Greater Ethiopia

  • Home
  • Greater Ethiopia

Greater Ethiopia A brand new Ethiopia which is progressive and forward-looking!!

13/03/2022
ጋማ!!
17/11/2021

ጋማ!!

የሸኔን ታጣቂ ኃይል ለዓመታት ሲያገለግል እና ሲመራ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
======= #=========

ለዓመታት በሽብርተኛነት የተፈረጀውን የሸኔ ታጣቂ ኃይል ሲያገለግል እና ሲመራ የነበረ እያሱ ዓለሙ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ በታጣቂ ኃይሉ ውስጥ አባል ሆኖ በቆየባቸው ዓመታት በውጪ አገራት ጭምር የተለያዩ ሥልጠናዎች መውሰዱን እና ለጥፋት ተልዕኮ ተሰማርቶ መቆየቱን ተናግሯል።

በ2007 ታጣቂ ቡድኑን እንደተቀላቀለ እና በቆየባቸው የጥፋት ዓመታት ከተራ ተዋጊ እስከ ሎጀስቲክስ ኃላፊነት እንደሠራ የገለጸው ወጣት እያሱ የጥፋት ቡድኑ በእንግሊዝ አገር የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት እንዲከታተል እና ተመልሶ የቡድኑን አባላት እንዲያሰለጥን እንዳደረገው ገልጿል።

ወጣት እያሱ በሸኔ የጥፋት ተልዕኮ በቆየባቸው ዓመታትም የጥፋት ቡድኑን ከሚደግፉ አካላት ከ15 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ ተቀብሎ ለታጣቂ ኃይሉ አመራሮች የማድረስ ተግባር እንደፈፀመ ተናግሯል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር በሽብር ሥራዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበረው ወጣት እያሱ መንግሥት ለታጣቂ ኃይሉ ይቅርታ ባደረገበት ወቅት የዕድሉ ተጠቃሚ ሆኖ በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ሥልጠና እንደወሰደ እና ሥልጠናውን እጠናቆ እንደወጣም በታጣቂ ኃይሎች አስገዳጅነት እንደገና የሸኔ አባል እንደሆነ አስረድቷል።

ግልሰቡ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ለሽብር ተግባር የሚውል ገንዘብ ከባንክ ለማውጣት በኅብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው የተገለጸው።

በሽብርተኛነት በተፈረጀው በሸኔ ቡድን የሚነገርው የሐሰት ውዥንብር እና መሬት ላይ ያለው እውነት እንደማይገናኝ ወጣት እያሱ መናገሩን በመከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ ገልጿል።

የደቡብ ዕዝ በቀጣናው በሚያከናውናቸው የሰላም ጥበቃ ሥራዎች ወጣት እያሱን ጨምሮ 4 የሸኔ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።

Via addis maleda

27/10/2021
06/02/2021
06/02/2021
16/11/2020

ድርድር እየተካሄደ አይደለም።

05/12/2011

QUIT IT now!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Greater Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share