አዲስ ክስተት/Adis Kstet

  • Home
  • አዲስ ክስተት/Adis Kstet

አዲስ ክስተት/Adis Kstet ወቅታዊ ና ትኩስ መረጃዎች በፍጥነት ና በጥራት እንዲሁም አስ?

18/02/2021

❤ወንዶች በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የሚፈልጓቸው 6 ነገሮች❤

13/02/2021

10 የኩላሊት በሽታ ምልክቶች
#ሼር

12/02/2021

ሴቶችን የሚያሸሹ የ ወንድ ባህሪያት!

11/02/2021
አርቲስት ጸጋዬ አበጋዝ ህይወታቸው አለፈ።ረቡኒ ፊልምን ጨምሮ በበርካታ ተወዳጅ ፊልሞች እና ትያትሮችን በመተወን አንቱታን ያተረፉት አርቲስት ጸጋዬ አበጋዝ ወይም አቦይ ዛሬ ረፋድ ህይወታቸው ...
24/01/2021

አርቲስት ጸጋዬ አበጋዝ ህይወታቸው አለፈ።

ረቡኒ ፊልምን ጨምሮ በበርካታ ተወዳጅ ፊልሞች እና ትያትሮችን በመተወን አንቱታን ያተረፉት አርቲስት ጸጋዬ አበጋዝ ወይም አቦይ ዛሬ ረፋድ ህይወታቸው ማለፉን ከታድያስ አዲስ ሰምተናል። አርቲስቱ በቅርቡ በሰይፉ በኢቤኤስ የቴሌቪዥን ሾው ላይ ቀርበው ሁለት እጃቸው አልታዘዝ እንዳላቸው፣ ህይወታቸውን ያለ ረዳት እየገፉ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።

አርቲስት ጸጋዬ በሰዎች እርዳታ በአዲስ አበባ ይኖሩ በነበሩበት ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል። በአርቲስት ጸጋዬ አበጋዝ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ ለአርቲስቱ ለአድናቂዎች እና ቤተሰቦች የመጽናትን እመኛለሁ

Via abel birhanu

ነብስ ይማር 😭ባዩሼ የመድረክ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎች ንግስቷ አርቲስት ባዩሽ አለማየሁ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ለቤተሰቦቿ ለጓደኞቿ እና  መፅናናትን ...
01/01/2021

ነብስ ይማር 😭

ባዩሼ የመድረክ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድራማዎች ንግስቷ አርቲስት ባዩሽ አለማየሁ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች

ለቤተሰቦቿ ለጓደኞቿ እና መፅናናትን ያድልልን።

በቅርቡም አዲስ ድባብ ድራማ ላይ በብቃት ስትተውን ነበር

ምንጭ :- አብረዋት አዲስ ድባብ ድራማ ከሚስሩት አረጋገጥን

ነብስ ይማር 😭

ከዚ ልጅ ምን እንማራለን!?በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አላማህን አትዘንጋ! ተስፋ ካልቆረጥክ ና ጠንክረህ ከሰራህ ያሰብክበት ትደርሳለህ!! ሁሉም ያልፋል!! ነገ ሌላ ቀን ነው!!!!መልካም...
30/12/2020

ከዚ ልጅ ምን እንማራለን!?

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አላማህን አትዘንጋ! ተስፋ ካልቆረጥክ ና ጠንክረህ ከሰራህ ያሰብክበት ትደርሳለህ!! ሁሉም ያልፋል!! ነገ ሌላ ቀን ነው!!!!

መልካም ቀን!

የ 12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጥር 30 ይጠነቀቃል!የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢፒድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮ...
28/12/2020

የ 12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጥር 30 ይጠነቀቃል!

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢፒድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል።

- በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

- ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

- ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

- ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

- ሁለት ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

- በትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ወደ አገር ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

- ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ታማኝ በየነ በመተከል ጉዳይ የሚከተለውን ፅፏል" አንድ ሾፌር መብራት ሲጥስ በህግ ይቀጣል፣ አንድ የመንግስት ሰራተኛ ከስራው ሲቀር በደሞዝ ይቀጣል። ሌላም ሌላም ነገርግን በየቀኑ ዜጎች እንደ...
24/12/2020

ታማኝ በየነ በመተከል ጉዳይ የሚከተለውን ፅፏል

" አንድ ሾፌር መብራት ሲጥስ በህግ ይቀጣል፣ አንድ የመንግስት ሰራተኛ ከስራው ሲቀር በደሞዝ ይቀጣል። ሌላም ሌላም

ነገርግን

በየቀኑ ዜጎች እንደ አውሬ በሚታደኑበት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ግን ይሄ ሁሉ ሁሉ ሰው እያለቀ ርዕሰ መስተዳድሩ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጎን ቁጭ ብሎ መግለጫ ይሰጣል
የመተከሉ አስተዳዳሪ ደግሞ ጭራሽ ግድያውን አልሰማሁም ይለናል
እንዴት በዜጎች ላይ እንዲህ ይቀለዳል?

