Lomi Tube - ሎሚ ቲዩብ

  • Home
  • Lomi Tube - ሎሚ ቲዩብ

Lomi Tube - ሎሚ ቲዩብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lomi Tube - ሎሚ ቲዩብ, Media/News Company, .

የታዋቂው ፈላስፋ ግራሽያን ባልታሳር ጠቃሚ የህይወት ምክሮች
14/08/2023

የታዋቂው ፈላስፋ ግራሽያን ባልታሳር ጠቃሚ የህይወት ምክሮች

የእውቁ ፈላስፋ የግራሽያን ባልታሳር ጠቃሚ የህይወት ምክሮች እና የብልህነት መንገዶች መካከል አምስቱ

ተተረጎመ ‼️አሳዛኙ የራሕዋ ገብረዋሕድ ደብዳቤ(ቆቦ፣ ደጋ በላጎ ከኪሷ ከተገኘ)***************************************************" ከታጋይ ራሕዋ( ሚጡ) ለመላ...
07/10/2022

ተተረጎመ ‼️
አሳዛኙ የራሕዋ ገብረዋሕድ ደብዳቤ
(ቆቦ፣ ደጋ በላጎ ከኪሷ ከተገኘ)

***************************************************
" ከታጋይ ራሕዋ( ሚጡ) ለመላ ቤተሰቤ፦

በመጀመሪያ ለተከበራችሁት ለምወዳችሁ ወላጆቼ ፣ ወንድም እኅቶቼና ቤተሰቦቸ ሆይ ! ይቺ ምትክ (አቻ) የማይገኝላት የእግዚአብሔር ፀጋ ለሆነዉ ጤናችሁ እንደምን አላችሁ? ለማለት እወዳለሁ። ደኅና እንደምትሆኑ ደግሞ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
- እኔ ግን ናፍቆታችሁ እንደ ዉኃ ይጠማኛል፤ እንደ እንጀራ ይርበኛል፤ እንደሰማይ ርቆኝ መቻል አቅቶኛል። ግን እችለዋለሁ። የማይቻል የለም። ኹሉንም ለፈጣሪ ሰጥቼዋለሁ። ጸሎቴንም አላቋረጥኩም። ኹሉም የእግዚአብሔር ፈቃድ እስከሆነ ድረስ የሚበልጠዉ በተስፋ መኖር ነዉ ብዬ ነዉ እማምነዉ።
-በተለይ ያቺ ሩሕሩሕ ፣የዋህ የሆነቺዉና ነፍሴን አሳልፌ የምሰጣት፣ ከሌሎች እናቶች ጋር የማላወዳድራት እናቴ (ኣብረኸትዬ ) የኔ ማር የሆንሽዉ አንድ ቀን እንኳ እፎይ ሳትይ ከችግር ወደ ችግር የሆነዉ ህይወትሽ እንዴት ኾኖ ይኾን ? አብረኸትዬ ዘወትር ባንቺ የተነሳ ሳስብና ስጨነቅ እዉላለሁ። አላረፍኩም።
በተለይ የኔን እገዛ በሚያስፈልግሽ ጊዜ አላገዝኩሽም። ከሁሉም በላይ ደጋፊ የሌለዉን ቤታችንን በህመም ምክንያት ሳልነግርሽ ትቸሽ ሄድኩ። ምክንያቱም ከፊቴ ስታለቅሺ ማየት አልፈለኩም። ከወንድሜ ከገ/ሕይወት ይልቅ እኔ እዘምታለሁ ብዬ ወስኛለሁ። ምክንያቱም እኔ ከማግዛችሁ ይልቅ እሱ የሚያግዛችሁ ስለሚበልጥ ነዉ። አትቅየሙኝ። አብረኸትዬ በኔም የተነሳ አታስቢ (አትጨናነቂ)። ደኅና ነኝ። አሁን በህልሜም በእዉኔም እየመጣ ከአቅሜ በላይ ሆኖ የሚያስቸግረኝ ጉዳይ የመልከኛዉ፣ ምሑሩ እና ልባሙ ወንድሜ የሃለቃ በርሄ ጉዳይ ነዉ።
ከቀናት በፊት መጥፎ ህልም አይሉት ቅዠት አየሁ። እዉነትም መሰለኝ። ከወንድሜ በርሄ ጋር የተያያዘ መስሎኝ ከእንቅልፌ ብድርግ ብዬ ተነስቼ ማልቀስ ስጀምር ጓደኞቼ "ምን ሆነሽ ነዉ?" ብለዉ ጠየቁኝ። እኔም ያስጨነቀኝን ቅዠት ነገርኳቸዉ። እነሱም ህልሙ ጥሩ መሆኑን ነግረዉ አፅናኑኝ። እኔም ኹሉንም ለበጎ ያድርገዉ ብዬ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ነገርኳት።
በርሄ ወንድሜ ጤናህ እንዴት ነዉ ? እንደቀድሞዉ መለስ አላለልህም? ከቤተሰቦችህ ጋር ቤተክርስቲያን እያገለገልክ ነዉ? ከጓደኞችህ ጋር እየተጫወትክ እንደማገኝህ በጉጉት እጠብቃለሁ።
በርሄ ወንድሜ በዚህ እገዛ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ትታኝ ሄደች ብለህ አደራ እንዳታዝንብኝ (እንዳትቀየመኝ) ! የኔ ማር ይቅርታ እየጠየኩህ ነዉ። ጊዜዉ ሲደርስ ደግሞ እክስሃለሁ። ሰላም ነዉ ያለኹት እንገናኛለን።
-ባባ (ገ/ዋሕድ ብርሃኔ) (ሣሙና) )፣ ወንድሜ ገ/ሕይወት ፣ እኅቴ ትርሓስ ፣ ማኅደር ፣ ዳናይት ፣ ዳንኤል (ፀጋዬ)፣ ወንድሜ አሉላ ፣ ወንድሜ ቢኒያም እስከምንገናኝ ኹላችሁንም ሰላም ሰላም ብያለሁ።
ለመገናኘት ደግሞ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መልካም ፈቃድ ነዉና ስለኔ አትጨነቁ:: በተጨማሪም ለኹሉም ጎረቤት ሰላም በሉልኝ።
- ለእናቴ (አብሻይ)፣ አረጋዊ ፣ ጨርቆስ ፣ ማርቆስ ብቻ ኹሉንም ሰላም በሉልኝ።
- ያዬ (ብርሃነ ግደይ) ሥ ደኅና ነዉ? እያረጀ ነዉ እንዴ? ምግበይሥ እንደምን ነዉ ? ዳንኤል ገ/ሄርንም ሰላም በሉልኝ። የሹስ ተሻላት ወይ ? ሰላም በሉልኝ:: በተጨማሪም ለኹሉም ቤተሰብ ሰላም በሉልኝ። ቻዎ ፣ ቻዎ !!

