MIZAN MEDIA ሚዛን ሚዲያ

  • Home
  • MIZAN MEDIA ሚዛን ሚዲያ

MIZAN MEDIA ሚዛን ሚዲያ Mizanawi Media (ሚዛናዊ ሚዲያ) - For free and fair Opinion

ከዋይት ሃውስ በመጠን እንጂ በጥራት ይበልጣል ኧውስ አይበልጥም? በኮሜንት ድምጽ ስጡበት!!!
19/02/2024

ከዋይት ሃውስ በመጠን እንጂ በጥራት ይበልጣል ኧውስ አይበልጥም?

በኮሜንት ድምጽ ስጡበት!!!

ታሪካዊው ብሔራዊ ቤተ መንግሥት #...

ከኮቪድ 20 እጥፍ የባሰ ገዳይ በሽታ እየመጣ ነው!!!!  ድ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምቀጣዩ ወረርሽኝ መከሰቱ እንደማይቀር ተገለጸ“በሽታ X መከሰቱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ ነው“ - ዶ/ር ቴዎ...
19/02/2024

ከኮቪድ 20 እጥፍ የባሰ ገዳይ በሽታ እየመጣ ነው!!!!

ድ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

ቀጣዩ ወረርሽኝ መከሰቱ እንደማይቀር ተገለጸ

“በሽታ X መከሰቱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ ነው“ - ዶ/ር ቴዎድሮስ
በዓለማችን ላይ የቀጣዩ ወረርሽኝ መከሰት የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አስጠነቀቁ፡፡

የሆነ ጊዜ ላይ “ወረርሽኝ X” የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ሰሞኑን መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ ለታደሙ ተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ “በቀጣዩ ወረርሽኝ ዝግጁነት ላይ አጣዳፊ ዓለማቀፍ ስምምነት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
”በሽታ X እያልን የምንጠራው ወረርሽኝ በኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ወይም በአዲስ ኮሮናቫይረስ አሊያም በአዲስ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ሊከሰት ይችላል፤ ስለመንስኤው ገና አላወቅንም” ብለዋል፤ የጤና ድርጅቱ ሃላፊ፡፡
ሳይንቲስቶች፣ ቀጣዩ “በሽታ X“ ከኮቪድ ወረርሽኝ ሃያ እጥፍ ገዳይ እንደሚሆንና አደገኛ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ ያስከትላል ብለው እንደሚያስቡ የዓለም ጤና ድርጅት ሰነድ ይጠቁማል፡፡

”አሁን ባለው ሁኔታ ዓለም ለቀጣዩ በሽታ X እና ለቀጣዩ ወረርሽኝ አልተዘጋጀም” ሲሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
በሽታ X የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀምነው በ2018 በተመሳሳይ መድረክና ጉባኤ ላይ ነው ያሉት የጤና ድርጅት ሃላፊው፤ አጠቃቀማችንም ገና ላላወቅነው ነገር ግን ዝግጁ ልንሆን ለምንችልበት በሽታ ነው ብለዋል፡፡

“ኮቪድ- 19 በሽታ X ነበር፤ አዲስ በሽታ የሚያመጣ አዲስ ተህዋስያን፡፡ ነገር ግን ሌላ በሽታ X ወይም በሽታ Y ወይም በሽታ Z ይኖራል” ብለዋል፤ የተቋሙ ሃላፊ፡፡

የዶ/ር ቴዎድሮስ ተቋምና ዓለማቀፍ መንግሥታት በዓለማቀፍ የወረርሽኝ ዝግጁነት ስምምነት ላይ ሲሰሩ መቆየታቸው የተጠቆመ ሲሆን፤ የስምምነቱ ቀነ- ገደብ በመጪው ግንቦት ወር ላይ እንደሆነና በፍጥነት እየተቃረበ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ለዚህ ዓለማቀፍ የወረርሽኝ ዝግጁነት ስምምነት አንዱ እንቅፋት፣ በዘፈቀደ የሚነዛው ውሸትና የሴራ ንድፈ ሃሳብ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ፡፡

”--ስምምነቱ የአገር ሉአላዊነትን ለዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት አሳልፎ የሚሰጥ ነው -- ዓለማቀፍ የጤና ድርጅት በአገራት ላይ የእንቅስቃሴ ገደብና የክትባት ግዴታ እንዲጥል ሥልጣን ይሰጠዋል --- ተቋሙ የሰዎችን የግል ህይወት ለመቆጣጠር ይፈልጋል--” የሚሉት እየተሰራጩ ከሚገኙት ውሸቶች ጥቂቶቹ መሆናቸውን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
“እነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ሃሰት ናቸው --- እንደዚህ የሚል ሰው አንድም መረጃው የለውም አሊያም እየዋሸ ነው” ብለዋል፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ፡፡

የስምምነቱ ረቂቅ ቅጂ በተቋማቸው ድረገጽ ላይ እንደሚገኝና ሁሉም ሰው ለራሱ እንዲያነበውም ሃላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
“አንድ ነገር ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ፡- ዓለማቀፍ የጤና ድርጅት በኮቪድ- 19 ወቅት በማንም ላይ ምንም ዓይነት ግዴታ አልጣለም፡፡ የእንቅስቃሴ ገደብም ሆነ የማስክና የክትባት ግዴታ አልጣለም” ብለዋል፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፡፡

“ያንን የማድረግ ሥልጣን የለንም፤ አንፈልገውምም፡፡” ሲሉም አክለዋል፡፡

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋነኛው የህገ ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ነው ብሎ ከዚህ በታች ያለውን ሀሳቡን አስቀምጧል:-የኢትዮጵያ የንግድ ባንክ በህገወጥ የባንኪንግ እንቅስቃሴ ላ...
17/02/2024

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋነኛው የህገ ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ነው ብሎ ከዚህ በታች ያለውን ሀሳቡን አስቀምጧል:-

የኢትዮጵያ የንግድ ባንክ በህገወጥ የባንኪንግ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፍ ባንክ እየሆነ ነው !