ተሸፋፍነው ቢተኙ ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ!!

አማራንም ሆነ ማንኛውንም ማህበረሰብ ማጥፋት አይቻለም። ቢቻልማ ኖሮ ከቤንሻንጉል ባለሰልጣናት ይልቅ ጣሊያን የተሻለ አቅምና መሳርያ ነበረው።

ይሄ ህገመንግስትና በዘር የተዋቀረ ልዩ ሀይል እስካለ ድረስ የመርዶው ዜና ነገም ይቀጥላል። "

Beyene

ጠቅላይ ሚኒስተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል!!👉"በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅ...
24/12/2020

ጠቅላይ ሚኒስተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል!!

👉"በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ። ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም።

👉የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው። ይህ የሚሳካ አይደለም።
መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል። የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራ ጥሪ አቀርባለሁ።"
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

አሳዛኝ ዜና ❗️የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የመኪና አደጋ ሲደርስባቸው የአንደኛው ህይወት አለፈ። ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ጋዜጠኞችን ይዞ ለስራ ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪ...
23/12/2020

አሳዛኝ ዜና ❗️

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የመኪና አደጋ ሲደርስባቸው የአንደኛው ህይወት አለፈ።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ጋዜጠኞችን ይዞ ለስራ ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን(ኢቢሲ) መኪና ከሎቤድ ጋር በመጋጨቱ የአንድ ጋዜጠኛ ህይወትም አልፏል።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ጉሻ ቀበሌ ልዩ ስሟ ብራንዲ በተባለች ቦታ በቀን 14/04/2013 ዓ/ም ከጥዋቱ 2 ሰዓት ላይ ወደ ቡሬ እየሄደ ያለ "3 ኢት 53636" ሎቤድ ወደ ባህርዳር በመሄድ ላይ ካለ "4 ኢት16851" ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የሆነ መኪና ጋር በመጋጨቱ የአንድ ጋዜጠኛ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 2 ሰው ከባድ እና 1 ሰው ቀላል አደጋ መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር አሰፋ ገበየሁ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጓጉሳ ወረዳ ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት

በወላይታ "መርካቶ ገብያ "ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ እሳት ቃጠሎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል ::
20/12/2020

በወላይታ "መርካቶ ገብያ "ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ እሳት ቃጠሎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል ::

Salut Our heroes! 🙏💚💛❤️🙏በዓለም አደባባይ ሰንደቃችንን ከፍ ያደረጉ 🇪🇹 🗣 " !" የሚል ድምፅ በተደጋጋሚ ያሰሙን ክብር ይገባቸዋል!🙏
17/12/2020

Salut Our heroes!
🙏💚💛❤️🙏
በዓለም አደባባይ ሰንደቃችንን ከፍ ያደረጉ 🇪🇹
🗣 " !" የሚል ድምፅ በተደጋጋሚ ያሰሙን ክብር ይገባቸዋል!🙏

የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኮሮና ተገኘባቸው!©አልጀዚራፈጣሪ ይማረው🙏
17/12/2020

የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኮሮና ተገኘባቸው!

©አልጀዚራ
ፈጣሪ ይማረው🙏

ይሄን ሰምተዋል!በቻይና የአውሮፕላን በረራ አስተናጋጆች ኮቪድን ለመከላከል  ሽንት ቤት እንዳይጠቀሙ ሲባል ዳይፐር አድርገው እንዲያስተናግዱ አዲስ ህግ ወጥቷል!👉መነሻውን ከቻይና ወይም ከሌላ ...
17/12/2020

ይሄን ሰምተዋል!

በቻይና የአውሮፕላን በረራ አስተናጋጆች ኮቪድን ለመከላከል ሽንት ቤት እንዳይጠቀሙ ሲባል ዳይፐር አድርገው እንዲያስተናግዱ አዲስ ህግ ወጥቷል!

👉መነሻውን ከቻይና ወይም ከሌላ ሀገር ወደ ቻይና ሲበሩ አስተናጋጆቹ ከፊት መሸፈኛ ና መነፅር በተጨማሪ ዳይፐር እንዲጠቀሙ የቻይና ሲቭል አቪዬሽን ትዕዛዝ ሰጥቷል ይህም የሆነው የኮሮና ቫይረስ በመፀዳጃ ቤት የመተላለፉ እድል ከፍተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል!

