Doba'a Times ዶ'ባዓ

  • Home
  • Doba'a Times ዶ'ባዓ

Doba'a Times ዶ'ባዓ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Doba'a Times ዶ'ባዓ, Media/News Company, .
(1)

አይ መንፈሳዊ ሙዝቀኞች😆🤨
01/02/2024

አይ መንፈሳዊ ሙዝቀኞች😆🤨

በጂቡቲ ፓርላማ ምክርቤት ደጅ ላይ 🚩⚔️የአዳሎች ወታደር👌
30/01/2024

በጂቡቲ ፓርላማ ምክርቤት ደጅ ላይ 🚩⚔️
የአዳሎች ወታደር👌

Afar Triangle 3🔼
26/01/2024

Afar Triangle 3🔼

አፍሪካ የሚለው የአህጉራችን ስያሜ የመጣው አፋር ከሚለው ቃል መሆኑ ስንቶቻችን እናውቃለን ?😍👌
22/01/2024

አፍሪካ የሚለው የአህጉራችን ስያሜ የመጣው አፋር ከሚለው ቃል መሆኑ ስንቶቻችን እናውቃለን ?😍👌

 #የጤፍ ምርት በአፋር !በበርሃ ጤፍ አይዘራም ብዘራም አይበቅልምና አትልፉ ሲባል የነበረው እርኩስ ምክር ስህተት ብቻ ሳይሆን ሞያዊና መዋቅራዊ ሴራም ጭምር ነው። አልፎም ሀገርና ህዝብን ያለ...
17/01/2024

#የጤፍ ምርት በአፋር !

በበርሃ ጤፍ አይዘራም ብዘራም አይበቅልምና አትልፉ ሲባል የነበረው እርኩስ ምክር ስህተት ብቻ ሳይሆን ሞያዊና መዋቅራዊ ሴራም ጭምር ነው። አልፎም ሀገርና ህዝብን ያለ ምክኒያት መግደልም ነው።

ይህ ከሥር የምትመለከቱት በአፋር ክልል ገቢ ረሱ (ዞን3) ሀንሩካ ወረዳ በመሰብሰብ ላይ የሚገኝ የጤፍ ምርት ነው።

የአፋር ህዝብና ሀገር ባለፉት በርካታ ዘመናት በአራት ኪሎ ገዥዎች በሚደረግበት መዋቅራዊና ሞያዊ ሴራ ስለባ ሆኖ ከሀገር ፖለቲካም ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮአዊ ገፀበረከትም እንዲገለል የተደረገ ህዝብ መሆኑ የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው።

ታሪክ ማንም ልከላከለው የማይችል ክስተቶችን ሁሉ መዝጋቢ ቋጥ ነው።

Afar Agiira🚩⚔️
11/01/2024

Afar Agiira🚩⚔️

 ?ዋናው ነገር ምን አለህ? ማነህ? የት ነህ ያለኸው? ወይም ደግሞ ደስተኛ የሚያደርግህን አሊያም የሚያስከፋህን ስራ አሁን እየሰራህ ነዎይ የሚለው አይደለም። ዋናው ነገር አንተ ስላለህበት እ...
13/10/2023

?

ዋናው ነገር ምን አለህ? ማነህ? የት ነህ ያለኸው? ወይም ደግሞ ደስተኛ የሚያደርግህን አሊያም የሚያስከፋህን ስራ አሁን እየሰራህ ነዎይ የሚለው አይደለም።

ዋናው ነገር አንተ ስላለህበት እውነታ ምን እያሰብክ ነው የሚለው ትልቅ ትርጉም ይ'ሰጠዋል።

ሊያጠቁህ ከሚፈልጉ ጠላቶችህ ይልቅ በውዳሴ -ከንቱ የሚያንበሸብሹህን ጓደኞች ፍራ።

ስኬትህን በውድቀቶችህ ላይ በመቆም አንጸው።

ውድቀት እና ብርታት ወደ ስኬት የሚያደርሱህ በአንድ የተሰሩ መወጣጫ ደረጃዎች ናቸው።

ለሰዎች መውደድ እንዲሰማህ እና ተጨማሪ ሁለት ጓደኞችን ለማፍራት ሁለት ወራት ይፈጅብሃል። ነገር ግን ሰዎች አንተን እንዲወዱህ ሁለት አመታት ይፈጅብሃል። የትኛው አድካሚ ይመስልሃል?

