Haaro Media House

  • Home
  • Haaro Media House

Haaro Media House A Media Company!

03/04/2023

ቀናችሁ የፈካ ይሁን!

Zelalem Coffee

02/04/2023

There are several reasons why people choose to drink organic coffee. One of the main reasons is that organic coffee is grown without the use of synthetic fertilizers, pesticides, or herbicides. This means that the coffee beans are free from harmful chemicals that can be harmful to human health and the environment. Organic coffee is also grown using sustainable farming practices that promote soil health, biodiversity, and water conservation. By supporting organic coffee farming, consumers can help to protect the planet and promote sustainable agriculture.

Another reason to drink organic coffee is that it is often of higher quality than conventionally grown coffee. Organic coffee is often grown in high-altitude regions, which can result in a slower growing process and a more complex flavor profile. Additionally, organic coffee is often shade-grown, which provides a more diverse ecosystem for birds and other wildlife. This can lead to a more balanced and flavorful coffee bean. By choosing organic coffee, consumers can enjoy a high-quality, flavorful cup of coffee while also supporting environmentally friendly farming practices.

Zelalem Coffee

07/12/2022
https://gudumaale.com/track/Dxltq44YTyYdIyT Ani Atera - Adugna Duumo - Faayya Baxillu Sirba - Gudumaale.com- Qaenna Nafa...
27/05/2022

https://gudumaale.com/track/Dxltq44YTyYdIyT
Ani Atera - Adugna Duumo - Faayya Baxillu Sirba - Gudumaale.com
- Qaenna Nafarchunni ha'nanni woyt jaalla, gobba, maatenna fiixu qalli yaanno. Konne sirba baxxinanni - qulli yiino'ne mannira koyisidhe.
Adugna Duumo - Ani Atera - Gudumaale.com aana Calla.!

Adugna Duumo - Ani Atera

08/05/2022
04/11/2021

ምርጥ የመኪና ማቆሚያ፣ ከአስተማማኝ ጥበቃ ጋር፣ በከተማዋ አዲሱ መናሐሪያ ፊትለፊት በምቹ መኝታና ደረጃቸውን በጠበቁ ክፍሎቻችን በኢትዮጵያዊ ስነምግባር ይስተናገዱ።
ቡርቅቶ ሆቴል ሁሉም አለ።

ባህል+ አገልግሎት --- ቡርቅቶ ሆቴል

አፍጋንን በቁጥር-የአፍጋኒስታን የ20 ዓመት ታሪክ በቁጥር ምን ይመስላል? ለአመክሮና ለተዘክሮ ይሆን ዘንድ እነሆ:- 9/11 (2001 እኤአ) - የሽብርተኞች ጥቃትን ተከትሎ ጆርጅ ቡሽ Oct...
22/08/2021

አፍጋንን በቁጥር
-
የአፍጋኒስታን የ20 ዓመት ታሪክ በቁጥር ምን ይመስላል? ለአመክሮና ለተዘክሮ ይሆን ዘንድ እነሆ:-

9/11 (2001 እኤአ) - የሽብርተኞች ጥቃትን ተከትሎ ጆርጅ ቡሽ Oct 7, 2001 አፍጋኒስታን ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ አስጀመረ፣

2014 (እኤአ) - ባራክ ኦባማ ጦርነቱ በይፍ እንደተጠናቀቀ አሳወቀ፣ "በድል ተጠናቋል" ነበር ያለው፣

19 - አሜሪካ በታሪኳ እረጅም ሁኖ የተመዘገበውን ጦርነት ለ19 ዓመታት አካሄደች፣

4 - አራት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች (ቡሽ፣ ኦባማ፣ ትራምፕና ባይደን) ከጦርነቱ ጋር ተነካክተዋል፣

800,000 - 20 ዓመት በሚጠጋው ወታደታዊ ዘመቻ ከ800,000 የአሜሪካ ወታደሮች ተሳትፈውበታል፣

2,352 - አሜሪካ ለቃ እስከወጣችበት ቀን ድረስ 2,352 የአሜሪካ ወታደሮች በሸማቂው ታሊባን ተገድለዋል፣

20,000 - ከ20,000 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ቁስለኛ ሁነዋል፣

66,000 - በአሜሪካ ሞግዚትነት የተቋቋመው የአፍጋን መንግስት 66,000 ወታደሮች (የራሱን ዜጎች) ገብሯል፣ ሙት!