👉የአውሮፕላን አብራሪው የኮሮና መከላከያውን ሙሉ ልብስ ብቻ የሚያደርግ ሲሆን አዲሱ ህግ ና ዳይፐር አስተናጋጆች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል !

እንዴት አገኛችሁት ሃሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን!

ምንጭ :- CNN

እጅግ የሚገርም ሰው! ከራስ በላይ ለሰው ያለ!👉በቡሌሁራ ከተማ ከፍተኛ አደጋ ከመድረሱ በፊት የተወሰደ አስደናቂ እርምጃ :-👉“ይሄ መኪና በነዳጅ ማደያ ላይ እንዳለ በእሳት ይያያዛል።ሰለሞን ...
16/12/2020

እጅግ የሚገርም ሰው! ከራስ በላይ ለሰው ያለ!

👉በቡሌሁራ ከተማ ከፍተኛ አደጋ ከመድረሱ በፊት የተወሰደ አስደናቂ እርምጃ :-

👉“ይሄ መኪና በነዳጅ ማደያ ላይ እንዳለ በእሳት ይያያዛል።
ሰለሞን ደመላሽ የተባለው ወጣት ሹፌር ለህይወቱ ሳይሳሳ መኪናውን በማስነሳት ከከተማ ወጣ ወዳለ ቦታ በመንዳት፣ ሊደርስ የነበረን ከባድ አደጋ ተከላክሏል።
ማደያው ቢያያዝ ይደርስ የነበረውን ማሰብ ይዘገንናል።
ልብ ያለው ጀግና አሽከርካሪ ማለት ይህ ነው

ስመኝ ታደሰ ዘውዴ

አሳዛኝ ዜና 👉የሀገራችን የመጀመሪያው የቴአትር ተማሪ የተዋጣለት አዘጋጅ ግሩም ተዋናይ እውነታን ተጋፋጭ ብእረኛ ባለ ብሩህ አእምሮ ሀያሲው አርቲስት ጋሽ ተስፋዬ ገሰሰ አርፏል:: ነፍስህ በሰ...
16/12/2020

አሳዛኝ ዜና

👉የሀገራችን የመጀመሪያው የቴአትር ተማሪ የተዋጣለት አዘጋጅ ግሩም ተዋናይ እውነታን ተጋፋጭ ብእረኛ ባለ ብሩህ አእምሮ ሀያሲው አርቲስት ጋሽ ተስፋዬ ገሰሰ አርፏል::

ነፍስህ በሰላም ትረፍ❗️
Anteneh Kebede

ኢትዮጵያዊነት ኩራት ነው!👉ዛሬ የሞራል አለቃ ነን የሚሉት ምዕራባውያን ወደኋላ መለስ ተብሎ ታሪካቸው ሲፈተሽ ብዙዎቹ በሰብአዊነት ላይ ስንቱን አሰቃቂ ነገር ፈፅመው እንደነበር እንገነዘባለን፡...
10/12/2020

ኢትዮጵያዊነት ኩራት ነው!

👉ዛሬ የሞራል አለቃ ነን የሚሉት ምዕራባውያን ወደኋላ መለስ ተብሎ ታሪካቸው ሲፈተሽ ብዙዎቹ በሰብአዊነት ላይ ስንቱን አሰቃቂ ነገር ፈፅመው እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ ደግሞ እኮ ሩቅ አይደለም - የአንድ ሰው እድሜ፣ 75 ዓመት ወደኋላ መለስ ስንል!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!🇪🇹🇪🇹

👉በደላችን በዝቶ እረፍት አልባ ሆነናል:: ከአንዱ ሀዘን ወደሌላ ሀዘን ከአንዱ ስብራት ወደሌላ ሰቆቃየወገንን ሬሳ እየቆጠሩ ነፍስ ይማር እያሉ መኖር ያማል!ዜጎች በገዛ ሀገራቸው መርጠው ባልተ...
02/11/2020

👉በደላችን በዝቶ እረፍት አልባ ሆነናል::
ከአንዱ ሀዘን ወደሌላ ሀዘን ከአንዱ ስብራት ወደሌላ ሰቆቃ
የወገንን ሬሳ እየቆጠሩ ነፍስ ይማር እያሉ መኖር ያማል!

ዜጎች በገዛ ሀገራቸው መርጠው ባልተወለዱበት ዘር ሳቢያ ውድ ህይወታቸውን ሲነጠቁ እንደማየት ሰቅጣጭ ነገር የለም!!!

ይበቃል! በአስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል!
አርቲስት መሰረት መብራቴ

አሳዛኝ ሰበር ዜና!በግንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አስገድደው በት/ቤት በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።በኦሮሚያ ክልል ግንቢ ዞ...
02/11/2020

አሳዛኝ ሰበር ዜና!
በግንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አስገድደው በት/ቤት በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ አሰቃቂ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈፀማቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።

በኦሮሚያ ክልል ግንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ በተባለ ቀበሌ በዛሬው እለት ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከ60 በላይ የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ጥቃት መፈፀማቸውን ከአደጋው የተረፉ ነዋሪዎች ተናገረዋል።
በጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ሰፍሮ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት እሁድ ከረፋዱ 6 ሰዓት አካባቢ ሙሉ በሙሉ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ቀበሌው የገባው መትረጊዬስና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቀው የኦነግ ሸኔ ጦር በአባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አስገድዶ ትምህርት ቤት ከሰበሰበ በኋላ በጅምላ ግድያ እንደፈፀመ ከአደጋው ያመለጡ ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች ተንበርክከው እባካችሁ ተው በሚል ቢለምኗቸውም በቦንብና በመትረጊዬስ ጭፍጨፋ ከመፈፀም አልተመለሱም ነው ያሉት።
ላለፉት 3 ወራት ሰፍሮ የቆየው የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ ከረፋዱ 6 ሰዓት አካባቢው ለቆ እንደወጣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የመከላከያ ካምፕን በመቆጣጠር ከፍተኛ ጥይት ሲተኩሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ድልድይውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቄሮዎችን ሰብስበው ከፍተኛ ዝርፊያ ፈፅመዋል እና ከአንድ መቶ በላይ የመኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።
ከዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ የቀበሌውን ነዋሪ የሆኑ አማራዎችን ለስብሰባ እንፈልጋችኋለን በማለት ህጻን፣ሴትና አቅመ ደካሞችን ሁሉ እንዲሰበሰቡ ካደረጉ በኋላ በጅምላ በጥይት ደብድበው ግድያ እንደፈፀሙባቸው ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው በስብሰባው ከ250 ያላነሱ አማራዎች ስለመሰብሰባቸው ተናግረዋል።
ምን ያህል እንደተገደለ እና እንደቆሰለ በትክክል እንደማያውቁት የተናገሩት ከጥቃቱ ያመለጡት ነዋሪዎች እባካችሁ መንግስት ካለ ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
እስካሁን የደረሰልን የፀጥታ አካል የለም ያሉት ነዋሪዎቹ መከላከያ ህዝብን አደጋ ላይ ጥሎ ለምን ለቆ እንደወጣ አልገባንም ብለዋል።
የዘር ጭፍጨፋ ተፈፅሞብናል ያለው አንድ ነዋሪ እህቴ ተመታለች፣ አባቴ በስብሰባው ላይ እንደነበር አውቃለሁ በህይወት ስለመትረፉ ግን የደረሰኝ መረጃ የለኝም ሲል የተናገረ ሲሆን ኦነጎችን በመጠራጠር ቀድሞ ከአካባቢው በሸሽቶ እንደነበር አስታውቋል።
የአማራ ሚዲያ ማዕከል ካነጋገራቸው አማራዎች መካከል እናቱ፣ባለቤቱና ልጆቹ ተገደው ወደ ስብሰባው መወሰዳቸውን ገልጾ በህይወት ተርፈዋል የሚል እምነት እንደሌለው ነው የተናገረው።
በጉሊሶ ወረዳ የጋዋ ቃንቃ ቀበሌ አስተዳዳሪ፣የቀበሌው ማናጀር፣ሚሊሻዎችም ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ቀድመው መሸሸታቸው ተነግሯል።

የተገደሉትን እንድንቀብር፣የቆሰሉትን ወደ ህክምና እንድናደርስ የአማራ፣የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የፌደራል መንግስት እንዲደርስልን አድርጉ ሲሉ በጫካ የተደበቁ አማራዎች ተማፅነዋል።

26/10/2020

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል!
👉አስታውስ አንተ ጋር ያለው ለሌለው ህልሙ ነው ሁሌም ባለህ ነገር አመስግን ደስተኛ ሁን አስቸጋሪ ጊዜያት ያሉህን ነገሮች እንድትረሳ እንዳያረጉህ🙏🙏