☑️ አየህ ስለመወደድህ ብዙ ጊዜ አታጥፋ፤ በህይወት መውደድህ በቂ የሚሆንበት ብዙ ገጠመኝ አለ። ሰው ያስፈልግሃል ማለት ሊወድህ ግድ ነው ማለት አይደለም። መውደድህ እንጂ መወደድህ ላንተ ሊረጋገጥልህ አይችልም። ሻሎም።🙌

በጠብታ ማር ደራሲ ዴል ካርኒጌ

#2ተኛው ዕትም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::

📗📙📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

👇
ቲክቶክ- https://www.tiktok.com/
ቴሌግራም- https://t.me/teklu_tilahun
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/booklandbook/

የፌድራል መንግስት ያለ ምንም ጥፋት ያሰሯቸው እነዚህ ወጣቶች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ እናሳስባለን !!!እነዚህ ሁለት ወጣቶች በአምባገነኑ አወል አርባ የቤተሰብ አገዛዝ እየተጨቆነና እየተ...
30/09/2023

የፌድራል መንግስት ያለ ምንም ጥፋት ያሰሯቸው እነዚህ ወጣቶች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ እናሳስባለን !!!

እነዚህ ሁለት ወጣቶች በአምባገነኑ አወል አርባ የቤተሰብ አገዛዝ እየተጨቆነና እየተዘረፈ ለሚገኘው ለአፋር ህዝብ የፍትህ ድምፅ ከማሰማታቸው ሌላ አንዳች ጥፋት ያላጠፉ መሆናቸው የሚታወቅ ነው።

የአፋር ሴቶች የፀጉር አሰራር ❤🙏
20/09/2023

የአፋር ሴቶች የፀጉር አሰራር ❤🙏

''እያየለ የመጣው የጨው ሀብት ዘረፋ, የጨው ምርጥ ለገበያ እንዳይቀርብ በመንግሥት መከልከሉ እንድሁም ከ6 ወራት በላይ ለአምራቾች ክፍያ አለመከፈሉ ህዝቡን ለከፍተኛ ቁጣ መደረጉን ከወደ-አፋ...
19/09/2023

''እያየለ የመጣው የጨው ሀብት ዘረፋ, የጨው ምርጥ ለገበያ እንዳይቀርብ በመንግሥት መከልከሉ እንድሁም ከ6 ወራት በላይ ለአምራቾች ክፍያ አለመከፈሉ ህዝቡን ለከፍተኛ ቁጣ መደረጉን ከወደ-አፋር የደረሰን ተጨባጭ መረጃ ይገለፃል

''በአገራችን ኢትዮጵያ በማዕድን ሀብት ክምችት ስመጥር ከሚባሉ ክልሎች የአፋር ክልል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ ።

''በክልሉ ከሚገኝ ከተለያዩ የማዕድን ሀብቶች የአፋር ማህበረሰብ በንቃት የሚሳተፉበትና ለመሰረታዊ ፈላጎት ማሟያ በቀደምትነት የሚሰራው የጨው አምራችነት እና አቅርቦት ስራ ነው ።
ይህ ለብዙሃን የኑሮ መሰረት የሆነው የጨው ምርት ስራ በውስን የመንግሰት ባላስልጣናት እና ከባለስልጣኖች ጋር በሽርክና በሚሰሩ በጥቂት ባለሀብቶች በሞኖፖል መያዙንና የሀብቱ ባለቤት የሆነው ሰፊው የአፋር የአርብቶ አደር ህዘብ ከዳር ሆኖ ለመመልከት መገደዱን ከወደ አፋር የደረሰን መረጃ ያትታል

''ከዚህ በተጨማሪ በጨው ምረጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ980 በላይ አምራቾች ለጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ላቀረቡት ጨው ምርጥ ከ6 ወራት በላይ ክፍያ አለመገኘታቸውን አስረግጦ ይናገራሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ብዙ መዋለ ንዋይ የፈሰሰበት የጨው ምርጥ ለገበያ እንዳይቀርብ በመንግስት በመከላከሉ አምራቾች ለከፍተኛ ኪሳራ መደረጋቸውን ይገልፃሉ

''የፍትሕ ያለህ ፍትሃዊ ጥያቄ በፍትሃዊነት ይመለስ !
,,ፍትህ አግላይ አይደለችምና ፍትህ ለሰፊው ህዝብ !
,,መንግሰት የተበዳዮችን ቅሬታ ልብ በማለት ፍትሃዊ ምላሸ እንዲሰጥና የተበዳዮችን እንባ እንዲያብስ እንማፀናለን..!
By: ነጋሽ መሀመድ

17/09/2023

''Record'ik Sah Calli Kah Weenim Matan'' Mr ''X'' 🙄

አዋሽ የቀይ ባህር ገባር 🐪🚧
30/08/2023

አዋሽ የቀይ ባህር ገባር 🐪🚧

Sahdayti Baxih Fayxi Qaran Kee Ardi Fanal Enna Itta Ginoona Kee Ginoona Caalatittek Inkih Mutcaag Tanim Kinnuk Badaay Ba...
29/05/2023

Sahdayti Baxih Fayxi Qaran Kee Ardi Fanal Enna Itta Ginoona Kee Ginoona Caalatittek Inkih Mutcaag Tanim Kinnuk Badaay Barril Inna Itta Mano Siiratittet Fantaaxaw Le Sahdayti Baxi Ginoona Lih Le Dagar Fayxi Kalah Ginoona Le Caalatitte Loowit Kee Abinal Inkih Edde Lowsiissa Misinkica Curriino Kee Doorit Margaqa Lem Kinnuk A Baadih Fanal Inna Itta Ginoona Isi Fayxit Koborak Loowsiisaamih Giclok Masoola....

Maqe Rabbi S.W Kah Iyyennah :-
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡

Tohih Taagah Sahdayti Baxi Aginoh Addal Suuruk Fayxil Loowite Waamak Sa Tanimiy Dagar Kee Misinkica Fayxi Kaak Loowittaah Faxxa Inkih Isih Elle Faxanna Kee Faxximtannal Lowsiisam Yalli Kaah Yecee Muxxot Duuduh Elle Kaa Duudusennal Duudam Raq Mali...

Maqe Rabbi S.W Kah Iyyennah :-
أَلَمْ تَرَوْا أَنَّ اللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَأَسْبَغَ عَلَيْكُمْ نِعَمَهُ ظَاهِرَةً وَبَاطِنَةً ۗ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

አላህ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን? ከሰዎችም ያለ ዕውቀትና ያለ መሪ፣ ያለግልጽ መጽሐፍም በአላህ የሚከራከር አልለ፡፡

وَسَخَّرَ لَكُمُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ وَالنُّجُومُ مُسَخَّرَاتٌ بِأَمْرِهِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፡፡ ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ፡፡


Tawayi Qasril Sahdayti Baxi Qaran Kee Ardi Fanal Yabixen Cinsikka Sinni Qeerih Tan Qamburre Koborak Makiinal Erra Heeh Baaxok Baaxo Beyak Roobuh Korsaanam Maadeh Geytima....

أَفَمَن يَخْلُقُ كَمَن لَّا يَخْلُقُ ۗ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን አትገሰጹምን

Tah Sahdayti Abem Cakkum Nel Takkem Mafaxximta Maqnah Sahdayti Baxi Anna lem Kee Kalah Tanim Ardi Kee Qaran Fanal Abu Duuduh Yalli Kaa Gine Wakaak Kaat Hee Muxxot Duudam Neh Warsem Kinnuk...

Maqe Rabbi S.W Kah Iyyennah :-

وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡

وَعَلَّمَ آدَمَ الْأَسْمَاءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمْ عَلَى الْمَلَائِكَةِ فَقَالَ أَنبِئُونِي بِأَسْمَاءِ هَٰؤُلَاءِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ (ተጠሪዎቹን) አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን (ተጠሪዎች) ስሞች ንገሩኝ» አላቸው፡፡

قَالَ يَا آدَمُ أَنبِئْهُم بِأَسْمَائِهِمْ ۖ فَلَمَّا أَنبَأَهُم بِأَسْمَائِهِمْ قَالَ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ إِنِّي أَعْلَمُ غَيْبَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَأَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا كُنتُمْ تَكْتُمُونَ

፡-«አደም ሆይ ስሞቻቸውን ንገራቸው» አለው፡፡ ስሞቻቸውን በነገራቸውም ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር ዐውቃለሁ፤ የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡

Allah Waqlm 🤲

ዳጉና- ዳጋና.በጂቡቲ ታጆራ ክልል የፋሽስት እስማኤል ኡመር ጌሌ ወታደር ካንፕ ላይ ከትላንት በስቲያ የጂቡቲ አፋር ነፃነት ግንባር በድንገት በተከፈተው ከባድ ጥቃት በጨቋኙ ጌሌ ወታደር ላይ ...
09/10/2022

ዳጉና- ዳጋና.
በጂቡቲ ታጆራ ክልል የፋሽስት እስማኤል ኡመር ጌሌ ወታደር ካንፕ ላይ ከትላንት በስቲያ የጂቡቲ አፋር ነፃነት ግንባር በድንገት በተከፈተው ከባድ ጥቃት በጨቋኙ ጌሌ ወታደር ላይ ከባድ ኪሳራና እርምጃ እንደተወሰደ ከስፍራው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች አረጋግጠዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ በእስማኤል ጌሌ ቤተሰባዊ አገዛዝ የሚመራው ሱሰኛ ወታደሮች አፀፌታዊ ምላሽ ለመስጠት በሚለው ሰበብ የአፋር ህዝብ የሚኖርበት የጂቡቲ ገጠር ክፍሎች ማለትም ምዕራባዊ የዴኼል ክልልና የታጆራ ክልል እንዲሁም የኦቦኽ ክልል ገጠራማ አከባቢዎች ላይ በማሰማራት በአከባቢዎች የሚኖሩ የአፋር ህዝቦች በኢሳ-ሶማሌ ጥምር ጦር እንዲፈጅ እያደረጉ ይገኛሉ!

ከጂቡቲ አፋር ነፃነት ግንባር በኩል ደሞ መሰል ጥቃቶች በብዙ የጂቡቲ ግዛቶች ላይ እንደአስፈላጊነቱ እንደሚደረግና እንደውም የእስማኤል ጌሌ ቤተሰባዊ አገዛዝ ለመገርሰስ የተሟላ ውጊያ በስርአቱ ወታደራዊ ማዕከላት ላይ እንደሚከፍቱ በማስረገጥ የጌሌን አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ከምድረ ገፅ እስኪወገድ የነፃነት ትግላቸው እንደማያስቆሙ እየገለፁ ይገኛሉ።

07/01/2022

As wr wb qafar sidiicamoh baarak

ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ተጀመረአዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስ...
25/12/2021

ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ዛሬ ተጀምሯል ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በመድረኩ ተገኝተዋል።

መድረኩ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ነው የተገለፀው ።

መድረኩ ጥቅምት ወር ላይ ባህር ዳር በተካሄደው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች መድረከ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ይገመግማል ።

እንደዚሁም ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።

በአልአዛር ታደለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

25/12/2021

የአፋር ህዝብ በመድፍ እየወተጋ ንብረቱና ህይወቱ እየጠፋ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ጦርነት ማድርግ አቁመናል የሚለው በምን መስፈርት ነው?

As written by S**o Lema."አብዓላ" ከአጋም የተጠጋችዋን ቁልቋል ታስታውሰኛለች፡፡አሸባሪው ቡድን-ህወሓት ከተወሸቀባት መቀሌ ከተማ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ በአፋር ክ...
25/12/2021

As written by S**o Lema.

"አብዓላ" ከአጋም የተጠጋችዋን ቁልቋል ታስታውሰኛለች፡፡

አሸባሪው ቡድን-ህወሓት ከተወሸቀባት መቀሌ ከተማ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ በአፋር ክልል የዞን 2 መዲና ናት፡፡ ተራራ እንደ ቀለበት የከበባት የሽብር ቡድኑ አይኑ የሚቀላባት ወሳኝ ከተማ፡፡ አብዓላ የራሱ የአብዓላ ወረዳ እና የከተማ አስተዳደሯም ተጠሪ ናት፡፡

"ወሮበላው ቡድን ንፁሃን ዜጎችን እና ከተሞችን ሲያፈራርስ ይህችን ሃገር 27 አመት ይቅርና 27 ቀን ያስተዳደረ አይመስልም" ያስባለኝን ሰዋዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለባት አሳዛኝ ስፍራ ሆናለች፡፡

