Abay Tube

Abay Tube Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and

facebook.com/EthioOnlineStoreSaleandbuy
23/08/2023

facebook.com/EthioOnlineStoreSaleandbuy

Professor
02/03/2023

Professor

ሰበር!ጥር 13/2105 (አዲስ አበባ): የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ከፍተኛ አባላቱን አገደየህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ ፦1. ደብረጽዮን ገብረሚካ...
21/01/2023

ሰበር!
ጥር 13/2105 (አዲስ አበባ): የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ከፍተኛ አባላቱን አገደ
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ ፦
1. ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. ፈትለወርቅ ገብረዝጊሔር
3. ጌታቸው ኣሰፋ
4. ኣለም ገብረዋህድ እና
5. ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ስራ ኣሰፈፃሚ አባልነታቸው አግዷል።
ኮሚቴው ከጥር 7 እስከ 10/2015 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስማቸው ከላይ የተጠቀሰውን አባላቱን ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ አግዷል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ያገዳቸው በጦርነቱ ለደረሰው ኪሳራ ሁሉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ በሚል እንደሆነም የመረጃ ምን ጮቻችን አረጋግጠዋል።
@ https://t.me/AbayonYouTube

I invite you to SUBSCRIBE me 💜 I'm starting my own You Tube channel, Facebook and Instagram accounts to create an honest and approachable conversation. Thank You !!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

•Facebook:- https://www.facebook.com/AbayOnYoutube/
•Instagram:- https://www.instagram.com/abayentertainment
•Telegram: - https://t.me/AbayonYouTube
•YouTube: - https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

ከሪዮ ዴጃንዬሮ  እስከ ዋሽንግተን በተጎነጎነው ሴራ የምክር ቤት አባላትን በማሳደም ኘሬዝደንት ዲልማ ሩሴፍ የመተማመኛ ድምፅ አጥተው ከስልጣን እንዲወርዱ ተደረገ። በዚህ አላበቃም ፤  አለ ቨ...
14/01/2023

ከሪዮ ዴጃንዬሮ እስከ ዋሽንግተን በተጎነጎነው ሴራ የምክር ቤት አባላትን በማሳደም ኘሬዝደንት ዲልማ ሩሴፍ የመተማመኛ ድምፅ አጥተው ከስልጣን እንዲወርዱ ተደረገ። በዚህ አላበቃም ፤ አለ ቨተባለው በሙስና ወንጀሉ የሉላ ዳሲልቫም እጆች ተነካክቷል በሚል በብራዚል ታሪክ እጅግ ተወዳጅ የተባሉትን የቀድሞ መሪም ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደረገ።

ክሳቸውን ሲመለከት የነበረው ፍ/ቤት ሉላ ዳሲልቫ በኘሬዝደንትነት ዘመናቸው ምዝበራን ፈፅመዋል በሚል የአምስት አመት እስር ፈረዶባቸው ወደ ማረሚያ ቤት ላካቸው።

ሂደቱ በፓለቲካዊ ሴራ የተመራ ፥ ውሳኔውም ፍትህ የተጓደለበት መሆኑን ሉላ አቤት ቢሉም ሰሚ አጥተው ከፍርግርግ ብረት ጀርባ ተከተቱ።

ብዙዎች ይህን ሁኔታ 'የፓርላማ መፈንቅለ መንግሰት' ሲሉ ይጠሩታል ፤ ከተለምዷዊው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እና የቀለም አብዮት በተለየ መንገድ ህጋዊ መንግስትን በተቀነባበረ ሴራ ከስልጣን የማስወገድ ስልት መሆኑን በመግለፅ።

ሁኔታውን በቅርበት የተከታተሉ አጥኚዎች የሉላ እስር ገፊ ምክኒያቶች ርዕዮተዐለማዊ እና ኢኮኖሚያዊ የጥቅም ፍላጎቶች እንደሆኑ ይገልፃሉ።

