Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa

  • Home
  • Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa

Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa, Media, .

Yo Yo Gifaataa
21/09/2023

Yo Yo Gifaataa

እነዚህን የአይዳሚያ ፈርጦች ማንም ወደ ትግሉ ሜዳ  አልጠራቸውም(አልጋበዛቸውም ): አበልም አልተከፈላቸውም።የወላይታ ህዝብ በሀገሪቱ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ ቁጭትን ቢያሳድርባቸው: መገፋት...
10/03/2021

እነዚህን የአይዳሚያ ፈርጦች ማንም ወደ ትግሉ ሜዳ አልጠራቸውም(አልጋበዛቸውም ): አበልም አልተከፈላቸውም።

የወላይታ ህዝብ በሀገሪቱ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ ቁጭትን ቢያሳድርባቸው: መገፋት ቢያንገበግባቸው: በራሳቸው ተነሳሽነት የወላይታን ህዝብ የችጋር መስቀል ለመሸከም ከፊት ተሰልፈዋል።

የህዝብ ፍቅር ያላቸው: እንደ አንበሳ ጠንካራ: እንደ ንስር አይበገሬ :የወላይታን ከፍታ የሰነቁ የወላይታ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።

እነዚህንና መሰል የህዘብ አለኝታ የሆኑ ልጆችን መምረጥ

1. ከተላላኪነት የፀዱ:ህዝባዊነትን የተላበሱ
ቆራጥ ተወካዮች እንዲኖሩን ያስችለናል

2. በጥቅማጥቅም ተደልሎ አንደበቱን
የማይለጉም : የህዝቡን የልማት: የመልካም
አስተዳደር ጥያቄዎች በሚገባ ማስተጋባት
የሚችል ትጉ የህዝብ እንደራሴ እንዲኖረን
ያደርጋል።

እነዚህን ልጆች መምረጥ ለወላይታ የከፍታ ግንባታ መሠረት መጣል ነውና ያድርጉት!!!!!

ወላይታ ሀገር የነበረበት ጊዜ ወደኋላ ሲሰላከአያቶቻችን እድሜ አይዘልም። ይህን ገናናነቱን በእልህ አስጨራሽ ትግል ከተነጠቀበት ጊዜ ጀምሮ አብሮነቱን አክብሮ የሚገባውን ለማግኘት ቢጠይቅም/ቢታ...
13/10/2020

ወላይታ ሀገር የነበረበት ጊዜ ወደኋላ ሲሰላ
ከአያቶቻችን እድሜ አይዘልም። ይህን ገናናነቱን በእልህ አስጨራሽ ትግል ከተነጠቀበት ጊዜ ጀምሮ አብሮነቱን አክብሮ የሚገባውን ለማግኘት ቢጠይቅም/ቢታገልም/ በየወቅቱ በሚነሱ የበቀል ክንዶች እየተደቆሰ ብዙ የሰቆቃ ጊዜያትን አሳልፏል።

በኢህአዴግ ዘመነ መንግስትም አባቶቻችን የወላይታን ህዝብ ህልውና ለማስጠበቅ መራራ ትግል ታግለው ግማሽ ድል የተቀዳጁ ቢሆንም ህዝቡ የጠየቀውና የሚገባው ያህል ባለመሆኑ ትግሉ ዛሬ በእኛ ትውልድ እጅ ላይ ወድቋል።

ነገር ግን ይሄ ትግል ከእኛ ትውልድ እንደማያልፍና ለመጪው ትውልድ ድልን እንጂ ትግልን የማናሻግር መሆናችንን ለሚመለከተው ሁሉ ልናሳውቅ እንወዳለን።