ባንኩ በከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት የሚዘወር ነው። የብልፅግና መንግስት የኔ የሚላቸውን ተላላኪዎችን በወሳኝ የባንኩ ሃላፊነት ቦታ ላይ በመመደብ በባንኩ ውስጥ የ Money Laundering ህገ ወጥ የዶላር ክምችት ወንጀልን የሚፈፅመው።

የአሁኑ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ ቀደም ሲል የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመድቦ ሲሰራ የነበረው አቶ ባጫ ጊና ከፍተኛ የህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ለሚሳተፉ ባለስልጣናት ትብብር በማድረግ ስማቸው ይጠቀሳል።

ለዚህ የዘረፋ ወንጀል እንዲመች ባንኩ ውስጥ ምንም እውቀትና ልምድ የሌላቸው ግለሰቦች ብሄረሰባዊ ማንነታቸው ተመርጦ እንዲቀጠሩ እና ባንኩን እንዲመሩ ተደርጓል::

በዚህ ባንክ ውስጥ የተሰገሰገው የዘረፋ ቡድን በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የዶላር ክምችት እያቀናበረ ሲሆን RIA በሚባለው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላለፊያ ቢሮ አማካይነት አንድ ዶላር እስከ 127 ብር እየቀየረ ይገኛል:: ይህ በህጋዊ exchange rate ከሚቀየረው የአንድ ዶላር ዋጋ 56.55 የ70 ብር ብልጫ ይኖረዋል።

ይህ ታላቅ የሀገሪቱ ባንክ የጥቁር ገበያ እንቅስቃሴ ላይ / black market በቀጥታ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ታዉቋል።
******
ያሰፈርነው መረጃ የሲሳይ አጌና ነዉ

Commercial Bank of Ethiopia

ኢትዮጵያ ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት እግር ኩዋስ ግጥሚያ ...እንዲሁ ቢሆንስ ለማለት ነው::
17/02/2024

ኢትዮጵያ ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት እግር ኩዋስ ግጥሚያ ...

እንዲሁ ቢሆንስ ለማለት ነው::

The tournament award winners at AFCON 2023:▪️Best Player: William Troost-Ekong (age 30)▪️Golden Boot: Emilio Nsue (age 3...
13/02/2024

The tournament award winners at AFCON 2023:

▪️Best Player: William Troost-Ekong (age 30)
▪️Golden Boot: Emilio Nsue (age 34)
▪️Best Goalkeeper: Ronwen Williams (age 32)

ወቅታዊ ፎቶ
09/02/2024

ወቅታዊ ፎቶ

አወዛጋቢው የታላቅ ሰው ሞት ሚስጥር"ወ/ሮ አስቴር ግን ታድላ ¡ " በማለት አወዛጋቢ የሆነውን የገነነ መኩሪያ ሞት ምክንያት ሚስጥር አሁናዊ መረጃ ቴድሮስ ተክለአረጋይ እንዲህ ብሎአል::***...
31/01/2024

አወዛጋቢው የታላቅ ሰው ሞት ሚስጥር

"ወ/ሮ አስቴር ግን ታድላ ¡ " በማለት አወዛጋቢ የሆነውን የገነነ መኩሪያ ሞት ምክንያት ሚስጥር አሁናዊ መረጃ ቴድሮስ ተክለአረጋይ እንዲህ ብሎአል::
********************
ገነነ መኩሪያን ያህል የሀገር ሀብት ለሞተበት ቤት ቀድሞውንስ የሞባይል ( የዕቃ ) መጥፋት ዜና መሆን ነበረበት ? ሞባይል ተገኘስ ጠፋ ምኑ ነው ዜና የሆነላት ? ይህን ያህል መረጋጋቷ ካልቀረ ለምን " እንዴት ገነነ ራሱን ሊያጠፋ ቻለ ? ምንድነው የገፋው ? " ለሚለው እንቆቅልሽ ወደ ሚዲያ ቀርባ መረጃ አትሰጠንም ? እውነቱ ምንም ይሁን ምን ራሱን ለማጥፋት ያበቃዋል ብላ የምትጠረጥረውን ፍንጭ ለምን አትሰጠንም ? ከገነነ ጋር ምን አጋጫቸው ? ግጭታቸው ራስን ለማጥፋት የሚያበቃ ነበረ ? መረጋጋቷ ፣ ፈገግ ማለቷ ካልቀረ ለምን ያህን አትነግረንም ?

👉 #ፀሐይ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ "ፀሐይ" አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባቸውን ገልፀው እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው መልእክት አጋርተዋል።ለመሆ...
31/01/2024

👉 #ፀሐይ

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ "ፀሐይ" አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባቸውን ገልፀው እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው መልእክት አጋርተዋል።

ለመሆኑ ፀሐይ አውሮፕላን ማነው ለሚለው ጥያቄ ተከታዪ የ Andinet Girma ግርማ ፅሁፍን እናጋራችሁ።

“አሁን ያለው የእትዮጵያ አየር መንገድ እንኳን ሊቋቋም ገና ሳይታሰብ በፊት በአፄ ኃይለስላሴ የተቋቋመ የአውሮፕላን ማምረቻ በ1927 ዓ/ም ተከፍቶ አውሮፕላን ማምረት ጀምሮ የመጀመሪያዋ አውሮፕላን ስሟ ኢትዮጵያ 1 ወይም ፀሀይ በመባል ተሰይማ ነበር።

ይህች አፍሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራችው አውሮፕላን የክንፎቿ አብዛኛው ክፍል ከእንጨት የተሰራ ሲሆን 115 የፈረስ ጉልበት ነበራት።

በ1927 በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአውሮፕላን ምርት ተጀምሮ እስከ 1928 ድረስ በአመት ሶስት አውሮፕላኖችን የማምረት ውጥን የተያዘ ቢሆንም በ1928 ኢጣሊያ ወረራ እስክትጀምር ድረስ አንድ ያለቀላት አውሮፕላን ተሰርታ አካሏ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ተቀብታ ፀሐይ ተብላ ተሰይማ ነበር።

ይህች የመጀመሪያዋ አውሮፕላን የመጀመሪያውን በረራዋን በ1928 ታህሳስ ወር ላይ በአዲስ አበባ ያደረገች ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ እስከ 6100 ሜትር መብረር የምትችልና በሰዓት ከ150 እስከ 185ኪሎ ሜትር መብረር የምትችል 115 የፈረስ ጉልበት ካለው ሞተር የተሰራች 7 ነጥብ 32 ሜትር ርዝመትና ሁለት ሰው መያዝ የምትችል ለ30 ሰአት የበረረች አውሮፕላን ነበረች።

