Ethiopian Capital Media

  • Home
  • Ethiopian Capital Media

Ethiopian Capital Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Capital Media, Media/News Company, .

08/01/2024
17/05/2023

መሳቅ እወዳለሁ ነገር ግን ቁምነገር አልዘነጋም! የህይወታችን ዋና ነገር ምንድን ነው? እርሱን አትርሱ! ዋጋም ክፈሉ! የተሻለ ቦታ ዛሬ ሳይሆን ነገ ትደርሳላችሁና።

#እየሠሩ መሳቅ

09/03/2023

በተመደበችበት ሁሉ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የምትታወቀው ከደቡብ ኢትዮጵያ የተገኘች የቀድሞ ጤና ሚንስቴር ደኤታ እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚንስቴር ወ/ሮ አለምፀሃይ ጳውሎስ!
የበቁ ሴቶች የማህበረሰቡ ምሰሶች ናቸው!

25/02/2023

ለወንድም ቦረና ህዝብ የተገኘውን አዋጥተናል! ህዝብህ ህዝበ ነው! ከዚህ ችግር እንድትወጣ በፀሎትም አግዛሃለሁ!

13/02/2023

ከነገ ጀምሮ የሲዳማ ክልል ፕረዚዳንት የክልሉ የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ያደርገኛል በሚል ከአለታ ወንዶ ከተማ ለመልስ ጥር የተገኘው ስሆን ከመገንጠያ ጀምሮ የመንገዱ መበላሸት ሀላፊነትን በገዛ ፍቃደ እንዳልቀበለው አድርጎኛል። ማነህ አላታን ነፃ አወጣለሁ ያልከኝ! እስቲ ሌላው ቢቀር እዛው እያለ የዱሮውን አስፓልት ወደ ነበረበት ቦታ መልስልኝ።

ዳግማዊትም የሲዳማውን መንገድ ሳትጀምር በአውሮፕላን ሀዋሳን እንደተመላለሰች በጥቁር ካርድ ተሸኝታለች መሠለኝ! ኤረ የመንገድ ልማት ያለህ?

በጣም የገረመኝ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት መብት የቆመ ቢሮ ይሄንን ግፍ እየሰማ ዝምታ መምረጡ ነው። በጣም የደነቀኝ የክልሉ ጤና ቢሮ ጉዳዩን እየሰማ እስካሁን ትንፍሽ አለማለቱ ነው!በጣም የ...
17/12/2022

በጣም የገረመኝ

ለሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት መብት የቆመ ቢሮ ይሄንን ግፍ እየሰማ ዝምታ መምረጡ ነው።

በጣም የደነቀኝ የክልሉ ጤና ቢሮ ጉዳዩን እየሰማ እስካሁን ትንፍሽ አለማለቱ ነው!

በጣም የደነቀኝ የፍትህ ተቋማት ቁንጮ ፖሊስ ኮሚሽንና ፀቃቤ ሕግ ምንም እንዳልተፈጠረ መሆኑ ነው!

እጅግ አንጀቴን የበላይ ሞቿ ይሄኔ "Killile'ya!" እያለች Yakka ከወጡ ሴቶች አንዱ መሆኑዋን ሳስብ ነው!!

በሴት የተወለዳችሁ በሙሉ ይህች ነፍስ ፍትህ ያስፈልጋታልና ሰለ እናት፣ እህትና ሴት ልጃችሁ ስትሉ ለፍትህ ቁሙ!!

እናንተ ባትቆሙም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሰማይ ይቆማል። ይህንን አምናለሁ!!

21/11/2022
26/11/2021

ሰበር ዜና‼️
***************************************************************
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማዶረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው። በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባርም ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሦ ላይ ነው።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

 ኢትዮጵያ 🇪🇹  " ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ " ለሚለው መርህ ባላት እምነት እና ቁርጠኝነት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለሚያደርገው ጥረት አክብሮት እንዳላት በጠ...
14/11/2021



ኢትዮጵያ 🇪🇹 " ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ " ለሚለው መርህ ባላት እምነት እና ቁርጠኝነት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለሚያደርገው ጥረት አክብሮት እንዳላት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ፡፡

ቢልለኔ ይህን ያሉቱ ከCGTN አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ተገኝተው ሰላምን ስለማምጣት የተወያዩት የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን አባሳንጆ በአፍሪካ ህብረት የተወከሉ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ችግሮችን ለመፍታት ስላለው ውሳኔ ኢትዮጵያ አክብሮት እንዳላት ገልፀው፤ ኦባሳንጆ በትልቅነታቸው፣ በአገር መሪነታቸውና የተለያዩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት ትክክለኛ ውክልናና ጥረታቸውም እንደሚሳክ እናምናለን ብለዋል፡፡

