EthioMereja.net

  • Home
  • EthioMereja.net

EthioMereja.net Welcome to EthioMereja.net
join on telegram t.me/ethio_mereja

 #የሰላም ንግግር🕊በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።ለጉዳዩ ቅርበት ያ...
08/11/2023

#የሰላም ንግግር🕊

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ መሆኑን ያስረዳል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር የተካሄደውን ድርድር የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ)፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና ኬንያ አስተባባሪ እና አሸማጋይ ሚና መውሰዳቸው ይታወሳል።

አሁን የተጀመረውን ንግግር ማን እንደሚያደራድር ግልጽ ባይሆንም፣ ኢጋድ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሚና ሳያስቀጥል እንዳልቀረ በቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘገባ ተጠቅሷል።ከዚህ በተጨማሪ " አዲስ ስታንዳርድ " ድረገፅ ሁለት የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በሰላም ውይይቱ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መሪ ኩምሳ ደሪባ / ጃል ማሮ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

#ጃል ማሮ በሦስተኛ ወገን አደራዳሪዎች አመቻችነት በምዕራብ ኦሮምያ ከሚገኝ ጫካ ወደ አቅራቢያው ወደሚገኘው የደንቢዶሎ አውሮፕለን ማረፊያ እንዲበር ከተደረገ ለኃላ ወደ ድርድሩ ቦታ በተዘጋጀለት ሂሊኮፕተር መጓዙን ተነግሯል።

በዚህም ጃል ማሮ ለመጀመሪያ ግዜ ከፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለውይይት መቀመጡ ተገልጿል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት ሳምንታት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም ሁለት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት ውጤታማ የተባለ የፖለቲካ ውይይቱ ተካሂዷል።ውይይቱ ውጤታማ ስለነበር እና በዚህም ምክንያት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት ትላንት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም በታንዛኒያ ዳሬሰላም መጀመሩን ተነግሯል።

ከሁለቱም ወገን ከሳምንታት በፊት በተካሄደው በቀደመው የፖለቲካ ውይይት ተካፋይ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች ድርድሩ በስኬት ከተከናወነ ለፊርማ ሥነ ስርአቱ ተካፋይ እንደሚሆኑ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል።

ውይይቱን በማመቻቸት ረገድ ኢጋድ ትልቁን ሚና መጫወቱን ፤ የኢጋዱ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዋና አወያይ መሆናቸውን " አዲስ ስታንዳረድ " ድረገፅ ስማቸው ይፋ እንዳይሆን የፈለጉ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባው ላይ ሰፍሯል።

እስካሁን ስለንግግሩ ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተባለ ነገር የለም

Today's Best photo
❤❤❤














-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja

ኡጋንዳ ግብረሰዶማዊ ነው ያለችውን ወጣት በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ተነገረ።የ20 አመቱ ወጣት በተከሰሰበት የግብረሰዶም መፈጸም ወንጀል ከሁለት ሳምንት በፊት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተነግሯል።በሀ...
31/08/2023

ኡጋንዳ ግብረሰዶማዊ ነው ያለችውን ወጣት በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ተነገረ።

የ20 አመቱ ወጣት በተከሰሰበት የግብረሰዶም መፈጸም ወንጀል ከሁለት ሳምንት በፊት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተነግሯል።በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ሶሮቲ በተባለች ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት የቀረበው ተከሳሽ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን እስኪመለከት እየጠባበቀ ነው ተብሏል።

ኡጋንዳ ከፈረንጆቹ 2005 ወዲህ የሞት ቅጣትን ተፈጻሚ አላደረገችም፤ ይሁን እንጂ የሞት ቅጣት ውሳኔ ማሳለፍን አልከለከለችም።ካምፓላ በግንቦት ወር ያወጣቸውና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚከለክለው ጠበቅ ያለ የጸረ ግብረሰዶም ህግ የሞት ቅጣትን የሚያስከትሉ ወንጀሎችን ዘርዝሯል።

አዲሱ ህግ በማንኛውም የግብረሰዶማዊነት ተግባር የተሳተፈ አካል በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ያዛል።ወንጀሉ የተፈጭጸመው በህጻናት እና በአቅመ ደካሞች ላይ ከሆነ ደግሞ በሞት እንደሚያስቀጣ ነው የሚያስቀምጠው።በዚህም ምክንያት የአለም ባንክ በቅርቡ ለኡጋንዳ ብድር መከልከሉ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒም “የዓለም ባንክ ባህላችንን እና ሀይማኖታችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው" በማለት የባንኩን ውሳኔ መቃወማቸው አይዘነጋም።

--ETHIO-MEREJA--

ለተጨማሪ መረጃ👇👇
T.me/ethio_mereja

"...መከላከያ ሰራዊት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ወደ ካምፕ ይመለስ” - አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የቀድሞው የአማራ ክልል ር/መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው የም/ቤት ውሎ ምን አሉ?የአስቸ...
14/08/2023

"...መከላከያ ሰራዊት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ወደ ካምፕ ይመለስ” - አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የቀድሞው የአማራ ክልል ር/መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው የም/ቤት ውሎ ምን አሉ?