ጣሊያኖች አትዮጵያ ከገቡ በኋላ የአፄው የግል ፓይለት ሉዲግ ዌበር ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና በማሳደር ስራውን በማስተጓጎል ፀሐይ ቆማ ከነበረችበት ጃንሜዳ በማስነሳት በአዲስ አበባ ኣካባቢ ካበረሯት በኋላ ወደሀገራቸው ወስደው በኢጣሊያን አቪየሽን ሙዚየም ውስጥ የንጉስ እውሮፕላን በመባል እሰከዛሬም ትጎበኛለች።

ሌላኛው ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው አውሮፕላን ፓቴዝ የምትባል ሲሆን :: ከፈረንሳይ የመጣችውም በ1922 ሲሆን የዚች አውሮፕላን ገጣጣሚዋ አንድሬ ሜሬዝ የተባለ ፈረንሳዊ ነበር፡፡

ፀሐይ መጠሪያዋን ያገኘችውም በአጼ ሃይለ ስላሴ ሴት ልጅ በልእልት ፀሐይ ሃ/ስላሴ ስም ነው::

28/01/2024

ብዙ ሚሥጥሮችን የያዘ ቃለምልልስ

አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስት እና ከገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት ተሰናበቱላለፉት 11 ዓመታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ ደመቀ መኮንን፤ ከመንግስት እና በገዢው ፓርቲ ...
26/01/2024

አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስት እና ከገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት ተሰናበቱ

ላለፉት 11 ዓመታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ ደመቀ መኮንን፤ ከመንግስት እና በገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት መሰናበታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ። አቶ ደመቀ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት በነበራቸው የኃላፊነት ቦታ ላይ፤ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መተካታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

ላለፉት አራት ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ስራን ደርበው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ደመቀ፤ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ሲካሄድ በነበረው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ “በክብር መሸኘታቸውን” ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ታዋቂና ተወዳጆቹ የፊልም ተዋናዮች ግሩም ኤርሚያስ እና አማኑኤል ሃብታሙ በመሪ ተዋናይነት የነገሱበት አፊኒ ፊልም AFFINI                                          ...
25/01/2024

ታዋቂና ተወዳጆቹ የፊልም ተዋናዮች ግሩም ኤርሚያስ እና አማኑኤል ሃብታሙ በመሪ ተዋናይነት የነገሱበት አፊኒ ፊልም AFFINI
"አፊኒ ፊልም " ተመርቆ ለእይታ የሚበቃበት ቀን ይፋ ሆነ::

ወጪው በመንግስት ተሸፍኖ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተሰራው አፊኒ ፊልም የፊታችን የካቲት 2/6/20 በሲዳማ ባህል አዳራሽ እንደሚመረቅ ነው የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ያስታወቀው::

የቢሮው ሀላፊ በመግለጫቸው "አፊኒ" የተለያዩ ኩነቶችን የያዘ ድንቅ የሲዳማ ባህል እንደሆነ ገልጸው ፊልሙ የሚዳስሳቸው አጠቃላይ የህዝቡን አኗናር አመጋገብ እንዲሁም የክልሉን መልከአ ምድር የዳሰሰ ሲሆን ትኩረቱ በሲዳማ የግጭት አፈታት መርሆች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ገልጸዋል::

የቢሮው ሀላፊ አክለውም የፊልሙ ወጪ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑን ገልጸው ተሰርቶ መጠናቀቁን ተከትሎ የፊታችን የካቲት 2/6/2016 በሲዳማ ባህል አዳራሽ በይፋ እንደሚመረቅ ገልጸዋል::

አቶ ጃጎ አገኘሁ በመግለጫቸው በስነ ስርአቱ ላይ የሲዳማ ክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሚኒስቴሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚገኙ ገልጸዋል::

የፊልሙ አሰሪ ኮሚቴ በበኩሉ የተሰራው ፊልም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው ከምርቃት ሥነ ስርአቱ በኃላ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ለእይታ እንደሚበቃ በመርሀ ግብር መያዙን ገልጸዋል::

Sidaamu Qoqqowi WTI Biironni qixxaabbinoti AFFINI filme Ammajje 2/2016 M.D Sidaamu Wogate Harira maassantanno.

AFFINI Sidaamu kipho tidhanno maalalete budu hornyonna ogimmaati.

Tini ogimma beeqqaasinchonna dimokiraasitte wodhi-woro ha’runsine araara dirrisatenni hegeraamo keere halashshate widoonni qara kipho tirate udiinnichooti.

Sidaamu budu yooaanchimmara ‘halaalu’ woy addu addanka luphiimu baychi noosihonna mannu hasatto, lao, akatoomme, sumiimmenna noo addi gobbaanni halaaliweello mitturino di”ikkanno. Kaphunni hadda moromme yekkeeramate kaayyono dino; diino fajjinanni.

Konnira, ‘affini’ kipho tirate hornyonna gumi araara dirrisatenni dagoomaho hegeraamu keeri rumuxxanno gede dandiissannoha ikkasinni tenne muxxe hornyo Sidaamu Daganni sae gobboomaho saeno kalqoomaho elate “AFFINI” filimete industire giddo leellanno gede assate seeda xeertinye qaanfoonni. Qoleno, gobbankera maccare ikkitinorinna muxxe ogimmaano artistooti beeqqitinoti ‘affini’ filme kuneeti jeefa gante federaalennirnna qoqqowunniri aliidiri mootimmate gashshaano, Sidaamu geerrinna cimeeyye, seesalote ogeeyye, fullahaanonna babbaxxitinori dagate mereerinni addi addi qarqarinni koysamino wosini leellannowa Ammajje 2/2016 M.D Hawaasi Quchumi giddo noo Sidaamu Wogate Harira faajjetenni maassamanno.

