![በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ መንጠር ቀበሌ በተቀሰቀሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 19 ቤቶች ከነ ሙሉ ንብረታቸው የተቃጠሉ ሲሆን 21 ሚሊየን 18 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የወረዳ ፖሊ...](https://img4.medioq.com/149/475/111553061494756.jpg)
21/03/2022
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ መንጠር ቀበሌ በተቀሰቀሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ 19 ቤቶች ከነ ሙሉ ንብረታቸው የተቃጠሉ ሲሆን 21 ሚሊየን 18 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አስታወቀ ።
በእዣ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ገፅታና ግንባታ ማስተባበር ስራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር አስራት ሀይሌ እንደገለፁት መጋቢት 7/2014ዓም ከቀኑ 10 :00 ሰዓት ገደማ በወረዳው መንጠር ቀበሌ ልዩ ስሙ የጉንብስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአቶ ሁሴን አወል ቤት ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀው ሁኔታ በተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ 15 የሳር ኪዳን ቤቶችና 4 የቆርቆሮ ኪዳን ቤቶች በድምሩ 19 ቤቶች ከነ ሙሉ ንብረታቸው መውደማቸውንም ገልፀዋል።
ዋና ኢንስፔክተር አስራት በወቅቱ በነበረው ሀይለኛ ነፋስ የእሳቱ አደጋው በፍጥነት እንዲስፋፋ በማድረግ አደጋው ከባድ እንዲሆን ያደረገው ሲሆን በድምሩ 21ሚሊየን 18 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሊወድም ችሏል ብለዋል ።
በቃጠሎውም በሰውና በዕንስሳት ላይ አደጋ አለመድረሱን የገለፁት ኢንስፔክተር ይህም ቃጠሎ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያመጣ ከወረዳው ዋና ከተማ አገና ድረስ ነዋሪዎች ቦታው በማድረስ ያደረጉት እርብርብ ከፍተኛ ነበር ብለዋል ።
ጉዳት የደረሰባቸውም የህብረተሰብ ክፍሎች የወረዳ ሚመለከታቸው አካል መረጃ የማደራጀት ስራ የተሰራ ሲሆን በቀጣይም በሚቻል መልኩ ድጋፍ ሊደረግ ይችላልም ብለዋል ።
ህብረተሰቡም ወቅቱ ደረቃማና ነፋሻማ በመሆኑ እንደዚህ አይነት የእሳት አደጋ ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል ።