Alexsabi Promotion & Production

  • Home
  • Alexsabi Promotion & Production

Alexsabi Promotion & Production Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alexsabi Promotion & Production, Media, .

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ===   ======   =====  ======መስከረም፦14 ቀን 2016 ዓ.ምየቡታጅራ ...
26/09/2023

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
=== ====== ===== ======
መስከረም፦14 ቀን 2016 ዓ.ም

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያሄጅ አቶ ተስፋዬ አህመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስራ አስኪያሄጁ በመልዕክታቸው እንደገለፁት የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓት እንዲሁም በጉራጌው ማህበረሰብ ዘንድ ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ በተጨማሪ በታላቅ ባህላዊ ስነ ስርዓት የሚከበር በዓል እንደመሆኑ እንግዶች ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ወደ ከተማዋ ይመጣሉ።

የከተማው ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር የእርድ ተረፈ ምርቶችን የከተማው ፅዳትና ውበት እንዳይበክሉ በተገቢው እንዲያስወግድ እና በከተማዋ ላይ ቆሻሻ ለሚያስወግዱ መኪኖች ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን በመለየት ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አስታውቋል።

የመስቀል በዓል ሁሉም የሐይማኖቱ ተከታዮች በደስታና በፍቅር የሚያከብሩት በዓል እንደመሆኑ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ ያለውን ለሌለው በማካፈል ከዚህ ቀደም የምንታወቅበት ውብ እሴታችን ልናስቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።

በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!!
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት

15/09/2023

#ሴራና አዲስ ፊልም ሙሉ በሙሉ በቡታጅራና አካባቢው የተሰራ #ቅዳሜ መስከረም 05/2016ዓ.ም ይመረቃል🎥

 #ሴራና አዲስ ፊልም መስከረም 05/017/2016ዓ.ምከቀኑ 10:30 ጀምሮ በልዩና ታላቅ ድምቀት ይመረቃል።Like & share
13/09/2023

#ሴራና አዲስ ፊልም መስከረም 05/017/2016ዓ.ም
ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በልዩና ታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
Like & share

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ እና ኢንዱስትሪ ክላስተር ማዕከል በሆነችው ቡተታጀራ ከተማ የክልል ቢሮ በይፋ ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡ የከተማና ኢንዱስተሪ ክላስተር  ቢሮዎች ...
10/09/2023

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ እና ኢንዱስትሪ ክላስተር ማዕከል በሆነችው ቡተታጀራ ከተማ የክልል ቢሮ በይፋ ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡

የከተማና ኢንዱስተሪ ክላስተር ቢሮዎች መቀመጫ በሆነችው ቡታጅራ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ስረውን በይፋ ጀምሯል ፡፡

የቡታጅራ ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወረዳ የህብረተሰብ ክፍሎች እንግዶችን በደማቅ ሁኔታ ተቀብለዋል

 #ወንድሜ ናትናኤል ገ/ማርያም ማክስኞ 30, 2015 ከ 67,000 በላይ አባላት ባሉት የ hope for all የቴሌግራም መማማሪያ ፕላት ፎርም ላይ የህይወት ልምዴን እንዳካፍል ጋብዞኛል መ...
04/09/2023

#ወንድሜ ናትናኤል ገ/ማርያም ማክስኞ 30, 2015 ከ 67,000 በላይ አባላት ባሉት የ hope for all የቴሌግራም መማማሪያ ፕላት ፎርም ላይ የህይወት ልምዴን እንዳካፍል ጋብዞኛል መታደም ለምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉ
Nati Nat:
https://t.me/HopeforaAll2021?videochat=e30373c1ac56abe58f

 #በዘመን ጅረት ውስጥ ከፍ ከፍ እንዳለ በስኬት መንገድ ላይ ብሩህ ተስፋ አለ!!!!🙏🙏🙏  የአዲስ አመት ፕሮሞሽን ስራ በብሩ ተስፋ ፈርኒቸር ሀላባ ጀምረነዋል ብሩህ ተስፋ ፈርኒቸር 👌👌👌
03/09/2023

#በዘመን ጅረት ውስጥ ከፍ ከፍ እንዳለ በስኬት መንገድ ላይ ብሩህ ተስፋ አለ!!!!🙏🙏🙏
የአዲስ አመት ፕሮሞሽን ስራ በብሩ ተስፋ ፈርኒቸር ሀላባ ጀምረነዋል ብሩህ ተስፋ ፈርኒቸር 👌👌👌

  ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ መርሃ ግብር በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናዋቸዉ ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎዎች አስመረቀ !!!የቡታጅራ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ዲን የተከበሩ "አቶ አብዱልዋሂድ መሀመድ...
03/09/2023

ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ መርሃ ግብር በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናዋቸዉ ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎዎች አስመረቀ !!!

የቡታጅራ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ዲን የተከበሩ "አቶ አብዱልዋሂድ መሀመድ በዛሬው እለት ኮሌጁ አሰልጥኖ ሲያስመርቅ ለ17 ኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬም በ9 የትምህረት መስኮች 634 ሰልጣኞች በወንድና በሤት ማስመረቁን ተናግረዋል::

ኮሌጁ ባለፉት25 ዓመታት ከ30 ሺ በላይ ሰልጣኞቾ አስመርቆ በሀገር ውስጥና በውጪ አገራት በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው እንደሚገኙ ተናግረዋል::

የዛሬ ተመራቂዎቹ ተማሪዊዎች እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በምዘና የተረጋገጠ መሆኑን ገልፀው ስራ መፍጠር እንዲችሉ ክህሎትንና እውቀትን አሰላስለው የራሳቸውን የስራ ህይወት መጀመር የሚችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በምረቃ ስነስርአቱ "የክልል የዞን "የወረዳና የከተማ አመራሮች "የሃይማኖት አባቶች "የከተማው ሙሁራኖች "የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሠቦች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች እና "የማረቆ ልዩ ወረዳ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።

