International Information

  • Home
  • International Information

International Information On this site we bring you the latest news from around the world, scientific inventions, and technolog

ህይወት ለራሷም አጭር ናት መሸጋገርያ አለም እንጂ መዘውተርያ አይደለችም ባለህ ጊዜ ካንተ ሚጠበቀውን ብቻ ሰርተህ አሻራህን አኑረህ እለፍ ከጊዜያት በኋላ አንተም ታሪክ ነህና!   የህይወት ጎ...
12/12/2020

ህይወት ለራሷም አጭር ናት መሸጋገርያ አለም እንጂ መዘውተርያ አይደለችም ባለህ ጊዜ ካንተ ሚጠበቀውን ብቻ ሰርተህ አሻራህን አኑረህ እለፍ ከጊዜያት በኋላ አንተም ታሪክ ነህና!
የህይወት ጎበዝ ሁን !

✨አዲስ ቀን አዲስ ተስፋ ብሩህ ስራ✨

ከመጽሐፍ ገጽ"ኋላቀር ሕዝብ እርስ በርሱ ሲሽቀዳደም ጊዜ ራሱ ቀድሞ ያመልጠዋል፡፡ ጊዜ ያመለጠው ሕዝብ ደግሞ ከኋላው ሌላ ሕዝብ ሊኖር አይችልምና ኋላቀርነቱን ማንም ሊወስድበትም ሆነ ሊወሰድለ...
12/12/2020

ከመጽሐፍ ገጽ
"ኋላቀር ሕዝብ እርስ በርሱ ሲሽቀዳደም ጊዜ ራሱ ቀድሞ ያመልጠዋል፡፡ ጊዜ ያመለጠው ሕዝብ ደግሞ ከኋላው ሌላ ሕዝብ ሊኖር አይችልምና ኋላቀርነቱን ማንም ሊወስድበትም ሆነ ሊወሰድለት አይችልም "

ሌላ ሰው : በዶ/ር ምህረት ደበበ

"ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!" ⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖ...
12/12/2020

"ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"
⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏⛏
በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡

"ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አሸየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ"

በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው"

ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡

አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡

ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡

ያለንበት ነባራዊ ሁናቴ እኛን ሊወስነን አይገባም!📡📡 📡 📡

ጠ/ሚ ዐብይ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ወደ ኬንያ አቅንተው የሞያሌ የድንበር መተላለፊያ በርን ይመርቃሉ!ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጀምሮ ወደ ኬንያ ሊያቀኑ ነው፡...
07/12/2020

ጠ/ሚ ዐብይ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ወደ ኬንያ አቅንተው የሞያሌ የድንበር መተላለፊያ በርን ይመርቃሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጀምሮ ወደ ኬንያ ሊያቀኑ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኬንያ የሚያቀኑት ለሁለት ይፋዊ የጉብኝት ቀናት ነው፡፡በመጀመሪያው ቀን (ረቡዕ) በመርሳቢት ግዛት ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተገናኝተው የሞያሌ የድንበር መተላለፊያ በርን ይጎበኛሉ፤ በይፋ መርቀው ይከፍታሉም ተብሏል፡፡መሪዎቹ በዚያኑ ቀን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን እና የኬንያ፣ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ፕሮጄክት አካል የሆነውን አዲሱን የላሙ ወደብን እንደሚጎበኙ የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ከዛሬ 2 ገደማ ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ከቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን መመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

Al-ain

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጠረ ********************የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር...
08/11/2020

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጠረ
********************
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር ማረፊያ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ ገለጸ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሰራዊቱ በምዕራብ ግንባር እያደረገ ያለውን የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጠረ
************************

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር ማረፊያ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ ገለጸ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሰራዊቱ በምዕራብ ግንባር እያደረገ ያለውን የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/

08/11/2020
17/10/2020

ትራምፕ እና ግብፅ!

ዶናልድ ትራምፕ የዛሬ አራት አመት ለፕሬዝደንትነት በተወዳደሩበት ወቅት እስካሁን ምንጩ ያልታወቀ 10 ሚልዮን ዶላር የግብፅ መንግስት ንብረት በሆነ ባንክ በኩል ለምርጫ ዘመቻ ቡድናቸው ደርሷል በሚል ጥርጣሬ ከሶስት አመት በላይ ማጣራት ሲሰራ ነበር ተብሏል።

ሲኤንኤን ምንጮቹን ጠቅሶ በሰራው ሰፊ ዘገባ ይህ ገንዘብ ለትራምፕ ቡድን ደረሰ የተባለው እ.አ.አ በ2016 ምርጫው ቀናት በቀሩት ግዜ ሲሆን በዛው ተመሳሳይ ግዜ የያኔው እጩ ትራምፕ እና የግብፁ መሪ አል-ሲሲ ኒውዮርክ በተካሄደው የተመድ ስብሰባ ጎን ተገናኝተው ነበር ብሏል።

ትራምፕ በወቅቱ አል-ሲሲን "ምርጥ ሰው" ብለው ያሞኳሻቸው ሲሆን አል- ሲሲም "ትራምፕ ቢመረጥ ጠንካራ መሪ እንደሚሆኑ እምነቴ ነው" ብለው ነበር።

አሜሪካ ለግብፅ በመወገን ኢትዮጵያ ላይ ያደረሰችው ጫና እዚህ ጋር ይመጣል፣ ይህ በራሱ የሚናገረው ነገር የለም?
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ሃሳብ:🔰

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when International Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share