ርዕዮተዐለማዊነቱ ፥ ከምዕራቡ አለም በተለየ ፓሊሲ የመጣውን የሉላ ዳ ሲልቫን ስኬቶች ሌሎች ሃገራት ተምሳሌት እንዳያደርጉት የማጠልሸት እና እውነታን መፋቅ ነው። ኢኮኖሚያዊ ግቡ ደግሞ ፥ የሃገሪቱ እና የውጭ ባለሀብቶች በስፋት የሚተውኑበት ልቅ ስርአትን መፍጠር እና አትራፊ የብራዚል መንግስት ድርጅቶችን ለግለሰቦች እንዲሸጡ ማድረግ ነበር።

🔹ለእውነት ቀን ሲወጣ
ሉላ መሰበርን አያውቁም ፤ ብርቱ ደጋፊዎቻቸውም ይህን ባህሪ ወርሰዋል እና በፍትህ አደባባይ እውነት ነፃ እስክታወጣቸው ከመታገል አልቦዘኑም ነበር።

ህዳር 2019 የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወዳጁ ሰው ሉላ ዳ ሲልቫ የአምስት አመት እስር ተፈርዶባቸው ወደ ማረሚ የገቡበት የፍርድ ሂደት ገለልተኝነት የጎደለው መሆኑን በማረጋገጡ ፣ ከ19 ወራት እስራት በኋላ ነፃ እንዲወጡ ወሰነ።

ከእስር ሲፈቱ እርጅና የተጫነው በሚመስለው ገፃቸው ውስጥ በተሸፈነ አዲስ የትግል መንፈስ ፥ አዲስ ታሪክን ለመፃፍ ጊዜ አላባከኑም።

ፓርቲያቸውን ከመንግስትነት አውርዶ እርሳቸውንም እስር ቤት የከተተውን ኘሬዝደንት ዣዬ ቦልሴናሮን በአመፅ ሳይሆን በምርጫ ለመበቀል ዳግም ወደ ፓለቲካው መድረክ ወጡ።

ቦልሴናሮ ሉላን እስር ቤት እንዲገቡ ካደረጉ በኋላ በ2018 የተካሄደውን ምርጫ ያለሁነኛ ተቀናቃኝ
በማሸነፍ ነበር ኘሬዝደንት የሆኑት ፤ እስካለፈው ወርም ሃገሪቱን መርቷል።

ሉላ ዣዬ ቦልሴናሮ እና አስተዳደሩ በግል ካደረሰባቸው በደል በላይ በአመራር ዘመናቸው ከፍታ ላይ አድርሰዋት የነበረችውን ብራዚል በአራት አመት ውስጥ በሁሉም መስክ ቁልቁል መውሰዱን በማስረጃ እየሞገቱ የሸፈቱ ደጋፊዎቻቸውን ልብ ሳይቀር መለሱ።

" እነ ቦልሴናሮ ያፈረሷትን ብራዚል ዳግም በፍርስራሹ ላይ እናቆማታለን " በሚል ቅስቀሳቸው እየተመሩ ባሳለፍነው መስከረም የተካሄደውን ምርጫ አብላጫ ድምፅ በማግኘት የ77 አመቱ ሉላ ኢናሲዮ ዳ ሲልቫ ለሶስተኛ ጊዜ የብራዚል ኘሬዝደንት በመሆን ተመረጡ።

ሉላ 19 ወራትን ያሰራቸውን እና በፓርቲያቸው ላይ መፈንቅለ መንግስት ያደረገውን ዣዬ ቦልሴናሮን በህዝብ ድምፅ ተበቀሉት !!

ሽንፈቱን ያልተቀበሉት ዣዬ ቦልሴናሮ በሉላ በአለ ሲመት ቀን ስልጣኑን ሳያስረክቡ አገሪቱን ጥሎ ወደ አሜሪካ ፍሎሪዳ አምርተዋል። ደጋፊዎቹ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል እንዲያምፁ ጥሪ እያደረጉ ነው።

የአልሸነፍ ባይነት ተምሳሌቱ ሉላ ግን ፥ ሌላ ክብርን ተጎናፅፈው ፣ የፅኑ ታጋይነትን ልክ ለሁሉ አስተምረው ከእስር ቤት ዳግም ወደ መንግስት ቤት ተመልሰዋል !!