አስተማሪ ታሪክ ነው አንብባቹ  #ሼር አድርጉት!ኪርዛይዳ ሮድሪግዝ ትባላለች.. ታዋቂ የፋሽን ፀሃፊ ና የፋሽን ሞዴል ስትሆን 508k የኢንስታግራም ተከታዮችን ያፈራች የ40 አመት ጎልማሳ እና...
23/10/2020

አስተማሪ ታሪክ ነው አንብባቹ #ሼር አድርጉት!
ኪርዛይዳ ሮድሪግዝ ትባላለች.. ታዋቂ የፋሽን ፀሃፊ ና የፋሽን ሞዴል ስትሆን 508k የኢንስታግራም ተከታዮችን ያፈራች የ40 አመት ጎልማሳ እና የ አንድ ልጅ እናት ነበረች

ኪርዛይዳ 4ኛ ደረጃ ላይ በደረሰ የሆድ ካንሰርን ባለፈው ወር ሴፕቴንበር 9 2019 ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች

ኪርዛይዳ ከመሞቷ በፊት የመጨረሻ ቃሏ አንዲህ ይል ነበር

*ብራንድ የሆኑ ዘመናዊ መኪኖች አሉኝ፣
*በምርጥ ዲዛይነር የተሰሩ ውድ ጫማዎች፣ልብሶች አሉ
*ባንክ አካውንቴን ብዙ ሚሊዮን ዶላር አጨናንቆታል
*እጅግ ዘመናዊ ቤትም አለኝ።🏣

እሁን ግን እዚህ 2በ2 በሆነ የሆስፒታል አልጋ ላይ እገኛለሁ
እነዚህ አሉኝ ያልኳቸው ነገሮች ሁሉ በህይወት ለመቆየቴ ምንም ናቸው ከሞት ሊያስጥሉኝ አይችሉም!!

በህይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር "ፍቅር" ነው
በህይወት ሳላቹ የሚወዷችሁ ሰዎች በእናንተ ደስተኛ እንዲሆኑ አድረጓቸው
ትርፋቸሁ ፍቅር ይሁን፣ አዎ ፍቅር ብቻ ይሁን ...

እናም ወዳጆቼ ሆይ ለዚች አጭር ህይወት፤ መቼ ትተናት እንደምትሄድ ለማናውቃት አለም በብሄር፣በሀይማኖት ተከፋፍለን እርስ በእርሳችን አንባላ እንዋደድ።

©ከ1 አመት በፊት የተፃፈ

22/10/2020

👉Don't Give Up:- Jack Ma

22/10/2020

👉ሶስት አይነት ሰዎች አሉ ይመልከቱ👇
እርሶ ከየት ውስጥ ኖት መልካም ቀን

New record 👏👏👏🇪🇹🇪🇹🇪🇹ትላንትና በጣልያን በተደረገ የጎዳና ላይ የ10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊዉ ሀጎስ ገ/ሕይወት 1ኛ በመውጣት ውድድር ሲጨርስከዚህ በፊት የነበረው የቦታው...
19/10/2020

New record 👏👏👏🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ትላንትና በጣልያን በተደረገ የጎዳና ላይ የ10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊዉ ሀጎስ ገ/ሕይወት 1ኛ በመውጣት ውድድር ሲጨርስ

ከዚህ በፊት የነበረው የቦታውን ሪከርድ በ10 ስከንድ በማሻሻል አዲስ ለሱም ለሀገሩም ሪከርድ አስገኝቷል:

2ኛ የወጣው ኢትዮጵያዊ ሲሆን ባይልኝ
ተሻገር ሆኗል

በውጤቱም :-

1ኛ . ሀጎስ ገ/ሕይወት ኢትዮጵያ🇪🇹 :- 29:49

2ኛ. ባይልኝ ተሻገር ኢትዮጵያ🇪🇹:- 30:00

3ኛ.ያሲን ራቺክ ጣሊያናዊ 🇮🇹 :- 30:23

የእንጀራ ነገር!ከታች በምስሉ የሚታዩት ወይዘሮ እታፈራሁ ይባላሉ። በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ ናቸው። የሚታዳደሩት ደግሞ በከተማዋ ጽዳት እና ውበት ቢሮ ተቀጥረው ነው።የእንጀራ ነገር ...
17/10/2020

የእንጀራ ነገር!

ከታች በምስሉ የሚታዩት ወይዘሮ እታፈራሁ ይባላሉ። በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ ናቸው። የሚታዳደሩት ደግሞ በከተማዋ ጽዳት እና ውበት ቢሮ ተቀጥረው ነው።

የእንጀራ ነገር ሆነና በዚህ መልኩ መላው ሰውነታቸው በውሀ ተዘፍቆ የከተማዋ ግዴለሽ ነዋሪ የሚወረውረውን ቆሻሻ ሲሰበስቡ ይውላሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እስኪ የቻላችሁ እኒህን እናት በገንዘብ እና ሞራል አግዟቸው። ቆሻሻን በዘፈቀደ ባለመጣልም እንተባበራቸው!