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከስሕተት ያለመማር ውጤት እንደኾነ ገዱ አንዳርጋቸው ተናግረዋል።

በዐማራ ክልል፣ እስከ 6ወር ተፈጻሚ እንዲኾን በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀውና ዛሬ ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ “ካለፉት 5 ዓመታት ስሕተቶቻችን ያለመማራችን ውጤት ነው፤” ሲሉ ነው አቶ ገዱ ተቃውሟቸውን የገለጹት፡፡

በአሁኑ ወቅት፣ በዐማራ ክልል የተስፋፋው ችግር መሠረታዊ ምክንያት፣ የብልጽግና መንግሥት የፖለቲካ አመራር ክፍተት ነው፤ ያሉት አንዱ የፓርቲው መሥራች አቶ ገዱ፣ ራሱ የሚፈጥራቸውን ፖለቲካዊ ችግሮች፣ በወታደራዊ ኀይል መፍታት የመንግሥት ባሕርይ ኾኗል፤ ሲሉ ተችተዋል፡፡

“ይህን ችግር በቅንነት ለመፍታት ከተፈለገ መፍትሔው፤ እስካሁን በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሞከር ከርሞ ሀገርን ወደ ከፋ ጥፋት ያመራው ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውይይት ነው የሚል እምነት አለኝ” ብለዋል አቶ ገዱ።

“የችግሩ መጀመሪያም መጨረሻ ፖለቲካዊ ነው” ያሉት አቶ ገዱ፤ “በአማራ ክልል ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከተፈለገ እኔ የሚታየኝ፤ 1ደኛ መከላከያ ሰራዊት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ወደ ካምፕ ይመለስ” ሲሉ መፍትሔ ይሆናል ያሉትን ምክረሃሳብ አቅርበዋል። ይህ ምክረሃሳብ ከሌሎች የፓርላማ አባላት ጉርምርምታ አስከትሏል።

አቶ ገዱ፤ ሲቀጥሉ “የአማራ ህዝብና የብልጽግና ፓርቲ ግንኙነት በማይጠገንበት ደረጀ ስለተበጠሰ፤ በአስቸኳይ ሁሉንም የአማራ ኃይሎች ያቀፈ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም ችግሩን ማቃለል ይችላል የሚል እምነት አለኝ” ሲሉ ተናግረዋል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በዲዛይናቸው በጣም ማራኪ እና በጣም ተወዳጅ እንዲሁም ለስጦታ ገራሚ እና ከየት አገኘኸው የሚያስብሉ ሰአቶችን ከኛ በቅናሽ ዋጋ ያገኛሉ!አሁኑኑ ሊንኩን👇 በመጫን "Join" ይበሉ!https://...
12/08/2023

በዲዛይናቸው በጣም ማራኪ እና በጣም ተወዳጅ እንዲሁም ለስጦታ ገራሚ እና ከየት አገኘኸው የሚያስብሉ ሰአቶችን ከኛ በቅናሽ ዋጋ ያገኛሉ!

አሁኑኑ ሊንኩን👇 በመጫን "Join" ይበሉ!
https://t.me/EthioBrandWatches
https://t.me/EthioBrandWatches

የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ☝️ ይቀላቀሉ

 #ጤናመረጃነጩ ሐኪም - ነጭ ሽንኩርትባለ ነጭ ልብሱ ነጭ ሽንኩርት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት!*የኮልስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ግፊትን ይከላከላል፡፡*ጉንፋንንና ሌሎች መሰል የላይኛው ...
12/08/2023

#ጤናመረጃ

ነጩ ሐኪም - ነጭ ሽንኩርት

ባለ ነጭ ልብሱ ነጭ ሽንኩርት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት!

*የኮልስትሮል መጠንን በመቀነስ የደም ግፊትን ይከላከላል፡፡
*ጉንፋንንና ሌሎች መሰል የላይኛው የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ይከላከላል፣ ይፈውሳልም፡፡
*በልጆች ላይ የሚከሰተውን የማያቋርጥ ሳል ለመከላከል ይረዳል፡፡

*ቲቢን ለማከም ይረዳል፡፡
*መግል የቀላቀለ ቁስልን ለማከም ይረዳል፡፡
*የአባላዘር በሽታን ለማከም ይረዳል፡፡
*ሜታቦሊዝምን ያነቃቃል፡፡

*ከካንሰር ዓይነቶች፣ የኮለን ካንሰር መስፋፋትን ይቀንሳል።
*የሐሞት ከረጢት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
*የፊንጢጣ ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
*የጡት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
*በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡

*የእርጅናን ሂደትን በተወሰነ መልኩ ለመግታት ይረዳል፡፡
*የአንጀት ውስጥ ትላትልና ተህዋስያንን ይገላል።
*የምግብ ፍላጎትንና መፈጨትን ይጨምራል፡፡
*በብዛት በእድሜ ሳቢያ የሚመጣው ካታራክት የአይን እይታ ችግርን ለማከም ይረዳል፡፡

*የደም መርጋትን ለማሟሟት ይረዳል፡፡
*ለስኳር በሽታ ህክምና ይረዳል፡፡
*የጥርስ ህመም ስሜትን ይቀንሳል፡፡
*የእንቅልፍ እጦት ችግር ላለባቸው ይመከራል፡፡
*የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ይገነባል፡፡
*የይስት ኢንፌክሽንን ለማከም ይረዳል፡፡
*የመገጣጠሚያ አካላት በሽታን ለማከም ይረዳል

