Addisu Ashenafi law office

  • Home
  • Addisu Ashenafi law office

Addisu  Ashenafi law office legal counselor and attorney at any court

06/08/2021

ይዞታ /Possession/
ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይዞታ ማለት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አሻሚ ወይም ድብቅ ባልሆነ ሁኔታ በቁጥጥር ስር በማድረግ ልታዝበት የምትችል ነው፡፡ መቆጣጠር እና ማዘዝ መቻል ብቻ ሳይሆን በንብረቱም መገልገል እና መጠቀምን ይጨምራል፡፡ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140
ይዞታ በአንድ ሰው በአንድ ንብረት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት የሚገልጽ እንጂ የንብረት ባለ ሃብትነት መብት ማለት አይደለም፡፡ ከባለ ሃብትነት መብት የጠበበ ነው፡፡
ይዞታ ለመኖሩ የሚያረጋግጡ መመዘኛዎች
1. አንድ ዕቃ መኖር አለበት ብቻ ሳይሆን በይዞታው ስር የማድረግ ሃሳብ /Animus) መኖር አለበት፡፡ ለመጠቀም እና ለመገልገል በሚል ሃሳብ የተያዘ መሆን አለበት፡፡ ይህም ሲባል ይዞታውን በቁጥጥር ስር ከማድረግ በተጨማሪ ማለት ነው፡፡
2. ተዘዋዋሪ ይዞታ በሚመለከት ደግሞ ዕቃው በሌላ ሰው እጅ የተያዘ ሆኖ ንብረቱን የመቆጣጠር እና የመጠቀም ሃሳብ ግን ከባለ ይዞታው ጋር ሊቀር ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሲታይ ግን ዕቃው ወደ ሄደበት ይከተላል፡፡
ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሁለት ንድፈ - ሃሳባዊ እነርሱም subjective & Objective ናቸው፡፡
1. ይዞታ የሚገኝበት ሁኔታ፡- በመቆጣጠር፣ ይዞታውን በመጠቀም የመገልገል ሃሳብ ሲኖር በመርሕ ደረጃ ሁለቱም ተሟልተው መገኘት አለበት፡፡
2. ይዞታ ቀሪ የሚሆንበት ሁኔታ፡- ሲጠፋ፣ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ፣ ባለ ይዞታው አያስፈልገኝም ብሎ የተወ እንደሆነ፣ በስጦታ ያስተላለፈ እንደሆነ ቀሪ ይሆናል፡፡

07/04/2020
08/11/2019

The fundamental test of juctice sys is its effectiveness in bringing offenders 2 justice .This means that Z Prosecution process is wellmanaged; the accused is given afair trial ;z guilt are convicted and z innocent are acquitted ;z needs of victims are met and all sections of z community are treated fairly