© መሰረት ወርቁ

Share በማድረግ እኒህን ጀግና እናት እናበረታታ!

አስተማሪ ታሪክ። ይነበብ!!ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም ለመግደል ታስባለች። ማታውን ስታሰላስል ታድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠረውና ...
17/10/2020

አስተማሪ ታሪክ። ይነበብ!!

ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም ለመግደል ታስባለች። ማታውን ስታሰላስል ታድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠረውና እርሷንም ወንጀለኛ በማያስደርጋት መልኩ መግደል እንደምትችል ለመመካከር እናቷ ጋር ትሄዳለች።እናቷም "ማንም በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ ያለብሽ ነገሮች አሉ።
1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም
2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ
3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር ያደርገዋል።
4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ።ፍቅር ሰጪው። ቅናት ቀንሺ።የሚናገረውን ጆሮ ሰጥተሽ አዳምጪው።
እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ?"ብላ ጠየቀቻት።እናቲቱ። "ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ።" አለች ልጅቷ።
"እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ አድምጪኝ።"አለች እናት።ልጅቷም በአትኩሮት መስማት ጀመረች።
"ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ እያዳከመው ይገድለዋል።" አለቻት። ልጅቷም መርዙን ይዛ በደስታ ቤቷ ሄደች። በተነገራት መሰረትም ለባሏ መስጠት ጀመረች።
ከወር በኋላ እንደገና እያለቀሰች እናቷ ጋር መጣች። "እማ አሁን ባለቤቴን መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል። እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው።እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ?ያለ እርሱ መኖር አልችልም። አለች ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች።
እናትም "አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር። በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ እየገደለው የነበረው። አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት አይነት መልካም ሰው እንደሆነ።ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት ሁኚለት።"ብላ ነገረቻት።
የኔ እህት ወንድ ልጅ የፈለገ አረመኔ ቢመስል ልቡ ገራገር ነው በፍቅር ልታሸንፊው ትችያለሽ። መልካም ሚስት ሁኚለት። ፍቅር ሁሌም ያሸንፋል።

#ሼር ለሌሎችም

አንዲት በስጋ ፋብሪካ ውስጥ የምትሰራ ሴት የዘወትር ተግባሯንስትከውንዋለች። በመጨረሻም ስጋ የሚቀመጥበትን ማቀዝቀዣ ክፍልለማየትወደማቀዝቀዣው ክፍል ገብታ ስጋዎችን በማስተካከል ላይሳለችየማቀዝ...
16/10/2020

አንዲት በስጋ ፋብሪካ ውስጥ የምትሰራ ሴት የዘወትር ተግባሯን
ስትከውን
ዋለች። በመጨረሻም ስጋ የሚቀመጥበትን ማቀዝቀዣ ክፍል
ለማየት
ወደማቀዝቀዣው ክፍል ገብታ ስጋዎችን በማስተካከል ላይ
ሳለች
የማቀዝቀዠው ክፍል በድንገት ተዘጋባት። የሚከፍትላት ሰው
በመፈለግም
በሩን ደጋግማ ደበደበች። ሰራተኞቹ ወተው ነበርና የድረሱልኝ
ጩኸቷን
የሚሰማት አላገኘችም። ቅዝቃዜው ሰውነቷን እያኮማተራት ነው።
ሞት
አፍጥጦ ከጣገቧ ደፍጦ ደቂቃ እየቆጠረ ነው። በዚህ ህኔታ
ለአምስት ሰአት
በፊሪጁ ውስጥ ቆየች። እስትንፋሷ ግን አልተቋረጠም። በድንገት
ግን
ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ። የፋብሪካው የጥበቃ ሰራተኛ በሩን
ከፍቶ ገባ። እሷ
ግን ለመናገር ትንፋሽም አጥሯት ነበር። ዘበኛው ግን
የማቀዝቀዣውን በር
ከፈተው። በሞት አፋፍ ላይ ያለችውንም ወይዘሮ ህይወት
ታደጋት። ድርጊቱ
ከሆነ በኃላ የዘበኛው በድንገት እዛ ክፍል መገኘት ያስገረማቸው
ሁሉ ይሄን
ጥያቄ ሰነዘሩለት።

የተቆርቋሪነት ጥግ🔺ዛሬ ብዙዎችን ያነጋገረዉ ክስተት በሜክሲኮ አንድ የፓርላማ አባል በክርክር ወቅት በፓርላማው ውስጥ ልብሶቹን ሁሉ በማውለቅ ... “እኔን እርቃኔን በማየታችሁ እርግጠኛ ነኝ ...
12/10/2020

የተቆርቋሪነት ጥግ🔺

ዛሬ ብዙዎችን ያነጋገረዉ ክስተት

በሜክሲኮ አንድ የፓርላማ አባል በክርክር ወቅት በፓርላማው ውስጥ ልብሶቹን ሁሉ በማውለቅ ...

