09/05/2020
📖በኑሮ ምሳሌ መሆን
“እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥1
✉ኑሮ የሚለው የየዕለቱን ምልልሳችንን የሚያሳይ ነው። ሐዋርያው ኑሮው ክርስቶስን ይመስላል። ስለዚህ በድፍረት የእኔን ምሳሌ ይከተሉ ይላል።
🎤በአንድ የሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ትማር የነበረች ልጅ እንዴት ወደ ጌታ እንደመጣች ስትመሰክር ፣"በመጀመሪያ አስተማሪዬን ወደድኩት ቀጥሎም የአስተማሪዬን አምላክ ወደድኩት" አለች። ሰዎች በእኛ ኑሮ ጌታን ይወዱታል ወይም ይጠሉታል። ስለዚህ የምንኖረው ኑሮ በዋናነት እግዚአብሔርን የሚፈራ ዓይነት ሰው መሆን አለበት። ጠንካራው ምስክርነታችንም ይኸው ኑሮአችን መሆኑን...አበክረን እንወቅ።
“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”
— ማቴዎስ 5፥16
✉መልካም ሥራ ብርሃን ነው። ብርሃን ደግሞ ጨለማን ያሸንፋል። ብርሃን ባለበት ጨለማ የለም። የእናንተን ኑሮ አይተው የእናንተን አባት እንዲያከብሩ መልካም ኑሮ ኑሩ ይለናል። ይህን መልካም ሥራ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረው፦
" የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ። እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።"
-/ሮሜ.12:14-17/ በማለት ይገልጸዋል።
📖ምሳሌ ሁን....!
✉ጌታ መንፈስ ቅዱስ አዕምሯችንን ይባርክ!
ይህ የወንድም አስራት ታደሠ የአገልግሎትገፅ 👌 ተከታታይ የመፀሐፍ ቅዱስ ጥናት 👌በተጋባዥ ዘማሪዎች መዝሙር 👌 አዳዲስ ያሬዳዊ ቅኝት ዝማሬዎች 👌 ግጥሞች የያዘ ቻናል ነው፡ Join ያድር....