@ https://t.me/AbayonYouTube

I invite you to SUBSCRIBE me 💜 I'm starting my own You Tube channel, Facebook and Instagram accounts to create an honest and approachable conversation. Thank You !!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

•Facebook:- https://www.facebook.com/AbayOnYoutube/
•Instagram:- https://www.instagram.com/abayentertainment
•Telegram: - https://t.me/AbayonYouTube
•YouTube: - https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

Good Morning
03/11/2022

Good Morning

22/10/2022
30/09/2022

Abay Tube | Ethiopia | News

ውድ የሀገሬ ልጆች ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and art. Like. Share and subscribe my channel. News, Vlogs, Entertainment, Music Video, films, Reaction Video and Tutorials are available.
https://youtu.be/uGz9GOx_7iQ
https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know
https://youtu.be/KQPGiALG9Yo
በዚህ ቻናል የተለያዩ መረጃዎች የስራ ሀሳቦች, የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማሽኖች ዋጋ,ፕራንክ, የፍቅር ታሪኮች, ሙዚቃዎች, ድራማዎች እና ሌሎችም ፕሮግራምች ይዘን እንቀርባለን ቤተሰብ በመሆን ይማሩበት ይዝናናሉ ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀላሉ። በስደት የምትገኙ ውድ የሀገሬ ልጆች ወንድሞቼ እና እህቶቼ ለናንተ ጠቃሚ የሆነ መረጃዎች እና መዝናኛ Video አቀርባለሁ እናንተም Like, Share እና ሰብስክራይብ በማድረግ አበረታቱኝ እናንተም በሰላም ወደ ሀገራችሁ መሬት ያብቃችሁ። በ Video ላይ ማንኛውም አስታያየት ጥያቄዎች ወይም አብራችሁ መስራት የምትፈልጉ ከታች ያለውን አድራሻ በመጠቀም መጠየቅ ትችላላችሁ ሰብስክራይብ ለማድረግ ይህን ይጠቀሙ።
•Facebook:- https://www.facebook.com/AbayOnYoutube/
•Instagram:- https://www.instagram.com/abayentertainment
•Telegram: - https://t.me/AbayonYouTube
•YouTube: - https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know
https://www.youtube.com/channel/UCvOuOX2nVqsK_gX-J0fcvsw
ስብስክራይብ ማድረጉዏን እንዳይረሱ ስለጉበኙን እናመሰግናለን።

27/09/2022

እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ

26/09/2022
🇪🇹Ethiopians 🇪🇹
18/09/2022

🇪🇹Ethiopians 🇪🇹

https://youtu.be/WW8jHoePoAk
10/09/2022

https://youtu.be/WW8jHoePoAk

Ethiopian New Year Music Collection ምርጥ የአዲስ ዓመት ዘፈኖች ስብስብ | Abay Tube Music |new yearmusicSong

https://youtu.be/8Dl1UKUEU30
05/09/2022

https://youtu.be/8Dl1UKUEU30

አርቲስት ሜላት ነብዩ ከሚዜዎቿ ጋር Abay Tube | Ethiopia | Entertainmentውድ የሀገሬ ልጆች ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑAbay Tube is a fully integrated audio, video and art. We al...

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን የማይናወጥ አቋም በየጊዜው ስትገልፅና ይህንኑ አቋሟን በተግባር ስታረጋግጥ መቆየቷ  የአ...
02/09/2022

በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!

ኢትዮጵያ ለሰላም ያላትን የማይናወጥ አቋም በየጊዜው ስትገልፅና ይህንኑ አቋሟን በተግባር ስታረጋግጥ መቆየቷ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ሆኖም ስለሰላም የተዘረጉትን እጆች አሻፈረኝ በማለት ለ3ኛ ዙር በሃገራችን ላይ የጥፋት በትሩን የዘረጋው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ተገደን ለመመከት ወደመከላከል መግባታችን ይታወቃል፡፡

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጰያውያን ላይ ተነግረው የማያልቁ እልፍ አዕላፍ መከራና ሰቆቃ ሲፈፅም የኖረ እኩይ እና ፀረ ህዝብ ቡድን በመሆኑ የጭካኔ በደሉ በበረታባቸው ኢትዮጵያውያን የጋራ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይህ የአሸባሪ ስብስብ አሁንም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብሮ አገራችንን የማፈራረስ ግብ አንግቦ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ሆኖም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊቻችንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አኩሪ ተጋድሎ የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ላንቃ እየተዘጋና ወረራውን በብቃት እየተመከተ ይገኛል፤ ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቅ ክብርና አድናቆት አለው፡፡ ምንጊዜም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆናችንን በተግባር እያረጋገጥን ሃላፊነታችንን በብቃት እንወጣለን፡፡