"ወታደሮቼን ከአፋርና አማራ ክልል ሙሉበሙሉ አስወጥቻለሁ፡፡ ጦርነቱንም አቁሜያለሁ" የቀረኝ ቢኖር የፌደራል መንግሥቱንና ጥምር ኃይሎቹን በር ለሰላም ማንኳኳት ነው" ሲል ለጋላቢዎቹ ጭምር እያስተጋባ የተለመደ የአዞ እንባውን ሲያነባ ነበር አሸባሪው ህወሓት፡፡ "ከወረርኳቸው አካባቢዎች የወጣሁት ፈቅጄ ነው፤ ተቀጥቅጬ አይደለም፡፡ አያይ...እነዛን የምድርም የሰማይም ድሮኖች እያዩ በተቻለ መጠን ወደ ኋላ አለመፈርጠጥ ከባድ ነበር" እያለም ወጋ ነቀል ሲያደርግ አለም እኩል ታዝቦታል፡፡ ለዚህ ነው ቡድኑ "መንታ ምላስ" ነው የሚባለው፡፡

ለማነኛውም ህወሓት ደርሶ "የሰላም ደቀ መዝሙር እኔ ነኝ" ያለበት ንግግሩ አግራሞት መፍጠሩን ሳያበቃ በሰሜናዊ አፋር-አብዓላ ከተማ ሌላ ጥቃት ከፍቷል፡፡

ሲሰናዳ ቆይቶላት አሁን ተረኛዋ አብዓላ ሆነች እንጂ የሽብር ቡድኑ በሌሎች ከተሞችም ያሳየን ተጠባቂ ክስተት ነው፡፡ ቀማኛው ቡድን ሲለው አልምቶ ሊቀማት፤ ሲሻው በቁሟ ሊዘርፋት ሲከጅላት የኖረች አዳጊ ከተማ ናት-አብዓላ፡፡ ግን ደግሞ የክፋት እጁን ተቋቁማ ብዙ ትግራዋዮችንም በጉያዋ አቅፋ እያያት አበበች፡፡ እስከ ቅርብ አመታትም እንደመዥገር ሲመጣት እንደነበር ለማወቅ ገጿን አጥብቆ መመልከት በቂ ነው፡፡ አብዓላ ይህ አጥፊ ቡድን በሞግዚትነት ሲያስተዳድራት የነበረች ከተማ ናት ማለት ይቻላል፡፡

በሆቴል ዘርፍ ጀምሮት የነበረው ድራማ በአስረጂ ምሳሌነቱ የሚስተካከለው የለም፡፡ በየትኞቹም የኢትዮጵያ ከተሞች ለማድረግ ቀርቶ ለማሰብ የሚከብደውን "55 ባለ 5 ኮከብ ኢንተርናሽናል ሆቴሎችን እገነባለሁ" በሚል የግንባታ ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ ሲያስገባ ቆይቶ የራሱንና የጥቅም ተጋሪዎቹን ሆድ ሞላባት፡፡ አብዓላም የሆቴል ሳይሆን የብረት ከተማ ሆና ቅይጥ መልክ ይዛ ቆማ ቀረች፡፡

ይኸው አሁን ደግሞ ዙሪያዋን የከበባትን ተራራ ተስታኮ በከባድ መሳሪያ እያደበያት ነው፡፡ የአፋር አናብስቶች ከከተማዋ ጠራርገው አስወጥተው ከተራራ አናት ቢሰቅሉትም፡፡

በአብዓላ ከተማ እንደሱ ሳይሆን እንደ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ተማምነው የኖሩ ትግራዋዮች በአፋር ወገኖቻቸው ላይ ከውስጥ እጃቸውን እንዲያነሱ አድርጓል፡፡ ብዙዎች "ዳግመኛ ደሴ" እያሉዋት ነው፡፡ የተቀሩትን ደግሞ ለክፉ ቀን ብሎ ባስቀመጠው ከባድ መሳሪያ ጠላቴ ካለው የአፋር ህዝብ ጋር አብሮ አስክሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ አድርጓቸዋል፡፡ ህወሓት ይህንን ሲያደርግ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ በፈራረሱ ግድግዳዎች ላይ ተመሰቃቅለው የቀሩ ያኔ የበላባቸው ወጨቶች እንኳ የሚታዘቡት ይመስላሉ፡፡