“እኔን እርቃኔን በማየታችሁ እርግጠኛ ነኝ ልታፍሩ ትችላላችሁ ፤ ነገር ግን በእናንተ ዘረፋ ምክንያት ህዝቤ በየጎዳናዎች እርቃናቸውን ባዶ እግራቸውን፣ፍትህ አጥተው ተስፋ የቆረጡ፣ሥራ አጥ የሆኑና የተራቡ ዜጎቻችንን ጎዳናዎች ላይ ስታዩ አታፍሩም አትሸማቀቁም፡፡"

በማለት ፓርላማውን በዓለም ታይቶ በማይታወቅ ክስተት ወቅሶ የዓለም ሚድያዎች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

In Mexico 🇲🇽 , a member of Parliament removes all his clothes in Parliament during debate... "You are ashamed to see me naked, but you are not ashamed to see your people in the streets naked, barefooted, desparate, jobless and hungry after you have stolen all their money and wealth".........he told the Parliament‼️

What a courageous man, this is how it should be.

© World press

በሱዳን መንግስት እና በአማጺያን መካከል የመጨረሻ የሰላም ስምምነት ተፈረመ!የሱዳን የሽግግር መንግስትና የሪቮሉሽናሪ ግምባር ጥምረት የመጨረሻውን የሰላም ስምምት የተለያዩ ከአለም አቀፍ ማህበ...
03/10/2020

በሱዳን መንግስት እና በአማጺያን መካከል የመጨረሻ የሰላም ስምምነት ተፈረመ!

የሱዳን የሽግግር መንግስትና የሪቮሉሽናሪ ግምባር ጥምረት የመጨረሻውን የሰላም ስምምት የተለያዩ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ፤ከአፍሪካና ከሱዳን የተውጣጡ ተወካዮች በታደሙበት በደቡብ ሰዱን ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋነኝነት በፀጥታ ፣ በመሬት ባለቤትነት ፣ በሽግግር ፍትህ ፣ በስልጣን ማጋራት እና በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የተሰደዱ ሰዎችን መልሶ ማቋቋም ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በተጨማሪም የአማጺ ኃይሎችን ማፍረስ እና ተዋጊዎቻቸውን ወደ ብሔራዊ ጦር ስለማቀላቀልም ይመለከታል፡፡ በፈረንጆቹ 2003 አማጺያን መሳሪያ ካነሱ በኋላ በዳርፉር ብቻ በተካሄደው ውጊያ 300ሺ ያህል ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሲጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡

በፊርማ ስነ ስርአቱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ፣የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት፣ የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣የቻድ ፕሬዚዳንቶች ፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎችም ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

በጣም አሳዛኝ ዜና ነው! 😭😭😭 ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ማረፋቸውን ዘ-ሐበሻ ከቤተሰብ አረጋግጧል::ነፍስ ይማር!!
30/09/2020

በጣም አሳዛኝ ዜና ነው!
😭😭😭

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ማረፋቸውን ዘ-ሐበሻ ከቤተሰብ አረጋግጧል::
ነፍስ ይማር!!

የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሽናፊ ውድድር 1ኛ በመውጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ና ዋንጫው ያሸነፈችው መቅደስ ግርማ አዳማ ከተማ ስትገባ በአዳማ ከተማ ከንቲባ ና በነዋሪዎች ትልቅ አቀባበል ተደረ...
28/09/2020

የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሽናፊ ውድድር

1ኛ በመውጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ና ዋንጫው ያሸነፈችው መቅደስ ግርማ አዳማ ከተማ ስትገባ በአዳማ ከተማ ከንቲባ ና በነዋሪዎች ትልቅ አቀባበል ተደረገላት::

ፎቶ ምንጭ :- OBN

ጉርሻዎች ነን
ከተምር ዛፍ ስር ቁጭ ብለን

የፋና ላምሮት የድምፃዊያን የአሸናፊዎች አሸናፊ * የ500 ሺህ ብር ና* የዋንጫ ተሸላሚመቅደስ ግርማ ሆናለች::እንኳን ደስ አለሽ🙏
27/09/2020