Credit :

የሲዳማ ልማት ማህበር የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ የመጨረሻው ትውልድ የትግል መሪዎች/ኤጄቶች እና ሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች ውስጥ በትግሉ ሂደት የተሰዉ ጀግኖችን ለመዘከር   ሙሉ የትምህርት ወጪ ሸ...
14/11/2021

የሲዳማ ልማት ማህበር የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ የመጨረሻው ትውልድ የትግል መሪዎች/ኤጄቶች እና ሰብዐዊ መብት ተሟጋቾች ውስጥ በትግሉ ሂደት የተሰዉ ጀግኖችን ለመዘከር ሙሉ የትምህርት ወጪ ሸፍኖ እስከመጨረሻው ለማስተማር ወስኗል።
****************************

በዚህም መሠረት የክልልነት ትግል ፊታውራሪ የነበሩና በትግሉ ሂደት ህይወታቸውን ያጡ ወንድሞቻችን #ፈቃዱ፣ ግርማ፣ እንዲሁም #ቡኢ/ተመስገን_ካዊሶ፣ ልጆችን እንዲሁም ታናሽ እህት ቤተሰብ በመረጠላቸው በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ በየትኛውም ትምህርት ቤት የትምህርትና ተጓዳኝ ወጪዎች ትምህርታቸውን እስከሚጨርሱ ድረስ ለመሸፈን የተቋሙ ማኔጅመንት ወስኗል።

በዛሬው ዕለት ድጋፉን አስመልክቶ በተደረገ ፕሮግራም ላይ ማረጋገጫ ደብዳቤ ርክክብ የተደረገ ሲሆን በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት 130 ዓመታት ለሲዳማ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ትግል የተሰዉ፣ የታሰሩ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የተሰደዱና የተጎሳቆሉ ወገኖቻችንን ሁሉም እንዲደግፍ መነሻ ለመሆን ሲሆን ከዚህም ባሻገር ትውልድ ባለውለታውን እንዳይረሳ የማድረግ ኃላፊነታችንን በመወጣት ለህዝብ ውግንና ያለው ታሪክ የሚሰራ ትውልድ እንዲፈጠር ለማበረታታት ታስቦ የተደረገ ነው።

ህዳር 3/2014 ዓ.ም
ሀዋሳ፤ ሲዳማ፤ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

17/10/2021

Sidaamu Ejjeetto miilla haameelote giddo goxxe huuccidhanno buxicho kayisse mine minte uyitino.
***************
Booni gaangaawi woradira Bashiiro gutte Ollii teessaancho Selaami Kia yinanni 12 diri qaaqqo qawaallanku quchumira haaameelote giddo goxxe huuccidhannota kaa'lo assite kayisssinota Ejjeetto sokka iillishshinonke.

Gobbate gobbaanni heedhanno Sidaamu qansoota, Shooshaqa wodana afidhino Sidaamu dureeyyanna babbaxxitino dagate bissawiinni womaashsha gamba assite qaaqqote qaera qorqorrote mine minte maasiisse aansa sokkinonke mashalaqqe leellishshanno.

Qaaqqo anna anje shiidhinota ikkasenni isenna lamala roduuwase kaa'lannohu nookki daafira shoole gereewo, diphanonna uduunne hattona sagale shiqishansa xawisse aanteteno saada hirte uyitannota kultinonke.

Qaaqqo Selaamawiti roso hanaffanno gede wo'ma rosu uduunne ejjeetto shiqishinoha ikkanna baankete widoonni aganunni lame kume birra maatete irko assitannotano ledde dhaantinonke, maatete hasiissanno irko assitanno gede Booni woradi gashshootiranna olluu geerrira eeggo aansano ledde xawissinonke.

Maaleda Miidiya.