በተመሳሳይ ዛሬም እንደ ትናንቱ በጦርነቱ ግንባር የአማራና የአፋር ንፁሃን ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ጉዳት የደረሰባቸውን ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ተግባራዊ በማድረግ እንቀጥላለን፡፡
ይህ እኩይ ቡድኑና ተላላኪዎቹ አልሆነላቸውም እንጂ በተደጋጋሚ አዲስ አበባንም ለማተራመስ የሽብርና የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ ለመክተት የማያባራ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ይህንኑ ቅዠታቸውን ለመፈፀም ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡

በተለይም በሃሰት ፕሮፖጋንዳ፤ ህዝብ ከህዝብ የሚያጋጩና አንድነታችንን የሚበትኑ የተፈበረኩ መረጃዎችን በማሰራጨት ፤ በከተማዋ ውስጥ የሽብር ቡድኖቹ የህወሓትና የኦነግ ሸኔን የተለያዩ የፅንፍ አስተሳሰብ የሚረጩ አባላትን በማስረግና የጥፋት ሴሎችን በማደራጀት ፤ ሰላማችንን ለማወክ፤ የጸጥታ ስጋት ለመፍጠርና የእኩይ እቅዳቸውን ለማሳካት በግልጽ እንቅስቃሴ እያካሄዱ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለረጅም ዘመናት በዘረጋው የሌብነትና የዝርፊያ አደረጃጀቶችና አሰርጎ ባስገባቸው ተላላኪዎች ተጠቅሞ በተለያዩ ወንጀሎችና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም፤ ህብረተሰቡን በማማረር መንግስት ላይ ጫና ማሳደር በሚለው ያረጀ ስልት ለመጠቀም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ስልቶችም መካከል፤ በየቦታው ህገ ወጥነትን ማስፋፋትና የመሬት ወረራ እንዲካሄድ በማድረግ፤ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የደረቅ ወንጀሎች እንዲስፋፉ በማድረግ፤ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲባባስና ህዝቡ አንዲማረር ለማድረግ የቀን ቅዠታቸውን ለማሳካት ግብ ያደረጉ እንቅስቃሴዎቻቸው በየአካባቢው መታየት ጀምረዋል፡፡

ይህ ከህዝብ ልብ ተተፍቶ የወጣ ሃይል ፤ በህዝብ ውስጥ ሊሸሸግ የሚስችለው አንዳችም እድል እንደሌለው የታወቀ ቢሆንም በማናቸውም ሁኔታ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆነው ያገኘናቸው አካላትም ሆኑ ሰዎች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡

የከተማችን ነዋሪዎችም ወቅታዊ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የከተማ አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን በማወቅ ፤ ለህገወጦች እቅድ ተጋላጭ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ ማሳሰብ እንወዳለን!
በተለይም ቀጣዮቹ ሳምንታት በርካታ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ እነዚህ በአላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የከተማችን ነዋሪ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አካባቢውን ብሎም ከተማውን በንቃት ተደራጅቶ እንዲጠብቅ ፤ ከፀጥታ ሃይሉ እና ከሰላም ሰራዊቱ አደረጃጀት ጋር በመተባበር እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በየአካባቢው በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ፤ ፀጉረ ልውጦችን፤ የሽብር ወሬ የሚነዙና የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የተለያዩ ህዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲስተጓጎሉ የሚያደርጉ አካላትን ለፀጥታ ሃይሉ በመጠቆም እንዲሁም በማጋለጥ አገራዊ ሃላፊነታችንን እንድንወጣም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም የከተማችን ህዝብና አስተዳደር ከግንባር እስከ ደጀን ለሰራዊታችን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን እያረጋገጥን ፤ ሁላችንም በየተሰማራንበት ውጤታማ በመሆን የእኩይ ሴራዎችን እያከሸፍን ፤የመዲናችንን ሰላም ዘላቂነት በማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ በተደራጀና በተቀናጀ አመራርና ከህዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራትን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

እውነትና ሃቅ ከኢትዮጵያ ጎን ነው፡፡ ኢትዮጵያ የያዘቸውን ምንጊዜም የማይናወጥ የፍትሃዊነትና ፤የሰላማዊነት አቋም የአሸናፊነት ጋሻዎቻችን ናቸው፡፡

ከሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እስከ ቅርብ ባንዳዎች ድረስ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ፣ የሞከሩት ሁሉ አሸንፈን መልሰናቸዋል። ዛሬም እንመልስላቸዋለን!!

አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትብብርና አንድነት ሃላፊነቷን በብቃት ትወጣለች!! ኢትዮጵያ ድል እያደረገች ትቀጥላለች!! አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ
☝️
በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇☝️

https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and art...

ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!!ከኢትዮጵያ አልፎ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆነው አሸባሪው የህውሓት ቡ...
28/08/2022

ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!!

ከኢትዮጵያ አልፎ በአጠቃላይ ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ የሆነው አሸባሪው የህውሓት ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ በአማራ ክልልና በአፋር ክልሎች ላይ የከፈተውን ደም አፋሳሽ ጦርነት የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በፅኑ ያወግዛል።

አሸባሪው የህውሓት ቡድን ለ27 ዓመታት የአገሪቱን ማእከላዊ ስልጣን ተቆጣጥሮ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ኢሰብአዊ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተጨማሪ በአገሪቱ ህዝቦች መካከል እርስ በርስ መተማመን እና መተባበር እንዳይኖር የሚያደርግ ጥላቻ በመንዛት የከፋ ስቃይና መከራ ያደረሰ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ቡድኑ የአገሪቱ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ በነበረበት ዘመን የሶማሌ ክልል ህዝብን ገድሏል፤ አፈናቅሏል ፣ ሴቶችን ደፍሯል፣ ተቆጥረው የማያልቁና ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ የጭካኔ ተግባራትን ሁሉ አንድም ሳያስቀር ፈፅሟል፡፡

ከዚህም አልፎ ለርካሽ ፖለቲካና ለስልጣኑ ቀጣይነት ሲል ሴራ በመጎንጎን የሶማሌ ህዝብ ለዘመናት አብረው ከኖሩት ኢትዮጵያዊ ወንድም እህቶቹ ጋር እንዲጋደልና ደም እንዲቃባ አድርጓል የክልሉን ሃብት በመዝረፍ እና የጥቂት ሰዎች ኪስ ማደለቢያ በማድረግም ክልሉ በልማት ወደ ኋላ እንዲቀር አድርጓል፡፡

ይሔ አሸባሪ ሀይል ባለፈው ግፍና በደሉ ከመፀፀት ይልቅ አሁንም የሶማሌ ክልልን በማተራመስ ህዝቡ ያገኘውን ሰላምና ነፃነት ለመንጠቅ በአንድ በኩል በክልሉ አዋሳኝ ከሚገኙ ወንድም ሕዝቦች ጋር ሰላም እንዳይኖረው ግጭት በመጥመቅ፣ በሌላ በኩል ከአልሸባብ ጋር ያልተቀደሰ የጥፋት አጋርነት በመፍጠር ክልሉን የማተራመስ እና አገር የማፍረስ ቅዠቱን ለማሳካት እየተራወጠ ይገኛል።

አሸባሪው ህውሓት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እየተጋለበ በከፈተው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚኖሩ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል፤ በእድሜ ልክ ድካም የተከማቸ የሚሊዮኖችን ሀብትና ንብረትም በከንቱ አውድሟል።

የዚህ ባንዳ ቡድን ዋነኛ ሀሳብ ኢትዮጵያን እኔ ወይም የኔ ተላላኪ የሆነ ሀይል ካልመራት አፈርሳታለሁ የሚል ሲሆን ይህን በጤነኛ አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ከክፋት ሁሉ የከፋ ሀሳቡን ለማስፈፀምም ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት በመክፈት ምስኪን የደሀ ልጆችን በአደንዛዥ እፅ እያደነዘዘ ወደ እሳት እየማገደ ይገኛል።