►የሰራ ሰው በሰራው ልክ ምስጋና እና ክብር ሲልም እውቅና መስጠቱ ለቀጣይ ትልቅ ተግባሮች እንዲዘጋጅና የተሻለ ነገር እንዲሰራ ያበረታታል "የበታጅራ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና የስራ ሀላፊዎች በሙሉ በርቱ🙏 "የተመረቃቹም ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ።

 #የባቦ የተኝቢ አህመድ ጀማል (መስቆ ሄላላየ)
02/09/2023

#የባቦ የተኝቢ አህመድ ጀማል (መስቆ ሄላላየ)

Ethiopian Music : Ahmed Jemal | አህመድ ጀማል - Yebabo Yetegnibi | የባቦ የተኝቢ - New Ethiopian Music 2023 (Official Video)Subscribe: http://goo.gl/vdthqbFacebook : h...

 #አዳብናየአዲስ አመት የባህል ገፀ በረከት ልዩ ስጦታ #ዘውዴ ተካልኝ አሪፍ የባህል ስራ የ2016ዓ.ም  #የመስቀል በዓል ማድመቂያ ይመልከቱት ይወዱታል
27/08/2023

#አዳብና
የአዲስ አመት የባህል ገፀ በረከት ልዩ ስጦታ
#ዘውዴ ተካልኝ አሪፍ የባህል ስራ የ2016ዓ.ም
#የመስቀል በዓል ማድመቂያ ይመልከቱት ይወዱታል

Ethiopian Music : Zewde Tekalign | ዘውዴ ተካልኝ - Adabena | አዳብና - New Ethiopian Guragigna Music 2023 (Official Video)Subscribe: http://goo.gl/vdthqbFacebook : h...

 #ፕሮሞተር አለማየሁ ወሰን (አሌክስ ሳቢ)ፔጃችንን   በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
22/08/2023

#ፕሮሞተር አለማየሁ ወሰን (አሌክስ ሳቢ)
ፔጃችንን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣትእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያ...
21/07/2023

ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ተሰጣት

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት ነው ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት የሰጠው፡፡

የክብር ዶክትሬቱን በወላጅ እናቷ በወ/ሮ ተናኜ አማካኝነት ተቀብላለች።

"አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ" ወይዘሮ እህተ በቀለ*****************ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራ...
20/07/2023

"አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ"
ወይዘሮ እህተ በቀለ
*****************

ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያስችል ጉዳት አለባት። ይህ ግን ለዮርዳኖስም ለእናቷም የዛሬ ስኬት እንቅፋት አልሆነባቸውም።

ዮርዳኖስ በእናቷ ድጋፍ ዛሬ ትምህርቷን አጠናቃ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል በማዕረግ ተመርቃለች፡፡

"አራት ዓመት ሙሉ ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ አጠናቅቄያለሁ። አራት ዓመት ለእኔ እንደ አራት ቀን ነው:: ምንም አልተሰማኝም ደስ ብሎኝ አልፏል" ብለዋል፤ እናት፡፡

በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዋ የሚሰጣትን ትምህርት ክፍል ውስጥ አብረዋት ቁጭ ብለው እየጻፉላት እንዳስተማሯት እናት ለኢፕድ ተናግረዋል።

"ዮርዳኖስ የማንበብ ችሎታዋን እወድላታለሁ። ያነበበችውን አለመርሳቷንና አስተዋይነቷን እወድላታለሁ፤ ልጄ ትጉህ ናት" ብለዋል፡፡

ዮርዳኖስ እስከ 12ኛ ክፍል በሞግዚት ድጋፍ የተማረች መሆኑን ጠቅሰው እንደምትችል መታየት አለበት ብዬ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ አብሬያት ዘልቀናል ብለዋል፡፡

አትችልም የተባለች ልጅ ለዚህ በመብቃቷ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቅሰው፤ የእርስዋ ብርታት እንደ ልጃቸው ቤት ለተዘጋባቸው ልጆች አርአያ የሚሆን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

መኖሪያ ቤታቸው ከዮኒቨርሲቲው ራቅ ያለ በመሆኑ ጠዋት 12 ሰዓት ተነስተው ለአራት ዓመታት ልጃቸውን ወደ ትምህር ገበታዋ በዊልቸር በማመላለስ ለምረቃ ያበቁት እናት ዛሬ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ተመልክተናል።

በማርቆስ በላይ
ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://t.me/ethiotimesmedia

"ግራ ቀኝ"ን አለማድነቅ ፈጽሞውኑ አይቻልምዳይሬክተሩ ድርብ ድል አሰፋ በትልቅ ስራ ተገልጧል። ከዚህ በኋላ በትኩረት ከምንከተላቸው እንደ አብርሐም ገዛኸኝ ካሉ ድንቅ አዘጋጆች ተርታ የሚሰለፍ...
06/07/2023

"ግራ ቀኝ"ን አለማድነቅ ፈጽሞውኑ አይቻልም

ዳይሬክተሩ ድርብ ድል አሰፋ በትልቅ ስራ ተገልጧል። ከዚህ በኋላ በትኩረት ከምንከተላቸው እንደ አብርሐም ገዛኸኝ ካሉ ድንቅ አዘጋጆች ተርታ የሚሰለፍ ዳይሬክተር መኾኑን በዚህ ስራ አስመስክሯል።

ድርብ ድል ድንቅ መጣኝ ነው። ተመልካችን አደብ አስይዞ ሸንጎ ውስጥ ጎልቶ የሚያውል አደንጋዥ ነገር ነው። ሁሉንም የስራ ዘርፎች በአግባቡ ተቆጣጥሮ መርቷል። መብራት፣ ቀረጻ ሜካፕ ምናምን እያልኩ አላደክማችሁም። ሁሉም የተዋጣለት ብቻ ሳይሆን ምጣኔውንም የጠበቀ ነው። እንደዚህ መጥኖ ለመስራት ብስለት ይጠይቃል።

ስለ ሚካኤል ታምሬ የትወና ከፍታ ምን ማለት ይቻላል? እናንተው ጨምሩበት። አበበ ባልቻንም ቢሆን በተለየ ገጸ ባሕሪ አየሁት። ለተራ ወሬ ያለው ስሜት ተደጋጋሚ ሳቅ አጭሮብኛል። ግሩሜ ሁሌም ግሩም ነው። እስከ አሁን በታዩት 3 ክፍሎች ላይ መጥተው የሄዱት ፍርደኛ ገጸ ባሕሪዎችን የተጫወቱ በሙሉ አስደናቂዎች ናቸው። ቀጣዮቹን ተዋናዮችም (የጠፉብን አቅም ያላቸውን ሁላ እንደምናይ ተስፋ በማድረግ) በጉጉት እንጠብቃለን።

በአዲስ አድማስ ጋዜጣ "ፖለቲካን በፈገግታ" በሚለው ታዋቂ አምድ ጸሐፊነቱ የሚታወቀው እያሱ አለማየሁ (በብዕር ስሙ ሃማ ቱማ) ድርሰት የሆነውን እና "Case of the Socialist Witchdoctor... " የተሰኘውን "የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ እና ሌሎችም" በሚል ርዕስ በሕይወት ታደሰ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ነበር። አሁን ደግሞ በድርብ ድል "ግራ ቀኝ" ተብሎ በተንቀሳቃሽ ምስል ለ3ኛ ግዜ ተወልዷል። ድንቅ ነው!

ሒዊ ታዴ ቃሏን ልዋሳትና ለETV Artistic ተሐድሶ ያዝልቅለት ያዝልቅልን ብዬ ልቋጨው።

ሚኪ ታምሬ ግን.... ፓ!

#ግራቀኝ

የትወና አናብስቱ በተለየ ጥምረት ሊከሰቱ ነው።ግሩም ኤርሚያስ ለሲኒማ ትወና እንደታመነ ጸንቶ ቆይቷል። ባላመነበት ስራ የማይሳተፍ ድንቅ የሲኒማ ተዋናይ ነው። አማኑኤል ሐብታሙ ደግሞ እሱ ከገ...
06/07/2023

የትወና አናብስቱ በተለየ ጥምረት ሊከሰቱ ነው።

ግሩም ኤርሚያስ ለሲኒማ ትወና እንደታመነ ጸንቶ ቆይቷል። ባላመነበት ስራ የማይሳተፍ ድንቅ የሲኒማ ተዋናይ ነው። አማኑኤል ሐብታሙ ደግሞ እሱ ከገባበት የማይቃና ስራ የለም። ሁለቱም የአገራችን ፊልም ትወና ጣዕሞች ሆነው የቆዩ ናቸው።

አሁን ደግሞ "አፊኒ" "AFFINI" በተባለ አዲስ ስራ ተጣምረዋል።

የሲዳማ ውብ መልክዐ ምድር ደግሞ የጥምረቱ ልዩ አጋጣሚ እንደሚሆን አልጠራጠርም።

የሲኒማ ባሕል መልሶ እንዲያንሰራራ ለሚሹ ሁሉ ይህ ድንቅ አጋጣሚ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ፖስተሮቹን እንዴት አገኛችኋቸው?

ይቅናችሁ!

04/07/2023

#የለሽም

🎯 ዘውድ እና ጎፈር 2 ~ ፊልም🎯  ከሰኔ 30 ጀምሮ ተጠባቂው ሊመረቅ ነው ከፊታችን አርብ፣ ሰኔ 30 እና ሐምሌ 1፣2 ሐምሌ 7፣8፣9  በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃል ።🎯 ...
03/07/2023

🎯 ዘውድ እና ጎፈር 2 ~ ፊልም

🎯 ከሰኔ 30 ጀምሮ ተጠባቂው ሊመረቅ ነው

ከፊታችን አርብ፣ ሰኔ 30 እና
ሐምሌ 1፣2 ሐምሌ 7፣8፣9
በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃል ።

🎯 የኤልያና ፊልም ኘሮዳክሽን 11ኛ ፊልም

ሀናን ታሪቅ መስፍን
ሀ/የሱስ (ጠጆ)
ነፃነት አይተፍሱ
ፈለቀ ካሴ
መላኩ በላይ እና ሌሎችም የተጣመሩበት ምርጥ ፊልም

 #የነብስ አድን ጥሪ !!!"ኑርሀሰን ሰማን" ይባላል የተወለደው በመስቃን ወረዳ "ግድዬና አቦራት ቀበሌ ሲሆን "የቡታጅራ ከተማ ልጅ ነው፣ አገሩን እንዲሁም አካባቢውን በጣም ይወዳል "ሲበዛ ...
02/07/2023

#የነብስ አድን ጥሪ !!!

"ኑርሀሰን ሰማን" ይባላል የተወለደው በመስቃን ወረዳ "ግድዬና አቦራት ቀበሌ ሲሆን "የቡታጅራ ከተማ ልጅ ነው፣ አገሩን እንዲሁም አካባቢውን በጣም ይወዳል "ሲበዛ የዋህና ለተቸገሩ ሰዎች በአቅሙ የሚረዳ "እድሜውን ሙሉ ለሌሎች የኖረ መልካም ሰው ነው ።

እንደ ማንኛውም ኢትዮጲያዊ "ንሮን ለማሸነፍ እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት "ሳዑዲ ስደት ከሄደ በርካታ አመታት አስቆጥሯል፣ ታዲያ ወንድማችን "በድንገት ይታመምና እዛው ስደት በሚኖርበት ሳዑዲን ላይ ህክምና ያደርጋል፣ የህክምና ውጤቱ ግን እንደጠበቀው አልነበረም "ሀኪሞቹ ሁለቱም ኩላሊቶች ስራ እንዳቆሙ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት አሳውቀውታል ።

ወንድማችን "ኑርሀሰን ለአንድ ወር በሳዑዲ ጊዜያዊ ህክምና እየተከታተለ ቢቆይም ከቀናቶች ቡኋላ ወደ እናት አገሩ "ኢትዮጲያ ይገባል፣ ነገር ግን ሀኪሞቹ እንዳሉት ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውጭ አገር ተመልሶ የኩላሊት "ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት አስጠንቅቀውታል፣ ለህክምናው ወጪ አስከ 5.000.000 (አምስት ሚሊየን) ብር እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል፣ በስደት ላይ ሆኖ ያጠራቀመው እና በአገርቤት ያሉ ቤተሰቦቹም ያላቸውን ገዘብ ጨምሮ የተጠየቀውን ያህል ገንዘብ መድረስ ባለመቻሉ፣ "እናንተ ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን ለማስቸገር ተገደናል፣ ይህ አይነቱ አሰደንጋጭ ክስተት በእናንተ እና በቤተሰቦቻችሁ አይድረስ እያልን "እናንተ ደጋግ ኢትዮጲያውያን "ሁሉም የአቅሙን ከ1ብር ጀምሮ በመለገስ "ከፈጣሪ ጋር "የወንድማችን ሂወት አድኑልን ይሉናል ቤተሰቦቹ !!!

"ተጠይቆ የማያሳፍረው እንዲሁም የተቸገረን አይቶ የማያልፈው "ታሞ እርዳታ ለሚሻ በሙሉ ከፈጣሪ በታች ተጋግዞ በማሳከም የሚታወቀው "የቡታጅራ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ በሙሉ፣ እንደተለመደው ተባብረን "የወንድማችን ሂወት ከፈጣሪ ጋር እንታደገው ።

"ወንድማችን መርዳት እየፈለገ በገንዘብ ማጣት መርዳት ያቃተው ዱዓ/ፀሎት በማድረግ እንዲሁም ይህ መልዕክት ለሌሎች እንዲደርስ ሁላችንም ሼር/share በማድረግ እንተባበር !!!

የወንድማችን ኑረሀሰን ሰማን ንግድ ባንክ አካውንት ቁ. 1000423256951

ለበለጠ መረጃ 0916743720 Jafer Seman የታማሚው ወንድም

"መልካምነት መልሶ ይከፍላል"

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በእስፔን በተደረገዉ የ 10ሺህ ኪሎ ሜትር አገር አቋራጭ ዉድድር አንደኛ በመዉጣት አሸናፊ ሆነ!!!ሰሌ እንኳን ደስ አለህ።
08/01/2023

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በእስፔን በተደረገዉ የ 10ሺህ ኪሎ ሜትር አገር አቋራጭ ዉድድር አንደኛ በመዉጣት አሸናፊ ሆነ!!!ሰሌ እንኳን ደስ አለህ።

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።           ሉቃ 2:11እንኳን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረስዎት መልካም...
07/01/2023

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
ሉቃ 2:11
እንኳን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረስዎት መልካም በዓል!!

06/01/2023

መልካም በዓል

 #አርቲስት መስፍን ሲማ በአዲስ ስራ እየመጣ ነው ።  good luck 🙏
06/01/2023

#አርቲስት መስፍን ሲማ በአዲስ ስራ እየመጣ ነው ።
good luck 🙏

የአለም ጤና ድርጅት አማካሪ እና የአለም አቀፍ የስነ ተዋልዶ ጤና የስልጠና ማዕከል መስራች የሆኑት ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሐ ውልጊቾ የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጎ...
06/01/2023

የአለም ጤና ድርጅት አማካሪ እና የአለም አቀፍ የስነ ተዋልዶ ጤና የስልጠና ማዕከል መስራች የሆኑት ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሐ ውልጊቾ የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጎብኝት አደረጉ
"" """"" """"""" """"""" """""""

የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና አሰጣጡን ለማዘመንና ደረጃውንም ለማሳደግ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሐ ውልጊቾ ፣ ቤተሰቦቻቸው እና የስራ ባልደረቦቸቻቸው በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጥና የህክምና ግብዓት ሁኔታ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝት ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሮፌሰር ሰናይትና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው በሆሰ‍ፒታሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እየተመራ የሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ፣ የእናቶችና የጨቅላ ህፃናት ክፍል ፣ የኦፕራስዮን ክፍል ፣ ሁሉም የተኝቶ ህክምና ክፍሎች እንዲሁም የተመላላሽና ሌሎችም የህክምና ክፍሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ አቶ አብዱረህማን እንደግባይ ጨምሮ የሐይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሆስፒታሉ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኃላ በሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያሄጅ በአቶ አንዱዓለም መንግስቱ እና በተኝቶ ህክምና ዳይሬክተር ዶ/ር አብነት ውለታው አማካኝነት የሆስፒታሉ የውስጥ አሰራር ያለበት ደረጃና ያጋጠሙ ተግዳሮት አጠቃላይ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ስራ አስኪያሄጁ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል በርካታ የህክምና ግብዓት ጉድለት ፣ የክፍሎች ጥበትና በቂ የሰለጠና ባለሙያ ችግር እንዲሁም ካለው የረጅም ጊዜ አገልግሎት አሰጣጥ አንፃር ተገቢውን ትኩረት ያላገኘ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ሆኖም ይህን ችግር እያለበትም የተቋሙ ባለሙያዎችና ሰራተኞች በሚያደርጉት ከፍተኛ ጥረት በተለያዩ ጊዜያት በፌደራልና በክልል ደረጃ ሽልማቶችን ማግኘቱን አብራርተዋል።

ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሐ ሆስፒታሉን ደረጃ ለማሻሻልና ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ወቅት ተገኝተው ጉብኝት ማድረጋቸው እንዳስደሰታቸው በመግለፅ ሆስፒታሉ ላይ የሚታዩት ችግሮች በአጭር ጊዜ እንዲቀረፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ የቦርድ አባልና የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቀለ አየለ እንደገለፁት ከ20 ዓመታት በፊት ይህ ሆስፒታል ሲገነባ የአካባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ርብርብ በማድረግ እንደመገንባቱ ዛሬም የሆስፒታሉ ደረጃ ለማሳደግና የህክምና አሰጣጡን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሐና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው በሆስፒታሉ አማካኝነት የምስጋና እና የክብር ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አሰተዳደር የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

 #አስገራሚ ለውጥ ላይ  የሚገኘው  ቡኢ ከተማ!ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 104 ኪ.ሜ  ርቀት ላይ ይገኛል። ከተማው ከተቆረቆረ  ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ እና  ...
05/01/2023

#አስገራሚ ለውጥ ላይ የሚገኘው ቡኢ ከተማ!

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 104 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ከተማው ከተቆረቆረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ እና በንጉስ ኃይለ ሥላሴ ዘመን እንደሆነ ይነገራል። የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ የፖለቲካ እና የንግድ ማዕከል ሆኖ ለበርካታ ዘመን አገልግሏል፤አሁንም እያገለገለ ይገኛል ።

ቡኢ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ውስጥ በፈጣን ዕድገት ላይ የሚገኝ ከተማ ነው። ሥነ ምህዳራዊ መገኛው በ8°19'N ኬክሮስ (Latitude) እና በ33°33'E ኬንትሮስ (Longitude) ሲሆን ከባህር ወለል 2045 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ወይናደጋ የአየር ጠባይ አለው።

የአካባቢው ማህበረሰብ ዋነኛው መግባቢያ (የአፍ መፍቻ) ቋንቋ ክስታኒኛ ሲሆን በከተማው ውስጥ በስፋት አማርኛ ይነገራል።

ከተማው ከተቆረቆረ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ ቢሆንም ምንም ዓይነት ዕድገት ሳያሳይ ለበርካታ ዘመናት ቆይቷል። በ2010 ዓ.ም የከተማ አስተዳደርነት መዋቅር ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ፈጣን ዕድገት እያሳየ ይገኛል።

በከተማ አካባቢ የማህበረሰቡን ህይወት በማቅለል እና የንግድ ሥርዓቱን በማሳለጥ ለአንድ ከተማ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከሚጫወቱ መሠረተ ልማቶች ውስጥ ዋነኛዎቹ የውሃ፣የመንገድ እና የኢሌክትሪክ ሀይል መሠረተ ልማቶች ናቸው ።

የቡኢ ከተማ በኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት በኩል በከተማው ውስጥ የሚገኘው የሀይል ማሰራጫ ጣቢያ ለከተማው ዕድገ ትልቅ ተስፋ ነው።

በመንገድ መሠረተ ልማት በኩልም በጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ፣ በውሃ ማፋሰሻ ዲች ግንባታ እና በመንገድ ዳር መብረት ዝርጋተም ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ይታያሉ።

የከተማውን ህዝብ የውሃ ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል ተብሎ በ114 ሚሊየን ብር ውጪ በማቺንግ ፈንድ የተጀመረው የውሃ ፕሮጀክት ሥራ እየተፋጠነ ይገኛል።

ከተማው ካለው ፍጹም ሰላምና መረጋጋት ፤ከመዲናችን አዲስ አበባ ካለው ቅርበት ጋር ተዳምሮ የበርካታ ባለሀብቶች ትኩረት እየሳበች ትገኛለች።

ከከተማው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙት በ1972 በዓለም ቅርስነት በዩኒስኮ የተመዘገበው ታሪካዊው የጥያ ትክል ድንጋይ መካነ ቅርስ እና በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተመሠረተ የሚነገረው የምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም ያሉ ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕቦች ተጨማሪ ዕድሎች ናቸው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታ አጠናቀው ሥራ በመጀመር በአሁኑ ሰዓት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከፈጠሩ የግል ድርጅቶች ውስጥ 274 ሚሊየን ብር ካፒታል በማስመዝገብ በቻይናውያን ባለሀብቶች የተገነባው ላዩን ፕሌይ ውድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።

በአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶች የተገነቡ እና ሥራ የጀመሩ የዱቄት ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን ሌሎች በርካታ ፋብሪካዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።

ለወደፊቱ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የገቢ ምንጭ በመሆን ዋነኛው የዓለም የኢኮኖሚ ዘዋሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው እና እንደሀገራችን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት የሚገኘው የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ነው።

የቡኢ ከተማም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማው ለሚመጡ እንግዶች ጥራት ያለው እና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የእንግዶቹ ቆይታ ያማረ እንዲሆን ለማድረግ እየሰሩ የሚገኙ በርካታ ሆቴሎች ይገኛሉ።