30/08/2021

በአንድ ሀገር እሄ ሁሉ ልዩነት መኖሩ ነገሮችን ከባድ እያደረገው ነው።

በ2014 ለቅዱስ ፓውሎስ የተመደበው በጀት 894,000,00 ሚልዮን ነው

ለሀዋሳ ዩንቨርስቲ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመደበው በጀት (215,000,000 ለሆስፒታልና 215,000,000ለኮሌጁ ሳይድ(በአጠቃላይ 430,000,000 ብር)

ልዩነቱ ((894,000,000-430,000,000= 564,000,000))

በአንድ ሀገር ይህ ሁሉ ልዩነት እየተፈጠረ ባለበት ሁኔታ በጊዜው የትርፍ ክፍያ አልተከፈለንም ማለት አግባብ አይደለም።

13/08/2021
02/08/2021

ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
~~~~~~~~~~~~~~
በዶ/ር ምህረት ደበበ

1. ይሰለቹሃል

አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው

የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም

"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል

አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው

ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ

ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ

ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን

ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።

9. ያለስስት አድንቅ

ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ

ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ

ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት

ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም

ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ

ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ

ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ

ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ

ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት

በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት

በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ

የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ

የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

12/07/2021

ሰበር ዜና
*****
አዲሱ የሲዳማ ክልል 200 የክልሉ ልዩ ሃይል ፖሊሶችን ወደ ወልቃይትና ራያ ሊልክ መሆኑ ታወቀ ። ውሳኔው ህዝቡን አስቆጥቷል።
**********
የሲዳማ ክልል ካድሬዎች 200 የልዩ ሃይል ፖሊሶች ከአማራ ክልል ጎን ተሰልፈው እንዲዋጉ ወደ ወልቃይትና ራያ ሊልክ እየተሰናዳ መሆኑን የማለዳ የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል። ፖሊሶቹ በቀጣይ ሶስት ቀናት እንዲንቀሳቀሱ እቅድ ተይዟል።

በተያያዘ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች እያንዳንዱ ቀበሌ 10 ሚሊሻዎችን እንዲያቀርብ ታዘዋል።

በጦርነቱ አንሳተፍም የሚሉ የልዩ ሃይልም ሆነ የሚሊሻ ሃይል አባላት "ግዳጅ እንደሆነ" እየተነገራችው መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

(በተጨማሪም አንድ አንድ ተርታ የልዩ ፖሊስ አባላት የህዳሴን ግድብ የሚጠብቀው ሃይል ስለተንቀሳቀሰ የምትሄዱት ግድቡን ለመጠበቅ ነው ተብሎ ቢገለፅላቸውም ነገሩ እንዳላሳመናቸው ለማለዳ ሚዲያ ተናግረዋል።)

ለአማራ ክልል ጦርነት ሲዳማ ፣ ኦሮሞ እና ሌሎች ሄደው የሚሞቱበት ጉዳይ ህዝቡ ዘንድ ተቃውሞ እያስነሳ መሆኑ ታውቋል።

ቀደም ሲል "የሰሜን እዝ ተጠቃ" በሚል ህዝብን ያንቀሳቀሰው የፖለቲካ ቡድን ያ የህዳር ወሩ ትርክት አሁን ውጤት የማያስገኝ በመሆኑ "ወልቃይት ለሃገሪቱ ቁልፍ ስትራቴጂክ መሬት ነው" በማለት ጦርነቱን የመላው ኢትዮጵያውያን ለማድረግ እየተሞከረ ነው።

ወልቃይት ለኢትዮዽያ ስትራቴጂክ መሬት ቢሆን እንኳን የትግራይም ሆነ የአማራ ክልል የኢትዮጵያ አካል እንደመሆኑ መሬቱ በየትኛቸውም ክልል ስር ቢተዳደር ለሌላው ክልል ነዋሪዎች ለውጥ አያመጣም የሚሉ በርካቶች ናችው።

ይልቁኑ የወልቃይት እና ራያ መሬቶች በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ክርክር ሲደረግበት የከረመ እንደመሆኑ ጉዳዩ በዋናነት የሁለቱ ክልሎች ነው።

ሌሎች ክልሎች ለአንዱ ክልል ወግነው ፖሊሶቻቸውን ማዋደቅ ታሪክ ማበላሸትና ሃገር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን የፖሊስና ሚሊሻዎቻቸው ህይወት በከንቱ እንዲጠፋና ቤተሰቦቻቸውም ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው።

