21/11/2023
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አምሪፍ ሄልዝ አፊሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
ቦሎሶ ሶሬ፦ ህዳር 11/2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አምሪፍ ሄልዝ አፊሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የቦሎሶ ሶሬ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኃ/ገብርኤል ካሣዬ በበኩላቸዉ አምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በተለያዩ ቀበሊያት በጤናው ዘርፍ ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ዘርፈብዙ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱን በመጥቀስ ለጤና አገልግሎት ጥራቱንና ተደራሸነቱን ለማሰፋፋት ከአጋር ድርጅት ጋር በቅንጅት መስራት የጎላ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።
አክለውም ድርጅቱ በወጣቶች ሥነ ተዋልዶ እና በቤተሰብ ጤና አገልግሎት በተጨማሪ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ዙሪያ ለማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ መቆየቱን አክሎ ገለፃ አድረገዋል ።
በባለፉት ጊዜያት የተስተዋሉ የጤና ተግባር ዝንፈቶችን በማረምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳዮችን ከወዲሁ በመለየት በአስተሳሰብ የበለፀገ ጤናማ ህብረተሰብ ለማፍራት በጋራ እንደሚሰሩም የወላይታ ዞን አምሪፍ ሄልዝ አፊሪካ አስተባባሪ አቶ ደምሰው ገ/ማሪያም ተናግረዋል።
የድርጅቱን ራዕይ እና ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በባለፉት የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ለውጤታማነቱ ሁሉም መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ያለ ዕድሜ ጋብቻና ያልተፈለገ እርግዝና ለተለያዩ ጤና እክል የሚያደረግ በመሆኑ ወጣቱ ከእንደዚህ አይነት አደጋዎች ራሱን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ቦልጣና ድርጅቱ በወጣቶች ሥነ ተዋልዶ እና በቤተሰብ ጤና አገልግሎት በተጨማሪ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ዙሪያ ለማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ መቆየቱን አክሎ ገለፃ ከተደረገ በኃላ በድርጅቱ የታቀፉ ቀበሌያትና ጤና ጣቢያዎች መካከል የሄምበቾ ማዘጋጃ ላይ የተሰሩ ሥራዎች ጉብኝት ተደርገዋል።