47,245 - በጦርነቱ የሞቱ ንፁሐን ዜጎች 47, 245 ደርሷል፣

51 - በዚህ ጦርነት ውስጥ 51 ሀገራት ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፣ በኔቶ ስም መሆኑ ነው፣

1,144 - ከላይ የተጠቀሱት 51 የኔቶ አባል ሀገራት 1,144 ሰራዊታቸን ገብረዋል፣

441 - ህይወታቸውን ያጡ የእርዳታ ሰጪ ድርጅት ሰራተኞች ቁጥር 441 ነው፣

75 - ጦርነቱ የበላቸው ጋዜጠኞችና የሚዲያ ሰራተኞች ቁጥር 75 ደርሷል፣

51,191 - የአሜሪካን የሞግዚት አስተዳደርን የተቃወሙ 51,191 ንፁሐን ዜጎች ደመ-ከልብ ሁነዋል፣

2,261,000,000,000 - አሜሪካ በዚህ ጦርነት ያወጣችሁ ከ2 ትሪሊየን $ በላይ መሆኑ ተመዝግቧል፣

145,000,000,000 - ለጦርነቱ በቀጥታ ከወጣው በተጨማሪ ከ146 ቢሊየን $ በላይ አፍጋኒስትንን መልሶ ለመገንባት አውጥተናል ይላሉ፣ "ቀልዱን ተይ" አለ ጥላሁን ገሠሠ

300,000 - አሜሪካ ደረጃ አንድ ስልጠና ሰጥቼ ዘመን ያፈራው መሳሪያ አስታጥቂያቸዋለሁ ያላቸው የአፍጋን ወታደሮች ቁጥር 300,000 ናቸው፣ እንደ ባይደን ገለፃ ይህ የሰለጠነ እና የታጠቀ ሰራዊት ከአብዛኞው የኔቶ አባል ሀገራት የተሻለ ነው፣ በአስር ቀን ውስጥ ድምጥማጡ እንደጠፋ አስታውሱ፣

2,500,000 - በጦርነቱ ምክንያት ስደት የገቡ፣ ሀገራቸውን የለቀቁ፣ የተባበሩት መንግስታት የሚያውቃቸው የአፍጋን ስደተኜች ቁጥር ከ2,500,000 በላይ እንደሆነ ተመልክቷል፣

10 - የአሜሪካ መንግስት ነቅሎ ሲወጣ ታሊባን ካቡል ለመድረስ የፈጀበት ቀን 10 ቀን ብቻ ነው።

የድምፅ አሰጣጥ ህደቱ  ቅደም ተከተል
20/06/2021

የድምፅ አሰጣጥ ህደቱ ቅደም ተከተል

Some houses in Nigeria*
20/06/2021

Some houses in Nigeria*

19/06/2021

የሶሻል ሚዲያ ፌክ አካውንት እንዴት ማወቅ እንችላለን?
መፍትሄው ምንድነው? Part II
with Samuel Tesfaye

መረጃ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትና የግብፁ ፕሬዚዳንት ሲሲ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከመሸ በስልክ ተወያይተዋል።በውይይታቸው ላይ የግብፅ ፕሬዚዳንት  ኢትዮጵያ በምትገነባው ግድብ ላይ አስቸኳይ ስምምነት ...
24/05/2021