ቡድኑ የያዘው እኩይ አላማ ለአገራችን ሁለንተናዊ ሰላም እና ልማት ፀር መሆኑን የሚገነዘበው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት እና ህዝብ በምስራቅ በኩል የህወሃት አጋሮች በሆኑት እንደ አልሸባብ ባሉ የሽብር ቡድኖች የሚሞከሩ ሙከራዎችን በማክሸፍ እና በመደምሰስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ከማስከበር ባሻገር በህወሃት ላይ በሚወሰደው እርምጃ እንደሁልጊዜው ያልተቆጠበ ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአፅንኦት እየገለፀ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡

በመጨረሻም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ቡድኑ የጀመረውን ጦርነት አቁሞ በኢትዮጵያ መንግስት የቀረበውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበል ተገቢውን ጫና እንዲያሳድር የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም
ጅግጅጋ
https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and ar...

ሰበር_ዜና የመከላከያ ሠራዊት፣ ኮማንዶ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጥምረት የቆቦን ከተማ መልሶ ተቆጣጠረ!የአራቱንም ጥምር ምት መቋቋም የተሳነው የህወሓት ጀሌ ቆቦን ለቆወደ አላማጣ ጉዞ ጀምሯል። እ...
28/08/2022

ሰበር_ዜና

የመከላከያ ሠራዊት፣ ኮማንዶ፣ ልዩ ኃይልና ፋኖ በጥምረት የቆቦን ከተማ መልሶ ተቆጣጠረ!

የአራቱንም ጥምር ምት መቋቋም የተሳነው የህወሓት ጀሌ ቆቦን ለቆ
ወደ አላማጣ ጉዞ ጀምሯል። እንደገና ዛሬ 4 ሰዓት አካባቢ በግዳን በኩል ለመግባት ሞክሮ አከርካሪውን ተመትቶ ተመልሷል።

-ዛሬ የተሰራው ኦፕሬሽን የሚደንው ነው። ኮማንዶዎች የወልዲያን ዩኒቨርስቲ መግቢያ በር፣ ወደ ባህርዳር የሚወስደውን መንገድ ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ከዘጉ በኋላ ነው የቆቦ ኦፕሬሽን የተከናወነው። የምሥራቁ ኮከብ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ከመከላከያና ከልዩ ኃይል ጎን ሆኖ የሰራው ጀብዱ ታሪክ የሚዘክረው ይሆናል።
-የደባርቅ ከተማ አስተዳደር
በከተማዋ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት ከልክሏል። የከተማ ባጃጆች ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ አይችሉም።

-አሁን ግምባር ላይ ያለው ወኔ፣ እልህና ቁጭት የሚገርም ነው። መከላከያ ነፍሱን እየሰጠ ነው፤ ልዩ ኃይሉ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው፤ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ ደሙን እያፈሰሰ ይገኛል። ከኛ የሚጠበቀው ሞራል፣ ስንቅ፣ ደጀንነት ብቻ ነው።

-ነገርግን እዚህ የሚኖረው በስነልቦናው ስልብ የሆነው የፌስቡክ ጀሌ መከላከያን ያህል የሀገር ተቋም ሲሳደብ፣ ሲያንቋሽሽ፣ ሲሳለቅ ይውላል፥ ኧረ ሞራል ወዴት አለሽ? በምን ሞራል ነው ደሙን እያንጠባጠበ፣ ላቡን እያፈሰሰ፣ ሸለቆ ውስጥ አጥንቱን እየከሰከሰ ያለ ወታደር የሚሰደበው?
ቤተሰብ፣ ሃይማኖትና ትምህርት ቤት የሚባሉ ተቋማት ይህን ትውልድ እንዴት አድርገው አስተምረው ቢያሳድጉት ነው እንዲህ ያለ የተሳሳተ ትውልድ (wrong generation) የተፈጠረው?

