሳሽነት እየደረሰበት ያለውን የህልውና ፈተና ለመግለጽ ነው:: የአማራን ህዝብ በውሸት ትርክት ማንፌስቶ ቀርጸው ሊያጠፉት ከተነሱበት ሀሰተኛ ገዥወች እራሱን ሊያድን የሚችለው ከሁለቱ የሶስና ምርጫወች የትኛውን ቢከተል ነው? ተዋርዶና ማንነቱን አጥቶ መሞት ወይስ እውነትን በመጋፈጥ በጀግንነት መፋለምና ከዚያም ማሸነፍ? ምርጫው የመላው አማራ ህዝብ ነው:: ሶስና በመጨረሻ ከሀሰተኛ መሪወች የሀሰት ክስ ለመዳን የትኛውን መንገድ መረጠች? ይህች ሴት ከነዚህ ሀሰተኛ መምህራን ጋር ማግጣ ማንነቷን አጥታ በነብሷ ከምትሞት ክብሯንና ማንነቷን ጠብቃ በስጋዋ መሞትን ወሰነች:: ሶስና ይህን ውሳኔ ስትወስን ከሞት እድናለሁ ብላ አልነበረም ነገር ግን በስጋ ፍላጎት ተሸንፋ እራሷን ከማጣ፥ ታሪኳን ከማበላሽት፥ የዘላለም ሞትን ከምሞት፥ ለሌሎች አርአያ በመሆን ስጋዋን ገድላ ትውልድ ማዳንን መርጣለች:: ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ ሆይ! ጠላቶቻችን ባሪያ ሆነን ብንገዛላቸው እንኳን እመኑኝ ከኛን ከምድረ ገጽ ከማጥፋት ወደኋላ አይሉም:: ምርጫችን አንድና አንድ ነው! ለነጻነት በመፋለም የአባቶቻችን ታሪክ መድገም:: ታሪክንና ማንነትን አጥቶ ተዋርዶ ከመሞት እንደ ሶስና በክብር ለመሞት መወሰን ወደር የማይገኝለት ጀግንነት ነው:: የአብይ አህመድንና ግብር አበሮቹን ወንበር ለማጽናት፥ አላማና ውጤቱ ዜሮ ለሆነ ጦርነት ስንት ልጆቻችን፡ ወንድሞቻችንና የምንሳሳላቸውን ወገኖቻችን ገብረናል :: ተነስ ወገኔ ተነስ! ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ የአባቶችህን ታሪክ ድገም ፥ለማይቀረው ጦርነት እራስህን አዘጋጅ! ሊጠፋ የተፈረደበትን ባለታሪ ህዝብ ከጥፋት ልንታደገው ይገባል:: ይህን ሰይጣን አምላኪ መንግስት እናሳፍረው ሁሉም በየመክሊቱ ይንቀሳቀስ አለበለዚያ ግን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል:: ድል ለአማራ ህዝብ! ሰላም ለሀገራችን!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ህዝባዊ ግንባር በአርማጭሆ/Amhara people's Front in Armachiho posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share