መረጃ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንትና የግብፁ ፕሬዚዳንት ሲሲ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከመሸ በስልክ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ላይ የግብፅ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያ በምትገነባው ግድብ ላይ አስቸኳይ ስምምነት እንዲደረስ አሜሪካ የሚጠበቅባትን፣ እንድትሰራ ጠይቋል። የናይል ወንዝ የግብፅ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ የግብፅ ህዝብና መንግስት የሚተማመንባት ወዳጅ ሀገር አሜሪካ በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮች ወደመሀል ገብተው እንዲያሸማግሉ ነው ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ሲሲ ፕሬዚዳንት «ጆ» ባይደንን ተማፅኗል።
«ጆ» ባይደን በበኩሉ፣ በህዳሴው ግደቡና በሊቢያ በእስራኤል ፍልስጤም ጉዳይ የሚመክር ልኡካን በቅርብ ቀን ወደ ግብፅ እንልካለን ያሉ ሲሆን፤ ግብፅ በመካከለኛው ምስራቅ በሰላምና ሽብርተኝነት በመዋጋት ደረጃ ለምታደርገው አስተዋጽኦ አመስግነዋል !
ሱሌማን አብደላ

24/05/2021

ገራሚ ቪዲዮ

ውብቷ ሀዋሳ
24/05/2021

ውብቷ ሀዋሳ

Every thing will be OK.TOKICHAW.
08/03/2021

Every thing will be OK.
TOKICHAW.

Jossi in the house : J Resort  | የአርቲስት ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ ኢን ዘ ሐውስ) በአዳማ ቀበሌ 10 የሚገኘው ጄ ሪዞርት
20/02/2021

Jossi in the house : J Resort

| የአርቲስት ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ ኢን ዘ ሐውስ) በአዳማ ቀበሌ 10 የሚገኘው ጄ ሪዞርት

👉ግማሽ የእድሜ ዘመን ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለለት ፍቅር!!👉ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ሰው ለማ ሀይሌ ይባላል ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ሲሆን ከ20 አመታት በላይ አሁን የቆመባት ቦታ ላይ ሆኖ...
19/02/2021

👉ግማሽ የእድሜ ዘመን ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለለት ፍቅር!!
👉ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ሰው ለማ ሀይሌ ይባላል ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ሲሆን ከ20 አመታት በላይ አሁን የቆመባት ቦታ ላይ ሆኖ አካባቢውን በዝምታ እየቃኘ ይጠብቃል።
👉አይናገር ፣አይጋገር፣ በቃ ረዥም የዝምታ አርምሞ ውስጥ ሆኖ ያለመሰልቸት መጠበቅ ነው ፍላጎቱ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም መንገደኞች የሚበላውንም ፍራንኩንም ይሰጡታል እንጂ አይጠይቅም::
👉ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ሰውየው ኢንጂነር ነበር ከረዥም አመታት በፊት አሁን የቆመበት ቦታ ላይ የሚወዳት ፍቅረኛው ቤተሰቦቿ ከእሱ ለመለየት ብለው ውደ ውጭ እንደሚልኳት በማወቋ ልትሰናበተው ሄዳ አብራው ልትሆን እንደማትችልና ጥላው እንደምትሄድ ነግራው ወደ ሃገረ አሜሪካ አቀናች::
👉ለማ ከዚያች ቀን ጀምሮ ስራውን ለቀቀ ጥልቅ ፀጥታ ውስጥ ገባ ጠዋት ይነሳና ከጀሞ ጎፋ ካምፕ ድረስ በእግሩ በመጓዝ የተሰነባበቱበት ቦታ ላይ ቀኑን ሙሉ በመጠባበቅ ይቆማል ጎዳናውን በአይኑ ይቃኛል።
👉የሚጠብቅው ሰው እንዳለም ለማወቅ አይከብድም ሲመሽ በዝምታው ውስጥ እንዳለ ቀጥ ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ መኖሪያ ይጓዛል አመታት ነጎዱ፣ አካባቢው ተለወጠ፣ ለማ ግን አሁንም ከሚያጨሰው የሲጋራ ጭስ ጋር አብሮ በሃሳብ እየነጎደ ያለመታከት ቆሞ ይጠብቃል። 👉ነፋስና ፀሐይ ፊቱን ቀይሮታል እሱ ግን ዛሬም በፀጥታ ተሞልቶ አይኑን ጎዳናው ላይ እያንከራተተ ዘንድሮም ይጠብቃታል ::
#ማብቂያ እና ወሰን የሌለው መጠበቅ!!
👉አማኑኤል ይልማ ግጥም እና ዜማ ሰርቶ ሀይለየሱስ ግርማ ዘፍኖታል ..."ከሌለሽበት_ቦታ_ያሚል " ሚካኤል በላይነህ- ደሞ ትመጪ እንደው እያልኩ የሚለውን ዘፍኖለታል
👉ከጥቂት አመታት በፊት ፍቅረኛው ስለ ለማ እየሆነ ያለውን በመስማት ልታገኘው አስባ መጣች ይዘዋት መጥተውም አገናኟት ያየችውን ማመን አቅቷት እየተመለከተችው አነባች::
👉ያ ለሰው የሚተርፈው ምሁሩ ለማ አሁን ከአለም ጋር ተጣልቶና ተጎሳቁሎ ስታየው ራሷን መቆጣጠር አልቻለችም ሮጣ ተጠመጠመችበት ነገር ግን ፊቱ ላይ ምንም አይነት የደስታም ሆነ የሃዘን ስሜት አልታየበትም ጭራሽ ማንነቷንም መለየት አልቻለም በተደረገለት ነገር ሁሉ ምንም አይነት ለውጦችን ማሳየት አልቻለም በሆነው ነገር ሁሉ አዝና ተመልሳ ወደ ሀገረ አሜሪካ አቀናች::
👉ከማንባት ውጭ ሊያውቃት አልቻለም። ለማ የሚጠብቃት ገና አልመጣችማ!!!
መሸ ነጋ, ቀናት አመታትን ወለዱ, መንግስታት ተቀያየሩ, የቆመበት አስፓልት ተቀየረ, ያኔ የተወለዱ ህፃናት ጎረመሱ, እሱም የወጣትነት መልኩ ረገፈ ተጎሳቆለ። ግን አሁንም እዛው ነው ይጠብቃታል።
#ለማ ዛሬም እዛችው ቦታ ላይ ቆሞ መጠበቁን አላቆመም:: 😟

የሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉዳዮች መምሪያ የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ የከተማችንን ፅዳትና ውበት በዘመናዊ የከተማ ልማት መርህ በመታገዝ መሻሻሎች የሚታዩበት አሰራርን እውን ለማድረግ አስተዳደሩ ያላሰለሰ...
23/01/2021

የሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉዳዮች መምሪያ የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ

የከተማችንን ፅዳትና ውበት በዘመናዊ የከተማ ልማት መርህ በመታገዝ መሻሻሎች የሚታዩበት አሰራርን እውን ለማድረግ አስተዳደሩ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

በዚህ ረገድ እየተከናወነ ያለው ተግባር ለበርካቶች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር ከተማችንን የውበት፣ ፅዳት እና አረንጓዴ ልማት ተምሳሌት በማድረግም እውቅና እንዲቸራት አስችሏል።

ይህ ጥረት ያለ ምንም መንጠባጠብ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስም የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላትና ግለሰቦች ጋር በመቀናጀት አዳዲስ አሰራሮችን እየተከተለ ይገኛል።

በዚህም ከፊታችን ሰኞ ማለትም ጥር 17/2013 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪ ወደ ከተማዋ ሲገባ ጭነቱ ላይ አንፀባራቂ ጨርቅ ሳያስር እንዳይንቀሳቀስ የሚያዝ አሰራር ይፋ ሆኗል።

በተመሳሳይም ለከተማዋ ፅዳት ስራ በማህበር እና በግለሰብ ደረጃ የተሰማሩ የደረቅ ቆሻሻ ሰብሳቢ ጋሪዎች በየትኛውም መልኩ ለጋሪዎቻቸው መሸፈኛ ሸራ ሳይጠቀሙ እንዳይንቀሳቀሱ በመመሪያ ደረጃ ይፋ ተደርጓል።

ይህን አሰራር ከዳር ለማድረስም የትራፊህክ አስተናባሪዎች፣ የፀጥታ አካላት እና የውበትና ፅዳት ዘርፉ በባለቤትነት ተግባራዊ የማድረጉን ድርሻ የሚወጡ ይሆናል።

የሐዋሳ ከተማ ነዋሪም ለመመሪያው ተፈፃሚነት እና ለከተማው ፅዳት እና ውበት በባለቤትነት እንዲተጋ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉዳዮች መምሪያ
ጥር 15/5/2013ዓ.ም
ሐዋሳ
Haaro Media

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ።
19/01/2021

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ።

 # No comment.
26/11/2020

# No comment.

 #ኑ!  በእንዳልካቸው ግርማ ~ለግማሽ ቀን የከተማችንን የበጎ አድራጎት ስራ ማእከል እንጎብኝ!~እኔ ከሳምንቱ የረፍት ቀን በአንዱ እድሉን አጊኝቼ ማእከሉን ጎበኘሁና ልቤ ሀሴት አድርጎ የቤት...
15/11/2020

#ኑ! በእንዳልካቸው ግርማ

~ለግማሽ ቀን የከተማችንን የበጎ አድራጎት ስራ ማእከል እንጎብኝ!

~እኔ ከሳምንቱ የረፍት ቀን በአንዱ እድሉን አጊኝቼ ማእከሉን ጎበኘሁና ልቤ ሀሴት አድርጎ የቤት ስራዬንም ይዤ ተመለስኩ!

~የትዝታችን ሰዎች ደግሞ የአንድ መለስተኛ ከተማ ያህል ቁጥራችን እያሻቀበ 20k እየደረሰ ነውና ይህችንም በጎ ተግባር ባስታውስ ብዬ ነው ይህን መጻፌ!

~ለነገሩ የወዳጅ ግብዣ ነውና ቆይታዬን ላካፍላችሁ!

~እናንተ የኢትዮጵያ ልጆች በሚመቸን በማነኛውም ቀን በሀዋሳ ብሩህ መንደር አቅራቢያ የሚገኘው እንጎብኝ!

~ልጆች ላይ መስራት የነገዋ ሀገር ላይ መስራት ነውና!

! አይደልስ ብሂሉ!

~ዘር ቀለምን የተሻገረ ሰውነትን በማእከሉ አይቻለሁ!

~አቶ #አርጋው አየለ ይባላሉ!

~ከአሜሪካዊት ባለቤታቸው ጋር በመሆን በሚኖሩባት ሀዋሳ ከተማ በተለያየ አጋጣሚ ህይወት ፊትዋን ላዞረችባቸው ለተገፉ ህጻናት ይህን ድንቅ የድጋፍ ማእከል ከመሰረቱ እነሆ 14 አመታትን ማሳለፋቸውን ነግረውኛል!

#በጠቅላላው የ5 የስጋ ልጆቻቸው ወላጅ አባትና እናት የሆኑት ባልና ሚስቱ የመንፈስ ልጆቻቸው ግና በመቶዎች የሚቆጠሩ በወላጆቻቸው የተጣሉ በማህበረሰቡ የተገፉ ሚስኪኖች ወላጆችም ጭምር ናቸው!

~ኑሮዋቸውን በቁዋሚነት በበጎ አድራጎት ስራ ታጅበው በሀዋሳ ካደረጉ በሁዋላ በሀዋሳ ምድር ሶስት ልጆችን በውቢት ሀዋሳ ማፍራት ችለዋል!

~የሀዋሳና አከባቢዋ ነዋሪዎች 05 አድቬንቲስት ቤተክርስትያን ከመደረሱ በፊት አስፋልት ዳር የሚገኙትን ህጻናት በመጎብኘት ሰንበትን አብራችሁ ብታሳልፉ የእውነት ልልባችሁ ሀሴት ለታዳጊዎቹ ደግሞ ትልቅ ምርኩዝ ትሆናችሁላቸው!

~በማእከሉ ከ100 በላይ የሚሆኑ በተለያየ እድሜና የእርዳታ ፍላጎት ላይ የሚገኙ ህጻናት ትኩረታችሁን ብቻ ይሻሉ!

~በሳምንቱ የረፍት ቀናት ማእከሉን ብትጎበኙ በርግጠኝነት የውስጥ የመንፈስ እርካታን ትጎናጸፋላችሁ!

#እኔ ግማሽ ቀን አብሬያቸው አሳልፌ የማህበራዊ ችግራችንን ጥልቀትና ስፋት ምን ያህል እንደሆነና ባለን አቅም ብንደጋገፍ መቅረፍ እንደምንችል ቁጭት ፈጥሮብኛል!

እንዲሉ በኮረናና በተለያዩ ምክንያቶች ከበጎ አድራጊዎች የወትሮ ትኩረት የተነፈጋቸው አሳዛኝ ህጻናትን የአንድ ሎሚ ድርሻን ይዘን እናግዛቸው!

~አቶ አርጋውና አሜሪካዊት ባለቤታቸው ከታዳጊ ልጆቻቸው ሳይነጥሉ ቀላቅለው ድጋፍና እንክብካቤያቸውን ያለመታከት እየሰሩ ነውና ሀዋሳዎች እየጎበኘን አለሁ እንበላቸው!

!

Breaking News White House chief of staff Mark Meadows has tested positive for coronavirus, NBC News confirmed Friday.የዋይ...
07/11/2020

Breaking News

White House chief of staff Mark Meadows has tested positive for coronavirus, NBC News confirmed Friday.
የዋይት ሀውስ ማርክ ሚዶውስ ኮሮና ቫይረስ ተገኘበት።

ዶ/ር ተዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ ኩዋራንቲን እንደገቡ ተገለፀ።በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፦...
02/11/2020

ዶ/ር ተዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በኮቪድ 19 ከተያዘ ሰው ጋር መገናኛታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለብቻ ኩዋራንቲን እንደገቡ ተገለፀ።

በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፦ በአሁኑ ሰዓትም ጤናቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ አንደሚገኝ እና ምንም አይነት የቫይረሱ ምልክት እንደሌለባቸውም አስታውቀዋል።

01/11/2020

ገበታ ለሀገር

ገበታ ለሀገር ጥሪ ከፋይናንስ ዘርፉ ባሻገር የመንግስት ሰራተኛው፣ ዳያስፖራው፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች አቅማቸው በፈቀደ ሁሉ ድጋፉ እያደረጉ ነው፤ ይህ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያን የምትቀየረው በልመና ሳይሆን በእኛ ጥረት ነው። -

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

30/10/2020

Wilt Chamberlain vs Sammy Davis Jr
😆 Wilt Chamberlain vs Sammy Davis Jr
🥊 Boxing Skit on “Rowan & Martin's Laugh-In”

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል!
29/10/2020

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

ሙዝ’ ተወዳጅ እና ተመራጭ ፍራፍሬ>>>>>>>>>>>>ይህን ካነበቡ በኋላ ለሙዝ ያለዎት አመለካከት በእጅጉ ይቀየራል::ሙዝ ሶስት የተፈጠሮ ስኳሮችን (ማለትም ሱክሮስ፣ ፍሩክቶስ እና ግሉኮስ) ...
26/10/2020

ሙዝ’ ተወዳጅ እና ተመራጭ ፍራፍሬ
>>>>>>>>>>>>ይህን ካነበቡ በኋላ ለሙዝ ያለዎት አመለካከት በእጅጉ ይቀየራል::
ሙዝ ሶስት የተፈጠሮ ስኳሮችን (ማለትም ሱክሮስ፣ ፍሩክቶስ እና ግሉኮስ) ከፋይበር ጋር አጣምሮ ይዟል::
እነዚህም የሰዉነታችንን ኃይል ከፍ የማድረግ አስተዋፅኦ አላቸው::
ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከዘጠና ደቂቃ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ በኋላ 2 ሙዝ የሚመገቡ ስፖርተኞች እንደገና ኃይላቸውን ማደስ ይችላሉ::
ለዚህም ነው – በዓለማችን ታላላቅ ስፖርተኞች ዘንድ ‘ሙዝ’ ተወዳጅ እና ተመራጭ ፍራፍሬ የሆነው:: ይህ ብቻ አይደለም: ሙዝ የሚመገቡ ሰዎች የተለያዩ ህመሞችና ከባድ ሁኔታዎችን የመከላከል አቅማቸው እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው::
ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፤
1. የአንጀት ቁስለትን ይከላልከላል
2. ከሀንግ ኦቨር (HANG OVER) በፍጥነት ያላቅቃል
3. አእምሮ እንዲነቃቃ ያግዛል
4. የደም ማነስ ችግርን ያስዎግዳል
5. የሰዉነት ሙቀትን ለመቆጣጠር ይረዳል
6. የድብርት ስሜትን ያስዎግዳል፤ እንዲሁም ራስን ለማረጋጋት ይጠቅማል
7. ለደም ግፊትን ያስታግሳል
8. የሰገራ ድርቀትን ይከላከላል
9. የወር አበባን ተከትሎ የሚመጣ የስሜት መለዋወጥን ይቀንሳል
10. ቃርን ያስወግዳል
11. ሌላው በጣም የሚገርመው ከወባ ትንኝ ንክሻ ይከላከላል (ቆዳዎትን በልጣጩ ከቀቡት) –
ይቺኛዋ መረጃ በተለይ በሞቃታማው የአገራችን ክፍል ለምትገኙ ትሁንልን ብለናል!!
በተጨማሪ: አንድ ሙዝ ከሌላ ፍራፍሬ ጋር ስናወዳድረው ለምሳሌ ከአንድ አፕል (an apple) ጋር ብናወዳደር:-
አንድ ሙዝ በውስጡ የአፕልን
• 4 እጥፍ ፕሮቲን
• 2 እጥፍ ካርቦሃይድረት
• 3 እጥፍ ፎስፈረስ
• 5 እጥፍ vit A እና ብረት(IRON)
• እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ፖታሽየም የያዘ ነው::
(ለሌሎች share ማድረግዎን እንዳይዘነጉ!)

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ትችት እያስከተለባቸው ነው*******************(ኢ.ፕ.ድ)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናን...
24/10/2020

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ትችት እያስከተለባቸው ነው
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ምሽት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ህድብ ዙሪያ የሰጡት አስተያየት ከተለያዩ ወገኖች ትችት እያስከተለባቸው ነው።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤል እና ሱዳን መሪዎች ጋር አዲስ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት "ኢትዮጵያ ያዘጋጀነውን ስምምነት ጥሳለች፤ ያንን ማድረግ አይችሉም፤ ማድረግ ይችላሉ ብዬም አላስብም። በዚህ ምክንያት ብዙ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ቆርጠናል በውሉ ካልተስማሙ በስተቀር ያንን ገንዘብ ደግመው አያገኙም" ማለታቸውን ተከትሎ ከተለያዩ አካላት ትችት እየደረሰባቸው ነው።

የዴሞክራት ፓርቲ ኮንግረስማን የሆኑት የኮሎራዶው ጃሶን ክሮው በትዊተር ገፃቸው ፕሬዝዳንቱ ግድቡን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ ሀላፊነት የጎደለው እና መረጃ ቢስ ሲሉ አጣጥለውታል::

ሚስተር ክሮው በዚሁ መልዕክታቸው አሜሪካ ሚዛናዊ አደራዳሪ በመሆን ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈጠር መስራት እንዳለባት በመጥቀስ የውጭ እርዳታን ማገድ ተገቢነት የለውም በማለት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተችተውታል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከወራት በፊት በሶስቱ አገራት መካከል ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት እንዳትጀምር የሚል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውና ኢትዮጵያም የግድቡን የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሊት ማከናወኗ ይታወሳል።

የግድቡ ግንባታም በአሁኑ ወቅት በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ አመት የግድቡን ወሳኝ ስራ ለማከናወን መንግስት እየሰራ መሆኑን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

24/10/2020

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haaro Media House posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share