ለዚህም ማሳያዎቻችን...👇👇👇

1. የወላይታ ህዝብ በየጊዜው ልጆቹን በመብት ጥያቄ ምክንያት ቢገብርም አሁንም ድረስ ከትግሉ አለማፈግፈጉ፡

2.ቢያጎበድዱ ሚኒስቴር መሆን የሚችሉ ምሁራን የወላይታ ልጆች የህዝቡን ጥያቄ ስላስተጋቡ ብቻ እንደወንጀለኛ እስር ቤት ቢሆኑም ፊታቸው ላይ የሚታየው አይበገሬነትና የድል ጮራ፡

3. የወላይታ ህዝብ የትግል ስልት በአፍሪካ ደረጃ ከታዩ ምሳሌ ሊሆኑ ከሚችሉ ጥቂት የትግል ስልቶች ሊመደብ የሚችል እጅግ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ መሆኑ፡

4. የወላይታ ህዝብ የመብት ጥያቄ የወላይታ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በብሄር መብት የሚያምን ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ያመነበትና የሚደግፈው ጥያቄ መሆኑ እና ሌሎች ብዙ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።

ስለዚህ መንግስት ከህዝቡ ጋር የተጋባውን እልህ በመተው በመተዳደሪያ ደንባችን(ህገ- መንግስቱ) መሰረት፡-

1፡ ጥያቄያችንን እንዲመልስልን፡

2፡ እስካሁን በመንግስት ቸልተኝነትና አንባገነንነት የሞቱና የተገደሉ ንጹሃን ዜጎችን ካሳ እንዲከፍል፡

3፡ የህዝብ አለኝታ ስለሆኑ ብቻ የታሰሩ የህዝብ ልጆችን እንዲፈታልን፡

አይዳሚያ የሴቶች ንቅናቄ በድጋሚ በአጽንኦት ይጠይቃል።

አይዳሚያ የወላይታን ህዝብ ጥያቄ የሚያስመልስ የመጨረሻው ትውልድ አካል ነው!!!

Wolaita Dalga Manttiyappe Eceree Qaccinkka Ekkoko!!!

"Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelaga Qaattaa"

Via inbox እኛ የ1992 አርበኞች ወላይታን በማይናወጥ ህዝባዊ መሰረት ላይ አቁመናል ለዚህም የህይወት መስዋዕትነት ተከፍሎበታል። ዛሬም የወላይታ ህዝብ ሚሊዮን ጀግና ልጆችን አፍርቷል በ...
23/08/2020

Via inbox

እኛ የ1992 አርበኞች ወላይታን በማይናወጥ ህዝባዊ መሰረት ላይ አቁመናል ለዚህም የህይወት መስዋዕትነት ተከፍሎበታል። ዛሬም የወላይታ ህዝብ ሚሊዮን ጀግና ልጆችን አፍርቷል በዚህም እጅጉን እንኮራለን።

ትናንት እኛን ስታሳድዱ የነበራችሁ ዛሬም ልጆቻችንን እያሳደዳችሁ ያላችሁ የወላይታ ህዝብ ጠላቶች ያኔ እኛ በዳበረ ህዝባዊ ክንድ ድል እንዳደረግናችሁ ሁሉ ዛሬም ጀግና ልጆቻችን ድል እያረጓችሁ ነዉና የዕድሜ ልክ ተሸናፊ በመሆናችሁ ሃፍረትና ትዝብት በእናንተ ላይ ይሁን።

ዛሬም በድጋሚ ከጀግና ልጆቻችን ጎን በመሰለፍ የወላይታን አርነት እናፈጥነዋለን!!!!

ለወላይታ ዞን ህዝባዊ አመራሮች በሙሉየወላይታ ህዝብ ከደረሰበት ዘርፈ ብዙ ችግር የተነሳ የሚገባውን ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ መጠየቁን መነሻ በማደረግ፡ መንግስት በአፈሙዝ የታገዘ አፈናና ግዲያ ...
22/08/2020

