ዜና ኢትዮጵያ

  • Home
  • ዜና ኢትዮጵያ

ዜና ኢትዮጵያ የዜና ኢትዮጵያ ቻናላችን አባል በመሆነዎት ብቻ ወቅታዊ መረጃዎች፥ ጠቃሚ ምክሮችን፥ አስተማሪ ቀልዶችን፥ የንባብ መጽሐፍትን እና ጋዜጣ ዘወትር ያገኛሉ።

14/05/2021
11/05/2021

Ethiopia Tourism is a learning blog website about Ethiopia Tourism, tourism visas, Ethiopian Passport, travel itinerary, destinations, etc

01/05/2021

እውነት ግን አፍሪካ እንዲህ ናት?
ከዚህ ምን ትማራላችሁ? ይህ ምን ይነግረናል?

09/02/2021

Alternative to Adobe Photoshop II Free Phot Editing II thumbnail for YouTube

28/01/2021

Free Softwares, Operating systems, 3D CAD, Graphic Design, Multimedia, Development, antivirus, Education, and much more free software.https://getintopc.com/W...

20/01/2021

Unity Park of Ethiopia is constructed by the initiative of Ethiopia Prime Minister Abiy Ahmed. Unity Park is located at the compound of

12/01/2021
26/11/2020

What happen at ....???
#ያማል!!!

25/11/2020

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ ብልህነት /artificial intelligence / ለመተባበር እየፈለጉ ነው::
************
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ኢሜሬትስ) እና ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (አይ ኤ) መስክ የትብብር አማራጮችን ሊመለከቱ እንደሚገባ ከአዲስ አበባ ኤምባሲ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው መግለጫ አመልክቷል ፡፡
Source: Google News

25/11/2020

Protestant Mezmur - Gospel Singer Samuel Odda #1- Full Album: ዘማሪ ሰሙኤል ኦዳ ቁጥር 1 ሙሉ አልበም፡፡ #የጴንጤመዝሙር === ሌሎች መረጃዎች ==== ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊ...

ያድምጡ!ከወደዱት ላይክ ያድርጉ።
21/11/2020

ያድምጡ!
ከወደዱት ላይክ ያድርጉ።

ሌሎች መረጃዎች :- ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊዘኛ መንፈሳዊ መጽሐፎችን ለማግኘት E-Library for Amharic and English Spiritual eBooks.👇👇👇👇👇👇👇 👉 https://elibrary.learning.et/ ✳️ - የአምልኮ ...

አያምልጠዎት!
17/11/2020

አያምልጠዎት!

ሌሎች መረጃዎች :- ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊዘኛ መንፈሳዊ መጽሐፎችን ለማግኘት Spiritual E-Library for Amharic and English Spiritual eBooks.👇👇👇👇👇👇👇 👉 https://elibrary.learning.et/ ✳...

የእርሰዎ ምርጫ
14/11/2020

የእርሰዎ ምርጫ

ሌሎች መረጃዎች :- ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊዘኛ መንፈሳዊ መጽሐፎችን ለማግኘት E-Library for Amharic and English Spiritual eBooks.👇👇👇👇👇👇👇 👉 https://elibrary.learning.et/ ✳️ - የአምልኮ ...

መንፈሳዊ የመዝሙር ክላሲካል ስብስብ
12/11/2020

መንፈሳዊ የመዝሙር ክላሲካል ስብስብ

ሌሎች መረጃዎች :- ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊዘኛ መንፈሳዊ መጽሐፎችን ለማግኘት Spiritual E-Library for Amharic and English Spiritual eBooks.👇👇👇👇👇👇👇 👉 https://elibrary.learning.et/ ✳...

https://youtu.be/xoOZqC5DcqU
06/11/2020

https://youtu.be/xoOZqC5DcqU

ሌሎች መረጃዎች :- ✳️ - ነፃ የአማርኛና የእንግሊዘኛ መንፈሳዊ መጽሐፎችን ለማግኘት Spiritual E-Library for Amharic and English Spiritual eBooks.👇👇👇👇👇👇👇 👉 https://eli...

07/09/2020
16/06/2020

ቤተሰብ ይሁኑ!

Do you know the SECRET POWER of PRAISE & WORSHIP? Do you know what will HAPPEN when you WORSHIP GOD? What wi It is Wonderful Blessings! Learn More from our website Gospel Mezmur.
Visit it now: https://www.learning.et/ or https://elibrary.learning.et/

18/04/2020

👉 |ሰብስክራይ ለማድረግ| subscription link - https://www.youtube.com/channel/UCLfq... የመጨረሻ ዘመን እና 666 ከመጽሐፍ ቅዱስ II What the Bible says about 666? What...

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========የኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ ረቂቅ ሪፖርት ቦይንግን ተጠያቂ አደረገከአንድ ዓመት በፊት የተ...
08/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
የኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ ረቂቅ ሪፖርት ቦይንግን ተጠያቂ አደረገ
ከአንድ ዓመት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ምክንያት የአውሮፕላኑ የዲዛይን ችግር እንደሆነ መርማሪዎች ለአሜሪካ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ያዘጋጁት የአደጋው ረቂቅ ሪፖርት አመለከተ።

ሮይተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ በረቂቅ ሪፖርቱ ላይ ቅሬታ ወይም እንዲለወጥ የሚያቀርበው ሃሳብ ካለው ዕድል እንደተሰጠው፤ ሪፖርቱ ይፋ ስላልተደረገ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሰዎች ተናግረዋል።

የቦርዱ ቃል አቀባይ ኤሪክ ዌይስ ጊዜያዊው ረቂቅ ሪፖርትን እንደተቀበሉ ቢገልጹም ድርጅታቸው ለውጥ እንዲደረግ ይጠቅ እንደሆነ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቦይንግ ሪፖርቱን በተመለከተ ምላሹ ምን እንደሆነ በሮይተርስ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።
ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ ለመጓዝ ከአዲስ አበባ ከተነሳ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር 302 የአውሮፕላኑ ሰራተኞችን ጨምሮ 157 ሰዎች ሞተውበታል።

ከዚህ አሰቃቂ አደጋ በኋላም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ተደርጓል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የበላይ ተቆጣታሪነት ስር ካናዳ ሞንትሪያል በሚገኘው የአቪዬሽን ኤጀንሲ ደንብ መሰረት፤ ኢትዮጵያ አደጋውን በተመለከተ የመጨረሻውን ሪፖርት በአደጋው አንደኛ ዕለት ይፋ ማድረግ ይኖርባታል።

32 ኬንያዊያን፣ 18 ካናዳዊያን፣ 18 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የ33 አገራት 157 ዜጎች ህይወታቸው ያለፈበትን የዚህን አደጋ አንደኛ ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ማክሰኞ አስቦት እንደሚውል ቢቢሲ አረጋግጧል።

ኮሮናቫይረስ አለብህ' በሚል ቡጢ የቀመሰው የኦክስፎርድ ተማሪኢሲያዊያን ከዚህ ኮሮናቫይረስ ወዲህ በየአካባቢው መገለል እየደረሰባቸው ነው። በቅርቡ በትዊተር የተሰራጨ አጭር ቪዲዮ 'ኮሮናዎች መ...
06/03/2020

ኮሮናቫይረስ አለብህ' በሚል ቡጢ የቀመሰው የኦክስፎርድ ተማሪ
ኢሲያዊያን ከዚህ ኮሮናቫይረስ ወዲህ በየአካባቢው መገለል እየደረሰባቸው ነው። በቅርቡ በትዊተር የተሰራጨ አጭር ቪዲዮ 'ኮሮናዎች መጡ" በሚል ቻይናዎች በኬንያ ናይሮቢ ውስጥ ሰዎች ሲሸሽዋቸው ያሳይ ነበር።

አሁን ደግሞ በእንግሊዝ ሎንዶን በጎብኚዎች በሚዘወተረው የኦክስፎርድ ጎዳና አንድ የ23 ዓመት ወጣት ከበድ ያለ ድበደባ ደርሶበታል።

ጆናታን ሞክ አደጋው የደረሰበት በምሽት ወደ ቤቱ እየሄደ ነው። 4 ወጣቶች "ቁም! ኮሮና አለብህ" በሚል ፊቱ እስኪያባብጥ ደብድበውታል።