Tenne muxxe hornyo agartenna qorobbe tenne ilamara iillishshinona Sidaamu woga annuwi Cimeeyye galatama hasiissannonsareeti!
Lowo heelli-buuffo giddoonni sa’e AFFINI filme jeeffanno gede babbaxxitino doogonni wodo baattiniri wo’munku filme maassote iillasenni Hawalle Hagiidhitinoonni! Hawalle Tashshi Yinonke!!

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ( ሊብሮ ) በጥቂት ሰዎች ክብሩን በማይመጥን መልኩ ተቀበረ ። ገነነ እውቀት እንጂ ቲፎዞ አልነበረውም ።         👉 ገነነን በድለነዋልና ፣ ክደነዋልና ሌላ መርኀ ...
25/01/2024

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ( ሊብሮ ) በጥቂት ሰዎች ክብሩን በማይመጥን መልኩ ተቀበረ ። ገነነ እውቀት እንጂ ቲፎዞ አልነበረውም ።
👉 ገነነን በድለነዋልና ፣ ክደነዋልና ሌላ መርኀ ግብር ተዘጋጅቶ በክብሩ ልክ ልንዘክረውና ይቅርታ ልንጠይቀው ይገባል ።
********************************************************
በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ዙሪያ ጥቂት ልብ ሰባሪ እውነታዎች ፦

👉 ሕይወቱ አልፎ የተገኘው ሆቴል መኝታ ክፍል ውስጥ ነው ። ለጥቂት ቀናት ከቤት ወጥቶ ሆቴል ነበረ የሚኖረው ።
👉 ከህልፈቱ ደቂቃ እና ሰዓታት በፊት ከጓዳጆቹ ጋር በስልክ ተነጋግሯል ። ወዳጆቹን ካወራ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነው ሞቶ የተገኘው ። በዚህና ሌሎች ምክንያቶች " ሕይወቱን በገዛ እጁ ነው ያጠፋው " የሚል የጎላ ጥርጣሬ አለ ።
👉 ፖሊስ ከትናንት በስቲያ በጥርጣሬ ባለቤቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ከመረመረ በኋላ ለቋታል ።
👉 ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የስኳር ህመምተኛ ነው ። በዚህ ምክንያት የዛሬ 4 ወር ገደማ ቀኝ እግሩ ከጉልበቱ በታች ተቆርጧል ። የእግሩን መቆረጥ ማንም ሰው እንዲሰማበት አልፈለገም ። እርግጥ ነው ጥቂት ሰዎች እውነታውን አውቀዋል ። ሰዎች በአካል እየመጡ እንዲጠይቁት ፍላጎት አልነበረውም ። ብዙውን ጊዜም የወዳጆቹን ስልክ አያነሳም ነበረ ። በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ድባቴ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል ።
👉 ሰው ሰራሽ እግር እንዲገጠምለት ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው ። ሊያሰራም ተለክቶ ሂደቱ ከቀጠለ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲቋረጥ ተደርጓል ። ይሁንና ገነነ ሰው ሰራሽ እግሩን ለሚሰራለት ባለሙያ " እባክህ ስራልኝና በእግሬ እንድሄድ አድርገኝ ። ከአማኑኤል አጂፕ ( መኖሪያ ቤቱ ) እስከ ምዕራብ ሆቴል በእግሬ እንድሄድ አድርገኝ ። ያለምንም ድጋፍ በእግሬ መሔድና ወደ ስራዬ መመለስ እፈልጋለሁ " ብሎ ተናግሯል ።
👉 ከሙያ ጓደኞቹ የቅርቡ እና እስከ መጨረሻው ከጎኑ ያልተለየው ጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር በገነነ ጉዳይ እጅግ መመስገን አለበት ።ሰዒድ በገነነ የጨለማ ወራት ውስጥ በመጠኑም ብርሀን ይዞ የተገኘ ሰው ነው ። አበበ ማንደፍሮ እና ሲሳይ ተሰማ የሚባሉ ወዳጆቹም እንዲሁ ከችግሩ ወቅት አንስቶ በአካልና በስልክ የሚያገኛቸው ወዳጆቹ ናቸው ። ሌሎች ወዳጆቹም አደጋው ከደረሰበት በኋላ ቀርበው ሊጠይቁት ቢፈልጉም ገነነ ( በራሱ ምክንያት ) ፈቃደኛ አልነበረም ።
👉 በመጨረሻ ላይ የሚሰራው አሻም ቴሌቪዥን ቢሆንም ገነነ ቤት ከዋለ በኋላ ደመወዙ ተቋርጧል ።
👉 ትናንት ጧት በመኖሪያ ቤቱ የተጣለው ድንኳን ውስ ከ20 የማይበልጥ ለቅሶ ደራሽ ነው የነበረው ።
👉 ገነነ እድሜውን የጨረሰው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ቢሆንም ከቀደምቶቹ ወጭ ቁጥር ያላቸው የዘመኑ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቀብሩ ላይ አልተገኙም ።

ይህን ታላቅ የመረጃ ጋዜጠኛ ነው ከእሱ አስተዋጽዖ አንጻር እዚህ ግባ በማይባል ቁጥር በቤቱም በቤተ ክርስቲያንም ተገኝተን የሸኘነው ። እንደ እውነቱ ከእኛ የሚጠበቀው ልካችን ይሄ ነው ። እንዲህ ስናደርግ ነው የኖርነው ። የካራማራውን ጀግና ዓሊ በርኪን ፣ ባለቅኔው ጸጋዬ ገ/መድህንን ፣ ሌሎች ሀገር የሰሩ ጀግኖችን እንዲህ ጥቂት ሰዎች ናቸው የሸኟቸው ። በአንጻሩ ምንም የሚጠቀስ ሀገራዊ አስተዋጽዖ ለሌላቸው ደግሞ በወቅቱ ያላቸውን አንድ ስራ ብቻ አይተን ሀገር ስናምስ ፣ የሕይወት ታሪክ ለማንበብ ያለው ዝግጅትና መገፋፋት ለጉድ ነው ። ገነነን ግን ለቅሶውን ማድመቅ ቢቀርብን እንኳን ቀብሩን አልደረስነውም ። " ትልልቅ " የሚባሉ ሚዲያዎችም ትኩረት አልሰጡትም ። ጭራሽ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን ያልዘገቡም አሉ ። የቴሌቪዥን ጣቢያ ተብለን ስንት ረብየለሽ የጎዳና ላይ ቧልት ለመቅረጽ ከምንጠቀምባቸው ካሜራዎች አንዱን እንኳን የገነነን ሽኝት ለመቅረጽ አላክንም ። ገነነን ከእንቶ ፈንቶዎቹ ምስሎቻችን የአንዱን ያህል እንኳን ቦታ አልሰጠነውም ። ለእኛ ልካችን ይሄ ነው ።