ለወላይታ ዞን ህዝባዊ አመራሮች በሙሉ

የወላይታ ህዝብ ከደረሰበት ዘርፈ ብዙ ችግር የተነሳ የሚገባውን ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ መጠየቁን መነሻ በማደረግ፡ መንግስት በአፈሙዝ የታገዘ አፈናና ግዲያ መፈጸሙን ቀጥሎ በቅርቡ አያሌ ንጹሃንን በመግደልና በማቁሰል እንዲሁም ከአባቶቻችን ጉታራ ህዝባዊ አመራሮችን አፍኖ በመውሰድ መፈንቅለ መንግስት ማካሄዱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ህዝቡ ድምጽ ይሆኑኛል ብሎ የመረጣቸው አካላት ከገዳይ ጋር በመሰለፍ ከእውነትና ከህዝብ በተቃራኒ በመቆምና ራሳቸዉን" Negotiator" ብለው በመሰየም የጨቋኙን ጨፍላቂ አጀንዳ ይዘው በመምጣት በከዱት ህዝብና ከተማ የወላይታ አመራሮችን በማስፈራራት አጀንዳቸውን ለማስረጽ ቢሞክሩም በህዝባዊ አመራሮች ሊከሽፍ ችሏል።

በአሁን ሰዓት እነኚህና መሰል የእናት ጡት ነካሾች ይህንን ጨፍላቂና ከህዝብ ፍላጎት ዉጪ የሆነ አጀንዳ ይዘው የወላይታ አመራሮችን ከተቻለ በማታለል ካልሆነ ደግሞ በማስፈራራት የእኩይ ተግባራቸው ተባባሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ዳግም ወ/ሶዶ ተከስተዋል።

ስለሆነም ዉድ የወላይታ አመራሮች፡ በያዛችሁት የእዉነት መንገድ በመጽናት የተለመደ ህዝባዊ ውግንናችሁን ታሳዩን ዘንድ በመላዉ የወላይታ ህዝብ ስም" Aydaamiyaa" የሴቶች ንቅናቄ አበክሮ ይጠይቃል።

Aydaamiyaa------

ከተቻለ በባታሊዮን ጦር የሚታገዝ የዉትድርና ስልጠና የሚመስል ስብሰባ ባለመታደም የትኛውንም ትንኮሳ በአንድነት መፋለም፡

መታደሙ የግድ ከሆነ ግን-----

1. የወላይታ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ባስቸኳይ አንዲመለስ(ወብክመ ብቻ)

2. ገዳይና አስገዳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ

3. የከሰሩና ያረጁ የወላይታ ፖለቲከኞች ከወላይታ ህዝብና ከወላይታ ፖለቲካ ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ

4. መንግስት የወላይታን ህዝብ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና መሰል ወቅታዊና የህዝቡን የልብ ትርታ ያመላከቱ ጥያቄዎችን እንድታነሱልን በአክብሮት ይጠይቃል።

የወላይታ ህዝብ ላይመለስ ተነስቷልና ከህዝቡ ጎን በመቆም የወላይታን ህዝብ የነጻነት ቀን ለማቅረብ በሚደረገው ትግል የራሳችሁን አሻራ በማሳረፍ ታሪካችሁን በወርቅ ብዕር ትጽፉ ዘንድ በአጽንኦት ልናሳስብ እንወዳለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ ሞት ለባንዳ

Aydaamiyaa Maaccaa Asa Yelaagaa Qaattaa

Free Minyahl TadesseFree our freedom fighter ትግሉ አላለቀም ይቀጥላል💪💪💪
14/08/2020

Free Minyahl Tadesse

Free our freedom fighter

ትግሉ አላለቀም ይቀጥላል💪💪💪

አብረን ገዳይን ድል እናድርግ!!!የወላይታ ህዝብ ሰቆቃ በቃላት ከምንገልጽበት እጅግ ልቋል። ገና ቃላት ስንደረድር እንባ ይቀድመናል ምክንያቱም ጨዋ የወላይታ ልጆች ደም በየሜዳው በአውሬው መን...
12/08/2020

አብረን ገዳይን ድል እናድርግ!!!