26/09/2019

የሕግና የሕገ-መንግስት ግንዛቤ አንድ (1)
የኢፊዲሪ ሕገ መንግስት ለየግለሰብ እና ለንብረት መብቶች የሚያደርገው ጥበቃ
1. የአካል ደህንነት መብት
ለመጀመር የኢፊዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 14 ስር እንደደነገገው አንድ ሰው የአካል ድህንነት /The security of person/ አለው ስለሆነም በአንቀፅ 16 መሠረት ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡ በተጨማሪም አንቀፅ 18 /1/ ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ጭካኔ በተሞላበት ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡
ይህ መብት ሰዎች የትም ቦታና ጊዜ የተከበረላቸው መብት ነው፡፡ በጥበቃ ስር ወይም በፍርድ የታሰሩ እንኳን ቢሆን በሰብዓዊ ክብር የመያዝ መብት አላቸው፡፡ ይህንኑ አንቀፅ 21 በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው ተደንግጓል፡፡
ይህ መብታቸው ሲጣስም ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት እንዳላቸው አንቀፅ 37 /1/ ስር ተደንግጓል፡፡
2. ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት
ኢትዮጵያውያን ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የውጪ ዜጎች በመረጡት የሀገሪቱ አካባቢዎች የመዘዋወር እንዳላቸው አንቀፅ 32 /1/ ደንግጓል፡፡ ይህ መብት በመረጡት የአገሪቱ አካባቢ የመኖሪያ ቦታ የመመስረት፣ በፈለጉት ጊዜ ከሀገር የመውጣትና የመመለስ መብትን እንደሚጠቀልል ይሄው አንቀፅ ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም ይህ መብት ሕገ መንግስታዊ መብት ነው ማለት ነው፡፡
እነዚህ መብቶች ሊጣሱባቸው ከሚችሉባቸው መንገዶች አንዱ በመያዝና በመታሰር ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 17 /2/ ስር ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጭ ሊያዝ ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይገባ ደንግጓል፡፡ ስለሆነም ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን ማጣት የሚቻለው ሕግ በደነገገው መሠረት አንድ ሰው ሲያዝ ወይም ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተፈርዶበት ሲታሰር ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሰዎች የመዘዋወር መብታቸው ቢጣስ በአንቀፅ 37/1/ መሠረት ጉያቸውን ራሳቸው ወይም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ፍርድ ቤት አቅርበው ወይም አስቀርበው የአካል ነፃነት የማግኘት መብት አላቸው፡፡
3. የክብርና የመልካም ስም መብት
ከላይ በጥቂቱ ለማስቀመጥ እንደሞከርነው ሰዎች ሰውነታቸውን አስመልክቶ ያላቸውን ሕገ መንግስታዊ መብት ተመልክተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች ከሰብዓዊ ክብራቸውና ከመልካም ስማቸው ጋር የተያያዙ መብቶች አላቸው፡፡ በመሆኑም አንቀፅ 24 /1/ ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩንና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡
ይህም በመሆኑ ምንም እንኳን አንቀፅ 29 ስር እንደተደነገገው የአመለካከት እና ሃሳብን በነፃ መያዝና የመግለፅ መብት እውቅና ያገኘና ጥበቃም የሚደረግለት ሕገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም እነዚህ መብቶች የሰውን ክብርና መልካም ስም ለማጥፋት መጠቀሚያ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በመሆኑም የሰውን ክብርና መልካም ስም ለመጠበቅ ሲባል አንቀጽ 29 ስር በተዘረዘሩት መብቶች ላይ ሕጋዊ ገደቦች ሊጣሉ እንደሚችሉ አንቀጽ 29 /6/ ደንግጓል፡፡ እነዚህ ገደቦች ደግሞ መጣስ ክልክል ነው፡፡ ስለሆነም አንቀፅ 29 /7/ ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ዜጋ ከላይ በተጠቀሱት መብቶች አጠቃቀም ረገድ የሚጣሉ ሕጋዊ ገደቦችን ጥሶ ከተገኘ በሕግ ተጠያቂ ሊሆን ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት የሰውን ክብርና መልካም ስምን ለማጥፋት ሊውሉ አይችሉም፡፡
4. የግል ሕይወት የማክበርና የመጠበቅ መብት
የግል ሕይወት /The right to privacy/ የሚለው ነው አንድ ሰው በመኖሪያ ቤቱ በሰውነቱ እና በንብረቱ ላይ ያለውን መብት ያጠቃልላል፡፡ ይህ መብት በግል የሚሰሩዋቸውን የሚፃፃፋቸውን፣ በፖስታ የሚልኳቸውን ደብዳቤዎች እንዲሁም በቴሌፎን ቤቴሌኮሙኒኬሽንና በኤሌክትሮኒክስ መሣሪዎች የሚያደርጋቸውን የግንኙነት መብቶችን ይጨምራል፡፡