በመሆኑም የሲዳማ እና የኦሮሚያ ክልል ህዝቦች ልጆቻቸው በካድሬዎች ተሸጠው በማይመለከታቸው ጦርነቶች እንዳይሳተፉ ማድረግ እንዳለባቸው አስተያይት ሰጪዎቻችን ጨምረው ያስረዳሉ።

ማለዳ ሚዲያ

08/07/2021

ሃዋሳ —

የኢትዮጵያ ዐሥረኛው ክልል ሆኖ ከተደራጀ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ሲዳማ ክልል ፖለቲካዊ ትያቄው ቢመለስም ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ችግሮቹ መፍትኄ እንዳልተሰጠው አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የሲዳማ ሕዝብ ለክልል አደረጃጀት የታገለው በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ውስጥ ንቁ እና ብቁ ተሳታፊ ለመሆንና በራሱ የራሱን ልማት ለማፋጠን በማለም መሆኑን የገለጹት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፤ የፖለቲካውን ጥያቄ ብናረጋግጥም የሕዝቡን የዕድገት ፍላጎት ገና አልመለስንም ብለዋል።

የሲዳማ ሕዝብ በክልል የተጀራጀበትን አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል እያከበረ ይገኛል።

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ሲዳማ ክልል በምጣኔ ሃብትና ማኅበራዊ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹና የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናገሩ

20/06/2021
31/05/2021
27/05/2021

የትላንቱ ገድል ይቀመጥ ዛሬ ግን ሀዋሳ ዩንቨርሲቲን በብቃት እየመራ እንደሆነ እኔ ምስክር ነኝ። እርሱ ስብሰባ መራ ማለት መምህሩም ይሁን አስተዳደር ሠራተኛው ጤና ባለሙያውም ሁሉም ዝም ፀጥ ብሎ ማዳመጥ ብቻ ነው። የአመራር ጥበብ ሄዶ ያረፈበት ይመስላል።ልምዱም ትምህርት ዝግጅቱም የጠቀመው ይመስላል የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ ባራሶ(PhD)። ሲዳማን የሚያሻግር ለኢትዮጵያም የሚጠቅም በጎሰኞች ሠፈር የማይገኝ በሲዳማ አንድነት የሚያምን ነው።

ለህዝባችን የሚጠቅሙ ግዙፍ #የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን በመሥራት ዩንቨርስቲውን በአለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ሥራ በመሥራት በኢትዮጵያ ምድር ይደምቃል የሚል እምነት አለኝ።

Long Live my President!!!

21/05/2021

አንድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ምዕራፊ አልፎ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ስሸጋገር ትልቁ ማነቆ የሚሆነው ፕሮግራሙን የሚያስፈፅሙ አካላት ናቸው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ, ብዙ ሃገራት ውጤታማ የሆኑበት የግብርና የውሃ ማቆር ፕሮግራም ወባ ማሰራጫ የሆነበት ጉዳይ አተገባበሩ ትልቅ ችግር ስለነበረበት ነበር። የብልፅግና ፕሮግራምም ከታች ካለው መመዘኛ አንፃር ሀገራችን የሁሉም ሀይማኖት መሆኗን ግልፅ አድርጎ ያሳየ ሲሆን ሌሎች ፓርቲዎች ግን በግልፅ ስድብ በሚመስል መልኩ እጮቻቸውን ከአንድ እምነት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት ሀገርቷን የሚወክል ፓርቲ የቱ ነው የሚለው ታውቆአል። ነገር ግን በሁሉም ክልሎች በፕሮግራሙ አስፈጻሚ አካላት ላይ ያለኝ አመኔታ ትንሽ ነው። እዚህ ላይ ከበሬታ ሀገራችን ያለምንም ጥርጥር ትበለፅጋለች።

Cup of Excellency
21/05/2021

Cup of Excellency

አንድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ምዕራፊ አልፎ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ስሸጋገር ትልቁ ማነቆ የሚሆነው ፕሮግራሙን የሚያስፈፅሙ አካላት ናቸው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሃገራት ውጤታማ የሆኑበት ...
21/05/2021

አንድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ምዕራፊ አልፎ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ስሸጋገር ትልቁ ማነቆ የሚሆነው ፕሮግራሙን የሚያስፈፅሙ አካላት ናቸው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሃገራት ውጤታማ የሆኑበት የግብርና የውሃ ማቆር ፕሮግራም ወባ ማሰራጫ የሆነበት ጉዳይ አተገባበሩ ትልቅ ችግር ስለነበረበት ነበር። የብልፅግና ፕሮግራምም ከታች ካለው መመዘኛ አንፃር ሀገራችን የሁሉም ሀይማኖት መሆኗን ግልፅ አድርጎ ያሳየ ሲሆን ሌሎች ፓርቲዎች ግን በግልፅ ስድብ በሚመስል መልኩ እጮቻቸውን ከአንድ እምነት አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት ሀገርቷን የሚወክል ፓርቲ የቱ ነው የሚለው ታውቆአል። ነገር ግን በሁሉም ክልሎች በፕሮግራሙ አስፈጻሚ አካላት ላይ ያለኝ አመሁኔታ ትንሽ ነው። እዚህ ላይ ከበሬታ ሀገራችን ያለምንም ጥርጥር ትበለፅጋለች።

Source" ሬዳት ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Capital Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share