የወላይታ ህዝብ ሰቆቃ በቃላት ከምንገልጽበት እጅግ ልቋል። ገና ቃላት ስንደረድር እንባ ይቀድመናል ምክንያቱም ጨዋ የወላይታ ልጆች ደም በየሜዳው በአውሬው መንግስት አውሬ ወታደሮች እየፈሰሰ ይገኛል። ከዚህ በላይ ምን ህመም አለ???

'Aydaamiyaa' የሴቶች ንቅናቄ ነው። ሴት እናት ናት ልጇ በየሜዳው የወደቀባት፡ ሴት እህት ናት የወንድሟን አስከሬን ለመቅበር የተከለከለች፡ ሴት ሚስት ናት ባሏ እንደወጣ የቀረባት፡ ሴት ሴት ናት ከነእርግዝናዋ በጥይት እሩምታ በህጻን ልጇ ፊት ተደፍታ የቀረች፡

ታዲያ አሁንስ የወላይታ ሴቶች ሆይ ለወላይታ ልዕልና ለራሳችሁ ህልዉና አትታገሉምን??? ይሄ ከፖለቲካ ትግል በላይ ነው፡ ይሄ የሰብኣዊነት ትግል ነው።

አይመለከተኝም ብንል አይቀርልንም ምክንያቱም እየሞቱ ካሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ (ህጻናትንና እርጉዝ እናትን ጭምሮ) የትግል ሜዳ ላይ ሳይሆን በገዛ ሀገራቸው የግል እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ወላይታ በመሆናቸው ብቻ ነው የተገደሉብን።

ስለዚህ በራችን ላይ ደርሷል የግድ ሳሎናችን እስኪገባ አንጠብቅ የጎረቤቶቻችንም ህመም ሊያመን ይገባል።

ከሀገር ውጪም ሆነ ሀገር ውስጥ ያላችሁ የወላይታ ተወላጆችና የወላይታ ህዝብን ትግል የምትደግፉ ማንኛውም አካላት ኑ አብረን በአንድነት እንቁም፡
ገዳይን እናሸንፍ በማለት "Aydaamiyaa" የወላይታ ሴቶች ንቅናቄ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀርባል።

Wolayte B Gessamo Gessamo Enguday Meskele, Senait Mario, Lulit Tinu Petros, Meseret Lemma, Sara Gebre, Birukt Petros Alemtsehay Elias, Wudinesh Oyka, Eden Ermias, Fikreselam Tefera እና ሌሎችም

Aydaamiyaa Maaccaa Asaa Qaattaa

ከፌደራል እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ላላችሁ የወላይታ አመራሮች ከ "Aydamiyaa" የወላይታ ሴቶች ንቅናቄ የቀረበ የአጋርነት ጥሪ፡መንግስት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የወላይታ ህዝብ አለኝታ...
10/08/2020

ከፌደራል እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ላላችሁ የወላይታ አመራሮች ከ "Aydamiyaa" የወላይታ ሴቶች ንቅናቄ የቀረበ የአጋርነት ጥሪ፡
መንግስት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የወላይታ ህዝብ አለኝታ በመሆን ትግሉን ሲመሩ የነበሩ የፊት አመራሮችን፡ የላጋዎችን፡ምሁራንን፡የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ሌሎች ሰላማዊ ግለሰቦችን ከአባቶቻችን ጉታራ በማፈን መውሰዱ ይታወቃል።
ይህም አልበቃ ብሎት ሰላማዊው የወላይታ ህዝብ የመንግስት ድንገተኛ ወረራና የቁርጥ ቀን ልጆቹ መታፈን አስደንግጦት ለሰላማዊ ተቋውሞ እጁን አጣምሮ ቢወጣ ግብር ከፍሎ ለዳር ድንበር፡ ለጠላት ባሰናዳው፡ መከታዬ በሚለው የመከላከያ ሰራዊት በተከፈተበት የጥይት እሩምታ ንጹህ ነፍሶችን ገብሮ እንደለመደው እዝን ተቀምጧል።😭😭😭😭