ገነነ በሚመጥነው መልኩ እንኳን በድምቀት ብንቀብረው አንዳች ለእሱ ጥቅም የለውም ። ቀና ብሎ አያያንም ። አሁንም እሱ " አዝኜባችኋለሁ " አላለንም ። የቋሚ ተስፋ ነው የሚሞተው ። ለሀገር መድከምና መስራት ፣ የራስን ጥቅም ትቶ ለሕዝብ መድከም ነው በቋሚዎች ልብ ውስጥ የሚሟሽሸው ። ቤተሰብ ነው ልቡ የሚሰበረው ። " ለምንና ለማን ነበር ያን ያህል እንቅልፍና ጤናውን ያጣው ? " የሚለው ።

መምህር እሸቱ በስርዓተ ቀብሩ ላይ ይህን ብለዋል ።

" ዛሬ በጨርቅ ጠቅልለን፣በሳጥን አሽገን ወደ መቃብር የምንሸኘው አንድ ተራ ስጋና ደም አይደለም ። መረጃን ፣ ባሕልን ፣ ትውፊትን ፣ እውቀትን ነው አሽገን እየቀበርን ያለነው ብዬ ነው የማምነው ። እኔ ዛሬ ትልቅ ፕሮግራሜን ሰርዤ የመጣሁት መረጃ ሲቀበር ፣ እውቀት ሲቀበር ፣ ትውፊት ሲቀበር ቤቴ አልቀመጥም ብዬ ነው ። ገነነን ያህል ሰው በዚህ መልኩ በመቀበሩ በጣም ነው የማዝነው ። ድብልቅልቅ ይላል የሚል ሀሳብ ነበረኝ። "

የሰው ሀቅ የምትቀሙ ፣ የሰውን ጥቅም የምታስቀሩ ፣ አጠገባችሁ ያሉ ወዳጆቻችሁ የስሜትና የገንዘብ እንዲሁም የመብት ጉዳት በደረሰባቸው ወቅት በቻላችሁት ሁሉ ዛሬ ድረሱላቸው ። ነገ የለም ። እናንተ የሚፈለገውን ሁሉ አድርጋችሁ ነገ ስትመጡ እነሱ በቦታው ላይ ላይኖሩ ይችላሉ ። ፀፀት ለእነሱ አይረዳቸውም ። መድረስ ላለባችሁ ሁሉ በተቻለ መጠን ዛሬ ድረሱ ፤ አሁን ። ነገ የለም ። በኋላም ላይኖር ይችላል ። አሁን ።

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ገነነን ቀበርነው እንጂ በክብር አልሸኘነውም ። ከመንግሥት ጀምሮ በእውቀቱ የተጠቀምን ሁሉ ሌላ መርኀ ግብር ተዘጋጅቶ ገነነን በክብሩ ልክ ልንዘክረውና ይቅርታ ልንጠይቀው ይገባል ። ትናንት ባደረግነው እንደ ሀገርና ሕዝብ ልናፍር ይገባናል ። ተስፋን ላንቀብር ይገባናል ። ለሀገርና ለሕዝብ ራስን መስጠትን ዋጋውን ላናረክሰው ይገባል ። የዚህን ታላቅ ሰው ቀብሩን እንኳ ያልዘገባችሁ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በተግባራችሁ እናንተ ልታፍሩ ይገባችኋል ። እፍረታችሁ ደግሞ በሀፍረትና በመደበቅ ሳይሆን ገነነ መኩሪያን በመዘከር መገለጥ አለበት ። ቲክቶክ ላይ ስለ ገነነ ምንም ባይባል አይገርመኝም ። እነሱ ገነነን አያውቁትም ። እነሱ ገንዘብ ለመሰብሰብ ጡት ሲገላለጡና ዱቄት ሲቀባቡ ገነነ ሀገር ስራ ላይ ነበረ ። የገነነን ስርዓተ ቀብር መንግሥት ትኩረት ሰጥቶት ቢሆን እነ " አለን " ም በመጡና ቀብሩ በደመቀ ነበር ። ዳሩ አልሆነም ። ትልቁ ችግር ገነነ እውቀት እንጂ ቲፎዞ አልነበረውም ። ከስኳር በሽታውም ጋር እየታገለ ለሀገር ፣ ለሕዝብ ፣ ለታሪክ እንጂ ለገንዘብና ለዝና አልሰራም ። ግሩም ዘነበ እግዜር ይስጠው ይህን የተደበቀ ታላቅነቱን አውቆ ወደ አሻም ቴሌቪዥን ባያመጣው ይህን ያህሉንም ቢሆን አናውቀውም ነበረ ። በእርግጥ አውቀነውም አልጠቀምነውም ። በቁሙ አላከበርነውም ። ሞቶ ቀብሩን እንኳን አልደረስነውም ።

ለአዋቂውና የመረጃ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ( ሊብሮ ) ሌላ የክብርና የይቅርታ መርኀ ግብር ሊዘጋጅለት ይገባል ።

ከ tewodros tekle aregay ገፅ የተገኘ ዘገባ

23/01/2024
ትልቅ የስፖርት ታሪክ ሰው አጣን!ህያው የታሪክ ላይብረሪአንደበተ ርቱዕ ተወዳጅ ጋዜጠኛ እና ፀሃፊ ወግ አዋቂው ገነነ መኩሪያ/ሊብሮ/ ከዚህ አለም ዳግም ላናገኘው አለፈ:: አሳዛኝ ዜና!የአሻም...
23/01/2024

ትልቅ የስፖርት ታሪክ ሰው አጣን!
ህያው የታሪክ ላይብረሪ
አንደበተ ርቱዕ ተወዳጅ ጋዜጠኛ እና ፀሃፊ ወግ አዋቂው ገነነ መኩሪያ/ሊብሮ/ ከዚህ አለም ዳግም ላናገኘው አለፈ:: አሳዛኝ ዜና!

የአሻም ቴሌቪዥን ጣቢያ ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩርያ(ሊብሮ) በአደረበት ህመም ህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ህይወቱ አልፏል።

ገነነ መኩርያ በአሻም ቲቪ "የገነነ" እና "ጥቁር እንግዳ" ትኩረቱን በስፖርት እና በታሪክ ያደረገ ፕሮግራም ለአመታት በአዘጋጅነት እና አቅራቢነት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን በማቅረብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር።

በተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች ፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል።

ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል።

የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎንደል ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው።

መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ የሚወድ ፣ ለሚናገራቸውም ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ የሚቀርብ በመሆኑ " ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት " የሚል ስያሜንም አግኝቷል።

ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ህይወቱ አልፏል።

***

ምንጭ - Ethio FM & Tikvah Sport

በተወዳጁ ጋዜጠኛ ህልፈት ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር 😭

አለም አቀፍ ወደብ ኦፕሬተር የሆነዉ ግዙፉ ዲፒ ወርልድ  የበርበራን ወደብ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ጋር "ድፍረት የተሞላበትን" እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ (ካፒታል : ጥር 12፤2016 ዓ.ም....
23/01/2024

አለም አቀፍ ወደብ ኦፕሬተር የሆነዉ ግዙፉ ዲፒ ወርልድ የበርበራን ወደብ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ጋር "ድፍረት የተሞላበትን" እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

(ካፒታል : ጥር 12፤2016 ዓ.ም.)

በዱባይ የሚገኘው የዓለማችን ግዙፍ የኮንቴይነር ወደብ ኦፕሬተር የሆነዉ ዲፕ ወርልድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የጋራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት “የማጠናከር” በሶማሊላንድ የበርበራ ወደብን በማሳደግና የወደፊቱን የአለም ንግድን ለመቅረጽ በጋራ እሰራለሁ ብሏል።

በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሚገኝ ሁለገብ ሎጂስቲክስ ኩባንያ የሆነዉ ዲፒ ወርልድ በካርጎ ሎጂስቲክስ፣ በወደብ ተርሚናል ኦፕሬሽን፣ በባህር አገልግሎት እና በነፃ ንግድ ዞኖች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ የሚገኝ የአለም አቀፍ የወደብ ኦፕሬተር ነዉ።

ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በስዊዘርላንድ በዳቮስ-ክሎስተር ከቀናት በፊት በተካሄደው 54ኛው የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም አመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ዉይይት ያደረጉት የዲፒ ወርልድ ስራ አስፈፃሚ እና ሊቀመንበር ሱልጣን አህመድ ቢን ሱለይም ውጤታማ ያሉትን ዉይይት ተከትሎ፣ ዲፒ ወርልድ ትብብሩን በማጠናከር ደስተኛ ነው" በማለት ተናግረዋል ።

"ለቀጠናው ትስስር ቁልፍ መግቢያ የሆነውን የበርበራ ወደብን ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታችንን ስንገልጽ በጣም ደስ ብሎናል" ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ "ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ ለዘላቂ ዕድገት መንገድ የሚከፍት ነው" በማለትም አጋርነታቸውን አሳይተዋል ።

ድፍረት የተሞላበት እርምጃ በማለት የገለፀውን አጋርነት በለውጡ ግንባር ቀደም በመሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ጥምረትና የወደፊት ጉዞ አመላካች ነዉ ብሎታል።

እ.ኤ.አ. በ 2005 በዱባይ ወደቦች ባለስልጣን እና በዱባይ ወደቦች ኢንተርናሽናል ውህደት የተቋቋመው ዲፒ ወርልድ 70 ሚሊዮን በማስተናገድ በዓመት ወደ 70,000 በሚጠጉ መርከቦችን የሚያመጡ ሲሆን ይህ በግምት 10 በመቶ የሚሆነው የአለም አቀፍ የኮንቴይነር ትራፊክ በ82 የባህር እና የውስጥ ተርሚናሎች ከ40 በላይ ሀገራት ውስጥ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በኢያሱ ዘካሪያስ

ካፒታል

የተዘቀዘቀ መስቀል ጉዳይ እንዴት ይታያል? ወይስ ቴዲ አፍሮ ስለሆነ....?
21/01/2024

የተዘቀዘቀ መስቀል ጉዳይ እንዴት ይታያል? ወይስ ቴዲ አፍሮ ስለሆነ....?

  MEDIA ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል!
20/01/2024

MEDIA

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል!

   " በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ተብሎዋል::ተሳፋሪዎች የጫነ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ከቀኑ 8:00...
18/01/2024



" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ተብሎዋል::

ተሳፋሪዎች የጫነ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ከቀኑ 8:00 ሰዓት አከባቢ አደጋ እንደገጠመው ተሰምቷል::

18/01/2024

የባሎች እና የሚስቶች መሰረታዊ ፍላጎቶች

ለሚስቶች . . .

ባሎች ከሚስቶች የሚፈልጓቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እነዚህ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ግን በፍጹም ሊዘነጉ አይገባቸውም፡፡

1. ባሎች መከበር ይፈልጋሉ

ባላችሁን በንቀት መናገር፣ ማመናጨቅ፣ እንደማይችል ማሳየት ወይም መናገር፣ ፍላጎቱን ችላ ማለት፣ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ከማድነቅ ይልቅ ጎዶሎ ነገሩን መልቀምና መናገር እና የመሳሰሉት ባል እንደተናቀ እንዲያስብ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን የምታንጸባቁ ከሆነ በጉዳዩ ላይ በሚገባ አስቡበት፡፡

2. ባሎች ቤት ውስጥ ሰላምን ይፈልጋሉ

በሆነ ባልሆነ ባላችሁን መጨቅጨቅ፣ ነገርን ባለመርሳት እየደጋገሙ ማንሳት፣ ጥፋትን ይቅር አለማለት፣ ያልተሟላ ነገር ላይ ማተኮር እና የመሳሰሉት ቤት ውስጥ ሰላም የሚነሱ ሁኔታዎችን ማድረግ፣ መናገር ወይም የማሳየት ዝንባሌ ካላችሁ በጉዳዩ ላይ በሚገባ አስቡበት፡፡

ለትዳራቸው ግድ የሚላቸውና የሚችሉትን በማድረግ የሚኖሩ ባሎች እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደጎደለባቸው ሲያስቡ፣ ብዙ ከታገሱ በኋላ ወደ ዝምታ፣ ስሜት-የለሽ ወደመሆን፣ ውጪ ውጪውን ወደማለትና ራስን ወደማግለል በመውረድ ሊደበቁ ይችላሉ፡፡ ይህ ተግባር ምንም እንኳን ትክክል ባይሆንም ለሆነባቸው ነገር መስጠት የሚችሉት የመጨረሻ ምላሽ እንደሆነ ራሳቸውን ሊያሳምኑት ይችላሉ፡፡

ለባሎች . . .

ሚስቶች ከባሎች የሚፈልጓቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ይህ አንድና ብቸኛ ነገር ግን በፍጹም ሊዘነጋ አይገባውም፡፡ ይህ ሁኔታ “ጥበቃ” (Security) ሲሆን ሁኔታውም በሶስት ይከፈላል

1. ሚስቶች የአካል ጥበቃ (Physical Security) ይፈልጋሉ
ይህ ማለት እናንተ እያላችሁ ማንም ሰው ሊጎዳቸው እንደማይችልና እንደምትጠብቋቸው እንዲያውቁ ማድረግ በተግባርም ማሳየት፡፡

2. ሚስቶች የአቅርቦት ጥበቃ (Provisional Security) ይፈልጋሉ
ይህ ማለት እናንተ እያላችሁ ምንም አይነት የኑሮ ሁኔታ እንደማይጓደልባቸውና አቅርቦትን እንደምታሟሉ እንዲያውቁ ማድረግ በተግባርም ማሳየት፡፡

3. ሚስቶች የግንኙነት ጥበቃ (Relational Security) ይፈልጋሉ
ይህ ማለት እነሱ እያሉ በፍጹም ከሌላ ሴት ጋር ምንም አይነት ከመስመር የወጣ ግንኙነት ውስጥ እንደማትገቡ እንዲያውቁ ማድረግ በተግባርም ማሳየት፡፡

ለትዳራቸው ግድ የሚላቸውና የሚችሉትን በማድረግ የሚኖሩ ሚስቶች እነዚህ ሶስት ነገሮች እንደጎደለባቸው ሲያስቡ፣ ብዙ ከታገሱ በኋላ በትዳራቸው ደስተኛ ወዳለመሆን፣ ወደ መጨቃጨቅ፣ ስሜታዊ ወደመሆንና የቤቱን ሰላም ወደመበጥበጥ ሊያዘነብሉ ይችላሉ፡፡ ይህ ተግባር ምንም እንኳን ትክክል ባይሆንም ለሆነባቸው ነገር መስጠት የሚችሉት የመጨረሻ ምላሽ እንደሆነ ራሳቸውን ሊያሳምኑት ይችላሉ፡፡

ከትዳር አጋራችሁ እናንተ የምትፈልጉትን ከመጠየቃችሁና ከመጠበቃችሁ በፊት በቅድሚያ እናንተ የትዳር አጋራችሁ የሚፈልግባችሁን ነገር ለማሟላት ብትሞክሩ ምን ይመስላችኋል?

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

17/01/2024

ጥበቡ ወርቅዬ - በስሎ የተገለጠ የእግዚአብሔር ሰው

ይህን ዘገባ ላለመቀበል ብዙ ምክንያት አያስፈልግም - ሃገሩን የማይወድ ብቻ መሆን በቂ ነው:: የመንግስት ሚዲያዎች ብዙውን ጊዜ የመንግስት ፕሮፓጋንዳን ብቻ ቢዘግቡም ይህ ዘገባ ግን እንደሃገ...
17/01/2024

ይህን ዘገባ ላለመቀበል ብዙ ምክንያት አያስፈልግም - ሃገሩን የማይወድ ብቻ መሆን በቂ ነው::

የመንግስት ሚዲያዎች ብዙውን ጊዜ የመንግስት ፕሮፓጋንዳን ብቻ ቢዘግቡም ይህ ዘገባ ግን እንደሃገር ኢትዮጵያ እንደህዝብ ደግሞ ለእኛ ለሁላችን ልንቀበለው እና ልንደግፈው የሚገባን ብሔራዊ ጉዳይ የያዘ ነው::

ግለሰብን በአቁዋሙ መንግስትን በፖሊሲው መጥላትና መቃወም ይቻላል:: በዚያ ምክንያት ለሃገር የሚጠቅምን ነገር ማጥላላት እንጭጭነት: ያላዋቂነት: መሃይምነት ነው::

በተለይም በሕዝቡ ዘንድ ዝነኛ አባባል ነው ተብሎ በሪፖርቱ የተጠቀሰው፣ "ከእንግዲህ ሞቃዲሾ የለችም፤ ከእንግዲህ ሶማሊያ የለችም፤ ሶማሊላንድ ነጻ ሀገር ናት፤ ዕውቅና እንፈልጋለን፤ .....

ቲክቶክ አትጠቀምም ። የኢንስታግራም አካውንት የላትም ። ከቤት ወጣች ትምህርት ቤት ፡ ከዛ መልስ ወደቤቷ ናት ። አሁን ካገባችው ሰው ጋር ከሰርጋቸው በፊት የተገናኙት ጥቂት ቀን ነው ። ለዛ...
17/01/2024

ቲክቶክ አትጠቀምም ።

የኢንስታግራም አካውንት የላትም ።

ከቤት ወጣች ትምህርት ቤት ፡ ከዛ መልስ ወደቤቷ ናት ።

አሁን ካገባችው ሰው ጋር ከሰርጋቸው በፊት የተገናኙት ጥቂት ቀን ነው ። ለዛውም ብቻቸውን አልነበሩም ። አብዛኛውን ጊዜ የሚያወሩት በስልክ ነው ።

ሰሞኑን ጥቂት ሰው ብቻ በተገኘበት ዝግጅት ሰርጋቸውን ካደረጉ በኋላ ባለቤቷ ባሉት ጥቂት የእረፍት ቀናት ከሚስቱ ጋር ሀኒሙን ማሳለፍ ፈለገ ።
ሆኖም የልጅቱ ወላጆች ፡ አይሆንም እንደውም ፡ ሰሞኑን ፈተና ስላላት ነገ ከነገ ወዲያ ወደ ትምህርቷ ትመለሳለች አሉት ።

የምናወራው ስለ አዲሷ የሳዲዮ ማኔ ሚስት Aisha Tamba ነው ። የዚህች ወጣት ቤተሰቦች ልጃቸውን የዳሩት ፡ በሴኔጋል ውስጥ እንደንጉስ የሚታይ በሁሉም ዘንድ ለሚወደድ ፡ ዝነኛ እና ሚሊየነር ታዋቂ ሰው ቢሆንም ፡ የጀመረችውን ትምህርት ሳትፈተን ሊልኳት አልፈቀዱም ።

እሷም አልከፋትም ። ሳዲዮም በሚስቱ ቤተሰቦች ልጃቸውን በጥብቅ ስነምግባር በማሳደጋቸው ተደሰተ እንጂ ቅር አላለውም ።
እናም አይሻና ሳዲዮ ከተጋቡ በኋላ በሁለተኛው ቀን ወደ ትምህርት ቤት ተመለሰች ። ይህ በምስሉ ላይ የሚታየውም ፡ አይሻ በሀፍረት የምትገባበት እስኪጠፋት ድረስ የትምህርት ቤቷ ተማሪዎች በአድናቆትና በእንኳን ደስ ያለሽ መልእክት ፍቅራቸውን እየገለፁላት ነው ።

Via Wasihun Tesfaye

ከኢትዮጵያዊያን ተወልዳ በአሜሪካ የሴቶች እግር ኩዋስ ብሄራዊ በድን ውስጥ ታዋቂ የሆነችው ናኦሚ ግርማ የ2023 ምርጥ ተጫዋች ተብላ ተመረጠች::
15/01/2024

ከኢትዮጵያዊያን ተወልዳ በአሜሪካ የሴቶች እግር ኩዋስ ብሄራዊ በድን ውስጥ ታዋቂ የሆነችው ናኦሚ ግርማ የ2023 ምርጥ ተጫዋች ተብላ ተመረጠች::

ስለሁለቱ አወዛጋቢ የስፖርት ጋዜጠኞች በቅርቡ ያጋራነውን በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አስመልክቶ ብዙ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር:: እነሆ አሁን ደግሞ አዲስ ዜና ተሰምቶዋል::ትርታ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ...
10/01/2024

ስለሁለቱ አወዛጋቢ የስፖርት ጋዜጠኞች በቅርቡ ያጋራነውን በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አስመልክቶ ብዙ አስተያየት ተሰጥቶ ነበር:: እነሆ አሁን ደግሞ አዲስ ዜና ተሰምቶዋል::

ትርታ ኤፍ ኤም ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው እና ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ እንየውን ከአየር ላይ አግጃለሁ አለ።
*******************************************************
ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚያስተዳድረው ትርታ 97.6 FM ጣቢያ ውስጥ በሴቲና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥር ይሠሩ በነበሩ የትርታ ስፖርት ተባባሪ አዘጋጆች መካከል ረቡዕ ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የትርታ 97.6 FM ጣቢያ የማኔጅመንት አባላት ባደረጉት ማጣራት የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፈዋል:: የትርታ ስፖርት ተባባሪ አዘጋጆቹ ሶፎንያስ እንየውና ግርማቸው እንየው በሥራ አጋራቸው ብሩክ ተስፋዬ ላይ ድብደባ መፈፀማቸው በሰውና በቪዲዮ ማስረጃ ተረጋግጧል::

የትርታ ስፖርት ተባባሪ አዘጋጆች በሥራ አጋራቸው ላይ የፈፀሙት ድብደባ በጣቢያው የሥነ ምግባር ደንብ መሠረትም ሆነ በየትኛውም ዓይነት መርህ ተቀባይነት የሌለውና በሕግ የሚያስጠይቅ ከመሆኑ ባሻገር፣ ለጋዜጠኝነት ሙያ ክብር ሲባል ድርጅቱ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል:: በመሆኑም የትርታ ስፖርት ተባባሪ አዘጋጆች የነበሩትን ሶፎኒያስ እንየውንና ግርማቸው እንየውን ከአየር ላይ ያገድን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::

በድጋሜ ስለ ተፈጠረው ነገር ሁሉ የጣቢያችን አድማጮችንና ቤተሰቦችን ይቅርታ እንጠይቃለን::
የትርታ 97.6 FM ጣቢያ የማኔጅመንት አባላት

08/01/2024

በላስቬጋስ ነው ነገሩ:: ዳኛዋ አመክሮ ስትከለክለው ነው ተወርውሮ የተከመረባት:: ለደቂቃ መቆጣጠር ያቃተው ብስጭቱ ጣጣውን አባሰበት::

04/01/2024

ጋዜጠኞቹ እና ስርአት አልበኝነታቸው

02/01/2024
ከዕስር በኋላ በፖለቲካ አካሄዱ ወይም የአደባባይ አጀንዳ በሚያደርጉ ንግግሮቹ ብዙ አወዛጋቢ የነበረው በሳል የብሔር ፖለቲካ ምሁር ጃዋር መሃመድ ሰሞኑን የሚለውን ሚስጥር ልንሰማ ነው:: እውቁ...
29/12/2023

ከዕስር በኋላ በፖለቲካ አካሄዱ ወይም የአደባባይ አጀንዳ በሚያደርጉ ንግግሮቹ ብዙ አወዛጋቢ የነበረው በሳል የብሔር ፖለቲካ ምሁር ጃዋር መሃመድ ሰሞኑን የሚለውን ሚስጥር ልንሰማ ነው:: እውቁ እና ተወዳጁ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ "በነገራችን ላይ" እያለ ሲጠይቀው ምላሹን እያየነው እንሰማለን::

እሁድ ይጠብቁ!!!

28/12/2023

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MIZAN MEDIA ሚዛን ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MIZAN MEDIA ሚዛን ሚዲያ:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share