በከተማው ግንባታውን አጠናቆ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ የሚገኝ ሲሆን አንድ ዲፖ ግንባታውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ሌሎች ማደያ ለመገንባት ባለሀብቶች ቦታ ርክክብ አድርገዋል።

በከተማው የቢዝነስ ሥርዓቱን የሚያቀላጥፉ በርካታ የፋይናንስ ተቋማት ይገኛሉ።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ 8 ባንኮች ቅርንጫፍ በመክፈት የንግድ ሥርዓቱን እያሳለጡ ይገኛሉ።ሌሎችም በርካታ አነስተኛ የገንዘብ ቁጠባ እና አበዳሪ ተቋማት ይገኛሉ።

መረጃው:-የቡኢ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !  | በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊ...
03/01/2023

የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !

| በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡

በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡

ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስተፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡

ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡

ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም

 #ቡታጅራ መልካም ስም ከተጎናፀፉ  ከተማዎች አንዷ ናት በዚህች ከተማ የማይቻል ነገር የለም ምክኒያቱ ደግሞ ለክፉ ስራ የማትመች ሰላሟ ውበቷ አየሯ የህዝቧ እንግዳ ተቀባይነት እንደ ፀጋ ልብ...
03/01/2023

#ቡታጅራ መልካም ስም ከተጎናፀፉ ከተማዎች አንዷ ናት
በዚህች ከተማ የማይቻል ነገር የለም ምክኒያቱ ደግሞ ለክፉ ስራ የማትመች ሰላሟ ውበቷ አየሯ የህዝቧ እንግዳ ተቀባይነት እንደ ፀጋ ልብስ ጎልቶ የሚታይባት የፍቅርና የአንድነት ምሳሌ ከተማ መሆኗን ያሳየችን የጋራ ቤታችን ናት

#ለ2ኛ ጊዜ በከተማችን ለሚከናወነው ሀበሻ ኢጅቲማዓ ሽር ጉድ እያለች ነው የገና በዓል የሚከበርበት ወቅት እንደመሆኑ ይሄን ሳምንት ከወትሮው በተለየ ሞቅ ደመቅ ትላለች ከክልል እስከ ፌደራል አለፍ ሲል ደግሞ አለም አቀፍ ፕሮግራም የማከናወን በሺህ የሚቆጠሩ እንግዶችን ማስተናገድ ልምድና ብቃት ያላት ከተማ መሆኗን ስታይ ከፊት የሚመጣው የከተማዎ ብሩህ ተስፋና ዕድገት ያጎጎሃል

#እንግዶች ፕሮግራማቸውን በሚያከናውኑበት ስፍራ በሀይማኖት ሳንለያይ ለወንድሞቻችን የጎደለውን በመሙላትና በማገዝ እንደ ካቻምናው ሁሉ ዘንድሮም
ለዚች ከተማ ያላቸው አክብሮትና ፍቅር የምስክርነት ቃል መቀበል ይኖርብናል
Alex sabi🙏🙏🙏🙏

አርቲስት  ማሪቱ  ለገሰ ከ22 አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሯ ተመለሰችዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ በቤተሰቦቿ...
03/01/2023

አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከ22 አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሯ ተመለሰች

ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ በቤተሰቦቿ፣በሙያ አጋሮቿ እንዲሁም በአድናቂዎቿ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

ከ6 ሰዓት ጀምሮም የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በተገኙበት በብሄራዊ ቴአትር ለሁሉም ሰው ክፍት በሆነ መድረክ የእንኳን ደህና መጣሽ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሰባት ዓመት በፊት ያበረከተላትን የክብር ዶክትሬት ለአርቲስቷ እንደሚያስረክብም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ቆይታዋ አዲስ አልበሟን ለአድማጭ የምታቀርብ ሲሆን÷ አዲስ አበባን ጨምሮ ደሴ፣ጎንደር እና ባህርዳር ከተሞች የሙዚቃ ሥራዋን ታቀርባለች፡፡

በዚህም የአምባሰሏ ንግስት ማሪቱ ለገሰ ታሕሳስ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ኮንሰርቷን በደሴ ከተማ እንደምታቀርብ ተመላክቷል፡፡

በሰላማዊት ተስፋዬ

ፔሌ በ82 አመቱ አርፏል 😣ከቀናት በፊት የእግር ኳስ ወዳዶችን እና ቤተሰቡን ተሰናብቶ በሆስፒታል ልዩ ክትትል ሲደረግለት የነበረዉ ብራዚላዊዉ የእግር ኳስ ጥበበኛ ፔሌ ከዚህ አለም በሞት ተለ...
29/12/2022

ፔሌ በ82 አመቱ አርፏል 😣
ከቀናት በፊት የእግር ኳስ ወዳዶችን እና ቤተሰቡን ተሰናብቶ በሆስፒታል ልዩ ክትትል ሲደረግለት የነበረዉ ብራዚላዊዉ የእግር ኳስ ጥበበኛ ፔሌ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ።

ሦስት የአለም ዋንጫን ያነሳ ብቸኛ ተጨዋች ነበር

አሳዛኝ ዜናታላቁ የጉራግኛ ድምፃዊ ዋቢ አብዱራህማንአረፈ ዋቢዬ ነብስህ በሰላም ትርፍ ሁሌም በጉራጌህዝብ ልብ ትኖራለህ
27/12/2022

አሳዛኝ ዜና

ታላቁ የጉራግኛ ድምፃዊ ዋቢ አብዱራህማን
አረፈ ዋቢዬ ነብስህ በሰላም ትርፍ ሁሌም በጉራጌ
ህዝብ ልብ ትኖራለህ

የሌማት ቱሩፋት
25/12/2022

የሌማት ቱሩፋት

  እለቱን በፎቶ የሀገሪቱ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንንና እና የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የስራ አላፊዎች ከልብ እንግዳ ተቀበይ ከሆነው ማህበረሰብ ዘንድ ተገኝተዋል ሸጋ የሆነ ቆ...
25/12/2022

