የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ቂርቆስ ክ/ ከተማ

  • Home
  • የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ቂርቆስ ክ/ ከተማ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ቂርቆስ ክ/ ከተማ የአማራ ህዝብን ታሪክ፣ ባህል ፣ወግ፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካ በስፋት ይተነተንበታል።
እንዲሁም የአማራ ብሄርተኝነትና አብን መርሆዎች ይዳሰሱበታል።

ድርድርን በተመለከተ---ክርስቲያን ታደለ---1) የገዥው ፓርቲን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአገርንና የሕዝብን ዘላቂ መብቶች፣ ጥቅሞችና ፍላጎቶች በተመለከተ ባለድርሻዎች እንጂ ብቸኛ ወሳኞች ...
03/08/2022

ድርድርን በተመለከተ

---ክርስቲያን ታደለ---

1) የገዥው ፓርቲን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአገርንና የሕዝብን ዘላቂ መብቶች፣ ጥቅሞችና ፍላጎቶች በተመለከተ ባለድርሻዎች እንጂ ብቸኛ ወሳኞች አይደሉም።

2) ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁለንተናዊ እጣፈንታቸው በጥቂት ቡድኖች የሚበየን የግል ንብረት አይደሉም።

Christian Tadele Tsegaye

የአማራ ክልል ምክር ቤት የአፈና ውሎ ቀጥሏል፣የሚያሣዝነኝ ነገር ቢኖር ቢያንስ ቢያንስ መናገርና ሃሣብህን መግለፅ ከምትችልበት ሁኔታ እንዴት የማትችልበት እጣፈንታ ይቀየራል። እኔ በኢህአዴግ ...
25/07/2022

የአማራ ክልል ምክር ቤት የአፈና ውሎ ቀጥሏል፣

የሚያሣዝነኝ ነገር ቢኖር ቢያንስ ቢያንስ መናገርና ሃሣብህን መግለፅ ከምትችልበት ሁኔታ እንዴት የማትችልበት እጣፈንታ ይቀየራል። እኔ በኢህአዴግ ጊዜ በማንኛውም አጋጣሚ ሃሣቤን ከመግለፅ ተገድቤም ታፍኘም አላውቅም። ለውጥ ብዬ ለለውጥ ታግዬ መጣ በተባለው የለውጥ ዘመን ግን የህግ ጥሠት አለ ሰነ ስረአት ይከበር ብዬ በመከራከሬ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አዳራሽ በፖሊስ ተይዠ እንድወጣ ትዛዝ ከተሠጠ በኋላ በምክር ቤቱ አባላት በተፈጠረ ጫጫት ፖሊስ ገብቶ ሣያወጣኝ ቢቀርም ነገሩ ግን እንዳልተፈፀመ አድርጌ አልወስደውም።

በመሠረቱ እኔ ሁሉንም ነገር ለመሆን የወሠንኩኝ ሠው መሆኔን ያላውቁ ሠዎች ጉዳዩን የተለያዬ ሠበብ አስባብ እየፈጠሩ ለማደናገር ቢሞክሩም አይሣካላቸውም። እኔ የአማራ ህዝብ ሞት እስከሚቆምና ጥያቄዎቹ እስከሚመለሱ ትግሉ የጠዬቀውን ዋጋ ሁሉ እከፍላለሁ።ይህንን ትግል ያለ ማቋረጥ በማንኛውም ያልተመቸ ሁኔታ ሣደርግ ስራ አጥቸ ጦም አዳሪ እንደምሆን ፣ታስሬ እንደምሠቃይ ፣ቀጥሎም የመጨረሻውን የሞት ፅዋ እንደምቀምስ በመዘጋት አይደለም። መኪናና እጀባ የጎድልብናል ብለው የአማራን ህዝብ በግዞት አስይዘው እንደሚቀልዱት ግን ለመቀለድ አልወሠንኩም። እኔ በምክር ቤቱ ውሎ ሃሣቤን ለመግለፅ እጀን ሣወጣ ብውልም እድል የሠጠኝ አካል የለም ። ሠው በህጋዊ መድረክ ከተከለከለ የሚጠቀመው የትግል መድረክ ያገኘውንና በእጁ ያለውን እድል ይሆናል። በመጨረሻም የታፈንኩት እኔ ብቻ ሳልሆን የአማራ ህዝብም ነው።

