12/04/2022
https://www.facebook.com/100063883683426/posts/373114681494652/?app=fbl
የሲዳማ ክልል ወጣቶች ጥያቄ
በሀዋሳ ከተማ ፤ የብልፅግና ፓርቲ ከሲዳማ ወጣቶች ጋር ለመምከር የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ መድረክ የተሳተፉ አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች ሲሆኑ ለበርካታ አመታት ያለ ስራ መቀመጣቸውን በመግለፅ ጠንካራ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" አሁን ወጣቱን አደራጅተን እንደዚህ እያደረግን ነው ብላችሁ እያወራችሁ ነው። የትኛውን ነው ?
ለምሳሌ ፦ ኮንቴነር በየክፍለ ከተማው ፈትሹ ያለውን ነገር ታያላችሁ ፤ አመራሩ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር። አደራጅ እና አስተባባሪ ተብሎ የተቀመጡ ሰዎች እነሱ እጅ ነው ያለው ኮንቴነር ለወጣቱ ይሰጥ ተብሎ የተሰራው ፤ የምን ብልፅግና ነው እናተ ምትመሩት ?
ይህንን ወጣት ፤ በቀን 3 ጊዜ መብላት ያልቻለን ህዝብ እየመራችሁ እንዴት ነው ? እናተ በV8 እና በተለያየ ላንድክሩዘር መኪኖች እየዘነጣችሁ የምትሄዱት ? በምን አግባብ ነው ? "
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ፦
" ... ብልፅግና ፓርቲ መነፅር ብቻ ነው የቀየራችሁት ። ሙሉ ኢህአዴግ የነበሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ለውጡን ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም። በሌብነት ፣ በዘረኝነት የተጠመዱ ሰዎች ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲ ቢያንስ ወጣቱን የሚሰማ ከሆነ እኛ በትዕግሥት መንግስቱ አልተረጋጋም ፣ ጫና አለበት የውስጥም የውጭም ብለን በትዕግስት ጠብቀናል ሶስት ዓመት ሙሉ አሁን 4ኛ ዓመት ልንይዝ ነው ሁሌ በዚህ ይቀጥላል ? የኛም ዝምታ በዚህ ይቀጥላል ? እሱን ጊዜ የሚፈታው ነገር ነው። "
ከዚህ በተጨማሪ የውይይት ተሳታፊዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ቢጥሩም እንዳልቻሉ ፤ በክልላቸው ዴሞክራሲና ነፃነት የለም ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።
እንዲሁም በክልሉ ፦
👉 ሰብአዊ መብቶች ይጥሳሉ፣
👉 የመልካም አስተዳደር ጉድለት አለ፤
👉 ሙስና ተንሰራፍቷል ፤
👉 ባለስልጣናት ለወጣቶች መገልገያ የተገነቡ ተቋማትን ለዘመዶቻቸዉና ለቤተሰቦቻቸዉ ሰጥተዋል፣
👉 ባለስልጣናት ዉሳኔዎችን የሚያሳልፉት ለእነሱና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሚጠቅም መልኩ ነዉ ብለዋል።
በወጣቶች ለተነሱት ጥያቄዎች በመድረኩ ከተገኙት አንዱ የሲዳማ ብልፅና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ ተከታዩን ብለዋል ፦
" ቁጥር ብዙ ለሆነ ወጣት ስራ እድል ያልተፈጠረለት ሁኔታ አለ። እየተፈጠረም ያለው እራሱ የባለሃብት ቤተሰብ ፣ የአመራር ቤተሰብ የሚለው ትክክል ነው።
ምን እያደረጋችሁ ነው ያላችሁት ? ቢሚል ለነሳችሁት መጀመሪያ የሚሆነው ይህን ሲፈፅም የነበረው ሊመራ ኃላፊነት የተሰጠው አመራር በአግባቡ ያልመራውን እርምጃ ወስደናል አሁን።
በዚህ ዓመት አሁን እስካለንበት ከ80 በላይ በሆኑት ላይ እርምጃ ተወስዷል። ይሄ ብቻም አላቆመም ቀጥሎም በኃላፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ በከተማ ፓርቲ ደረጃ ፤ በመንግስት ደረጃ የሚኬድበት ሁኔታ ይቀጥላል "
የብልፅግና ወጣቶች ሊግ አመራር አንዱ ታረቀኝ ለገሰ ፦
" የምታነሷቸው ጥያቄዎች በሰፊው አሉ። ስራ አጥነት አለ። የ3 ዓመት ብቻ አይደለም ፤ የ7 ዓመት ስራ ያልተቀጠረ ወጣት ፤ ስራ ያላገኘ ወጣት ያለው እኛ ጋር በዝርዝር አለ። እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር ይዘናል ፤ እንደተባለው ቀጥታ ይሄ ለፌዴራል ብልፅግና ፓርቲ ግብአት ሆኖ የሚሄድ ነው። "