የፋና ላምሮት የድምፃዊያን የአሸናፊዎች አሸናፊ

* የ500 ሺህ ብር ና
* የዋንጫ ተሸላሚ

መቅደስ ግርማ ሆናለች::

እንኳን ደስ አለሽ🙏

አንጋፋዋ አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ ህይወቷ ያለፈው አርቲስቷ የመረጃውን ትክክለኝነት ለማጣራት FastMereja የአርቲስቶች ወዳጅ...
25/09/2020

አንጋፋዋ አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ ህይወቷ ያለፈው አርቲስቷ የመረጃውን ትክክለኝነት ለማጣራት FastMereja የአርቲስቶች ወዳጅ ወደ ሆነው አቻሬ ደውለን ነበር መረጃው ትክክል ነው ስርዓተ ቀብሯም ነገ በቅድስት ስላሴ ካቴድርያል የሚፈፀም ይሆናል ብሎናል። ለወዳጅ ዘመዶቿ አድናቂዎቿ መፅናናትን እንመኛለን።
ነብስ ይማር🙏
via fast mereja

አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ህመም አጋጥሞት በህክምና ላይ ይገኛል!የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት 2 ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲ...
23/09/2020

አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ህመም አጋጥሞት በህክምና ላይ ይገኛል!

የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት 2 ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

አርቲስት አሊ ቢራ ስላለበት ሁኔታ ለBBC ተከታዩን ብሏል ፦

"በፊት ላይ በጣም አሞኝ ነበር። አሁን ግን ተሽሎኛል። አሁን ያለሁበት ሆስፒታል ጥሩ ክትትል እያደረጉልኝ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን እየተሻለኝ ነው።

አንዳንድ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስለ እኔ ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት ሰዎችን እያስደነገጡ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሰዎች የመረጃዎችን እውነትነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።"

አርቲስት አሊ ቢራ አሁኑ የውስጥ ደዌ ህክምና እየተደረገለት ሲሆን ከዚህ ቀደምም የልብ እና የስኳር በሽታዎች ታማሚ መሆኑን ተናግሯል።



ፈጣሪ ይማርህ🙏🙏

👉ለመኖር ብቸኛው አማራጭ፣ ሌላው እንዲኖር መፍቀድ ነውማህተመ ጋንዲ
20/09/2020

👉ለመኖር ብቸኛው አማራጭ፣ ሌላው እንዲኖር መፍቀድ ነው
ማህተመ ጋንዲ

Manyazewal Mane Big Respect🙏
20/09/2020

Manyazewal Mane Big Respect🙏

አይለያቹ😍😍
19/09/2020

አይለያቹ😍😍

👉ሎዛ አበራ ነገ ትሞሸራለችበኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ስኬታማዋ ሴት እግር ኳስ ተጨዋች የሆነችው ሎዛ አበራ ነገ መስከረም 10 ቀን ትሞሸራለች።እኛም የሀገራችን ኩራት ለሆነችዋ ጀግኒ...
19/09/2020

👉ሎዛ አበራ ነገ ትሞሸራለች
በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ስኬታማዋ ሴት እግር ኳስ ተጨዋች የሆነችው ሎዛ አበራ ነገ መስከረም 10 ቀን ትሞሸራለች።
እኛም የሀገራችን ኩራት ለሆነችዋ ጀግኒት መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንላት እንመኛለን
እንኳን ደስ ያለሽ በሏት🙏

ነፍስ ይማር 😥ድምፃዊ ግርማ ተፈራ ካሳ ልጅ ኤፍራታ ግርማ በወሊድ ምክንያት ዛሬ ህልፈተ ህይወቷ ተሰምቷል። ኤፍራታ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘ ወጣት ነበረች። ኤፍራታ ግርማ ባለፈው ዓመ...
19/09/2020

ነፍስ ይማር 😥

ድምፃዊ ግርማ ተፈራ ካሳ ልጅ ኤፍራታ ግርማ በወሊድ ምክንያት ዛሬ ህልፈተ ህይወቷ ተሰምቷል።

ኤፍራታ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘ ወጣት ነበረች።
ኤፍራታ ግርማ ባለፈው ዓመት ከሴንት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት በዲግሪ የተመረቀች ነበረች።

ለቤተሰቦቿ እንዲሁም ለወዳጀቿ በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ።

ነፍስ ይማር!!

©️petros Ashenafi kebede

እናት በወሊድ ማጣት እጅግ መራር ሀዘን ነው 😥😥😥

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ክስተት/Adis Kstet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share