24/08/2022
Be sudan bekul yetelat mesarya chino Ethiopia wust yegeba yetelat awuropilan bejeginaw serawit temeto wodikal! kibr lejeginawu serawitachin!
ኦቢኤን ነሀሴ 18/2014 - የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል፡፡
የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል።
ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።
በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።
ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።
በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።
ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ የማንንቱ ያልታወቀ አውፕላንም በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች ቢኖሩም የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያነ ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ ምህናቸውን ጠቅሰዋል በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል አሁን የመከላከል ርምጃ እየተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የማጥቃት ርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው የጠቀሱት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡ http://facebook.com/OBNAmharic
ዩትዩብ፦ Youtube.com/OBNoromiyaa
ቴሌግራም፦ https://t.me/OBN_VoiceOfthepeople
ትዊተር፦ https://twitter.com/OBNoromiyaa
የአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡ http://facebook.com/OBNAfaanoromo
OBN English ፌስቡክ: http://facebook.com/OBNEnglish.
OBN Radio https://zeno.fm/radio/obnradio/
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!