እለቱን በፎቶ የሀገሪቱ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንንና እና የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የስራ አላፊዎች ከልብ እንግዳ ተቀበይ ከሆነው ማህበረሰብ ዘንድ ተገኝተዋል ሸጋ የሆነ ቆይታ አሳልፈዋል

የድምፃዊ  #ፈለቀ ማሩ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ምረቃ!ቅዳሜ ታህሳስ 15 ከምሽት 12:00 ጀምሮ የት ለመሆን አስበዋል?ካርል አደባባይ አጠገብ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብና አዳራሽ ቢያ...
22/12/2022

የድምፃዊ #ፈለቀ ማሩ አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ምረቃ!

ቅዳሜ ታህሳስ 15 ከምሽት 12:00 ጀምሮ የት ለመሆን አስበዋል?

ካርል አደባባይ አጠገብ በሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብና አዳራሽ ቢያሳልፉስ? ልዩ ልዩ ደማቅ ሁነቶች ያጅብዎታል።

ወጃጅዎን ይዘው ይምጡ፤ አብረን እናምሽ! አክብሮትም ተዝናኖትም ነው!
===
via ሶዶ ለማ

  ❤❤❤ Like & Shareባህላችንን ለማስተዋወቅ የሰራነው የዘቢዳር ፍሬዎች ሁለት
22/12/2022

❤❤❤ Like & Share
ባህላችንን ለማስተዋወቅ የሰራነው የዘቢዳር ፍሬዎች ሁለት

Ethiopian Music : Alemayehu Wesen | አለማየሁ ወሰን - Yegena Jenber | የገና ጀንበር - New Ethiopian Music 2020 (Official Video)Google+ : https://plus.google.com/+hoples...

 ❤❤❤❤ Like & Shareከተማችንን ለማስተዋወቅ የሰራነው የዘቢዳር ፍሬዎች አንድ
22/12/2022

❤❤❤❤ Like & Share
ከተማችንን ለማስተዋወቅ የሰራነው የዘቢዳር ፍሬዎች አንድ

Ethiopia: Alemayehu Wesen - Wubit Butajira - New Ethiopian Music Video 2016

19/12/2022

ይሄን ከማየት በላይ ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ

 #ጋሞ የአለም ቤት የሰላም ሰገነት #የአለም አምባሳደር የትጋት ምሳሌ  #ኢትዮጲያዊነት ነው ይሄ ነው ባህሌ #በቀልን አርቆ ፍቅርን ሲጠራ  #በሚያኮራ ተግባር በሚያስደንቅ ስራ ጋሞ ከ❤❤❤❤...
16/12/2022

#ጋሞ የአለም ቤት የሰላም ሰገነት

#የአለም አምባሳደር የትጋት ምሳሌ
#ኢትዮጲያዊነት ነው ይሄ ነው ባህሌ
#በቀልን አርቆ ፍቅርን ሲጠራ
#በሚያኮራ ተግባር በሚያስደንቅ ስራ
ጋሞ ከ❤❤❤❤ ወድድድድድድ

ትዝብት...😡  | “የሳቃችን ምንጭ” ያልነው ተዋናይ ሕይወቱ የሀዘን ጅረት ነበረ፤ ዓይኑም ሰው እንደራበው አረፈ     ለተዋናዩ ፣ ለመልከ መልካሙ ፣ ለዝነኛው ተዋናይ ታሪኩ ብርሀኑ “አረፈ...
12/12/2022

ትዝብት...😡

| “የሳቃችን ምንጭ” ያልነው ተዋናይ ሕይወቱ የሀዘን ጅረት ነበረ፤ ዓይኑም ሰው እንደራበው አረፈ

ለተዋናዩ ፣ ለመልከ መልካሙ ፣ ለዝነኛው ተዋናይ ታሪኩ ብርሀኑ “አረፈ” የሚለው ቃል ይገልጸዋል። ታሪኩ ብርሀኑ በእርግጥም ከዚያ የመከራ ሕይወት አረፈ። ያ መልከ መልካም ፣ የሀገራችን ፊልም አበባ ፣ የሁላችንም ሳቅ ምንጭ ትክክለኛ ሕይወቱ በመራር ሀዘን የተሞላ ነበረ ። እኛን በስራው የሚያስፈነድቀን ትንግርተኛው ተዋናይ ወደራሱ ሕይወት ሲመለስ ግን መልኩ ሌላ የማናውቀው አይነት ነበረ ። ማናችንም ስለ ስራው እንጂ ስለ ሰውየው ግድ የለንም ። ኑሯችን እንዲህ ነው ። ማናችንም ስለማናችንም ሕይወት ደንታ የለንም ። ታሪኩ በተለይ ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ያለው ሕይወቱ ሀዘን የሞላበት ነበረ ። ትዳሩ የፈረሰበት መንገድና ተያያዥ ጉዳዮች ፣ የፊልሙ ገበያ መቀዛቀዝና ያ ተፈላጊ ተዋናይ በስራ አለመጠመዱ ታሪኩን በስነልቦና ሰብረውታል ። ብቸኝነት ጎድቶታል ። በሕዝብ ዓይን በጉጉት የሚታየው ብርቱው ተዋናይ ዓይኑ ሰው ተርቧል ። ሰው ፈልጎ ሰው አጥቷል ። እንደ መጀመሪያው ሁሉ በመጨረሻም እናቱ ብቻ ከጎኑ ነበረች ።

