Duretettaa ogiyaa

  • Home
  • Duretettaa ogiyaa

Duretettaa ogiyaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Duretettaa ogiyaa, Media/News Company, .

30/08/2023
30/08/2023

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከነገ ጀምሮ በሁሉም ክላስተር ማዕከላት መደበኛ ስራቸውን እንደሚጀምር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለክት በጽህፈት ቤታቸው ለሚዲያዎቹ መግለጫ እየሰጡ ነው

ዝርዝር ዘገባዎችን ይዘን እንመልሳለን

30/08/2023

"ህዝቡ ለክልሉ ምስረታ ያበረከተውን አስተዋጽ በልማቱ ስራ መድገም አለበት" ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 24/2015 የክልሉ ህዝብ አዲሱን ክልል ለመመስረት ያበረከተውን አስተዋጽ በልማት ስራው እንድደግም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ ጥላሁን ጠየቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለክት ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥቷል።

ክልሉ ከነገ ከነሐሴ 25/2015 ዓ ም ጀምሮ በሁሉም ክላስተር ማዕከላት መደበኛ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በጽህፌት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።

በክልሉ በስድስቱ ማዕከላት አመራሮች ዋና ዋና ምደባዎች በዚህ ሳምንት እንደምጠናቀቁና ከነባር ሰራተኞች ጋር በማቀናጀት ወደ ስራ የማስገባት ዝግጅት መደረጉንም ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።

የክልሉን ሠላምና ደህንነት የማጠናከር ስራ ከሁሉም ቅድሚያ ተሰጥቶ እንደሚሠራ የገለጹት አቶ ጥላሁን በዚሁም "የሠላሙ ባለበት የሆነው ህዝባችን ለተግባራዊነቱ የራሱን ድርሻ እንድወጣ እጠይቃለው" ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በግብርናው መስክ የመኸር ስራውን በግብዓት መደገፍ፣ መስኖ ገብ አከባቢ ስራዎችን ማጠናከርና የምግብ ዋስትና ስራዎች ላይ ያተኮሩ ስራዎች ላይ ያተኮሩ ድጋፎች እንደሚካሄዱም ገልጸዋል።

ያደሩ የፕሮጀክት ስራዎችን ማጠናቀቅም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸው፣ የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በሁሉም ክላስተር ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል።

የክልሉን ህዝቦች ከሚያለያዩት በላይ የሚያቀራረቡት ይበዛሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ የክልሉን ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በሁሉም ማህበራዊ መሠረቶች ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

የክልሉ ምስረታ በሰላም እንድጠናቀቅ የክልሉ ህዝብ ላበረከተው አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና አቅርበው ይህንን በጎ ተግባር በቀጣይ በልማትም እንድደግም ጠይቀዋል።

28/08/2023

የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን እናፅና!

እኩልነት የሚረጋገጠው፣ ፍትህ የሚነግሰው፣ ሰላም የሚሰፍነው ሁላችንም ለህግ ተገዥ ስንሆን ብቻ ነው። የህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን እንቅፋት የሆኑትን ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን በህግ የበላይነት ማክሰም ያስፈልጋል፤የህግ የበላይነት ካልተከበረ ስርዓት አልበኝነት አገርን እና ህዝብን ዋጋ ማስከፈሉ ሳይታለም የተፈታ ነው።

ስርዓት አልበኝነት በታኝ እንጅ አይሰበስብም፤አፍራሽ እንጂ አይገነባም ፤ለዚህም ነው የህግ የበላይነት መከበር ትናንትም ዛሬም የህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄ የሆነው። መንግስት ደግሞ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሀላፊነትብቻ ሳይሆን ግዴታም አለበት።

የተናጠል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታቸውን ለህዝባችን በሚደግሱት የሁከትና ብጥብጥ ጥሪ ለማሟላት የሚጥሩ ሃይሎችን ስርዓት ለማስያዝ መንግስት የሀይል አማራጮችን ከመጠቀም በመቆጠብ የሚያሳየው ሆደ ሰፊነት ብዙውን ጊዜ ከመጠን ያለፈ መሆኑን ብዙዎች አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል።

መንግስት ለውይይት እና ለምክክር ቅድሚያ በመስጠት ለህዝብ እና ለአገር ህልውና እንደ መጨረሻ አማራጭ ሀይልን መጠቀምን ሲያዘገይ የአቅም ውስንነት የሚመስላቸው የዋሆች ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለዓለም ሰላም የድርሻቸውን የሚወጡ ጀግኖች አገር መሆኗን ጠላትም ወዳጅም የሚረዳው ሀቅ ነው።

የውይይት ባህልን ማዳበር እና የሀሳብ ልዩነቶችን ማስተናገድ ለምንገነባው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ጉልህ ሚና ስለሚጫወቱ ብልፅግና እንደ ፓርቲ እየወሰዳቸው የሚገኙ አበረታች እርምጃዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል።

በሌላ በኩል ደግሞ የእኩልነት፣ የአብሮነት እና የሰላም ፀር የሆኑት ፅንፈኝነት፣ ስርዓት አልበኝነት እንዲሁም አክራሪነት ለህብረ ብሔራዊ አገራዊ አንድነታችንም እንቅፋት ስለሆኑ ህዝባችን ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ለህግ የበላይነት መከበር እያደረገ ያለውን ጉልህ አስተዋፅኦ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