በፊት መከላከያ የቅጥር ማስታወቂያ ሲያወጣ ተመዝገቡ፣ ዐማራ በልኩ ውክልና ያግኝ፣ ዘመናዊው መሳሪያዎችና ሥልጠናዎች የሚገኙት ከዚህ ተቋም ነው ስንል "አይሆንም" ብለው ሰፊ ዘመቻ ከፍተው የሚመዘገቡ ጠፍቶ ክልሉ የሚያስመዘግበው ሰው አጥቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። የትናንቱ ረስተው ዛሬ ደግሞ በመከላከያ ተከዳን የሚል ትናንትና ውስጥ ይገኛሉ። አሁንም የምመክረው ወቀሳውን ከፖለቲካ አመራሩ ላይ አድርጉ እጃችሁን ከመከላከያ ላይ አንሱ!

-በጣም ያስገረመኝ ወያኔ ከጦርነቱ በፊት በድጅታል ሚዲያ ሊያግዛት የሚችል ይህን ያህል አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ግብረ ኃይል ታዘምትብናለች ብዬ በፍጹም አልጠበቅሁም ነበር።

የሆነው ሆኖ ባንዳ አንገቱን ደፍቶ ይቀራል የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት ድል ማድረጉን ይቀጥላል።
https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and ar...

 #ወልድያየወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እን...
28/08/2022

#ወልድያ

የወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።

" የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው " ያለው የወልድያ ከተማ " የአካባቢው ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ይቀጥል " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ከተማ አስተዳደሩ " የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም " ያለ ሲሆን ሾልኮ ለማለፍና በወሬ ለመፍታት የተደረገው ስልትም እስካሁን አልሰመረም ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መልዕክቱን ያሰራጨው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ #በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር በማጣራት መሆኑን አመልክቷል ።

Subscribehttps://www.youtube.com/c/AbayTube_Know
27/08/2022

Subscribe

https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and ar...

https://youtu.be/IXVvIWh9rE0
25/08/2022

https://youtu.be/IXVvIWh9rE0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ውይይት Abay Tube | Ethiopia | Newsወጣቶች በሥራ ላይ የሚያተኩሩ፤ ሀገራቸውን ለ....

24/08/2022



ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ?

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።

በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል።

ዜጎችን ከ "ህወሓት" ጥቃት ለመጠበቅም አጠቃላይ የፀጥታ ኃይል በተጠንቀቅ መቆሙን አስገንዝቧል።

የለሊቱ ጥቃት ፤ ከሰሞኑን ከነበረው ትንኮሳ የቀጠለ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ የተሰነዘረውን ጥቃት በድል እየመከቱት ይገኛሉ ብሏል።

ከኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ ቀደም ብሎ ህወሓት የፌዴራል መንግስት ከለሊት 11:00 ጀምሮ በጩቤ በር ፣ ጃኖራ ፣ ጉባጋላ እና በያሎው አቅጣጫ ወደ አላማጣ ፣ ባላና ብሶበር መጠነሰፊ ጥቃት ከፍቷል ሲል ክስ አሰምቷል።

ባለፉት ቀናት ፤ በደቡብ ግንባር በየግንባሩ የነበሩትን እና ከሌላ አካባቢ የተሰባሰቡ የአማራ ልዩ ኃይል ክ/ጦሮች ፣ የወሎ ፋኖና ሚሊሻ ወደፊት የማስጠጋት እንቅስቃሴ ነበር በኃላም የፌዴራል መከላከያ ኃይል ተጨምሮ ዛሬ ጥቃት ተከፍቷል የሚል ክስ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ግን ይህ የህወሓት ክስ " ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል " እንደሚባለው ቀድሞ የተካነበት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ብሎታል።

ትንኮሳው በራሱ በ " ህወሓት " መፈፀሙን የገለፀው መንግስት ትንኮሳውን ከፈፀሙ በኃላ " እራሳቸው እየጮሁ " ነው ብሏል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፤ የህወሓት ቡድን የትግራይ የወጣቶችን ለማስጨረስ እያደረገ ያለውን የጦርነት ጉሰማ እንዲያቆም ጠንካራ ግፊት ማድረግ አለበትም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ የሚያገኘው በሰላም ነው ያለ ሲሆን ዛሬም ነገም የሰላም አማራጭ የመጀመሪያ መፍትሄ እንደሆነ በፅኑ እንደሚያምን ገልጿል።

