Wollo Media News

  • Home
  • Wollo Media News

Wollo Media News W.M.N

ሰበር ዜና ******ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና የወሎ ፋኖ በአሁኑ ሰዓት ጎብየን በቁጥጥር ስር አውሏል። የጄኔራል ሀሰን ከረሙ ጦር ጠላትን ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ ...
08/09/2022

ሰበር ዜና
******
ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና የወሎ ፋኖ በአሁኑ ሰዓት ጎብየን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የጄኔራል ሀሰን ከረሙ ጦር ጠላትን ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ ጠላትን እየወቃው ነው።
ዘመን ተሻጋሪው

መረጃ   ቆቦ ግንባር ከመደምሰስ የተረፉት የወያኔ ታጣቂዎች እግሬ አውጭኝ ብለው እየፈረጠጡ ነው። ፎኪሳ ፣ዞብል፣ ቃሊም፣ተኩለሽ ሁሉም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር ነው ያለው። የጁንታው ታጣ...
07/09/2022

መረጃ ቆቦ ግንባር

ከመደምሰስ የተረፉት የወያኔ ታጣቂዎች እግሬ አውጭኝ ብለው እየፈረጠጡ ነው። ፎኪሳ ፣ዞብል፣ ቃሊም፣ተኩለሽ ሁሉም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር ነው ያለው። የጁንታው ታጣቂዎች ጎብዬ፣ ሮቢት፣ ቆቦ ከተማ ይገኛሉ።

አስቸጋሪ የሚባሉ ወይም ከፍተኛ ቦታዎች በጥምር ጦሩ እጅ ናቸው። ከትናንት ጀምሮ በተኩለሽ፣ ዞብልና ቃሊም አካባቢ ከመደምሰስ የተረፉት የወያኔ ታጣቂዎች እግሬ አውጭኝ ብለው እየፈረጠጡ እንደሆነ ከቦታው ለማረጋገጥ ችለናል።

ባራንቶ አባሴሩ

03/09/2022

ራያ ግንባር በየሾሎቆው ተወትፎ የነበረው የወራሪው ሃይል እግሩ ወደመራው እየጠፋ መሆኑ ታውቋልና እየጠበክ መሳሪያውን ቀምተህ ታጠቅ ።

ሰበር መረጃ የግንባር ሁኔታ፦ የወገን ጦር በምእራብ ግንባር አብዛኛውን የጠላት ሃይል እየደመሰሰ የደደቢት በረሃ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። የተበተነው አብዛኛው የጠላት ታጣቂ እግሬ አውጪኝ እያ...
02/09/2022

ሰበር መረጃ የግንባር ሁኔታ፦

የወገን ጦር በምእራብ ግንባር አብዛኛውን የጠላት ሃይል እየደመሰሰ የደደቢት በረሃ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። የተበተነው አብዛኛው የጠላት ታጣቂ እግሬ አውጪኝ እያለ ሲሸመጥጥ ግማሹ በድንጋጤ በክረምቱ ዝናብ ከአፍ እሰከ ገደፉ በሞላዉ የተከዜ ወንዝ ውስጥ ነፍሱን ያዳነ መስሎት ገብቷል።

ሌላው ደግሞ መሳሪያውን ጥሎ ወደ ሱዳን በመሻገር አሻባ በሚባለዉ የስደተኞች ካምፕ ዉስጥ አስጠልሉኝ በሚል ልመና ውስጥ ገብቷል። ሱዳኖች ግን በመጣቹበት እግራችሁ ተመለሱ እያሉ ሲሆን ታጣቂውን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው ለመስጠት በአንድ ቦታ ላይ እያሰባሰቡት መሆኑን ከወደ ሱዳን የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማል"

 ||  ||☞ቁልፍ  መረጃወች፦ወራሪው ሀይል የራያን ህዝብ እንደ ዋሻ እየተጠቀመበት ነው‼___________________________________ወራሪው ሃይል ተጠቅሎ የራያ ሸለቆ ውስጥ ገብቷ...
01/09/2022

|| ||☞ቁልፍ መረጃወች፦
ወራሪው ሀይል የራያን ህዝብ እንደ ዋሻ እየተጠቀመበት ነው‼
___________________________________
ወራሪው ሃይል ተጠቅሎ የራያ ሸለቆ ውስጥ ገብቷል። በጎሊና እና አላ ውሃ ወንዞች የአማራና አፋር ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች ከጎብየ በደቡብ በኩል እስከ ዲቢ መገናኛ ቆላ መውረጃ በሰፊው ተሰግስጓል።
ቁጥሩ ከ30-50ሺህ የሚገመት ሃይል በዚህ ሸለቆ ውስጥ ገብቷል። የያዟቸው መሳሪያዎች ብሬይን፣ ዲሽቃ፣ መትረየስ፣ ስናይፐር፣ ከሶስት የማይበልጡ ዙ-23 እና አንድ መድፍ ይዟል።

በጎሊና እና አላ ውሃ ወንዞች መሃል የመሸገውና የወርቈን ተራሮች አጥሮ የተቀመጠው ይሄ ሃይል የጉዞው አላማ ምንድነው?

