አቢቹ ሚዲያ

  • Home
  • አቢቹ ሚዲያ

አቢቹ  ሚዲያ Freedom to our nation!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነገ ያስመርቃል**************የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በነገው እለት ከፍተኛ...
29/01/2024

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ነገ ያስመርቃል
**************
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በነገው እለት ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ያስመርቃል።

የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችም አሉት።

በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየም ያካተተ ነው።

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው ****************** ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል "ግድቤን ለማጠናቀቅ ቃሌን አድሳለሁ" በሚል መሪ ...
21/09/2023

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው
******************

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል "ግድቤን ለማጠናቀቅ ቃሌን አድሳለሁ" በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ሊካሄድ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር፤ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ ለአንድ ወር ለሚቆየው መርሐ-ግብሩ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄው በሁሉም አካባቢዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚዘልቅ መሆኑን ጠቁመው፣ ለስኬቱ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ጠይቀዋል።

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ከ500 እስከ 700 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን ጠቅሰው፣ "ለግድባችን ሁለንተናዊ ድጋፋችን ይጠናከር" የሚል መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

4ኛው እና የመጨረሻው ዙር የውኃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክታቸውንም ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በ2016 ዓ.ም ለግድቡ ግንባታ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ታቅዷል።

Highest paid musicians in Africa- charges per show.1.Wizkid ($200k to $1million2. Burna Boy (200k to $1million3. Davido ...
25/08/2023

Highest paid musicians in Africa- charges per show.
1.Wizkid ($200k to $1million
2. Burna Boy (200k to $1million
3. Davido OBO ($200k to $1million
4.Rema ($150k to $300k
5.Tiwa Savage ($150k to $300k
6. Diamond Platinumz ($100k
7.Black Coffee ($80k
8.Fally Ipupa ($50k
9.Alikiba($50k
10.Sarkodie ($45k
11.Sauti Sol($40k
12.Shatta Wale ($30k
13.Stonebwoy ($30k
14.Harmonize ($25k
15.Nyashinski ($20k
This is the facts about your favorite celebrities payment on show if you inviting them to rock your stage

Keep following us for more update

ርሑስ በዓል ኣሸንዳ !!
22/08/2023

ርሑስ በዓል ኣሸንዳ !!

ድል ለአትሌቶቻችን‼️🇪🇹🇪🇹🇪🇹በ19ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ሀንጋሪ የ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ከደቂቃዎች በኋላ ኢትዮጵያን ወክለዉ✅   ለተሰንበት ግዴይ✅   ...
19/08/2023

ድል ለአትሌቶቻችን‼️
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በ19ኛው ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቡዳፔስት ሀንጋሪ
የ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር ከደቂቃዎች በኋላ ኢትዮጵያን ወክለዉ
✅ ለተሰንበት ግዴይ
✅ ጉዳፍ ፀጋይ
✅ እጅጋየሁ ታዬ እና
✅ ለምለም ሀይሉ ይጠበቃሉ።
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን‼️

አቶ ዮሐንስ ቧያለዉ ፋሪስ ዛሬ ባህርዳር ቀበሌ 11 ጆይ መናፈሻ አባይ ማዶ፣ አንድ ማካሮቭ ሹጉጥ ከሰምንት መሰል ጥይት እና አንድ ሳተላይት ስልክ እንደያዘ ቁጥጥር ስር ውሏል።በነገራችን ላይ...
15/08/2023

አቶ ዮሐንስ ቧያለዉ ፋሪስ ዛሬ ባህርዳር ቀበሌ 11 ጆይ መናፈሻ አባይ ማዶ፣ አንድ ማካሮቭ ሹጉጥ ከሰምንት መሰል ጥይት እና አንድ ሳተላይት ስልክ እንደያዘ ቁጥጥር ስር ውሏል።

