Gurage news

Gurage news ስለ ጉራጌ ማህበራ,ኢኮኖሚዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በስፋት ?
(1)

በወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዝርፊያ ተፈፀመ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዘረፋ ተፈፀመበት። በዘረፋው በርከት ያለ ጠመንጃ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መ...
14/05/2024

በወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ዝርፊያ ተፈፀመ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዘረፋ ተፈፀመበት። በዘረፋው በርከት ያለ ጠመንጃ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መዘረፋቸው ከምንጮቻችን ሰምተናል። የፖሊስ ፓትሮል መኪናም ከተዘረፉት ንብረቶች መካከል እንደሚገኝ ተሰምቷል። መኪናው ዛሬ ቱሉላሜ የሚባል የገጠር መንደር ውስጥ ጥለውት ሄደው ተገኝቷል።

ዝረፊያው የተፈፀመው ሰኞ ሚያዝያ 5/2016 በግምት ከምሽቱ 7 ሰአት አካባቢ ሲሆን የዘራፊዎቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም።

ፖሊስም ሆነ መንግስት ስለ ጉዳዩ እስካሁን በይፋ የሰጡት መረጃ የለም።

የከተማው ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ጋር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ እጅ ስልካቸው በመደወል ለማግኘት ሙከራ ብታደርግም ስልካቸውን ሳያነሱ ቀርተዋል።

በአሁኑ ሰአት ፖሊስ በአካባቢው እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ነግረውናል። የወልቂጤ ፖሊስ ጣቢያ ተመሳሳይ ዘረፋ ሲፈፀምበት ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑ ይታወቃል።

ተጨማሪ መረጃዎች እናደርሳለን።

Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ

ጉራጌማ ሀገር ነው !  ባለረዥምና ጠንካራ ፍትሐዊ የፖለቲካ አስተዳደር ሥርዓት ባለቤት ነው፥ ይህ ራስን የማስተዳደር ሥርዓት በትንሹ ከስምንት መቶ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል(አንድ ቀን እመለስ...
31/07/2022

ጉራጌማ ሀገር ነው !
ባለረዥምና ጠንካራ ፍትሐዊ የፖለቲካ አስተዳደር ሥርዓት ባለቤት ነው፥ ይህ ራስን የማስተዳደር ሥርዓት በትንሹ ከስምንት መቶ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል(አንድ ቀን እመለስበታለሁ🙏)
ጉራጌ ፈቸት/ኬርታ የተሰኘ እጅግ የከበረ በዘመናት የዳበረ ማሕበራዊ ሥርዓትም አለው፤ አሉታዊ ነገሮችን በበጎ ዕሴቶች ሽሮ ሀገርን የማጽናት ውብ የኢትዮጵያ ልጆች መገለጫ ነው ።
ጉራጌ የሚጠይቀውን ብቻ ሳይሆን፥ መቼ እንደሚጠይቅ፣ እንዴት እንደሚጠይቅና ለምን እንደሚጠይቅ ጠንቅቆ ያውቃል፤ ጥያቄው በኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነትና ሉዓላዊነት ማዕቀፍ ስር በፍጹማዊ ዴሞክራሲያዊነት እየቀረበ ያለ ነው።
በዚህ መልኩ ተምሳሌታዊ ሆነው የሚቀርቡ እንደክልልነት ያሉ የአስተዳደራዊ ሥርዓት ጥያቄዎችን አጢኖ በወቅቱ መመለስ ይገነባል፣ ይጠቅማል፤ በስነአመክንዮ ከተነጋገርን የአንዱ ትክክል ከሆነ የሌላውም እንደዚያው አይደል? እንጂ ጉራጌማ ሀገር ነው !

Via woubshet taye

Let's Go Gurage Regional State...
31/07/2022

Let's Go
Gurage Regional State...