ነገር ግን ህወሓት በትንኮሳው ከቀጠለ ሀገር የማዳን ህጋዊ፣ ታሪካዊ እና ሞራላዊ ግዴታ ስላለበት ህወሓት ወደደም ጠላም ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ፤ አሁን አሁን ጠንከር ብለው እየታዩ ያሉት ምልክቶች ከዚህ ቀደም እንደነበረው የለየት ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይወልድ ብዙዎችን አስግቷል። የተጀመረው የሰላም ሂደትም እንዳይደናቀፍ ተፈርቷል።

ከወራት በፊት ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ መተላለፉ አይዘነጋም ፤ ይህን ተከትሎ የሰላም ጭላንጭሎች መታየት ችለው ፤ ዜጎችም ከጦርነት እና ግጭት ስጋት ይላቀቃሉ የሚል ተስፋን ሰጥቶ ነበር።

በኃላም ችግሩን በሰላም ድርድር ለመፍታት መወሰኑን ተከትሎ በርካቶች " እፎይ ሰላም ሊገኝ ነው " የሚለው ተስፋቸው እጅግ ተጠናክሮ፤ በዚህም ተደስተው ነበር ነገር ግን ይህ ከሆነ ወራት ሳይቆጠር ዳግም የጦርነት ድባብ አንዣቧል።

ዜጎች የከዚህ ቀደሙ ጉዳት እና ህመማቸው ሳይባባስ ፣ ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት ፤ ሴቶች አረጋዊያን ሳይፈናቀሉ ፣ ምንም የሰው ህይወት ሳይጠፋ ፣ የሀገር ሀብት ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ሳይጎዳ ፤ አሁን እየታዩ ያሉት ምልክቶች ቆመው በፍጥነት ሰላም ወርዶ ፤ ችግሮች ተፈተው በደስታ እንቀበለው ይሆን ? ተስፋ እናደርጋለን ! ለሰላም መቼም ጊዜው አይረፍድም።

https://youtu.be/41ZGDxCFRqk
24/08/2022

https://youtu.be/41ZGDxCFRqk

የሳምንቱ ምርጥ TikTok ቪዲዮ ስብስብ [Best TikTok CollectionAbay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange ta...

https://youtu.be/LOEZfPeVcZ4
24/08/2022

https://youtu.be/LOEZfPeVcZ4

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and art...

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artist...
24/08/2022

Abay Tube is a fully integrated audio, video and art. We also put on concerts around the world and mange talented artists who share passion for music and art. Like. Share and subscribe my channel. News, Vlogs, Entertainment, Music Video, films, Reaction Video and Tutorials are available.
https://youtu.be/uGz9GOx_7iQ
በዚህ ቻናል የተለያዩ መረጃዎች የስራ ሀሳቦች, የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማሽኖች ዋጋ,ፕራንክ, የፍቅር ታሪኮች, ሙዚቃዎች, ድራማዎች እና ሌሎችም ፕሮግራምች ይዘን እንቀርባለን ቤተሰብ በመሆን ይማሩበት ይዝናናሉ ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀላሉ። በስደት የምትገኙ ውድ የሀገሬ ልጆች ወንድሞቼ እና እህቶቼ ለናንተ ጠቃሚ የሆነ መረጃዎች እና መዝናኛ Video አቀርባለሁ እናንተም Like, Share እና ሰብስክራይብ በማድረግ አበረታቱኝ እናንተም በሰላም ወደ ሀገራችሁ መሬት ያብቃችሁ። በ Video ላይ ማንኛውም አስታያየት ጥያቄዎች ወይም አብራችሁ መስራት የምትፈልጉ ከታች ያለውን አድራሻ በመጠቀም መጠየቅ ትችላላችሁ ሰብስክራይብ ለማድረግ ይህን ይጠቀሙ።
•Facebook:- https://www.facebook.com/AbayOnYoutube/
•Instagram:- https://www.instagram.com/abayentertainment
•Telegram: - https://t.me/AbayonYouTube
•YouTube: - https://www.youtube.com/channel/UCvOuOX2nVqsK_gX-J0fcvsw
ስብስክራይብ ማድረጉዏን እንዳይረሱ ስለጉበኙን እናመሰግናለን።

ABAY Entertainment Channel trailer for people who haven't subscribedouTube Intro Theme https://youtu.be/uGz9GOx_7iQEthiopian:habesha funny tiktok video|9th s...

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abay Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share