*ኪንታሮትን ለማከም ይረዳል፡፡
*አንዳንድ የቆዳ በሽታዎችን እና ብጉንጅና መሰል እብጠቶችን ለማከም ይረዳል፡፡
*ፋይቶንሳይድስ የተሰኘ ኬሚካል ያላቸው የነጭ ሽንኩርት ዓይነቶች የአስም በሽታን ለማከም ይረዳሉ፡፡
*አደገኛ የብሮንካይተስ ህመምን ለማከም ይረዳል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja (Join)

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ! ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን ሀምሌ 9...
09/08/2023

በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን ሀምሌ 9 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ 8ሰአት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ጎሮ 32 መንገድ ከሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ነበር አስገራሚ የሆነውን ተግባር የፈፀመው።

ተከሳሹ የግል ተበዳዮችን በር ሰብሮ ከገባ በኋላ ጤረጵዛ ላይ ታብሌት ስልክ ተቀምጦ ይመለከታል እሱን ይዞ ለመውጣት ያስብና ቀና ሲል ውስኪ ብፌ ውስጥ ያያል ልቡ ሸፈተ ቆይ በዚህ ውስኪ ለምን ትንሽ ዘና አልልም ይልና ብርጭቆ አቅርቦ ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ ተቀምጦ ልክ እንደራሱ ቤት እየተዝናና እያለ ነበር ከተወሰነ ሰአት በኋላ የግል ተበዳዮች መምጣታቸውን ይሰማና ጠረጴዛ ላይ የነበረውንና የዋጋ ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ ታብሌት ስልክ ብድግ አድርጎ በድንጋጤ ሽንት ቤት ይደበቃል፣ የግል ተበዳዮችም ወደ ቤታቸው ሲገቡ ውስኪውን እና ብርጭቆ ጤረጴዛ ላይ ይመለከታሉ ታዲያ በዚህ ሰአት ማነው እዚህ ቤት የገባው ብለው በድንጋጤ ቤታቸውን ሲፈትሹ ተከሳሹን ግለሰብ ከነሰረቀው ንብረት ሽንትቤት ውስጥ እጅከፍንጅ በመያዝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይደውላሉ።

በዚህም መሰረት ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ ወደ ጣቢያ ይወሰዳል ለፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀልም በአቃቤ ህግ ክስ ይመሰረትበታል።

በፖሊስ ተጣርቶ በአቃቤ ህግ የተመሰረተበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እንዳሻው ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በሶስት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ዘገባው የድሬዳዋ ፖሊስ ነው።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 #ጤናመረጃቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር...
09/08/2023

#ጤናመረጃ

ቲማቲም ለፊት ጥራት ያለው አስደናቂ ጥቅም!!

ቲማቲም ለቆዳችን እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡ ቲማቲም ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታካሮቲን፣ ላይኮፔን እና ፍላቮኖይድስን አለው፤ ይህን ንጥረ ነገር ደግሞ ለፊት ጥራት ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ መዋቢያዎች ይጠቀሙበታል፡፡

በቀላሉ የምናገኘው ቲማቲምን በመጠቀም ቡጉርን፣ የቆዳ ጥቁረትንና ጥቁር ነጠብጣቦችን ከፊታችን ላይ ለማጥፋት ይረዳናል፣ በተጨማሪም ቲማቲም የቆዳን እርጅና እና መሸብሸብ ፍጥነትን የመቀነስ ችሎታ አለው፡፡

ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገሮች -

- 1 ቲማቲም
- 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
- 2 የሻይ ማንኪያ ማር
- 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ >>

አዘገጃጀት

1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን፡፡

2) ቲማቲሙን ይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡

4) ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል፡፡
6) ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡

7) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል፡፡ ማስጠንቀቂያ:- ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡ .....
በተጨማሪም ቲማቲም ለቆዳ ጤንነት ያለውን ጥቅም በቀላሉ ሞክሮ ማየት ካስፈለገ የሚከተለውን ማድረግ ይቻላል።

👉ከ8 እስከ 12 የሚሆኑ ቲማቲሞችን ልጦ የልጣጩን የውስጠኛ ክፍል ፊት ላይ መለጠፍ፡፡ ቢያንስ ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ልጣጮቹን አንስቶ ፊትን መታጠብ፡፡ ከዛም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ለውጡን ማስተዋል እንችላለን።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

🛑ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች “አንዳንድ የዞንና የወረዳ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን” እንዲሁም በተወሰኑ ቦታዎች “ወንጀለኞችን ከማረሚያ ቤት ማስለቀቃቸውን” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መ...
06/08/2023

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች “አንዳንድ የዞንና የወረዳ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን” እንዲሁም በተወሰኑ ቦታዎች “ወንጀለኞችን ከማረሚያ ቤት ማስለቀቃቸውን” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መመሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።

አቶ ተመስገን “ዘራፊ” ሲሉ የጠሯቸው እነዚሁ ኃይሎች፤ “የክልሉን መንግስት በማፍረስ ወደ ፌደራል ስርዓት የመሄድ” ፍላጎትና ግብ ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ይህን የተናገሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠ/መመሪያ ዕዝ ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ዛሬ ሐምሌ 30 ከተደረገ ስብሰባ በኋላ በሰጡት ማብራሪያ ነው። የዕዙ ሰብሳቢ በዚሁ ማብራሪያቸው በ“ጎጃም ቀጠና” ላይ በታዩ “የጸጥታ መደፍረስ እንቅስቃሴዎች”፤ “የመንቀሳቀስ መብት የሚገድቡ ሁኔታዎች ተስተውለዋል” ብለዋል።

በማብራሪያቸውም በአማራ ክልል የተቋቋመው ኮማንድ ፓስት የአማራ ክልልን በ4 ኮማንድ ፓስቶች ስር መከፈሉን

1ኛው የምዕራብ አማራ ኮማንድ ፓስት ሲሆን፤ ምስራቅ ጎጃምን፣ ምእራብ ጎጃምን፣ ደብረማርቆስ ከተማንና የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንን እንዲሁም የባህርዳር ከተማ አስተዳደርን የሚይዝ ነው።

2ኛው ኮማንድ ፓስት የሠሜን ምዕረብ አማራ ኮማንድ ፓስት ሲሆን ይሄ ደግሞ፤ ሰሜን ምዕራብ ማዕከላዊ ጎንደር ከተማን ደቡብ ጎንደርን ደብረታቦር ከተማን የያዘ ነው።

3ተኛው የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፓስት ሲሆን፤ ደብረብርሃን ከተማን ሰሜን ሸዋንና የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞንን ያካለለ መሆኑን አቶ ተመስገን አስታውቀዋል።

የምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፓስት 4ኛው ኮማንድ ፓስት ሲሆን፤ የደቡብ ወሎን የደሴ ከተማን ኮምቦልቻን የሰሜን ወሎን ወልዲያ ከተማንና የዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞንን ያካለለ መሆኑን ገልጸዋል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

ወደ መደበኛ ኃይል አልገባም ብሎ የአመፅ መንገድን የመረጠውን የፋኖ ኃይል "በመረጠው መንገድ መስመር አስይዘነዋል"- ጄኔራል አበባው ታደሰየጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ...
21/07/2023

ወደ መደበኛ ኃይል አልገባም ብሎ የአመፅ መንገድን የመረጠውን የፋኖ ኃይል "በመረጠው መንገድ መስመር አስይዘነዋል"- ጄኔራል አበባው ታደሰ

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ መከታ ከተባለ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከፋኖ ጋር ያለውን ግጭት በተመለከተ ተናግረዋል።

በዚህም "ፖሊስ የሚሆን ፖሊስ፤ መከላከያ የሚሆን መከላከያ ይግባ ብለን ክፍት አድርገንለታል" በማለት ተናግረዋል።የሀገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት ጄኔራሉ፤ የመንግስትን ፕሮግራም አልቀበልም ያሉና የኃይል አማራጭ የተከተሉትን የፋኖ ኃይሎች በሁለት መንገድ አስተናግደናል ብለዋል።ፕሮግራሙን ለማስረዳትና ለማወያየት ከፍተኛ ጥረት አድርገናል ያሉ ሲሆን፤ "አብዛኛው ሊባል የሚችለው ወደ ተፈለገው መስመር ገብቷል" በማለት ተናግረዋል።

"አሻፈረኝ ብሎ የአመጽ መንገድን የመረጠውን ግን ህጋዊው አሰራር የግድ ተግባራዊ መደረግ ስለነበረበት በመረጠው መንገድ ሄደን መስመር አስይዘነዋል" ብለዋል።አጠቃላይ ሲታይ መንግስት እቅዱን እንዳሳካ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ተናግረዋል።

ጄኔራል አበባው ታደሰ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘም አሁን ላይ “ምንም በልዩ ሃይል የሚታዘዝ አደረጃጀትና የኮማንድ ስርዓት ያለው አሁን የለም፤ እንደ ሃይል ወይ መከላከያ ሆኗል ወደ መደበኛ ፖሊስ ሆኗል ወይም ደግሞ ፌዴራል ፖሊስ ሆኗል። ይሄ በተሳካ መንገድ ነው የተፈፀመው” ብለዋል።

የትግራይ ኃይልን በተመለከተ ከትግራይ ጋር ተያይዞ ያለውም እንደ ማንኛውም ክልል እሱም የሚኖረው መደበኛ ፖሊስ እና ሚሊሻ ብቻ ፤ በተቀመጠለት ስታንዳርድ ብቻ ነው የሚሄደው ሲሉም ምክትል እታማዦር ሹሙ ተግናረዋል።(አልአይን)

--ETHIO-MEREJA--

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል!    Congratulations 🎉🎊🪅ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦- ጅማ ዩኒቨርሲቲ- ወለጋ...
20/07/2023

በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል!

Congratulations 🎉🎊🪅

ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦

- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ)
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
- ዲላ ዩኒቨርሲቲ
- እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
- ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ)
- መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
- ቀብሪ ድሃር ዩኒቨርሲቲ
- ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ
- ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
- ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

በተያያዘ ዜና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር)÷አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሀገሯን ሙዚቃና እና ባህል እንዲሁም የተወለደችበትን የአገው ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለዓለም ህዝብ በማስተዋወቋ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ሲሰጣት ታላቅ ክብር ይሰማዋል ብለዋል፡፡

የ2015 ተመራቂዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
Congratulations 🎉🎊🪅

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ኮድ 3 ኦሮ 74276 5L መኪና ቅዳሜ 8/11/2015  ከለሊቱ 10፡00 ሰአት ላይ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ ተስርቋል በመሆኑም በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን መኪና...
20/07/2023