እነዚህን መብቶች የመንግስት ባለሥልጣኖች የማክበርና የማስከበር ግዴታ እንዳለባቸው አንቀፅ 26 /3/ ስር ተደንግጓል፡፡ ስለሆነም ሊገደቡባቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች በዚሁ ንዑስ አንቀፅ ስር ተብራርተዋል፡፡ በመሆኑም አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩና ብሔራዊ ደህንነትን የሕዝቡን የሞራል ሁኔታ በመጠበቅ ወይም የሌሎችን መብትና ነፃነት በማስከበር ዓላማዎች ላይ በተመሰረቱ ዝርዝር ሕጎች መሠረት ካልሆነ በስተቀር የእነዚህ መብቶች አጠቃቀም ሊገደብ እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ እነዚህ መብቶች ሰው መኖሪያ ቤቱ ሰውነቱ እና ንብረቱ ሊፈተሹ ወይም ሊመረመሩ የሚችሉት ሕግ በሚለው መሰረት ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም በግል ይዞታው ስር ያለ ንብረትም ሊያዝ የሚችለው በሕግ አግባብ ብቻ ነው፡፡
5. የሴቶችና የሕፃናት መብት
ሁሉንም የሴቶችና የሕፃናት መብቶች እዚህ አንወያይም፡፡ ለዚህ ትምህርት የሚጠቅሙንን ብቻ ነው የምናየው፡፡ በተለይም የተከለከሉትን፡፡ ስለሆነም አንቀፅ 35 /4/ ስር እንደተደነገገው ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ላይ በአእምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጎችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶች ሰውነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ልማድ በመሆኑ የተከለከለ ተግባር ነው /35/ በተመሳሳይ ሁኔታ ሕፃናትን አስመልክቶ በትምህርት ቤቶች ወይም በሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በሕፃናት ላይ በአካላቸው ላይ ጭካኔና ኢሰብአዊ የሆነ ቅጣት መፈፀም ክልክል ነው (36/1/)፡፡ እንዲያውም ወላጆችና ሕጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሠረት የነፃ ማንነታቸውን የመልካም ሥነ ምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አንቀፅ 27 /4/ ደንግጓል፡፡
6. የግል ንብረት መብት
ንብረት በሁለት ይከፈላል፡፡ አንዱ በግል የመያዝ ባህሪያ ያለው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በመንግስትና በሕዝብ ንብረትነት የመያዝ ባህሪይ ያለው ንብረት ነው፡፡ አንቀፅ 40 /3/ እንደደነገገው የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም መሬት በግል ሀብትነት የማይያዝ የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው፡፡
ከዚህ ውጪ ያሉት የግል ሀብት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ይከበርላታል ስለሆነም ይህ መብት ሕገ መንግስታዊ መብት ነው ማለት ነው፡፡
መሬት የሕዝብና የሕዝብ የጋራ ንብረት ሲሆን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በነፃ መሬት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን አንቀፅ 40 /4/ እና /5/ ደንግጓል፡፡ በተጨማሪም የግል ባለሀብቶች በሕግ የተወሰነውን ክፍያ ከፍለው በሊዝ የመጠቀም መብት ሕገ መንግስቱ አጎናፅፏቸዋል፡፡ ስለሆነም የይዞታ መብት በዛ መሬት ላይ አላቸው ማለት ነው፡፡ በዚህ ይዞታ ባለ ሀብቱ በገንዘቡ ወይም በጉልበቱ ቋሚ ንብረት ሊገነባ ወይም ሊያሻሽል ሙሉ መብት አለው፡፡ ስለሆነም ይህ መብት ሕገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ለዚህ መብት ደግሞ ሕገ መንግስቱ ጥበቃ አድርጎለታል፡፡ ስለሆነም አንቀፅ 26 /1/ ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ንብረቱ ከመመርመር እንዲሁም በግል ይዞታው ያለ ንብረት ከመያዝ የመጠበቅ መብት አለው፡፡
አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችም ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብት እንዳላቸው አንቀፅ 40 /4/ እና /5/ ደንግጓል፡፡ ስለሆነም አርሶ አደሮችም አርብቶ አደሮችም እንዲሁም የግል ባለሀብቶችም የግል ንብረት ባለቤነትም ሆነ የመሬት ባለይዞታነት መብታቸው በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠ ስለሆነ ይህን መብት በሕግና በራሳቸው የማስከበር መብት ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡
በሌላ ሃሳብና ግንዛቤ እስክንገናኝ ድረስ መልካም ጊዜ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addisu Ashenafi law office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share