ጆናታን ሞክ ትውልዱ ከሲንጋፖር ነው። ከአራቱ ደብዳቢዎቹ ሁለቱ ገና የ16 እና 15 ዓመት ልጆች ሲሆኑ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ካደረገ በኋላ ለቋቸዋል።

አሜሪካ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ እንደሌላት ገለፀችበመሃል አሜሪካ እንዲሁም ዳርቻዎች የኮሮናቫይስ ስርጭት እየጨመረ ቢሆንም አገሪቱ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ እንደሌላት ዋይት...
06/03/2020

አሜሪካ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ እንደሌላት ገለፀች
በመሃል አሜሪካ እንዲሁም ዳርቻዎች የኮሮናቫይስ ስርጭት እየጨመረ ቢሆንም አገሪቱ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ እንደሌላት ዋይት ሃውስ አምኗል።

ምክትል ፕሬዘዳንቱ ማይክ ፔንስ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ ሳምንት ውስጥ ያስፈልጋል የተባለውን አንድ ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ ማሟላት እንደማይችል በግልፅ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ኮንግረስ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው እንቅስቃሴ የድንገተኛ እርዳታ በጀት ለማፅደቅ ባልተለመደ ሁኔታ እየተጣደፈ መሆኑ ተሰምቷል።

በትናንትናው እለት በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱም ታውቋል። በአሁኑ ወቅትም በመላ አገሪቱ 200 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በ20 ግዛቶች ውስጥ ተመዝግበዋል።

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት የበሽታው ክስተቶች የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው።

ሦስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ አብዛኛው ሞት የተመዘገቡት ደግምኦ በቻይና ውስጥ ነው።

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========የሀዋሳ የከተማ ፀጥታና ሰላም ጉዳይየሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የከተማው ፀጥታና ...
06/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
የሀዋሳ የከተማ ፀጥታና ሰላም ጉዳይ

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የከተማው ፀጥታና ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የወንጀል መከላከል ሥልትና የሥምሪት ሥርዓት በመቀየር ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን አስታወቀ።

ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተሽከርካሪዎችን ጭምር ሰረቀዋል ያላቸውን የተለያዩ ወንጀለኞች ማሰሩንና “የኢትዮጵያ ገንዘብ አታሚ ነኝ” ይላል ያሉት ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ አንድ ግለሰብ ከህገወጥ ገንዘብ ማተሚያ መሳሪያ ጋር መያዙን ገልጿል።

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========አሰቃቂ መከራን አልፋ ለህይወት ስኬት የበቃቸው ሄለንወይዘሮ ሄለን ወረደ፤ ሦስት ልጆችዋን ብ...
06/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
አሰቃቂ መከራን አልፋ ለህይወት ስኬት የበቃቸው ሄለን
ወይዘሮ ሄለን ወረደ፤ ሦስት ልጆችዋን ብቻዋ ያሳደገች ነገር ግን በድንገት ከእቅፍዋ የተነጠቀችው እናት ናት።

እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ 'መላዕክቶቼ' ብላ የምትጠራቸውና በአሰቃቂ ሁኔታ ላጣቻቸው ለሦስት ልጆችዋ፣ ለእህቷና ለእህቷ ልጅ ያላት ፍቅር ዘላለማዊ እንሆነ ትናገራለች።

"ለብቻ ልጆች ማሳደግ ቀላል አይደለም፤ ቢከብድም ግን የልጆቼን ትምህርት በአግባቡ እከታተልና ሥራዬን እሰራ ነበር። ሦስቱም ልጆቼ የተለያየ ትምህርት ቤት ይማሩ ስለነበር እነሱን ማመላለስና መልሶ ወደ ሥራ መሄድ አስቸጋሪ ነበር" ትላለች።

ነገር ግን ግን ሁል ጊዜ በፍቅር የምትወጣው ኃላፊነት ስለነበረ እንደለመደችው እና "ስሰራበት የነበረው የሥራ መስሪያ ቤቴ ሁኔታዬን በመረዳት ያግዘኝ ስለነበር ከብዶኝ አያውቅም።"
የ13 ዓመቱ ዮሴፍ፣ የ5 ዓመቱ ያሴን ሻማምና የ6 ዓመቷ ኒስረን ሻማም፤ ሄለን በተለያዩ ጊዜያት የወለደቻቸው የህይወቷ ጌጦች ነበሩ።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን፤ የዚህ ቤተሰብ ህይወት ባልተጠበቀ ሁኔታ የሚቀይር ክፉ አጋጣሚ ተከሰተ።

ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በአውሮፓዊያኑ ሐምሌ 2010 ዕለተ ቅዳሜ ረፋድ ላይ፤ ሰማይና ምድር የሚያናውጥ ኡኡታ የወይዘሮ ሄለን ቤት ካለበት አካባቢ ተሰማ። ሃዘናቸውን የሚገልጹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሲያትል ውስጥ ተሰብስበዋል።

የልጆቹ እናትም "ልጆቼን ነው የምፈልገው" እያለች ደረትዋን እየደቃች ወደ መሃል መንገድ ትሮጥ ስለነበር፤ "ሊያቅፏትና ሊያጽናኗት የሚከተሉዋት ሴቶችም ነበሩ" ሲል ሲያትል ታይምስ የወቅቱን ክስትት ጽፎ ነበር።
ሄለን በዚያች መጥፎ ዕለት በተመሳሳይ ሰዓትና በተመሳሳይ አደጋ ሦስቱንም ልጆችዋን፣ የ22 ዓመት እህቷንና የእህቷን ልጅ በድንገት አጣቻቸው።

በእያንዳንዷ ቀን ገደብ አልባ ፍቅርና እንክብካቤ በመስጠት ሳቅና ደስታ እየፈጠረች በስስት ለብቻዋን ስታሳድጋቸው የነበሩትን ልጆችዋን በእሳት አደጋ የማጣት መዓት ወደቀባት።

በወቅቱ የእሳት አደጋው በሲያትል በአስርት ዓመታት ውስጥ ያጋጠመ ከባዱ የእሳት አደጋ እንደነበርም ተነግሯል።

ሄለን ከቤተሰቦቿ ጋር በመጨረሻ ያሳለፈችውን ዕለት ፈጽማ አትረሳውም። አርብ ማታ ነበር፤ ሄለንና ሦስት ልጆችዋ፣ እህቷና የእህቷ ልጅ አንድ ላይ ፊልም በፍቅርና በደስታ ቅዳሜ መልሰው እንደሚገናኙ በማሰብ ወደ መኝታቸው አመሩ።
ነገር ግን ቅዳሜ ይህ ቤተሰብ እንደወትሮው አንድ ላይ የሚያሳልፋት ቀን አልሆነችም፤ እልቁንም ሄለንን ብቻዋን ያስቀረች ዕለት ሆነች።

ከቤቱ ውስጥ የተነሳው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ እጅግ ከባድ ነበር፤ አደጋውን ለመቆጣጠር ይጥሩ ለነበሩት የእሳት አደጋ ሠራተኞችም አዳጋች ሆነ። ከባድ ጭስና የእሳት ነበልባል ሌሊቱን በፍቅር አቅፋቸው ካደረችው ቤት መውጣቱን ቀጠለ።

እሳቱን ሊቆጣጠር የመጣው የእሳት አደጋ መኪና የውሃ ሞተር ውሃ መግፋት አልቻለም። ሌላ እርዳታ የሚሰጥ መኪና እስኪ መጣ ደግሞ ደቂቃዎች አለፉ፤ በዚህም በእሳት በሚጋየው ቤት ውስጥ ያሉትን የአምስት ሰዎችን ነፍስ ማዳን ሳይቻል ቀርቶ በእሳቱ ተበሉ።

በዚህ ክስተትም ሲያትል ላይ ከባድ ሃዘን ሆነ፤ ክስተቱን የሰሙ ሁሉ በእሳቱ ከተቀጠፉት ልጆች በተጨማሪ ከባዱ ሃዘን ለወደቀባት ሄለንም አነቡ፤ የበርካቶች ልብም በሃዘን ተሰበረ።
"ለእኔ ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ውጪ ነበር፤ የውዶቼን ህይወት ማዳን የምችልበት አቅም አልነበረኝም። ስለዚህ ጉዳይ በጭራሽ ማውራት ይከብደኛል። እንዴት ብዬ ልንገርሽ? እህህህ . . . በቃ ከባድ ነው" ትላለች ሄለን ያለፈውን አስታውሶ ለማውራት አቅም እንደሌላት በመግለጽ።