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ኮድ 3 ኦሮ 74276 5L መኪና ቅዳሜ 8/11/2015 ከለሊቱ 10፡00 ሰአት ላይ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ ተስርቋል በመሆኑም በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን መኪና ያለበትን ያየ ወይም ያወቀ ከታች ባላው ስልክ ቁጥር ያሳውቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።(ሼር)

👉 0777193684
👉 0923284733

🛑ኢትዮ-መረጃን በቴሌግራም ይቀላቀሉ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 የመውጫ ፈተና ላላለፉ ተማሪዎች ዲግሪ የሚሰጡ የትምህርት ተቋማት በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች  #ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በ...
20/07/2023



የመውጫ ፈተና ላላለፉ ተማሪዎች ዲግሪ የሚሰጡ የትምህርት ተቋማት በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር

የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች #ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች እየተመዘገቡ ፈተና ይወስዳሉ!

ዘንድሮ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና፤ 62 በመቶ የመንግሥት እና 17 በመቶ የግል ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ዲግሪ ለማግኘት መስፈርት የሆነውን የመውጫ ፈተና #ላላለፉ ተማሪዎች ዲግሪ ሲሰጡ ከተገኙ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ዲግሪውን ይዘው ከተገኙም እንደ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይቆጠራል ብለዋል፡፡ የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች #ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች እየተመዘገቡ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የማስፈጸሚያ መመርያ ወጥቶለት ለተካሄደው የመውጫ ፈተና ከተቀመጡ ከ150 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከል 61 ሺህ ተማሪዎች 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 #ጤናመረጃበጠዋት ዉሃ የመጠጣት 8 የጤና በረከቶች!በጠዋት ከእንቅልፍ እንደተነሱ በባዶ ሆድ ውሃ የመጠጣት 8 ጥቅሞች :-1) የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል እንዲሁም አንጀትዎን እና ፊ...
20/07/2023

#ጤናመረጃ

በጠዋት ዉሃ የመጠጣት 8 የጤና በረከቶች!

በጠዋት ከእንቅልፍ እንደተነሱ በባዶ ሆድ ውሃ የመጠጣት 8 ጥቅሞች :-

1) የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል እንዲሁም አንጀትዎን እና ፊኛዎን ከተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ ይረዳል።

2) አንጀትን ያጸዳል፣ ንጥረ ምግቦችን በቀላሉ ለመምጠጥ ያስችላል።

3) የእርስዎን የንቃተ ህሊና፣ የማስታወስ እና የአዕምሮ ብቃትን ይጨምራል።

4) የአዲስ የጡንቻ ሴሎችን እና የደም ሴሎችን መመረት ይጨምራል፣

5) የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።

6) የሚያበራ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፤ ውሃ ከደም ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማጽዳት ይረዳል፣ ይህም ቆዳዎ ብሩህ እና ንጹህ እንዲሆን ይረዳል።

7) ጤናማ አንፀባራቂ ፀጉር እንዲያድግ ያበረታታል ።

8) የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያጠናክራል እና የሊምፍዎን(lymph) ሚዛን ያስተካክላል፣ እነዚህ እጢዎች የእለት ተእለት ተግባራትን እንዲያከናውኑ፣ የሰውነትዎን ፈሳሽ ማመጣጠን እና ኢንፌክሽንን ለመከላከል እና ለመዋጋት ይረዳሉ።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያጋሩ! ሼር!

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 #ሬሜዲያልትምህርት ሚንስቴር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተላከ ደብዳቤ የሬሜዲያል ውጤት አያያዝን በተመለከተ አቅጣጫ አስቀምጧል!!ደብዳቤው በሐምሌ 11 /2015 ዓ/ም በትምህርት ሚኒ...
19/07/2023

#ሬሜዲያል

ትምህርት ሚንስቴር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተላከ ደብዳቤ የሬሜዲያል ውጤት አያያዝን በተመለከተ አቅጣጫ አስቀምጧል!!

ደብዳቤው በሐምሌ 11 /2015 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ነው።

በዚህም ደብዳቤ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ኘሮግራም ማጠቃለያ ላይ በተከታታይ ምዘና በየተቋማቸው የተደረገው ምዘና 30% ፤ ከማዕከል የተዘጋቸው የማጠቃለያ ፈተና ከ70% እንዲያዝ ከዚህ በፊት የተላከው ሴርኩላር እንደተጠበቀ ሆኖ እንደሚቀጥል ይገልጻል።

ከዚህ ባለፈ የታሪክና የፊዚክስ ኮርሶች ሳይካተቱ ከአጠቃላይ 50 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ በየተቋሙ (በተማሩበት ዩኒቨርሲቲ) የ2016 ፍሬሽማን ተማሪዎች እንደሚሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት 150 ከ 300 እና 200 ከ 400 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝርዝር ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እንደዚሁም ለትምህርት ሚኒስቴር አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ እንዲላክ ማሳሰቢያ ተላልፏል።



🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በጋምቤላ ክልል በተከሰተ "የፀጥታ ችግር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ‼️በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ...
19/07/2023

በጋምቤላ ክልል በተከሰተ "የፀጥታ ችግር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ‼️

በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ ካቢኔ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ችግሩን መነሻ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል።

ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪም ሆነ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።
ከተመደቡ የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውንም ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሆነ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት ከነገ ጀምሮ መደበኛ ስራውቸዉን እንዲያከናዉኑ ካቢኔዉ ዉሳኔ አሳልፏል። ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን በክልሉ ነዋሪ ከሆኑ ዜጎች ለመስማት ተችሏል። የክልሉ መንግሥት ከሰሞኑን በተነሳው የፀጥታ ችግር ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተ...
19/07/2023

አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ። የተከሳሾችን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ በድረ ገጻቸው የጫኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን እንዲያወርዱም ፍርድ ቤቱ አዝዟል።

ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 12፤ 2015 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው። ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ትዕዛዞችን በሰጠበት ቅጽበት፤ ተከሳሾች በጭበጨባ የታጀበ መፈክር አሰምተዋል። የተከሳሾቹ መፈክር እና ጭብጨባ፤ የችሎት ውሎ ተጠናቅቆ ታዳሚዎች ከአዳራሽ ከወጡ በኋላም አላቋረጠም ነበር።

በተከሳሾች ጭብጨባ የተጠናቀቀው ችሎት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው፤ ጠበቆች ባቀረቡት የተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት እና ከዚህ በፊት የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈጻጸም ለመከታተል ነበር። የተከሳሾችን የዋስትና መብት በተመለከተ ከ20 ቀናት በፊት በነበረ የችሎት ውሎ በተደረገ ክርክር፤ ጠበቆች የደንበኞቻቸው የዋስትና ጉዳይ ሊታይ የሚገባው “የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ እና በህገ መንግስቱ እንጂ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ አይደለም” ሲሉ ተከራክረዋል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 #ጤናመረጃሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 12 የጤና በረከቶች!ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም ፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮ...
19/07/2023

#ጤናመረጃ

ሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 12 የጤና በረከቶች!

ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም ፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮዲንና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢ፣ኤፍን ይዛል።

1- የሀይል ምንጭ ነው:- ሙዝ በውስጡ ቫይታሚን፣ሚኒራል እና ካርቦሀይድሬት በመያዙ ሀይል ለማግኘት ይጠቅማል፡፡

2- ለምግብ መንሸራሸር ይጠቅማል:- ይህም የሚሆነው ሙዝ በውስጡ የቃጫ ባህሪ(ፋይበርነት) ስላለው ነው፡፡

3- የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል:- ጨጓራ ጠንካራ ግድግዳ እንዲኖረው እና በጨጓራ ውስጥ ያለውን አሲድነት በመቀነስ ህመምን ያስታግሳል፡፡

4- የልብን ጤንነትን ይጠብቃል:- ሙዝ በፖታሲየም የበለፀገ ስለሆነ ይህም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡

5- ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ አነስተኛ ቅባት እንደዚሁም ብዙ ፋይበር ሰለያዘ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6- አኔሚያን ለማከም ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ በዛ ያለ የብረት ማእድን ስለያዘ ይህም የቀይ የደም ሴልን ማነስ ይከላከላል፡፡

7- ነብሰጡሮችን ከህመም ይታደጋል:- ነብሰጡር ሴቶችን የሚያጠቃ የጠዋት ህመም የሚባለውን ለማከም ይረዳል፡፡

8- የአይንን ጤና ያሻሽላል:- ሙዝ ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የአይን በሽታን ይከላከላል፡፡

9- በወባ ትንኝ የተነደፈን ይፈውሳል:- የተነደፈበት ቦታ በሙዝ ልጣጭ በማሸት ከህመሙ ይፈውሳል፡፡

10. ጥርስን ያነጣል፦ በሙዝ ልጣጭ ጥርስዎን ሁልጊዜ ጥርስዎን ሲፍቁ ለአስደናቂ ፈገግታ ይኖርዎታል።

11. የተጎድ የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል፣ የፊት መሸብሸብና የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል።

12. ክንታሮትን ያድናል:-ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ስለሆነ ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያጋሩ! ሼር!

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

ጥንቃቄ!በውሸት “ታግቻለሁ” በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሺሕ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለሳይታገት “ታግቻለሁ” በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሺሕ ብር የጠየቀው ተጠርጣሪ ግለሰብ...
17/07/2023

ጥንቃቄ!

በውሸት “ታግቻለሁ” በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሺሕ ብር የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ሳይታገት “ታግቻለሁ” በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሺሕ ብር የጠየቀው ተጠርጣሪ ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በፖሊሰ ቁጥጥር ሥር መዋሉ የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ ከደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ ወደ ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በካራ ጉቱ ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን በገመድ ዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና በስልክ 500 መቶ ሽሕ ብር ላኩልኝ በማለት የነገራቸው ሲሆን፤ ቤተሰቦቹም ጉዳዩን ለፓሊስ ማመልከታቸው ተገልጿል፡፡

ፓሊስም የደረሰውን ጥቆማ ትኩርት በመስጠት ልዩ የመረጃ መረቡን በመዘርጋት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል “ታግቻለሁ” እያለ ቤተሰቦቹን እና የአካባቢውን ሰው ያስጨነቀው ተጠርጣሪ ከሌሊቱ 07:00 ሰዓት በሕብረተሰቡ ጥቆማ መነሀሪያ አካባቢ አልጋ ቤት ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ገልጿል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተመራቂ ተማሪዎችን ውጤት ለተቋማት የመላክ ስራ እየሰራ ይገኛል።የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በሰጡት ቃል፤ ለእያንዳንዱ ተቋም...
16/07/2023



ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተመራቂ ተማሪዎችን ውጤት ለተቋማት የመላክ ስራ እየሰራ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በሰጡት ቃል፤ ለእያንዳንዱ ተቋም የተማሪዎችን ውጤት በዝርዝር ከመቶ ስንት እንዳስመዘገቡ መላክ እንደተጀመረ አመልክተዋል።

የመንግሥት ተቋማት ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ዝርዝር ውጤት ትላንት ተልኮ የተጠናቀቀ ሲሆን የግል ተቋማት ቁጥራቸው ብዙ ስለሆነ እስከ ማክሰኞ ድረስ ተልኮ ይጠናቀቃል ሲሉ ገልጸዋል።

👉ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ እንደሚችሉ ት/ት ሚንስቴር አስታውቋል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 የመውጫ ፈተናውን 61,054 ተማሪዎች (40.65%) ብቻ አልፈዋል!!በ2015 የመውጫ ከወሰዱ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ወስጥ 61,054 ተማሪዎች ብቻ እንዳለፉ ተገለፀ!!"የ2015 የመውጫ...
15/07/2023



የመውጫ ፈተናውን 61,054 ተማሪዎች (40.65%) ብቻ አልፈዋል!!

በ2015 የመውጫ ከወሰዱ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ወስጥ 61,054 ተማሪዎች ብቻ እንዳለፉ ተገለፀ!!

"የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ የነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች ሲሆኑ የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ ብቁ ሆነው የተመዘገቡት ከ48 መንግስት ተቋማት 84,627 እና ከ171 የግል ተቋማት 109,612 በድምሩ 194,239 ተማሪዎች ናቸው፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመውስድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77,981 ተማሪዎች ከተመዘገቡት 92.15 ከመቶ እንደዚሁም ከግል ተቋማት 72, 203 ተማሪዎች 65.87 ከመቶ በድምሩ 150,184 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደዋል፡፡

👉በመንግስት ተቋማት ለፈተና ከተቀመጠት ውስጥ 48,632 ተማሪዎች 62.37 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡

👉በተመሳሳይ ከግል ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 12,422 ተማሪዎች 17.2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡ በድምሩ ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 61,054 ተማሪዎች 40.65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡

ውጤታቸውንም #ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ ብሏል።

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

የ8ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድን በመጥለፍ ወንጀል የተጠረጠረው ወጣት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ በሐዋሳ ከተማ ሰሞኑን ተጠልፋ የነበረችውን የ8ተኛ ክፍል ተማሪ ሜላት መሀመድን ...
19/06/2023

የ8ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድን በመጥለፍ ወንጀል የተጠረጠረው ወጣት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

በሐዋሳ ከተማ ሰሞኑን ተጠልፋ የነበረችውን የ8ተኛ ክፍል ተማሪ ሜላት መሀመድን በመጥለፍ ወንጀል የተጠረጠረው ወጣት ሳምሶን ሸኑ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የፖሊስ መምሪያው አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ፤ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል እና በደረሰው መረጃ መሰረት በይርጋለም ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ፍል ውሀ አካባቢ በአንድ ቤት ውስጥ በተደበቁበት በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 5:30 ላይ ሜላት መሀመድና ተጠርጣሪውን ሳምሶን ሸኑ በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል።

አክለውም፤ "ወንጀል የሰራ ለጊዜው ይደበቃል እንጅ ከህግ አያመልጥም" ያሉ ሲሆን፤ የምርመራ ሂደቱን በተመለከተ በየጊዜው ይፉ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከቀናት በፊት በከተማዋ ፀጋ በላቸው የተባለች ወጣት ላይ የጠለፋ ወንጀል ፈፅሞ የተሰውረውና በፖሊስ ክትትል ሲደረግበት የነበረው ተጠርጣሪ ሣጅን የኃላሼት መብራተ ከሁላ ወረዳ በሀገረ ሰላም ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ይታወሳል።

ተጠርጣሪው በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ተከፍቶበት የቀረበ ሲሆን፤ መርማሪ ከሳሽ በተጠርጣሪው ላይ 14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ችሎቱም የምርመራ መዝገብን አስቀርቦ ከተመለከተ በኃላ ከተጠየቀው 14 ቀን ውስጥ 12 ቀን ፈቅዶ ለዛሬ ሰኔ 12/2015 መቀጠሩ ተገልጿል።

🛑ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

 #ሀዋሳ📍ወ/ሪት ጸጋ በላቸው ተገኝታለች!!ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ተጠልፋ የተወሰደችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው መገኘቷ ተሰምቷል።ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መግባቱዋም ...
01/06/2023

#ሀዋሳ📍
ወ/ሪት ጸጋ በላቸው ተገኝታለች!!

ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ተጠልፋ የተወሰደችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው መገኘቷ ተሰምቷል።

ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ ወደ ሀዋሳ መግባቱዋም ታውቋል። ተጠርጣሪው ግለሰብም ተበዳይዋን ጥሎ ወደ ጫካ በመግባቱ በከፍተኛ ክትትል ውስጥ ይገኛል።

ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሰን እናቀርባለን።

🛑ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

🔖ዘመናዊ ሂወት - በስማርት ሰአትዎ!💯Original Smartberry W26+ ስማርት ሰአት⌚️📌ባትሪው ከ3-5 ቀን የሚቆይ (እንደአጠቃቀማችን)♦️ውሃ አያበላሸውም(  )📌የራሱ ስፒከር አለው፣...
30/05/2023

🔖ዘመናዊ ሂወት - በስማርት ሰአትዎ!