በነገራችን ላይ አቶ ዮሀንስ ቧያለው በሰጠው ቃል እራሱን ስራ አጥ ብሎ አስመዝግቧል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የዓለም ዓቀፍ ሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ሼህ መሀመድ ቢን አብዱልከሪም አል ኢሳ ባለ 19 ወለል የአውሊያ የእርዳታ እና የልማት ድርጅት ህንጻ መሰረት ድንጋይ አ...
15/08/2023

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የዓለም ዓቀፍ ሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ሼህ መሀመድ ቢን አብዱልከሪም አል ኢሳ ባለ 19 ወለል የአውሊያ የእርዳታ እና የልማት ድርጅት ህንጻ መሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዘመናት ትውልድን በመደገፍ ለሚታወቀው አውሊያ የሚደረገው ይህ ድጋፍ የትብብር እና የአንድነት ማሳያ ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዶ/ር ሼህ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ፣ የዓለም ዓቀፍ ሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ሼህ መሀመድ ቢን አብዱልከሪም አል ኢሳ እንዲሁም ሌሎች ተጋዝባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

10/08/2023

ጉራ ብቻ❗️

06/08/2023

አራት ኪሎ መግባት በሁለት መንገዶች ብቻ ነው።
1, ለጉብኝት
2, በሠላማዊና ዴሞ/ዊ ምርጫ

02/08/2023

ኡበርህን ትነዳለህ እንጂ ከእንግዲህ ላይ ቁጭ ብለህ የኢትጵያን ህዝብ እያባላህ ገንዘብ አታገኝም::

ተሳክቷል::በ500 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 566 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይን ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
17/07/2023

ተሳክቷል::

በ500 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 566 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይን ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር በበርካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይ...
11/07/2023

ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር በበርካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል

3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ችግር የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ፥ ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ያጋጠመውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው፡፡

ችግሩ እንደተቀረፈም የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቱ ወደነበረበት እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ገቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሁለተኛ ዙሪ የአረንጓዴ አሻራ ልማት  መርሃ-ግብር በጌዴኦ ዞን...
03/07/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ገቡ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሁለተኛ ዙሪ የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ-ግብር በጌዴኦ ዞን ለማካሄድ ወናጎ ከተማ የገቡት፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

  በሙሉእንኳን ለ1444 ዒድ አል አድሃ(አረፋ) አደረሳቹ                      💚💛❤
27/06/2023

በሙሉ
እንኳን ለ1444 ዒድ አል አድሃ(አረፋ) አደረሳቹ

💚💛❤

ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በአንድነት እና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል - ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በአንድነት፣ በመረዳዳትና የተቸገሩ ወገኖችን በመደ...
26/06/2023

ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በአንድነት እና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል - ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ

ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር በአንድነት፣ በመረዳዳትና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ገለጹ፡፡

ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ÷ለ1 ሺህ 444ኛ ዓመተ ሂጂራ የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሳዑዲ ዓረቢያ የሃጂ ስነ ስርዓት ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ ÷በዘንድሮው የሐጂ ጉዞ ከኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሁጃጆች የተሳተፉበት መሆኑን ገልጸዋል።

የአረፋ በዓልን ሕዝበ ሙስሊሙ ሰላሙን በማጽናት፣ በአንድነት፣ በመረዳዳትና የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊያሳልፉ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ሸህ ሀሚድ ሙሳ በበኩላቸው÷ዕለቱ ከሰማይ ወደ መሬት የወረዱት አደምና ሐዋ ከመጠፋፋት በኋላ በሳዑዲ ዓረቢያ አረፋ ተራራ የተገናኙበትን ክስተት እና ከረመዳን ጾም ቆጥሎ የሚፈጸም ኢስላማዊ ስርዓት ነው ብለዋል።

ሐጂ ማለት ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ሁጃጆች ያለምንም ልዩነት ዱዓ እያደረጉ የአደም ልጅነታቸውን ብቻ የሚያስምሰክሩበት የመዳን ዕለት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ይከበራል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሶዶ ከተማ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ጎበኙ  የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣ...
19/06/2023