28/08/2023

"የአማራ ሕዝብና መንግሥት ጽናት ያለው እና አስተዋይ ሕዝብ መኾኑን አሳይቷል" አቶ ጥላሁን ከበደ

ወላይታ ሶዶ: ነሐሴ 20/2015 የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር በዓለ ሲመት በባሕርዳር ተካሂዷል።

በበዓለ ሲመቱ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ብዙዎች የአማራ ሕዝብና መንግሥት ጽናት ያለው እና አስተዋይ ሕዝብ መኾኑን በሳምንታት ውስጥ አሳይቷል ነው ያሉት።

የጀግንነት ድል በክብር የሚያከብር ሕዝብ በጥቂት ችግር አይንበረከክም ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ወግ እና ባሕል ያለን፤ ፈጣሪን የምንፈራ በመኾናችን ችግሮቻችንን በሰላም እንፈታለን ነው ያሉት። በፈተና ውስጥ ብልህ አመራር እንደሚፈጠርም ገልጸዋል።

ከአባቶቻችን የወሰድነውን ጽናት ዛሬ ላይ መውሰድ ከቻልን ፤ ፈጣሪን ከፈራን እና ከተከባበርን ችግሮቻችን ይፈታሉ ነው ያሉት።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከአማራ ክልል ጎን እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።

የአማራን ሕዝብ ችግር ላልተረዱና ችግሩን ለሚያባብሱ ሰዎች ጆሮ መስጠት የለበትም ብለዋል። ሀገር የሚመራው በቆራጥ አመራር መኾኑንም ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

25/08/2023
25/08/2023

ሁላችንም ማንነታችን ተከብሮ፣ ወግ እና ባህላችን ተጠብቆ በቋንቋችን፣ በአመጋገባችን በእሴታችን ሳንሸማቀቅ በጋራ የምንኖርባት ሀገር መፍጠር የምንችለው ኢትዮጵያዊነት የሚባል የወል ማንነት እንዳለን ስንረዳ እና ያንን ማንነታችንን እንደጋራ እሴት ወስደን መኖር ስንችል ብቻ ነው።

ቆንጆ ኦሮሞ ሆኖ ውብ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል፣ ውብ ትግራዋይ ሆኖ ቆንጆ ኢትዮጵያዊ መሆን ይችላል።ቆንጆ ሶማሌ፣ አፋር፣ ሲዳማ ወላይታ ሆኖ ዉብ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል።

ኢትዮጵያዊነት አብረን ለመኖር፣ እርስ በእርሳችን ለመደጋገፍ፣ በጋራ ለማደግ የምንገነባው በውስጣችን ተተክሎ የኖረ ለመቀጣጠል ማገዶ የማይፈጅ፣ ከተቀጣጠለ ዳግም የማይበርድ ለዋልታ ረገጦች የሚፋጅ እቶን ማንነት ነው።

25/08/2023

ኢትዮጵያ የብሪክስ ሀገራት አባል ሆነች

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን በአባልነትን ተቀላቀለች።

ምንጭ፦ ኢ ፕ ድ

25/08/2023

የክልሉን አቅም አሟጦ በመጠቀም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል--ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የክልሉን አቅም አሟጦ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ለማምጣትና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በቅርቡ የተመሰረተውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚመሩ አመራሮች ተመድበው ሥራ ጀምረዋል።

በክላስተር አወቃቀር የተደራጀው ክልሉ ስድስት መቀመጫ ከተሞችን በመምረጥ በዋናነት የመንግስትና የህዝብ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ቢሮዎችን የማደራጀት፣ የሰው ሃይል የመመደብና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አቶ ጥላሁን ገልጸዋል።

ቀድሞ የነበረው ክልል ለአንዳንድ አካባቢዎች ርቀት ስለነበረው የመንግሥት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ክፍተት ከመኖሩ ባለፈ የህዝብን ተጠቃሚነትና ወቅታዊ ፍላጎትን ያላማከለ እንደነበር አስታውሰዋል።

ይህንን ሁኔታ ለመቀየር፣ የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላትና ባለቤትነቱን በተጨባጭ ለማረጋገጥ ክልሉ መመስረቱንም አቶ ጥላሁን አስታውቀዋል።

ለክልሉ በመቀመጫነት የተመረጡት ከተሞች ለህዝቡ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመዘርጋትና መልካም አስተዳደርን ማስፈጸም የሚያስችል ነው ብለዋል።

ይህም ህዝቡ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኝ፣ የከተሞችም እድገት የተመጣጠነና የተቀራረበ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።

ክልሉ የተፈጥሮ ጸጋን የተጎናጸፈ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይ ለሜካናይዜሽን ግብርና ልማት አመቺ የሆነ ሰፊ ያልታረሰ መሬት፣ አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች፣ ሰፊ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃ ሀብት ባለቤት መሆኑንም አመልክተዋል።

በክልሉ በሁሉም መስክ በተነደፉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ እቅዶች ፈጣን ልማት ለማረጋገጥና ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት አበክሮ ይሰራል ብለዋል።

ይህንን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የባለሀብቱንና የህዝቡን ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ አቅም አሟጦ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ለማምጣትና ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ ክልሉ የገቢ አቅም እንዳለው የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከተለያዩ አካላት ጋር በመምከር የገቢ አቅምን ከፍ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

በቀጣይ በክልሉ ልማትና እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉም አካላት የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዚአ ዘግቧል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Duretettaa ogiyaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share