💯Original Smartberry W26+ ስማርት ሰአት⌚️

📌ባትሪው ከ3-5 ቀን የሚቆይ (እንደአጠቃቀማችን)
♦️ውሃ አያበላሸውም( )
📌የራሱ ስፒከር አለው፣ ስልክ ያስወራል፣ ሚሴጅ ይቀበላል።

📌 Bluetooth call, message, music, f.b፣ Sport፣ heartrate፣ Calories፣ blood pressure ሌሎችም

🌀color- black ብቻ | Addisababa📍

➡️Price💸 2500birr ብቻ| ይደውሉ!
በTelegram ለማዘዝ 📲
በPhone ለማዘዝ ☎️ 0901882392/ በስራሰአት
👉👉 t.me/ethiobrandwatches

አሳዛኝ ዜና🕯🕯በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን " #ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን በኦርቶዶክሳዊያን ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ መፈፀሙን ተዋህዶ ሚዲያ ማ...
30/05/2023

አሳዛኝ ዜና🕯🕯

በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን " #ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን በኦርቶዶክሳዊያን ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ መፈፀሙን ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘገበ!

በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ( በቅርብ ርቀት የሚገኝ) በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን በግንቦት 20 ለ 21 ቀን 2015 አጥቢያ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ጀምሮ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ጥቃት ደርሷል።

የዚህም ጥቃት ሰለባ የሆኑትና በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የተፈጸመባቸው ቄስ ታደለ የቡልጋወርቅ እድሜ 46 ሲሆኑ የስድስት ልጆች አባት እና የቤተሰብ ኃላፊ ፣ ቄስ ካሱ መንገሻ እድሜ 72 አዛውንት ሲሆኑ የአራት ልጆች አባት እና የቤተሰብ ኃላፊ ፣ ወጣት እንዳለ የቡልጋወርቅ እድሜ 34 የአንድ ልጅ አባት ፣ አቶ አድነዉ ቶላ የቤተክርስቲያን የጥበቃ ሠራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸውም 55 አመታቸው እና የሁለት ልጆች አባት ናቸው ሲሆኑ በጥይት በግፍ ገድለዋቸዋል።

በተጨማሪ ፋንታሁን ዳኛቸዉ እና ስንታየሁ ዳንኤል የ12 ዓመት ሴት ልጅ አፍነው ወስደው ለመልቀቅም ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅ ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

በአከባቢው እና በአቅራቢያው ያሉ ንፁሀን ዜጎችም ለደህንነታቸው ስጋት እንዳደረባቸው እና መንግስት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በአፅንኦት ጠይቀዋል።
ፎቶ - ስምዐ ተዋሕዶ

--- CR(ምንጭ ፣ ተሚማ) ---

🛑ለፈጣንና ተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

በሀዋሳ ልታገባ ቀናቶች ብቻ የቀሯት ወጣት መጠለፏ ተሰማ!የዳሽን ባንክ ሰራተኛና የሀዋሳ አላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው በሀዋሳ ከንቲባ የግል ጠባቂ በሆነው ...
30/05/2023

በሀዋሳ ልታገባ ቀናቶች ብቻ የቀሯት ወጣት መጠለፏ ተሰማ!

የዳሽን ባንክ ሰራተኛና የሀዋሳ አላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው በሀዋሳ ከንቲባ የግል ጠባቂ በሆነው ተጠርጣሪ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ(ተጠልፋ) ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዷም ተገልጿል።

ፀጋ በላቸው ትባላለች፤ ትውልድና እድገቷ በወልቂጤ ከተማ ሲሆን ግንቦት 15 2015 ዓ.ም ስራዋን አጠናቃ ወደቤቷ በምታመራበት ሰዓት (አሮጌው መነሀሪያ አከባቢ፤ ከምሽቱ 1 ሰዓት) ከዚህ ቀደም ይዝትባት በነበረና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር ፀጋዬ ቱኬ የግል ጠባቂ በሆነው ተጠርጣሪ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ(ተጠልፋ) ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዳለች። ከተጠለፈች 6 ቀን አልፏታል።

ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳወቅና የፍርድ ቤት መጥሪያ በማውጣት ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተደረገው ሙከራ ጥረት ካለማስገኘቱም በላይ የህግ አካላት ድርጊቱን ቀለል አድርገው ለመመልከት ሞክረዋል።

በሐዋሳ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተበራከቱ መምጣቸው የከተማዋን ስም የሚያጎድፍ፤ የሴት እህቶቻችንን የግል ውሳኔ የማያከብርና የነዋሪውን ነፃነት የሚጋፋ በመሆኑ የከተማው፣ የክልሉና የሚመለከታቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች ይህንን ለመፍታት ተገቢውን ርቀት በመጓዝ ተጠርጣሪውን ለህግ እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።

ቤተሰቦቿ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።
ፍትህ ለእህታችን (ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ )

SHARE | ሼር

🛑ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ይቀላቀሉን👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEqH1UZ3r1Ou91JgoA
👉 T.me/ethio_mereja

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioMereja.net posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EthioMereja.net:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share