Hadiya.Tv

Hadiya.Tv Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hadiya.Tv, TV Network, .

25/10/2019

Ethiopian activist Jawar Mohammed called for calm on Thursday a day after 16 peo...

16/10/2019
16/10/2019

በኬተሪንግ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር፣ የፖለቲካ ተንታኝና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፕሮፌሰር ህዝቄል ገቢሳ ከሀዲያ ሚዲያ ኔት ወርክ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ የተለያዩ ጉዳዮችን ዳሰዋል፡፡ ከዳሰሷቸው ጉዳዮች መካከል የደቡብ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ያነሱትን ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች እና ጥያቄዎችን ለማፈን ደኢህዴን እየሄደበት ያለውን አካሄድ አስመልክተው ያነሷቸው ነጥቦች ቀልብ የሚስቡ ናቸው፡፡ ቃለ ምልልሱን ላልተከታተላችሁ የሚዲያችን ተከታዮች ዋና ዋና ነጥቦችን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

• የደቡብ ብሄሮች እያነሱት ያለው ጥያቄ የሚፈቀድና የማይፈቀድ ሳይሆን ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ነው፡፡ የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎቹ በኢትዮጵያ ህገመንግስት ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የመብት ጥያቄ ነው፡፡ የህዝብ ጥያቄ ህገ መንግስታዊ መሰረት ካለው ማንም ሊቀለብሰው አይችልም፡፡

• በደቡብ ክልል እየተነሱ ያሉ የሰብዓዊ መብት፣ የዲሞክራሲ እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ላይ እኛ ብቻ አይደለንም እየታገልን ያለነው፡፡ የዓለም ህዝብ ሁሉ ከእኛ ጋር ነው፡፡ ከምንም በላይ ጥያቄያችን እውነት ላይ የተመሰረተ ስለሆበነ፣ ሀቅ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ጥያቄዎቹ ሁሉም የሚመለሱ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ትክክለኛ ህጋዊ፣ ህገ መንግስታዊ፣ ሰው ልጅ መብት ጥያቄ ነው፡፡

• ኢትዮጵያ ውስጥ እየተጠየቀ ያለው የእኩልነት ጥያቄ ነው፡፡ እኩልነት ጥያቄ መጠየቅ ወንጀል ከሆነ እኩልነትን ልናገኝበት የምንችልበትን ሌላ መንገድ እንፈልጋለን፡፡ የህዝብ ጥያቄ ጊዜ ይፈጃል እንጂ ምላሽ ማግኘቱ የማይቀር ነው፡፡ ስለዚህ ተረባብረን ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡

• በሲዳማ የተፈጠረውን መጠነኛ ችግር ተከትሎ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ኮማንድ ፖስት ማወጅ እጅግ አሳፋሪ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ዋጋ ያለው ነገር አይደለም፡፡ የሚውል የሚያድር አይደለም፡፡

• በተለይም በደቡብ አካባቢ ያለውን ህዝብ ካልናቅከውና፣ መሃይም ነው፣ የፖለቲካ ስራ አይገባውም ብለህ ካላሰብክ ባስተቀር ስለ ብሄረሰቡ ጉዳይ፣ ራሱን በራሱ ስለማስተዳደር ጉዳዮች ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎቼ ናቸው ብሎ እየጠየቀ ያለውን ህዝብ አታልዬ የፓርቲ ስም ቀይሬ ምርጫ አሸንፋለሁ የሚለው ለኔ አይገባኝም፡፡

• ደኢህዴን አደረጃጀቱ ያለቀለት ይመስለኛል፡፡ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልም አሁን ባለንበት ሁኔታ አሁን ያለቀለት ይመስለኛል፡፡


• ደቡብ ላይ ያለው አደረጃጀት ህገ መንግስቱ ከሚሰጠው መብት ጋር እየሄደ አይደለም፡፡ በዚያ ክልል ውስጥ በሀይል ተይዞ የነበረው ከምባታ፣ ሀዲያ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ሀላባ፣ ከፋ እና ሌሎችም የህገ መንግስቱን አካሄድ ተጠቅመው መብታቸውን ሊያስከብሩ እየሄዱ ባሉበት ሰዓት ደኢህዴን አሁንም ጨፍልቄ እይዛለው ብሎ የሚሄድበት መንገድ አስቸጋሪ ነው፡፡

• እነዚህ ጥያቄዎች የፓርቲዎቸ ጥያቄ አይደሉም፣ የልህቃን ጥያቄ አይደለም፣ ሀዲያ ክልል የመሆን ጥያቄ የሀዲያ ልህቃን የሚያቀርቡት ጥያቄ አይደለም የህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ የሲዳማ ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ የሌሎችም እንዲሁ፡፡ ይህን ለማፈን መሞከር አስቸጋሪ ነው፡፡

• ስለዚህ አፍኜለሁ ማለት የሚቻለው ለዛሬ የመንግስትን ሀይል ተጠቅመህ፤ የመከላከያን ሀይል ተጠቅመህ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጠቅመህ ለጊዜው ማፈን ይቻላል፡፡ ማፈን ግን ምን እንደሚያመጣ እናውቃለን፡፡ ማፈን ለጊዜው ታፍናለህ፡፡ በኋላ ግን ይፈነዳል፡፡ ይህ ፖለቲካ አይደለም ፊዚክስ ነው፡፡ ካፈንከው ይፈነዳል፡፡ ስለዚህ የህዝብን ጥያቄ ማፈን አይቻልም፡፡ ማፈንም አይገባም፡፡

• በተለይም አሁን ባለንበት በመገናኛ ብዙሃንም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ህዝቡ መብቱ ባወቀበት ሰዓት የወታደርን ሀይል ተጠቅመህ ማፈን አትችልም፡፡ ምክንያቱም ወታደር ውስጥ ያለው እኮ ሀዲያ ነው፡፡ ወታደር ውስጥ ያለው እኮ ሲዳማ ነው፡፡ ወታደር ውስጥ ያለው እኮ ከምባታ ነው፡፡ ወታደር ውስጥ ያለው እኮ ኦሮሞ ነው፡፡ ወታደር በራሱ ህዝብ ላይ እየተኮሰ አይኖርም፡፡

• አሁን ወታደር ነው እየገዘ ያለው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወታደር መተኮስ እየተወ ከህዝቡ ጋር መወገኑ አይቀርም፡፡ ኢኮኖሚውም እየተዳከመ ይሄዳል፡፡ ስለዚህ መቆጣጠር የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱ የማይቀር ነው፡፡

• ታሪክን ያየን እንደሆነ ወደ ኋላ ለመመለስ የሚፈልጉ አሸንፈው አያውቁም፡፡ ታሪክን ያየን እንደሆነ ኢምፔራሊስቶች አሸንፈው አያውቁም፡፡ ስለዚህ ማየት ያለብን ወደፊት ነው፡፡

25/09/2019
23/09/2019
23/09/2019
22/09/2019
19/09/2019

አዲስ የሀዲይኛ የባህል ሙዚቃ በቅርብ ቀን ለህዝብ ጆሮ እንደሚያሰማ ድምፃዊ ስንታየሁ ጥላሁን(ሂቦንጎ) አስታውቋል።

ሙዚቃው በቅርብ ቀን ይለቀቃል ብሏል!

19/09/2019
17/09/2019
17/09/2019
17/09/2019
17/09/2019
17/09/2019
07/09/2019

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya.Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share