አብዓላ አሁን የእምነት ተቋማቶቿ ሳይቀሩ ተቀጥቅጠውባት መልኳ ወይቧል፡፡ ከ"አጋም የተጠጋችዋ ቁልቋል"ም አይደለች? ሰርክ እንባ ይፈሳታል፡፡ ታነባለች፡፡ አጋሙ በቧጨራት/በወጋት ቁጥር ቁልቋላ ማልቀስ ግዷ ነው፡፡ ለየብቻ ቢፈጥራቸውም አብረው አሉና!
እና አብዓላ ታለቅሳለች፡፡ ያኔ በቁም አሁን በሞት አፋፍ ባሩድ ለብሳ፡፡

አጭር ግጥም ለአደዋ ባ*ዳና የአጎዋ እድል ነሽዋ ባ*ዳ !''ኢትዮጲያ በአደዋ ባ*ዳዎች አጥታለች የአሜሪካ አጎዋ'' 😃አሜሪካ ለአደዋ ባ*ዳዎች ወግና አጥታለች በአፍሪካ ህልውናዋ!የአደዋ ባ*ዳ...
24/12/2021

አጭር ግጥም ለአደዋ ባ*ዳና የአጎዋ እድል ነሽዋ ባ*ዳ !

''ኢትዮጲያ በአደዋ ባ*ዳዎች አጥታለች የአሜሪካ አጎዋ'' 😃

አሜሪካ ለአደዋ ባ*ዳዎች ወግና አጥታለች በአፍሪካ ህልውናዋ!

የአደዋ ባ*ዳዎች ደሞ አጥተዋል ስልጣንና አደዋ!

የኢትዮጲያ ህዝብ የራሱን ህልውና አስከብረዋል በአንድነት ባ*ዳዎችን እየተዋጋ .😎💪

አፋር በአለም ደረጃ ከቻይና ቀጥሎ 1.5 ሚልዮን የጦር ሠራዊት ያለው ህዝብ ነው። 😎
24/12/2021

አፋር በአለም ደረጃ ከቻይና ቀጥሎ 1.5 ሚልዮን የጦር ሠራዊት ያለው ህዝብ ነው። 😎

ሰበር ዜናየትግራይ ወራሪ ሀይል የአፋር ሰሜናዊው ዞን ዋና ከተማ በሆነቺው አብዓላ ወረዳ ላይ አድስ የወረራ ግንባር በመክፈት መቃብሩን እያስፋፋ ይገኛል።በጣረሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው የትግራይ...
18/12/2021

ሰበር ዜና
የትግራይ ወራሪ ሀይል የአፋር ሰሜናዊው ዞን ዋና ከተማ በሆነቺው አብዓላ ወረዳ ላይ አድስ የወረራ ግንባር በመክፈት መቃብሩን እያስፋፋ ይገኛል።

በጣረሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው የትግራይ ወራሪ ሀይል በአፋር ዳግም ወረራ መክፈቱ የህወሓት ውድቀት ከማፋጠን ባሻገር በሌሎች የአፋርና ወሎ ግንባሮች እንደተቀበሩ ከመቀበር ውጭ የሚያመጡት አንድም ተአምር እንደሌለ እርግጥ ነው ።

ድል ለጀግኖቻችን 💪🤲

26/11/2021

ጁንታው በአፋር ህዝብ ላይ በየትኛውም ዘመን ያልተፈጠረ፣ ታሪክ የማይረሳው ከትውልድ ትውልድ የሚዘከር ግፍ አድርሷል!

አሸባሪወ የህወሀት ጁንታ የአፋር ህዝብ ላይ መቼም የማይረሳ ጠባሳ አሳርፏል፣ ያደረሳችሁት የዘር ማጥፋት ወንጀል በታሪክ ተመዝግቧል! በ #ጋሊኮማ ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ አሸባሪው ህወሀት የፈፀመው እጅግ አረመኔያዊ ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል ከባድ ነው።

አሸባሪው የህወሀት ቡድን ሰላማዊውን የአፋር ህዝብ ለሰላም ቅድሚያ ባለ፣ ኢትዮጵያዊነትን ባለ የተለያዩ ወረዳዎች ማለትም ከ ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ፣ ጎሊና፣ አውራ እና ኡዋ ወረዳዎች፣ ከኪልበቲ ረሱ በራህሌና መጋሌ ወረዳዎች፣ ከአውሲ ረሱ ዞን ጭፍራ እና አድ ደአር ወረዳዎች እንዲሁም ከሀሪ ረሱ ዞን ተላለክ፣ ደዌና ሰሙሮቢ ወረዳ /አደድሌ ሄንጌግ ቀበሌ/ ዘልቆ በመግባትና በመውረር፣ በርካታ ሴቶች፣ ህፃናትንና አዛውንቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ በከባድ መሳሪያ በመደበደብ አረመኔያዊ የዘር ጭፍጨፋ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ ፈፅሟል። በርካታ የህዝባዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ዘርፏል፣ መስጂዶችንና የሀይማኖት ትምህርት መስጫ መድረሳዎችን አውድሟል፣ አርክሷል።

ይህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትም የአፋር ህዝብን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያስቆጣ፣ ሴት ወንዱ ሁሉም ይህን እኩይ ተግባር ለመመከት እና እርምጃ ለመውሰድ እንደ አንድ ሰው ሆኖ የዘመተበት እና ወራሪው ጁንታ ሰርጎ በገባባቸው ግንባሮች ሁሉ የእጁን ያገኘበት ነው።

ወትሮውም ለሰው ልጅ ምን አይነት ርህራሄ የሌለው እና ባደረሰው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሌላ ሁለተኛ ጉዳት ትርፍ የሚፈልገው እና የአስመሳይነት አባዜ የተጠናወተው አሸባሪው ህወሀት ለ 27 አመታት የአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ሰብአዊ ኪሳራ አልበቃ ብሎት፣ በቅርቡ ያደረገው ወረራ እና የአፋርን መሬት ወደ ራሱ በማካለል "ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ እንመሰርታለን" በማለት ያደረገው ሙከራ አልሳካ ሲል "የአፋር ፌደራሊስት ሀይሎች" በሚል በማወናበጃ በሪሞት የሚያንቀሳቅሰው ቡድን ለመመስረት ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛል።

በቅርቡ እንኳን ያደረሰውን በደል ወደ ኋላ በመተው አዛኝ በመምሰል በአፋር ህዝብ ላይ ሌላ ግድያ፣ ሌላ ዝርፊያ ለመፈፀም የሚደረግ ሙከራ መሆኑን የአፋር ህዝብ የሚያውቀውና የሚረዳው በመሆኑ ፕሮፖጋንዳቸው መሰረተ ቢስና ተቀባይነት የለውም።

ከዚያም አልፎ በስሙ "መግለጫ" መሰል ማወናበጃ ፕሮፖጋንዳም ለመንዛት እየሞከረ ይገኛል። እዚህ አሸባሪው ህወሀት እያወቀ እንዳላወቀ የሚሆነው ነገር የአፋር ህዝብ በውሸት ፕሮፖጋንዳ የሚደናበር ሳይሆን ከጥንት ከአያት ቅድመ አያት ሲወራረሰው የመጣ የመረጃ ማጣሪያ እና ማስተላለፊያ ስርአት #ዳጉ ባለቤት መሆኑን ነው። ለዚህም ነው በርካታ ፕሮፖጋንዳዎችን በአፋር ህዝብ ላይ ቢነዛም አንድኛውም ግብ ሊመታለት ያልቻለው፣ ነገም ከነገ ወዲያም አይሳካም፣ ምክንያቱም አፋር በእውነተኝነት ላይ የተገነባ፣ ለእውነት የሚሰዋ፣ ካልነኩት የማይነካ፣ ከነኩት ደግሞ፣ ጠላቱን ልክ የሚያስገባ፣ እጅግ ሲበዛ ታጋሸ ፣ ነገር ግን በደልንና ኢ ፍትሀዊነትን መሸከም የማይችል ጀግና ኢትዮጵያዊ ነውና።

አፋር በማንነቱ የሚኮራ፣ ራሱን በራሱ በማስተዳደር ላይ ያለ፣ በኢትዮጵያዊ አንድነቱ ላይ ፈፅሞ የማይደራደር፣ አፋርነቱ እና ኢትዮጵያዊነቱ ፈፅሞ ተጋጭተውበት የማያውቅ እውነተኛ ፌደራሊዝምን የሚከተል አብሮነትን እና አንድነትን ከራስ ማንነት ጋር የሚሰብክ የኢትዮጵያ ደጀን ህዝብ ስለሆነ ሽብርን እና ሰላም ማደፍረስ በፍፁም አይታገስም፣ በማወናበጃም ሆነ በማደናገሪያ አይሸበርም።