በተረፈ እኔ የማቀርበው ሃሣብ የዚህን ያህል ሚዛን ተሠጥቶት የሚፈራ መሆኑን አልገመትኩም ነበር ከዛሬ ስብሰባ የገባኝ ነገር ተከራክረው እኔን ማሸነፍ እንደማይችሉ ነው።

ሃሣብና እውነት ያሸንፋል !! ጉልበትና አፈና ይሸነፋል።

በእስራኤል የአብን ድጋፍ ማህበር በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ግንቦት 11/2014 ዓም
19/05/2022

በእስራኤል የአብን ድጋፍ ማህበር በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ
ግንቦት 11/2014 ዓም

🙏🙏🙏በአማራ ልሂቃን ላይ መንግሥታዊ እገታ በመፈጸም የሚቆም ጥያቄም ሆነ የሚጸና ሥልጣን የለም!በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአማራ ክልል ምክር ቤት ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ተወካይ ...
18/05/2022

🙏🙏🙏

በአማራ ልሂቃን ላይ መንግሥታዊ እገታ በመፈጸም የሚቆም ጥያቄም ሆነ የሚጸና ሥልጣን የለም!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአማራ ክልል ምክር ቤት ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ተወካይ አባላት የተሰጠ መግለጫ፤
* * *
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ በሚፈጸሙ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እና መፈናቀሎችን በዘላቂነት በማስቆም መንግሥታዊ ሚናውን እንዲወጣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እንደ ድርጅትና በልዩ ልዩ ምክር ቤቶች ሕዝብ ‘ተናገር በከንፈሬ’ ብሎ የላካቸው ተወካዮቹ ሲወተውቱ መክረማቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ የአማራ ተወላጆች በግሬደር ሲቀበሩ፣ ከተሞች ሲወድሙ ጭምር የመንግሥትነት መሠረታዊ ሥራዎችን ማለትም የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ፣ ሕግና ሥርዐትን ማንበርና የተሳለጠ አመራር መስጠት ያልቻለው መንግሥት ሕዝባችን በህልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ጊዜ በአማራ ሊቃን ማለትም በአብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላትና አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችን ማንነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የአፈና፣ የሕገ-ወጥ እስራት እና የመንግሥታዊ እገታ ሥራዎች ላይ መጠመዱ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ተወካይ አባላትን አሳዝኖናል።
ይህ መንግሥታዊ የእገታና የአፈሳ ዘመቻ ‘ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ፤ ከአማራ ጋር ሒሳብ አወራርዳለሁ’ ብሎ በዕብሪት አገሪቱን እያመሰ ያለው ትሕነግ የጦር ነጋሪት በሚጎስምበት፣ ከፊል የአማራ ሕዝብ በዚህ ዕቡይ የሽብር ቡድን መዳፍ ውስጥ ሆኖ በሚሰቃይበትና መላው የአማራ ሕዝብ ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ቆሞ አሸባሪውን መመከት በሚገባው ወቅት መሆኑ ደግሞ የመንግሥታዊ አፈናው ዓላማ ሕዝብን ለዳግም ጥቃት የማመቻቸት እና ከሽብር ቡድኑ ትሕነግ ጋር እንደመተባበር የሚቆጠር ነው።
በመሆኑም እኛ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ተወካይ አባላት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ ከተወያየን በኋላ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል፤
፩. በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት ላይ እየተደረገ ያለው የአፈና እና እስራት ዘመቻ እንዲቆም፣ የታሰሩትም በአስቸኳይ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። አብን ሕጋዊና ሰላማዊ ፓርቲ ሲሆን በፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮች ምክንያት የሃሳብ ልዩነት የያዙ አባላት እና አመራሮች ላይ የሚደረገው ወከባ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ መንግሥት ከመሰል ተግባራት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን። በአንድም በሌላም መልኩ ለዚህ ሕገ-ወጥ እስራትና መንግሥታዊ እገታ ተባባሪ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሃሳብ ልዩነቱን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እናሳስባለን።
፪. በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች ላይ እየተደረገ ያለው አፈና፣ እስራት፣ ትጥቅ ማስወረድና መንግሥታዊ እገታ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በዚህ ሕገ-ወጥ ዘመቻና መንግሥታዊ እገታ የታፈኑና የታሰሩ ዜጎች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን።
፫. አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የፀጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግሥታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ የጦር መኮንኖችንና የፀጥታ አመራሮች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን።
፬. ሕግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌዴራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌዴራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በማፋለስ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ

09/05/2022

.......ማሳሰቢያ
ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
ዛሬ ማለትም በ01/09/2014 ዓ.ም የተለያዩ አካላት ላይ እርምጃ ወስደናል ሚል መግለጫ አውጥታችሁ ተመልክተናል። የመግለጫውንም ይዘት ስንመለከተው ስራ አስፈፃሚው አሁንም የፓርቲውን የስልጣን የበላይ አካል የሆነውን ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅን እንደ ከከዚህ በፊቱ ባለመቀበልና የፓርቲውን መርህ የጣሰ ሆኖ አግንተነዋል። ስለዚህ የተሰጠው መግለጫ ይቅርታ ተጠይቆ እንዲነሳና ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መጋቢት ላይ የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ የሪፎርም ስራውን እንዲሰራ እንጠይቃለን። በተጨማሪም አብን የአማራ ህዝብ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተቋም እንጅ የግለሰቦች አለመሆኑን ተረድታችሁ ከመሰል ድርጊታችሁ እንድትታረሙ በጥብቅ እናሳስባለን። በአጠቃላይ የዛሬው መግለጫ የፓርቲው ሳይሆን የግለሰቦች ነው ብለን ስለምናምን የማንቀበለው መሆኑን እናሳውቃለን።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ
ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሮኬት ሳይንስ ማዕከል በአጼ ቴዎድሮስ ሥም የሰየመውን ሮኬት ስኬታማ በሆነ መልኩ ማስወንጨፉ ቢታወቅም... ጉዳዩን በንቃት ሲከታተሉ የከረሙ አንዳንድ አካላት በሮኬቱ...
16/04/2022

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሮኬት ሳይንስ ማዕከል በአጼ ቴዎድሮስ ሥም የሰየመውን ሮኬት ስኬታማ በሆነ መልኩ ማስወንጨፉ ቢታወቅም... ጉዳዩን በንቃት ሲከታተሉ የከረሙ አንዳንድ አካላት በሮኬቱ ዙሪያ ሐሳባቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። 😆 👏👏

ከዘመኑ ቀድመው የተፈጠሩ ድንቅ መሪ******የመይሳው  ካሳ  ልጅ    ከዛሬ 161 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ሚያዚያ 5/1853 ዓ.ም ተወለደ 💚💛❤️  መይሳው ካሳ የወንዶች ቁና ስለ እ...
14/04/2022

ከዘመኑ ቀድመው የተፈጠሩ ድንቅ መሪ
******
የመይሳው ካሳ ልጅ ከዛሬ 161 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ሚያዚያ 5/1853 ዓ.ም ተወለደ 💚💛❤️ መይሳው ካሳ የወንዶች ቁና ስለ እናት አገር ኢትዮጵያ በዘውዱ ብቻ ሳይሆን በአንድያ ልጁ ጨከነ !!

12/04/2022
ከታሪካዊ የአማራና ትግሬ የአስተዳደር ወሰን ተከዜ ወንዝ።የአማራን ኢ ተነጣጣይ የግዛት አንድነት ማስከበር የትውልዱ ታሪካዊ አደራ ነው።
09/04/2022

ከታሪካዊ የአማራና ትግሬ የአስተዳደር ወሰን ተከዜ ወንዝ።
የአማራን ኢ ተነጣጣይ የግዛት አንድነት ማስከበር የትውልዱ ታሪካዊ አደራ ነው።

የመጀመሪያው ፎቶ "የእህቴ ጠባቂ ነኝ" የሚሉ  ወይዛዝርት ስብሰባ ነው። ኹለተኛው ፎቶ የሚጠብቃቸው ያጡ ወይዛዝርት የሰው እጅ ጠባቂ ኾነው ነው።Animut Abrahamይናገሩታል እንጅ አይኖሩ...
10/03/2022

የመጀመሪያው ፎቶ "የእህቴ ጠባቂ ነኝ" የሚሉ ወይዛዝርት ስብሰባ ነው።

ኹለተኛው ፎቶ የሚጠብቃቸው ያጡ ወይዛዝርት የሰው እጅ ጠባቂ ኾነው ነው።

Animut Abraham

ይናገሩታል እንጅ አይኖሩትም

21/02/2022

ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ሸዋ ወሎዬ የሚባል Cultural Identity እንጂ ፣ ጎንደሬ ወይም ጎጃሜ፣ ሸዋ ወይም ወሎዬ የሚባል Political Identity የለም።

የነገ እጣ ፈንታህ አንድ ነው። ሸኔም በለው ወ*ያኔ አሜሪካም በለው ብልጽግና "አማራ" ብሎ ነው የሚውያቅህ!

ትንግርቱ ገ/ጻድቅ (ረ/ፕሮፌሰር)

17/02/2022

አድዋ
💚💛❤️
ቀጣዩ ክብረ-በዓል! . . .

በአላማህና ግብህ ፅናDessalegn Chanie
06/02/2022

በአላማህና ግብህ ፅና
Dessalegn Chanie

17/01/2022

በ ዶ/ር Tewodros Hailemariam የአብን የውጭ ጉዳዮች ክፍል ሀላፊ።
***
በርባንን የፈታው ማነው?
ማህበራዊ እረፍት የመንሳት አስር አጀንዳዎች
=================
1. አደገኛው የብልፅግና መዛነፍ
በአንድ በኩል የህወሓትን የአውራ ድርጅት ሌጋሲ የማስቀጠል አባዜ ኦፒዲኦ ያለፍሬን እየነዳው ነው። በሌላ በኩል ሳይወለድ የጨነገፈው
የትግራይ ብልፅግና የህወሓትን ሚና ሊተካ አለቻለም ፤ ደቡብም በአባ ብላ ተመትሯል። ብአዴን ያው ጥንተ ሀብሶ ነው። ይህ መሠረታዊ ጉዳይ
የፈጠረውን የውስጠ ፓርቲ ትርምስና የኃይል አሰላለፍ መዛነፍ ብልፅግና ሊፈታ አልቻለም።
በዚህም የተነሳ ክፉኛ የተከፋፈለ ፣ ምንደኞች የተጣቡትና አቅመ ቢስ መንግሥት በፌክ ምርጫ ተቀባብቶ ተኮፍሷል። ከትብስ ይሻላል ብለን
ደም የተቃባንበት መንግሥት ህዝብን አንድ አድርጎ "ወደ ብልፅግና" ሊመራ ቀርቶ መሠረታዊ የሰላምና ደህንነት ማስከበር ግዴታውን አልተወጣም።
ሀገሪቱ የጦር አበጋዞች የሚፈነጬባት ፣ የንፁሃን እንባና ደም የሚጎርፍባት አኬልዳማ ሆናለች። መንግሥት የአንድ የንዑስ ቡድንን የአመፅ ጦርነት እንኳን ተዋግቶ ለማሸነፍ የማይችል ደካማ መሆኑ በገሀድ ታይቷል።
የሰሜን ዕዝ የክህደት ጭፍጨፋ ፣ በኦሮሚያ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በደቡብ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው የማያባራ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ፣ የትግራይ ወራሪ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ያደረሰው የአጥፍቶ መጥፋት ውድመት በሙሉ የመንግሥት ከያቅጣጫው መናቅ የጋበዘው ነው።
ለዚህ ሁሉ ግዙፍ ስህተትና ጥፋት ማነው ተጠያቂው ህዝብ መርጦኛል የሚለው ብልፅግና በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ቅሌት ወንጀለኛ መኮንኖችን እየሾመ እየሸለመ ነው። ለሰሜን ዕዝ ደም ለአማራና አፋር ውድመት የተጠየቀ የጦር መሪ የለም። የተሸነፉ ፊልድ ማርሻሎችና ሙሉ ጄኔራሎችጨ ነገረ ዓለሙን የትልቅ ትራጂ - ኮሜዲ ዝንፈት መድረክ አድርገውታል።
ወደፊት ጠ/ሚ/ዶ አብይ ፣ ካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ፣ አፈግፋጊ ጄኔራሎቻቸውና አማካሪዎቻቸው በታሪክ ችሎት ቀርበው ይሙት በቃ እንደሚፈረድባቸው አልጠራጠርም።
Tewodros Hailemariam

11/01/2022
09/01/2022
08/01/2022

ፊልድ ማርሻል እሸቴ ሞገስ💪❤👌❤💪❤

አጋሩን!የእኛን ስቃይ ለተሰቃያችሁ!በአሸባሪው ስር ሆናችሁ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ስቃይ ያሳለፋችሁ ወገኖች ያሏችሁ የፎቶ ግራፍ፣ የቪዲዮ መረጃዎች፣ ገጠመኞች፣ ታሪኮች እንዲሁም ያላችሁበትን...
02/01/2022

አጋሩን!

የእኛን ስቃይ ለተሰቃያችሁ!

በአሸባሪው ስር ሆናችሁ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ስቃይ ያሳለፋችሁ ወገኖች ያሏችሁ የፎቶ ግራፍ፣ የቪዲዮ መረጃዎች፣ ገጠመኞች፣ ታሪኮች እንዲሁም ያላችሁበትን ሁኔታ ለምታውቁት ሰው በውስጥ መስመር አጋሩት። አጋሩን!

ለወራት ድምፃችሁ ታፍኗል። ብዙ ስቃይ አሳልፋችኋል። ብዙ ጀግንነት ሰርታችኋል። ሚዲያዎች የሁላችሁንም ታሪኮች ሊነግሩን አይችሉም። ፌስቡክ ተከፍቷልና ያለፋችሁበትን ሌላውም ይጋራው። ጀግንነታችሁ ያበረታናል። ድምፃችሁ መሰማቱ እፎይታ ይሰጣል። ጫናችሁን የሚጋራ አይጠፋም።

የከረማችሁበትን ለምዳችሁት ይሆናል። እናንተ ያን ሁሉ ስላያችሁ ምንም የሚመስላችሁ ለሌላው ወገናችሁ አዲስና ትልቅ ነገር ነው። አጋሩን። ለምታውቁት አጋሩ!

01/01/2022
27/12/2021
24/12/2021

ክቡር ጠ/ሚ/ዶ አብይ
ይሄ ስህተትዎ የመጨረሻው እንዲሆን እመኛለሁ ‼️
==========:========
1. የህግ ማስከበር የተባለውን የመጀመሪያውን ዘመቻ በዚያ በታሪካችን እጅግ አሳፋሪ በሆነ ውርደት አጠናቀቃችሁ። የሠራዊቱ ደም በከንቱ ፈስሶ ቀረ። እናንተ ወታደራዊ ፍርድ ቤት መቅረብ የሚገባችሁ አመራሮች ጭራሽ ዱቄት አድርገነዋል የሚል ክህደት ካዳችሁ የኢትዮጵያን ህዝብ።

2. ሙሉ በሙሉ አጠናክራችሁት የሸሻችሁት ወያኔ ያንን ሁሉ ውድመት ሲያደርስ ፣ የአማራና የአፋር ህዝብ የሞት ሽረት ሲፋለም እናንተ የጎረቤት ሀገር እንኳን የተወረረ ሳይመስላችሁ ፣ ችግኝ ስትተክሉ ፣ የሰንበት ፓርቲ ስትደንሱ አራት ወር ሙሉ ተኛችሁ። ህዝብ የጣለባችሁ አደራ በአምስተኛው ወር ትዝ ሲላችሁ ዘመቻ ህልውና ብላችሁ የፎቶ ዘመቻ አደረጋችሁ።

3. የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገር ወዳድ ፣ መሪ አክባሪ ነውና ያለፈው ይቅር ብሎ በሙሉ ኃይሉ ከጎናችሁ ቆመ። ጠላቱን ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ተረባረበ ፣ ደማ ፣ ሞተ። እነናንተ ግን ገና ጥቂት ውጊያዎችን ማሸነፍ ሲጀመር የህልውና ስጋት የለም የሚል ዘፈን አመጣችሁ። ዱሮም የአማራና የአፋር ህልውና አይገዳችሁም።

4. ዛሬ በተለመደው የህዝብ ንቀት ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚልና ወያኔን ነፃ የሚያወጣ መርዝ በምሥጢር ቀምማችሁ መጣችሁ። ህዝብን በግድ ለመጋት በስህተት ላይ ስህተት እየሰራችሁ ነው። በምን ተአምር ነው የከዳችሁትንና በከፊል ያፈረሳችሁትን ሀገር አንድ የምታደርጉት ? በሌላ ክህደት?

5. የሚገርመው በራሳችሁ ላይ የምታደርጉት ተሳልቆ "በስሜት" አንወስንም የሚል ሆኖ መጣ። እስካሁን ሀገራችን በአጠቃላይና የአፋርና የአማራ ህዝብ እንዲሸከሙ የተደረገው ዓመት የፈጀ መከራ በሌላ መንግሥት መሪነት አልተፈፀመም። ስለዚህ ዓመት ሙሉ የሰራችሁት በጥናትና በስሌት ያደረጋችሁት ነው?

በራስ ላይ መሳለቅ የህሊና ማስተንፈሻ ሊሆን ይችላል። ከእንግዲህ በቆሰለ ህዝብ ላይ መሳለቅ ግን ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል!

21/12/2021

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሸባሪ ጋር መደራደር ካሰቡ ምን እንደሚከሰት ልንገርዎ፦
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬

➔በዚህ ዘመቻ ያገኟት ተቀባይነት እጅዎ ላይ ትሟሟለች።

➔ኢትዮጵያ የምትባል አገር ቀርቶ ወንበር አይኖርዎትም።

➔ህውሓትን ከጎንዎ አሰልፈው የአፋርን እና የአማራን ሕዝብ መግ*ጠም ይጠበቅብዎታል።

➔አሸባሪው ሃይል ለፈጸማቸው ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂው እርስዎና ፓርቲዎ ይሆናሉ።

➔ከአሸባሪ ጋር ድርድር በጀመሩ ማግስት ከኦነግ ሸኔ ውጭ የሚደግፍዎ ሕዝብ አይኖርም።

➔ብልጽግና የሚባል ፓርቲ ያበቃለታል።

19/12/2021
13/12/2021

ትክክለኛው ፔጃችን 180,000 የደረሰው ይህ ብቻ ነው።
በስማችን ተመሣሥለው የተከፈቱ ፔጆችን Unlike አድርጉ።

06/12/2021

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ እና ባቲ ከተሞች በወገን ጦር ቁጥጥር ስር በመግባታቸው ደስታውን ይገልፃል።

ሕዝባዊ ኃይሉ ሁሉም የአማራ ግዛቶች ነፃ ወጥተው ጠላት የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ የማይሆንበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ሁሉን አቀፍ ትግል የሚያደርግ መሆኑንም ለመላው ህዝባችን በድጋሚ ያረጋግጣል።

ክብር ለነፃነታችን ለተዋደቁ ጀግኖች!

አዲስ ትውልድ! አዲስ ተስፋ! አዲስ አስተሳሰብ!

ሕዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

06/12/2021


05/12/2021
07/11/2021
29/10/2021

ዳሞት…እዳው ሞት…የአማራ አንገቱ አንድ ነው ብሏል!

28/10/2021

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ቂርቆስ ክ/ ከተማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share