27/03/2020
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች 16 ደረሰዋል!
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-
ታማሚ 1 ፦
የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ ሲሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው፡፡ መጋቢት 13፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 6 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 2፦
የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ በተገኘው መረጃ መሠረት ግለሰቡ የውጭ የጉዞ ታሪክ ባይኖራቸውም በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸዉ፡፡
ታማሚው ግለሰብ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቻውን አግልለው እንደቆዩና መጋቢት 16፣ 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ሪፖርት ባደረገው መሰረት በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 3 ፦
የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የመጨረሻ ጉዞዋም መጋቢት 12፣ 2012 ዓ.ም እስራኤል ሀገር ደርሳ የተመለሰች ናት፡፡ ግለሰቧም በቀን 16፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከታማሚዋ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 7 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን ማጣራት ሂደት
እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 4 ፦
የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ቢሆንም የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ እና ግለሰቧም በቀን 17፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