ጁንታው ህወሀት "ሀ" ብሎ በአፋር ህዝብ ላይ ሽብር ሲያውጅ በማይሆን ስሌት ለአፋር ህዝብ ያለውን ንቄት በቪዲዮ ተለቆ እያንዳንዱ አፋር ጆሮ እና አይን ደርሷል፣ ስሌታቸው እጅግ የተሳሳተ እንደነበረም የአፋር ህዝብ ከሁሉም ጫፍ ተንቀሳቅሶ በሁሉም ግንባሮች ድልን በመጎናፀፍ በሚገባው ቋንቋ ምላሽ ሰጥቷል።

አሁንም ቢሆን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አሸባሪው ህወሀት ማታለያ ተደልለው የጁንታው ቀበሮ ጉድጓድ የገቡ ጥቂት ግለሰቦች የአፋርን ህዝብ የማይወክሉ፣ የአፋርን ህዝብ ለመውጋት እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚተባበሩ አካላት ከአሸባሪው ህወሀት ፈፅሞ ተለይተው የማይታዩ መሆናቸውን ልብ ሊሉ ይገባል። የአፋር ህዝብ የአፋር ህፃናት ፣ ሴቶችና አዛውንቶችን የጨፈጨፈ እና ተባባሪ የሆኑ አካላትን ለመመከት እና ለማጥቃት ከጫፍ ጫፍ ተነስቷል።

በመጨረሻም አሸባሪው ህወሀት ዛሬም ነገም ሊረሳው የማይገባው ነገር አፋር ያው አፋር ነው፣ ትናንት የነበረው አፋር ዛሬም ነገም የሚኖረው ያው አፋር ነው፣ በአፋራዊ ማንነቱና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ጀግና ኢትዮጵያ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን ሊዘነጋ አይገባም!

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ሰመራ

ለአፋር ሕዝብ ጠላትን የሽንፈት ካባ ማከናነብ አኩሪ የጀግንነት ባሕሉ ነው******************* (ኢ ፕ ድ) ለአፋር ሕዝብ ጠላትን የሽንፈት ካባ አከናንቦ መመለስ ጥንትም የነበረ አኩ...
26/11/2021

ለአፋር ሕዝብ ጠላትን የሽንፈት ካባ ማከናነብ አኩሪ የጀግንነት ባሕሉ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ለአፋር ሕዝብ ጠላትን የሽንፈት ካባ አከናንቦ መመለስ ጥንትም የነበረ አኩሪ የጀግንነት ባሕሉ ነው ሲሉ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሙሳ አደም ገለጹ፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሰርጎ በገባባቸውና ወረራ በፈጸመባቸው የአፋር አካባቢዎች የፀጥታ መዋቅሩና ሕዝቡ ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሠብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ወደ መጣበት ተመልሷል።

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሙሳ አደም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአፋር ሕዝብ ከህወሓት ጋር እያደረገ ባለው ራስን የመከላከል ጦርነት አንጸባራቂ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የአፋር ሕዝብ ሰላም ወዳድ ነው ያሉት አቶ አደም ሊወረው የመጣን ጠላት ግን አሳፍሮና የውርደት ካባ አከናንቦ መመለስ ጥንትም የነበረ አኩሪ የጀግንነት ባሕሉ ነው ብለዋል፡፡

ድል ያለ መስዋዕትነት እንደማይገኝ የአፋር ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፤ ለዚህም አስፈላጊውን ሁሉ እየከፈለ ወረራውን እየመከተ ይገኛል ነው ያሉት።

ድል ሁሌም ከሃቀኞች ጎን በመሆኑ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ የአፋር ሕዝብም በአሸባሪው ህወሓት እብሪት ተገዶ በገባበት ጦርነት በወራሪው ላይ ድል እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል፡፡

አቶ ሙሳ የአፋር ሕዝብ ከአባቶቹ የወረሰው 'ዳጉ' የተሰኘው ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ባሕል ያለው መሆኑም ሌላው የድሉ ምስጢር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሕዝቡ ማኅበራዊ ስሪት በትንሹ የማይበረግግና ለጠላት የማይመች እንደሆነም ነው የገለጹት።

የአፋር ሕዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሠላም ነው ያሉት አቶ ሙሳ፤ ህወሓት የማን አለብኝ እብሪቱን የሚቀጥል ከሆነ እስከመጨረሻው ለመታገል ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doba'a Times ዶ'ባዓ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share