22/07/2022

የብሔረሰብ ፌደራሊዝም እስከቀጠለ ድረስ የጉራጌ ህዝብ የጠየቀው ክልል የመሆን መብት ሊነፈግ አይገባም! ለሙስሊም ክርስቲያን ፍቅር፣ ለባህላዊ ታሪክ፣ ለቱሪዝም... ማሳያ ሞዴል ክልል የመሆን ብርቱ አቅም አለውና። (ዝ)
Taye bogale

ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) ......ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ በ1863 ሶዶ (ክስታኔ) ውስጥ በምትገኝ አጋምጃ በምትባል ቦታ (ደቡብ ሸዋ) የተወለዱ ሲሆን ታላቅ የጉራጌ ጀግና ናቸው። በጣሊያ...
01/03/2022

ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) ......
ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ በ1863 ሶዶ (ክስታኔ) ውስጥ በምትገኝ አጋምጃ በምትባል ቦታ (ደቡብ ሸዋ) የተወለዱ ሲሆን ታላቅ የጉራጌ ጀግና ናቸው።

በጣሊያን (ፋሽስት ) ወረራ ወቅት በመጀመሪያ በመቀሌ ጦርነት ቀጥሎ ደግሞ በአደዋ ጦርነት ጀግንነት የፈፀሙ ታላቅ ሰው ነበሩ ።

(ገበየው ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ)
ተብሎ እስከመገጠም የደረሰ ጀግንነት ሰርተዋል ።

ከአደዋ ጦርነት በኋላ በ1898 እስከ 1908 የሲዳሞ ሀገረ ገዢ ሆነው አገልግለዋል። ከዛ በ1907 የደጃዝማች ይልማ መኮንን ሞት ተከትሎ ደግሞ ከ1910 እስከ 1914 ድረስ የሀረር ሀገረ ገዢ ሆነው አገልግለዋል ።

ከ1917 እስከ 1928 ደግሞ በድጋሚ የሲዳሞ ሀገረ ገዢ ሆነው አገልግለዋል።........

፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤

የ80 ዓመት አርበኛ ዘማች ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ

"ሸምግያለሁ መሞቴ እንደው አይቀር ግነ በሰማይ ንጉስ ምኒልክ በኢትዮጵያ ላይ ማነው የነገሰው ቢሉኝ ምን ብዬ እመልሳለሁ"
አርበኛ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ

የደጃዝማች ባልቻ ሙሉ ስም ባልቻ ሳፎ ይባላል፡፡
"ባልቻ" የሚለው የክስታኔኛው ትርጉሙ (ባሊቅ)ታላቅ ” ማለት ነው። "አባ ነፍሶ" የፈረስ ስማቸው ነው፡፡

(እንኳን ለአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ )

  !
22/02/2022


!

አስራ አንደኛው ቅርንጫፍ ሀይሌ ሪዞርት በወልቂጤ 👏👏
06/02/2022

አስራ አንደኛው ቅርንጫፍ ሀይሌ ሪዞርት በወልቂጤ 👏👏

የአገው ብሔረሰብ እና የጉራጌ ህዝብ ብዙ የታሪክ እና የባህል ቅርርቦሽ አላቸው።
31/01/2022

የአገው ብሔረሰብ እና የጉራጌ ህዝብ ብዙ የታሪክ እና የባህል ቅርርቦሽ አላቸው።

አልነገርሁህም ወይ ባጥር ተንጠልጥዬ የቆንጆ መፍለቂያ ጉራጌ ነው ብዬ 😋😋
24/01/2022

አልነገርሁህም ወይ ባጥር ተንጠልጥዬ
የቆንጆ መፍለቂያ ጉራጌ ነው ብዬ 😋😋

በዚህ ወቅት ላይ በጉራጌ ማህበረስብ ካለው ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ውስጥ ቋንቋው አቀላጥፎ መናገር የሚችለው 25 ፐርሰንቱ (25%) ብቻ መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ስትሰማ ምን ይሰማሃል😭 ...
24/01/2022

በዚህ ወቅት ላይ በጉራጌ ማህበረስብ ካለው ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ውስጥ ቋንቋው አቀላጥፎ መናገር የሚችለው 25 ፐርሰንቱ (25%) ብቻ መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ስትሰማ ምን ይሰማሃል😭 ?

GMH

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share