07/08/2022

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቀ ዕቃ ተቀብለው በሚገዙ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ኦፕሬሽን ከ1ሺህ 200 በላይ ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ::

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክ/ከተሞች የተሰረቀ ዕቃ ተቀብለው በሚገዙ ግለሰቦች ላይ ጥናትን መነሻ ተደርጎ በተደረገ ኦፕሬሽን ከ1ሺህ 200 በላይ ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥናትን መነሻ አድርጎ ባደረገው ኦፕሬሽን በአራዳ፣በልደታ፣በቂርቆስ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣በየካ፤በአዲስ ከተማ፤ በአቃቂ ቃሊቲ እና በቦሌ ክ/ከተሞች የተሰረቀ ዕቃ ተቀብለው የሚገዙ ግለሰቦች ዕቃዎቹን ደብቀው በሚያስቀምጡባቸው ቤቶች ላይ ባከናወነው ኦፕሬሽን እና በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ ልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አለማየሁ አያልቄ ተናግረዋል፡፡

ብርበራ ከተደረገባቸው 82 ቤቶች ውስጥ 1ሺህ 2 መቶ 32 ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ 87ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ የመሰረተ ልማት ኬብሎች፣ 231 ስፖኪዮ ፤ 3 ቴሌቪዥን፤ 6 ፕሌስቴሽን፤ 1 ወታደራዊ ሬዲዮ እና ሌሎች በርካታ የተለያዩ የመኪና እቃዎች መያዛቸውን የገለፁት ረዳት ኮሚሽነር አለማየሁ፤ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 69 ተጠርጣሪዎች እና ኤግዚቢቶችን በህግ አግባብ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ የሚፈፀሙትን የቅሚያ፣ የስርቆት እና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል የጀመረውን ስራ በማገዝ በኩል በቀናነት መረጃ በመስጠት ተባባሪ ለሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ረዳት ኮሚሽነር አለማየሁ አያልቄ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም እንዳብራሩት የሚፈፀሙ ማነኛውም አይነት የወንጀል ተግባራትን ለመከላከል የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ንብረት የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች ቀርበው ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው መውሰድ እንደሚችሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

07/08/2022



የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lomi Tube - ሎሚ ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share