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሶዶ ከተማ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ጎበኙ

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በወላይታ ዞን ሁለተኛው ዙር ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡

በዞኑ 12 ጊዜያዊ የምርጫ ማስተባበሪያ ማዕከላት 1 ሺህ 812 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኙ 192 የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሠላማዊ መንገድ ድምፁን እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የዞኑ ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ከአየር መንገዱ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይ...
16/06/2023

ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ከአየር መንገዱ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ

አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ፡፡

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዣዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ለፋና ብሮድካስቲንግ በላከው መረጃ ፥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ ከማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በተለያዩ የጋራ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ÷ ከማህበሩ ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉንና አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ በበኩላቸው ÷ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በአቪዬሽን ዘርፍ ያካበቱት የዳበረ የአመራር ልምድ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መልካም እድል መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ኪያ ለማ አክለውም ፥ ከምንጊዜዉም በተሻለ ሁኔታ የሰራተኛዉን ጥቅም በማስከበር ረገድ ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ ያላቸዉን እምነት በመግለጽ ማህበሩ አስፈላጊዉን ድጋፍ ሀሉ የሚሰጥ መሆኑን አረጋግጠዉ መልካምና ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸዉ ተመኝተዋል፡

ሌተናል ጀነራል ይልማ ፥ የሠራተኛ ማህበሩ እያደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑንና ወደፊትም የሠራተኛዉን ጥቅም ከማሳደግ አንጻር ከማህበሩ ጋር በበለጠ አብሮነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡

በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ላይ በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ‼️  ዩኤስኤአይዲ (USAID) ሰሞኑን አጣርቻለሁ ብሎ ባወጣው መግለጫ ለሰብአዊ እርዳታ የመጣን እህል ከሌሎች መንግስታዊ አካላት ጋር በመሆን መከላ...
10/06/2023

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ‼️

ዩኤስኤአይዲ (USAID) ሰሞኑን አጣርቻለሁ ብሎ ባወጣው መግለጫ ለሰብአዊ እርዳታ የመጣን እህል ከሌሎች መንግስታዊ አካላት ጋር በመሆን መከላከያ ሰራዊታችንም እንደተጠቀመ አድርጎ ያቀረበውን ሪፖርት የተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘግቡት አስተውለናል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥብቅ ድስፕሊን የሚመራ ዘመናዊ ሰራዊት ነው፡፡ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚደረግላቸውን ወገኖቹን ቀለብ ሊቀማ ቀርቶ፤ ከቀለቡ ቀንሶ የሚያካፍል ሰራዊት መሆኑን የሃገሩ ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ በአጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም ማስከበር በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ የዕለት ከዕለት ተግባሩ መሆኑን የደረሰላቸው ህዝቦች፤ መንግስታት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሁሉ የሚያውቁት ሰመ ጥር ህዝባዊ ሰራዊት ነው፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ለሰራዊቷ ደመወዝና ቀለብ መስጠት ከጀመረች፤ ቀዳሚ ነን ከሚሉ ሃገራት ተርታ የምትሰለፍ ነፃ እና ታሪካዊት ሃገር ናት፡፡

ሰራዊታችን ዘመናዊ ነው ከሚያስብሉት አንዱ ደግሞ ይኸው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የሎጅስቲክ ግዥ እና አቅርቦት ጉዳይ ነው፡፡ የሰራዊታችን ቀለብ ለሃገር ውስጥ ነጋዴዎች እድሉን በመስጠት በግልፅ ጨረታ ተወዳድረው ስንዴም ሆነ ሌሎች ምግብ ነክ ፍጆታዎች የሚቀርብለት በተሟላ አሰራር እና አመራር የሚመራ ሰራዊት ነው፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት፤

