26/09/2023
የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
=== ====== ===== ======
መስከረም፦14 ቀን 2016 ዓ.ም
የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያሄጅ አቶ ተስፋዬ አህመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ስራ አስኪያሄጁ በመልዕክታቸው እንደገለፁት የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓት እንዲሁም በጉራጌው ማህበረሰብ ዘንድ ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ በተጨማሪ በታላቅ ባህላዊ ስነ ስርዓት የሚከበር በዓል እንደመሆኑ እንግዶች ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ወደ ከተማዋ ይመጣሉ።
የከተማው ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር የእርድ ተረፈ ምርቶችን የከተማው ፅዳትና ውበት እንዳይበክሉ በተገቢው እንዲያስወግድ እና በከተማዋ ላይ ቆሻሻ ለሚያስወግዱ መኪኖች ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን በመለየት ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አስታውቋል።
የመስቀል በዓል ሁሉም የሐይማኖቱ ተከታዮች በደስታና በፍቅር የሚያከብሩት በዓል እንደመሆኑ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ ያለውን ለሌለው በማካፈል ከዚህ ቀደም የምንታወቅበት ውብ እሴታችን ልናስቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!!
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት