07/04/2024
ኦክሎክ ሞተርስ “ስሜን አጥፍቷል” ላለው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ምን ምላሽ ሰጠ ?
ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር ፤ በቱሪስት ታክሲ ማኀበራት " የስም ማጥፋት ዘመቻ ተፈጽሞብኛል " በማለት ኮንኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁንን የድርጅቱ ስም ጠፋ ያሉበትን ምክንያት ጠይቋል።
አቶ ታመነ ካሳሁን ፦
“ ‘ሕዝቡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ድሃዎችን እያስለቀሰ ነው። 1.2 ቢሊዮን ብር ወስዶ እየሰራበት ነው’ የሚለው በሕዝብም በመንግሥትም ዘንድ ተቀባይነት እንድናጣ ለማድረግ የተደረገ ሩጫ ነው። ” ብለዋል።
በተጨማሪ ፦
“ ... እነዚህ ሰዎች (1.2 ቢሊዮን ብር ከፈሉ የተባሉት) የከፈሉት 110 ሚሊዮን ብር ነው። ያመጣነው መኪና ግቢ ውስጥ እንኳ የቆመው ብቻ 200 መኪና ነው። 200 መኪና በትንሹ እንኳ በ1 ሚሊዮን 950 ሺሕ ብር ስናባዛው ከ400 ሚሊዮን በላይ ነው። ስለዚህ የዛን ያህል ዋጋ ከፍለን ስናመጣ እኛ ከእነርሱ (ከማኀበራቱ) የተቀበልነው ገንዘብ ግን ያን ያህል (110 ሚሊዮን ብር) ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
- ኦክሎክ ጋር የነበረው ውል ምንድን ነው ? ለምን ተቋረጠ ?
- የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት አባላት ፥ “ ኦክሎክ በስማችን የመጣውን መኪና ” ስለሚለው ምን ምላሽ አላችሁ ? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች አቅርቧል። የኦክሎክ ሥራ አስኪያጅ በዚህ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።