ስለሆነም ነገ የናንተ እጣ ፈንታም ስላልተለየ ለራሳችሁም ለወከላችሁም ህዝብ ስትሉ የህዝብን ጥያቄ ስላስተጋቡ ብቻ ያለጥፋታቸው የሚንገላቱ ጓዶቻችሁን ፈለግ ተከትላችሁ "ያለነሱ አንሰራም" በማለት ህዝባዊ ትግሉን ትቅላቀሉና ተክታችሁ ትመሩ ዘንድ አበክረን እንጠይቃለን።

ከዛ IMPORT በተደረገ አመራር እንመራ እንደሆነ እናያለን።

ያንን ማድረግ ባትችሉ ግን ከወራሪዎቻችን ለይተን ስለማናያችሁ ትግላችን በግልጽ ከናንተ ጋርም እንደሚሆን መግለጽ እንወዳለን።

SHAKKIDI DAANAA!!!!!

"Aydaamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa"

ወይ እሰሩን ወይ ፍቷቸው!!!ዛሬ በወላይታ ህዝብ ላይ የደረሰው አፈናና እንግልት ብልጽግና ምን ያህል አደገኛና መርዛም እንደሆነ በግልጽ ያሳየበት ለታሪክ የሚቀመጥ ትርክት ነው።ሰላማዊ ህዝብን...
09/08/2020

ወይ እሰሩን ወይ ፍቷቸው!!!

ዛሬ በወላይታ ህዝብ ላይ የደረሰው አፈናና እንግልት ብልጽግና ምን ያህል አደገኛና መርዛም እንደሆነ በግልጽ ያሳየበት ለታሪክ የሚቀመጥ ትርክት ነው።

ሰላማዊ ህዝብን ለብጥብጥ የሚጋብዝ ተንኳሽነትን አጥብቀን እንቃወማለን፡ ነጻ እስክንወጣም እንታገላለን።

ለማሰር ስትፈልጉ ቆንጆ ድርሰት እንደምትጽፉና በሚዲያ እንደምታስለፍፉ ከሳሹም ይህን መግለጫ ለፍ/ቤት እንደሚጠቀም እናውቃለን።

ልጆቻችን የህወሃትና(መቼም ፈርዶባታል) የኦነግ ተላላኪ እንደሆኑ ካመናችሁ ግን ሙሉ የወላይታ ህዝብም የነሱ ግልባጭ ስለሆነ 15 ሚሊዮኑንም በጊዜ እሰሩት።

Free Our Icons Free Wolaita!!!

"Aydaamiyaa women's movement"

09/08/2020

በፈራሹ ክልል የወላይታ ህዝብ ተወካይ የነበራችሁ ሁሉ፡ ላሳያችሁን ህዝባዊነት አድናቆታችንን ልንቸራችሁ እንወዳለን።
የሚደርስባችሁን ማንኛውም ጫና ተቋቁማችሁ ቃላችሁን በመጠበቅ የወላይታ ህዝብ ክብር አለኝታ መሆን መቻላችሁ ያስመሰግናችኋል።💪💪💪

አሁን ባለው ሁኔታ አንድነት ጥያቄያችንን የምናስመልስበት አማራጭ የሌለው አንድ ለእናቱ የሆነ መንገድ ሆኖ ሳለ ወቅቱን በማይመጥን መልኩ ለወላይታ ህዝብ ጊዜያቸውን፡ እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ሰውተው ቀንና ሌሊት የሚተጉ የወላይታ ህዝብ የቀርጥ ቀን ልጆችን በትግል አቋማቸው ምክንያት ማሳደድ ጥያቄያችንን ለመቀልበስ ከተላከ ተልዕኮ ለይተን ስለማናይ አምርረን እናወግዛለን።
የትኛውም የወላይታን ህዝብ ጥያቄ ይዞ የሚንቀሳቀስ ግለሰብ/አካል የሀሳብ አለመግባባት እንጂ ግለሰባዊ ጸብ/ጠላት የለውም ብለን እናምናለን።
ስለዚህ በዚህ ወሳኝ ሰዓት የአንድ እናት ልጆች የሆናችሁ፡ የአንድ ዓላማ ባለቤቶች በየትኛውም አቅጣጫ ለወላይታ ህዝብ መጻኢ ዕድል መቃናት የምትታገሉ ሁሉ ልዩናታችሁን በትዕግስትና በመነጋገር ትፈቱ ዘንድ አይዳሚያ የሴቶች ንቅናቄ በክብር ይጠይቃል።