1ኛ. ሠራዊታችን በቂ ሎጄስቲክ ያለው በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉትና በድርቅ ለተጎዱት በዓይነትና በገንዘብ የሚረዳ እንጂ ተቸግሮ ከአሰራር ውጭ የሚጠቀም አይደለም።

2ኛ. ሠራዊታችን ማንኛውንም ዓይነት ምግብ በበጄቱ በሕግና በግልፅ ጫረታ ገዝቶ የሚጠቀም እንጂ ተቸግሮ የሕዝብ እርዳታ አካባቢ ሄዶ እርዳታ ላይ የሚሻኮትበት ዓይነት ድህነት የለበትም። ጥቆማ የሰጠ አካል እንኳ ቢኖር እስኪጣራ ሳይጠበቅ፤ እንደ ተቋምና እንደ ሠራዊት ስም የሚያጠፋ የሚዲያ ሽፋን መስጠት የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ክብር ይነካል።

3ኛ. ምንም እንኳ አገራችን በሚሊዮን የሚቆጠር እርዳታ ጠባቂ ሕዝብ ቢኖራትም ሠራዊቷን መመገብ የምትችልና በቂ ምግብና በጄት በመመደብ ሠራዊቱ ራሱ በሕግና በተቋም ሎጄስትክ አማካኝነት የምትመግብ አገር ናት። ሠራዊታችንም ኩሩና የችግረኞችን ስንዴ የማይሻማ ፕሮፌሽናል ሠራዊት ነው። ስለሆነም የእርዳታ ስንዴ የሚጠቀም ተቋም ወይም ዩኒት ወይም ወታደር የለንም።

4ኛ. ዩኤስኤአይዲ (USAID) በሠጠው መግለጫ መሠረት ምናልባት የመከላከያ አባል የሆነ ወታደር በማይመለከተው ገብቶ ከመዋቅር ውጪ ሕግ የማስከበር ሥራውን ተጠቅሞ ከሌቦች ጋር በመተባበር እርዳታ ተሰርቆ እንዲወጣ በግል የተባበረ ካለ እና ተጣርቶ ከተገኘ የአገር መከላከያ ሠራዊት አመራር የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል።

መከላከያ ሰራዊት ለሃገሩም ሆነ ለዓለም አቀፍ ሰላም መከበር መሰዋትነት የሚከፍል ምስጉን ሰራዊት ሆኖ እያለ፤ በአገራችን ውስጥና በውጪ አገር ያሉ ጥቂት የአገር መከላከያ ሠራዊት ጥላቻ ያላችው ፅንፈኞች እንዳሉ እናውቃለን። መካላከያን የማጠልሸት ሥራ የቆየና የለመድነው ነው።

የመከላከያ ሠራዊታችንን ህዝባዊ ተፈጥሮ፣ አሰራርና ሥርዓት ሳይታወቅና መረጃ እንኳ ቢመጣ፤ አጣርቶ ሳይታወቅ፤ መረጃ የቀረበበት አካል ሳይጠየቅ፤ የሚዲያ ሽፋን መሰጠት ትክክል አይደለም ብለን እናምናለን። የሚመለከታቸው የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያጣሩ እንተባበራለን። ከተጣራ በኋላ ሁሉንም ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን።

“'ዛሬ ነገን እንትከል'! ይህ ዛሬ ለምንጀምረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሁለተኛው ምእራፍ ጅማሮ መሪ ሐሳብ ነው:: 25 ቢሊዮን ችግኞችን የተከልንበት የመጀመሪያ ምእራፍ ተሳክቷል። በ...
08/06/2023

“'ዛሬ ነገን እንትከል'! ይህ ዛሬ ለምንጀምረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሁለተኛው ምእራፍ ጅማሮ መሪ ሐሳብ ነው:: 25 ቢሊዮን ችግኞችን የተከልንበት የመጀመሪያ ምእራፍ ተሳክቷል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ ኢትዮጵያ 25 ቢሊዮን ችግኞችን ትተክላለች። አረንጓዴ ዐሻራ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ነው። የአየር ንብረት ለውጥን እና የአካባቢ መራቆትን ለመቋቋም የወጠንነው ሀገር በቀል አካሄዳችን ነው። የሥራ ዕድል ለመፍጠር አንዱ መንገዳችን ነው። እንዲሁም ለምግብ የሚውሉ ዕጽዋትን በመትከል የምግብ ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነው።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ 😘😘
28/05/2023

እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ 😘😘

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር ተወያዩ*************************ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር በጽህፈት...
27/05/2023

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር ተወያዩ
*************************

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር በጽህፈት ቤታቸው በመገኘት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ከንቲባ አዳነች ከከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር እና አመራሮቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የአዲስ አበባ እና የዋሺንግተን ዲሲ የእህትማማችነት ስምምነት ወደ ተግባር እንዲለወጡ ለማስቻል ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ የትስሰር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አመልክተዋል።

በተለይ በመንግስት እና የግል አጋርነት በሚገነቡ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከተማን መልሶ በማልማት፣ የተሻለ ገቢ አሰባሰብ ፣ የውሃ ማከም ፣ በትራንስፖርት፣ በዙሪያ ካሉ ከተሞች ጋር የልማት ስራዎችን በማቀናጀት ላይ ልምዶችን በመቀመር እና በመለዋወጥ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን አስረድተዋል።

ከንቲባ አዳነች በመንግስት እና የግል አጋርነት በሚገነቡ፣ ከተማን መልሶ የማልማት እና መልሶ በመጠቀም ስራዎችንም መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ለ16 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የርክበ ካሕናት ምልዓተ ጉባዔ ተጠናቀቀአዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ16 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የርክበ ካሕናት ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው እለ...
24/05/2023

ለ16 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የርክበ ካሕናት ምልዓተ ጉባዔ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ16 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የርክበ ካሕናት ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ÷ ምልዓተ ጉባዔው ለቤተክርስቲያኗ አንድነት፣ ሀዋሪያዊ ተልዕኮ እና መንፈሳዊ እድገት እንዲሁም ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በብፁዓን ሊቃነጳጳሳት የሚመራ፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ካሉ ተቋማት ጋር የሚሰራ በመንግስትም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰይሟልም ነው ያሉት፡፡

በኦሮሚያ በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ የነበረው ወቅታዊ ችግር እንዲቀረፍ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ከፌደራልና ኦሮሚያ ክልል ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሱ መወሰኑንም ተናግረዋል።

በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች አህጉረ ስብከቶች ላይ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙንም ነው የገለጹት፡፡

በትግራይ አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነት እንዲቀጥል ቀደም ሲል የተሰየመው ልዑክ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል መወሰኑንም ነው የተናገሩት።

በቅድስት አባተ

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች  አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ባደረባት ህመም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በ...
12/05/2023

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አንጋፋዋ ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ድምጻዊት ሒሩት በቀለ ባደረባት ህመም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በህክምና ስትረዳ ቆይታ ህይወቷ ማለፉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቿ ተረድቷል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው ክልላዊ መድረክ ተጠናቀቀ***********************************የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያፀደቃቸው የክልሉ መልሶ...
11/05/2023

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው ክልላዊ መድረክ ተጠናቀቀ
***********************************

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያፀደቃቸው የክልሉ መልሶ ግንባታ እቅዶችንና አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ ሲካሄድ የቆየው ክልላዊ መድረክ ተጠናቋል።

መድረኩ በትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ ለማካሄድ ከክልል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር የሚሰሩ እቅዶች ስትራቴጂዎችና አቅጣጫዎች ላይ የተሟላ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ታልሞ የተካሄደ ነው ተብሏል።

በመድረኩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት፣ የወረዳና ከተሞች የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረት በክልሉ ከላይኛው እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ያለው አመራር በታያዙት ዕቅዶችና ስትራቴጂዎች ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ፖለቲካዊ ስነ ምህዳር የማስፋት ጉዳይ ለትግራይ ህዝብ የተሟላ ነጻነት ከማረጋገጥ ውጭ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ እንደሌለም አብራርተዋል።

በዚህም በዴሞክራሲ ያሉትን ግድፈቶች ማሟላትና ማስፋት፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን ማረጋገጥ ይገባልም ነው ያሉት።

ህዝብ የማይፈልገውን አመራር ልናስቀጥል አንችልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው፣ በአስተዳደር ያለ ችግር በአስተማማኝ ደረጃ እስከተፈታ ድረስ ሊንቀሳቀስ የሚችል አቅም እንዳለና የፋይናንስ ችግርንም ማቃለል እንደሚቻል መግለጻቸውን የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

አንጀቴ በርሀብ መታጠፉን አውቃ ትጠብቀኛለች እራቴን አሙቃ።
10/05/2023

አንጀቴ በርሀብ መታጠፉን አውቃ
ትጠብቀኛለች እራቴን አሙቃ።

82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው*******************************82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ ...
05/05/2023

82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
*******************************

82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ እየተከበረ ነው።

በዓሉ አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል ።

"አብሮነት ለጽናትና ድል" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የመታሰቢያ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከድል ሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በመታሰቢያ በዓሉ ላይ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች ፣ አባትና እናት አርበኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም ንጋት ላይ መድፍ ተተኩሷል።

አርበኝነት የመላው ኢትዮጵያውያን የነጻነትና የአንድነት መገለጫ በመሆኑ በመስዋዕትነት ሃገርን በአንድነት ላቆዩልን ጀግኖች ዐርበኞቻችን በየዓመቱ ሚያዝያ 27 በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

በዋለልኝ ታምር

እንኳን ለዐርበኞች ቀን(የድል በዓል) አደረሳችሁኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ያላት ሀገር ነች። ነጻነታቸውን በምንም ነገር ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት እናቶቻችን እና አባቶቻችን ...
05/05/2023

እንኳን ለዐርበኞች ቀን(የድል በዓል) አደረሳችሁ

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ያላት ሀገር ነች። ነጻነታቸውን በምንም ነገር ለመቀየር ፈቃደኛ ያልሆኑት እናቶቻችን እና አባቶቻችን ለነጻነት ሲሉ ዋጋ ከፍለዋል።

እናቶቻችን እና አባቶቻችን ሕይወት ከፍለው ያቆዩልን ነጻነት ብቻቸውን አይቆምም። በሌሎች ነጻነቶች መደገፍ አለበት። ሀብት፣ ኅብረትና አገልጋይነት ሊደግፉት ይገባል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ በርትተን ሀገራዊ ሀብት ካልፈጠርንና ከርዳታ ካልተላቀቅን ነጻነት ብቻውን ሩቅ አይወስደንም። ኩሩ ድኻ ያደርገናል እንጂ። ኅብረት ፈጥረን መለያየትንና መከፋፈልን ካላሸነፍን ነጻነት ብቻዉን ኃይል አይሆነንም። በኅብረት ያገኘነው ነጻነት በመለያየት በፈቃዳችን እናጣዋለንና።

ሀገርንና ሕዝብን በቅንነትና በትጋትና በንጽሕና ለማገልገል ካልወሰንን ነጻነት ብቻውን ዕድገት አያመጣም። ሙስና፣ ኋላ ቀር አሠራርና ስንፍና ወደኋላ ይጎትቱናልና።

የድል ቀናችንን ስናከብር ከዐርበኞቻችን ድል በኋላ ያስመዘገብናቸውን ድሎች በመቁጠር መሆን አለበት። ድል የማይወልድ ድል ድል አይባልም።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዚያ 27፣ 2015 ዓ.ም

የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል (በፎቶ) 📸፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
04/05/2023

የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል (በፎቶ)

📸፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቢቹ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share