ታሪኩ ከህመሙ በላይ ህመም የሆነበት ሰው ማጣቱና ብቸኝነቱ ነበረ ። እንደዚያ ውድ የነበረው ተዋናይ በህመምና በስሜት ስብራት ታሞ እናቱ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በወደቀ ጊዜ ማንም ዞር ብሎ አላየውም ። " እግዜር ይውሰድህ " ሊለው እንኳ ቤቱ የሚሄድ ወዳጅ አልነበረውም ። በዚህ የተነሳ የታሪኩ የቀንና ሌሊት ሀሳብ ዳግም ከወደቀበት ተነስቶ ሰው መሆኑን ማሳየት ነበረ ። እንደገና ከአስገራሚ ትወናው ጋር ካሜራ ፊት መቆም ነበረ ። ግን አልሆነም ።

ዛሬ የታሪኩ እናት ቤት በታዋቂ አርቲስቶች ተሞልቷል ። ዛሬ ለታሪኩ አልቃሹ ብዙ ነው ። ነገ ቀብሩ ይደምቃል ። የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ወጥቶለታል ። የአበባ ጉንጉን ይጎርፍለታል ። ይህ ሁሉ ግን ለታሪኩ አንዳች የሚረባው የለም ። ዛሬ ለቅሶውን ካደመቁት አርቲስቶች ጥቂቶቹ እንኳ ከጎኑ ቆመው ቢሆን ምናልባት በትዳሩ መፍረስ ፣ በሚስቱ ፣ በስራ ባልደረቦቹ ፣ በሰው እጦት ከተፋጠነው ሞቱ ማገገም ፣ ምናልባትም መዳን በቻለ ነበር ። በሰው ተከቦ ኖሮ ብቻውን ተኝቶ አለፈ ። ታሪኩ ዛሬ ከብዙ ስቃይ ነው ያረፈው ።

ታሪኩ ብርሀኑ ሰው እንደሌለው ሰው ተስፋ ቆርጦ ተመልሶ እናቱ ቤት በተኛ ወቅት ከእነዚያ ሁሉ ወዳጆቹና ፈላጊዎቹ ተክለ ሆስፒታል አስተኝታ የመድሀኒትና ሙሉ የህክምና ወጪውን የሸፈነችው ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ ብቻ ነበረች ። እኔ ይቺን ልጅ የማመሰግንበት ቃላት የለኝም ። ካሁን ቀደምም ሰው የታጣበት ቦታ ላይ እንዲሁ ሰው ሆና ተገኝታ አመስግኛታለሁ ። አሁንም በድጋሚ አመሰግናታለሁ ። በተረፈ ጥቂት ወዳጆቹ ፊልም አሳይተው ገንዘቡን ሊሰጡት ቢጠይቁት ታሪኩ ፈቃደኛ አልሆነም ። ምናልባት ብዙ ምክንያት ይኖረዋል ። አንድ ተዋናይ የቀድሞ ወዳጁ ታሪኩ ወደተኛበት ተ/ሀይማኖት አካባቢ የእናቱ ቤት ሊጠይቀው ሲሄድ አልቅሶ ነበረ የተቀበለው ። ሰው ማጣቱ የዚያን ያህል ነው ።

እናንተ ግብዞች አያችሁ ዝናና ተወዳጅነትን ( በተለይ ፊልሙ መንደር ) የታሪኩን ያህል እጁ ያስገባ አልነበረም ። አሁን የእሱን ቀብር ማሳመር ሰው አያደርጋችሁም ። " ታሪኩን ብታጫውቱት ፊልማችሁ ገበያ ያገኛል " የተባላችሁና ተለማምጣችሁ ያሰራችሁት ፕሮዲዩሰሮችና የሙያ አጋሮቹ አሁን የታሪኩን ለቅሶ ተዉት ። ዓይኑ እናንተን በተራበ ጊዜ አጠገቡ አልነበራችሁም ። መታከሚያ ባጣ ጊዜ አልከፈላችሁለትም ። ዛሬ ደረታችሁን ብትደቁ ምንም አትጠቅሙትም ። ይልቅ ህሊናችሁ ከወቀሳችሁ ልጃቸውን በማስታመምና በመጨረሻም ያን ሸበላ ልጃቸውን ያጡት እናቱን " አለንልዎት " በሏቸው ። ለታሪኩ ልታደርጉ የምትችሉት የመጨረሻው ነገር እናቱን መደገፍ ነው ። ቀብር ማሳመርን ለቀብር አስፈጻሚዎች ተዉላቸው ።

ወንድምዓለም ነፍስህ በሰላም ትረፍ 🙏🙏🙏

Teklearegay

ነፍስህ በሰላም ትረፍ !! ሌላ ምን ይባላል
11/12/2022

ነፍስህ በሰላም ትረፍ !! ሌላ ምን ይባላል

ሞሮኮ ዳግም ታሪክ ሰራች ፖርቹጋልን በማሸነፍ ወደ 4 ውስጥ ገብታለች
10/12/2022

ሞሮኮ ዳግም ታሪክ ሰራች ፖርቹጋልን በማሸነፍ ወደ 4 ውስጥ ገብታለች

ሺ ፍቅር የተሰኘዉ ፍልም  ታሀሳስ 22 በሴራና  ሁለገብ አዳራሽ ለእይታ ይቀርባል ይመረቃል
10/12/2022

ሺ ፍቅር የተሰኘዉ ፍልም ታሀሳስ 22 በሴራና ሁለገብ አዳራሽ ለእይታ ይቀርባል ይመረቃል

17ኛ የኢትዮጲያ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀዋሳ 2015ዓ.ም
08/12/2022

17ኛ የኢትዮጲያ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀዋሳ 2015ዓ.ም

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alexsabi Promotion & Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share