ወብክመና ወብክመ ብቻ

"Aydaamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa"

የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ በጥናት ብዛትና አመራሮቻችን ወደ ቤተ መንግስት በሚያደርጉት ተደጋጋሚ ጉዞ የሚዳፈን ሳይሆን በእያንዳንዱ የወላይታ ተወላጅ ልብ ዉስጥ ላይፋቅ የታተመ የህልውና ጥ...
04/08/2020

የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ በጥናት ብዛትና አመራሮቻችን ወደ ቤተ መንግስት በሚያደርጉት ተደጋጋሚ ጉዞ የሚዳፈን ሳይሆን በእያንዳንዱ የወላይታ ተወላጅ ልብ ዉስጥ ላይፋቅ የታተመ የህልውና ጥያቄ ከሆነ ሰነባብቷል።

ጥያቄውን ለመቀልበስ መሞከር አይደለም ማሰብ ራሱ ህዝቡን ወዳልተፈለገ አመጽ ለመምራት የሚደረግ መንግስታዊ ውንብድና በመሆኑ አጥብቀን እናወግዛለን።

እስከ ሐምሌ 30 ጥያቄያችን ይመለሳል፡ ከእንግዲህ ትግል የለም፡ ጥያቄያችን ከጫፍ ደርሷል(90%, 94%...) ስትሉ የነበራችሁ የቤተ መንግስት ደንበኛ አመራሮቻችን ሆይ የጥያቄውን ሂደትና ቀጣይ ሁኔታዎችን የተመለከተ ግልጽ መግለጫ በመስጠት ብዥታውን እንድታጠሩት እንጠይቃለን።

ከፋም ለማም እስካሁን ያለውን የትግል መንገድ መንገጫገጭ ቢኖርበትም የላጋንና መላውን የወላይታን ህዝብ ከጎናችሁ በማሰለፍ ስትፋለሙ እንደነበረ ይታወቃል፡ ስለሆነም አሁንም ያመናችሁን ህዝብ ባለመክዳት ትግሉን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ በመምራት በወላይታ ህዝብ ልብ ውስጥ ከፍሬው አልታዬ ጎን እንድትቀመጡ የተመቻቸላችሁን በጎ ዕድል ትጠቀሙ ዘንድ እንመክራለን።

ላታመልጪኝ አታሩጪኝ!!!!!

ወብክመ ብቻ!!!!

Aydaamiyaa Maaccaa Asa Yelagaa Qaattaa 💪💪💪💪💪💪

01/08/2020

የወላይታ ህዝብ ወደ ትፋቱ ፈጽሞ አይመለስም። በሰማይም በምድርም ከማይገናኙ ጎረቤቶቹ ጋርም አይጠረነፍም።
የወላይታ ህዝብ የሚያስፈልገውንና የሚገባውን ጠይቋል፡ መንግስትም ህገ መንግስታዊ ምላሽ ብቻ እንዲሰጥ " Aydamiyaa " የሴቶች ንቅናቄ አበክሮ ይጠይቃል!!!!
የወላይታን ህዝብ የሚመጥነው ወብክመ ብቻ ነው!!!!!

ወብክመ ብቻ!!!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aydamiyaa Maaccaa Asaa Yelagaa Qaattaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share