ወይዘሮ ሄለን የአሜሪካ ህልም በመቋደስ የእራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ላይና ታች ከሚሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ነች።

"በዚች አገር ብዙ እድሎች አሉ፤ ጭንቅላታችንን ከፍተን ከፈለግን የምናጣው ነገር የለም። ዋናው ነገር ለመማርም ሆነ ለመስራት ዝግጁ መሆን ነው" ትላለች።

ሄለን ወረደ፤ እትብቷ ከተቀበረበት ቀዬ ወጥታ ወደሌላ አገር ስትሄድ ገና የሁለት ዓመት ህጻን ነበረች።

ቤተሰቦችዋ ወደ ሱዳን አቅንተው እዚያ ስምንት ዓመት ሱዳን ላይ ኖረዋል። ሄለን የ10 ዓመት ልጅ ስትሆን ደግሞ ወደ አሜሪካዋ ሲያትል ተጉዘው ኖሯቸውን እዚያው አደላደሉ።

ሄለን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ልጆች ወልዳ ልጆችዋን የማሳደግ ኃላፊነትን ለብቻዋን በመወጣት ላይ ሳለች ነበር የወጣትነት እድሜዋን ደስ እያለት መስዋዕት ያደረገችላቸው ልጆቿን በድንገት ያጣችው።
ሄለን በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ አልፋ እናቷን፣ የሲያትል ማኅበረሰብንና ጓደኞችዋን አንስታም ሆነ አመስግና አትረካም።

ዘወትር ከልቧና ከንግግሯ የማይጠፉትን በዚያ ዘግናኝ አደጋ ያጣቻቸው ልጆችዋና እህቷ ደግሞ 'ፋይቭ ኤንጅልስ' [አምስቱ መላዕክ] ስትል ትጠራቸዋለች።

ሄለን የገጠማትን መከራ የዘወትር የሃዘኗ ምንጭ ከማድረግ ይልቅ በህይወቷ ውስጥ የሚከሰቱ መልካም ነገሮች አድርጋ ነው የምታስበው።
በሌላው አዲስ የህይወቷ ምእራፍ ያገኘቻቸውን ነገሮች በሙሉ ደግሞ፤ አምስቱ መላዕክት መርቀው ሰጥተውኛል" በማለት ፈጣሪዋን ተመሰግናለች።

"ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እግዚአብሔር ለእኔ ያሰበው ነገር ስለነበር ያጋጠመውን ነገር ሰጠኝ። ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና የሲያትል ማኅበረሰብ በሰጠኝ ብርታት ሁሉንም ነገር አለፍኩት። ከዚያ በኋላም መንታ ወንድ ልጆች ተሰጠኝ። አሁን አምስት ዓመት ሆኗቸዋል። ስለዚህ ሁሉም የሆነው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው" ትላለች።

ሄለን ከእንደዚህ አይነት እጅግ አሰቃቂ አደጋና ሞት በኋላ ለመኖር ተስፋ የምታደርግበት ሌላ ህይወት አለ ብላ ታስብ ነበር። "የነበረህን ለማጣት ምክንያት አለው። የሚያበረታህ፣ ተስፋ የሚሰጥህ ሰው አጠገብህ ሲኖር ደግሞ ሁሉንም አሸንፎ እንደገና መሳቅ፣ በህይወት መኖርና ህይወትን እንደ አዲስ መጀመር ይቻላል" ትላለች።

ከገጠማት ከባድ መከራ አንጻር "ቤት አልባ፣ የተጎሳቆለች፣ በሽተኛ ነበር የምሆነው። ግን ደግሞ እግዚአብሔር ያንን እንዳልፈው ጥንካሬ ሰጠኝ፣ ትክክለኛውን ነገር እንዳደርግ ደግሞ መራኝ። እኔም ሁሉንም ነገር ለፈጣሪዬ፣ ለእናቴና ለሁሉም ከጎኔ ለነበሩ ሰዎች አሳልፌ ሰጠኋቸው" ትላለች።

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========በኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ ገለጸ...
06/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
በኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ ገለጸ
በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም እንኳን ግፊት ቢደረግበትም ወደቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥ በድጋሚ አሳወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንደተናገሩት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን ማቋረጥ መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም በቫይረሱ ምክንያት ቻይናን ማግለል ፍትሃዊ አይደለም ብለዋል።

"የቀጥታ በረራዎችን ማቋረጥ ቫይረሱን አይገታውም፤ ምክንያቱም ተጓዦች ከቻይና ከሌሎች አገራት በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ይገባሉ። በዚህም ነው ዓለም እርስ በርሷ ተሳስራላች የሚባለው" ሲሉ መናገራቸውን የቻይናው ዢንዋ የዜና ወኪል ዘግቧል

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========ኮሮናቫይረስ፡ የቫይረሱ ክትባት መቼ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል?ኮሮናቫይረስ በዓለማችን 60 አ...
06/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
ኮሮናቫይረስ፡ የቫይረሱ ክትባት መቼ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል?

ኮሮናቫይረስ በዓለማችን 60 አገራት ተሠራጭቷል። ገና በርካታ የኮሮና ተጠቂዎች ወደፊት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል።

ኮሮናቫይረስን የሚገታ ክትባት እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን ምርመራው ቀጥሏል። አሁን ዋናውን ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን - መቼ ይሆን የኮሮናቫይረስ ክትባት የሚገኘው?

አጥኚዎች ቫይረሱን ይገታል ያሉትን ክትባት አምርተው እንስሳት ላይ መሞከር ጀምረዋል። ይህ ማለት ሰው ላይ እስኪሞከር ወራት ሊፈጅ ይችላል። ምናልባትም በፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ገደማ ሊሆን ይችላል።

ሳይንቲስቶች ክትባቱን አግኝተው ቤተ-ሙከራ ውስጥ በደስታ ፈነደቁ እንበል። ዋናው ቁም ነገር ግን ክትባቱን በገፍ ማምረት ነው።

በዚህ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ክትባቱ ተገኝቶ ጥቅም ላይ እስኪውል ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሊፈጅ ይችላል።

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•°°°°°°°°°°°°°°°°°°አርእስተ ዜና፣========መግለጫው እንደገለፀው ትራምፕ ግብፅ ሁለገብ ፣ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ እንደሆነች የሚዘገበውን ...
04/03/2020

•ዜና ኢትዮጵያ || ZENA ETHIOPIA•
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አርእስተ ዜና፣
========
መግለጫው እንደገለፀው ትራምፕ ግብፅ ሁለገብ ፣ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ እንደሆነች የሚዘገበውን ስምምነቷን ለመፈረም መልካም ሀሳብዋን እና ሀቀኛ የፖለቲካ ፍላጎትዋን አረጋግጣለች ብለዋል ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጨምረው በበኩላቸው መንግስታቸው የህዳሴው ግድብ ስምምነት እስከሚፈረምበት ጊዜ ድረስ ከግብፅ ፣ ከሱዳን እና ከኢትዮ Ethiopiaያ ጋር በመሆን በዚህ አስፈላጊ ፋይል ላይ ጥረቱን እንደሚቀጥልም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አክለዋል ፡፡ ኤል-ሲሲ ውይይቱን በማካሄድ የአሜሪካ መንግስት ሚና መጫወቱን በመግለጽ ግብፅ ለግብፅ ህዝብ ጥቅም እና ለወደፊቱ ትልቅ ጠቀሜታ ጉዳይ ስለሆነ ጉዳዩ ለዚህ ጉዳይ ቅድሚያ እንደምትሰጥ ገልጸዋል ፡፡
ግብፅ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን አርብ አርብ በተጠናቀቁት የሁለት ቀናት ውይይቶች የመጨረሻ ጊዜ ላይ ሜጋ-ግድብ ላይ የመጨረሻ ስምምነት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል ፣ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ያልተሟሉ የሀገር ውስጥ ውይይቶችን በመጥቀስ ውድድሮችን አቋርጣለች ፡፡
ግብፅ ስምምነቱን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቀረበች።

የዩኤስ የግምጃ ቤት ዋና ፀሀፊ የሆኑት ስቲቨን ሚንክች ማክሰኞ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት እምብ ካለች በኋላ ዋሽንግተን እንዳዘነች ተናግረዋል ፡፡

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዜና ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዜና ኢትዮጵያ:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share