ትጥቁን በግመልና አህያ ጭኖ በራያ ጨርጨር ዞብል ተራራ አድርጎ በራማ-ቦረን-ጋቲራ-ዲቃሎን አድርጎ እጅግ በጣም ብዙው ሃይል ወርቄ ገብቷል።፡ሌላኛው ሃይል ቦረን ተነስቶ አረቁቴ ወርዶ ገደመዩ ነዲ ተራራን ተገን አድርጎ ወደ ዲቢና አጋምሳ መንደሮች ወርቄ ገብቷል። ይሄ ሁሉ ሃይል ወዴት እየሄደ ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። አላማው ሚሌ ነው!! መንገዱ ግን ተራራማውና ቆላማው የወሎ ክፍል ነው።
ወራሪው ሃይል ገላጣና በርሃማ መስመሮችን ረዥም ርቀት መጓዝ የቱን ያክል አክሳሪና አዋራጅ መሆኑን ከባለፈው ውርደቱ ተምሯል። ስለሆነም ሰሜን ወሎ የግዳንና ዋግ ትግል ጠንክሮ ወራሪውን ሃይል ልቡንና አቅሙን ካልከፈለው የሚከተሉት መስመሮች በከባድ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ፥

1) በወርቄ አላ ውሃ ወንዝን ተሻግሮ ሃሮን ታኮ ወደ ድሬ ሮቃ ሰዶማና ቢስቲማ መስመሮችን በዋናነት ያልማል።
2) በወርቄ ምስራቅ በኩል ወርዶ በኡዋ በላይ ማለፍም ያስብ ይሆናል።

በመሆኑም አሁን እየተደረገ ያለውን ትግል በሚገባ በመቆስቆስ ወርሪው ከገባበት የራያ ሸለቆ እንዳይወጣ ማድረግ ያስፈልጋል።
ይሄንንም ለማድረግ የተጠቀሱን መስመሮች በሁሉም አቅጣጫ መክበብ፣ በግዳን ስር እና ዋግ አከባቢ የሚደረገውን ትግል በማጠናከር ትግሉን በድል ማጠናቀቅ ይቻላል።

ለዚህ ትግል ህዝባዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፣ የጥምር ሃይሉ መናበብ ና መግባባት ቁልፍ ነገር ነው። ራሽንንና ተተኳሽ በሚገባ ማሰራጨት ፣ጥራትና ወቅታዊ የሆነ መረጃ ቅብብሎሽና ትንተና ወሳኝ ነው።

መውጫ!
ጁንታው መጠለያ ያደረገው የአርሶ አደሮችን መኖሪያ ቤትና ግቢያቸውን ነው። ቀን የትም ውሎ አመሻሽ ላይ መኪኖቻቸውን ራቅ አድርገው ያቆሙና ወደ አርሶ አደሮች መኖሪያ ይገባሉ፣ አዳራቸውን በዛው ያደርጉና 11፥00 ንጋት ላይ ይወጣሉ። ህዝባችን ለጦርነታቸው እንደ ዋሻ እየተጠቀሙበት ነው!!
Mohamed Ali

ሰበር ዜና‼   አይበገሬወቹ 3 መኪና ሬ* አጋድመው ውለዋል‼የወርቄ ወጣቶች ህወኃት በ3 መኪና ጭኖ የወጣውን ግዳይ አስጥለውታል!!==========================ከስፍራው መረጃውን ...
30/08/2022

ሰበር ዜና‼
አይበገሬወቹ 3 መኪና ሬ* አጋድመው ውለዋል‼

የወርቄ ወጣቶች ህወኃት በ3 መኪና ጭኖ የወጣውን ግዳይ አስጥለውታል!!
==========================
ከስፍራው መረጃውን በስልክ ያገኘው ያሲን ሙሀመድ እንድህ ሲል ፅፎታል።
«ይሄንን አታምኑኝ ይሆናል፣ ግን ወላሂ ሆኗል!!
በወርቄ ሰዱ ግንባር ብቻ ዛሬ ሙሉ ቀን በተደረገ እልክ አስጨራሽ ትግል የወርቄ ወጣቶች ህወኃት በ3 መኪና ጭኖ የወጣውን ግዳይ ጥለዋል። ትግሉ በከረም ማዶ የወርቄ ገመገም ላይም በሀገር መከ እና የወሎ ፋኖዎች ጥምር ትግል ታሪክ ተሰርቶበታል።
-------

የወርቄ ወጣቶች ገድል ከቃል በላይ ነው!
የራያ ወጣቶች ያጡትን በራስ መተማመንና ጀብደኝነት በወርቄ በኩል እያወራረድንው ነው። ይሄንን እውነት ስነግራችሁ "በሰው ደም ቀልድ"የምትሉ ሁሉ አትጠፉም። ሃቁ ግን ልጆቻቸውን በትነው ህወኃት ጋር እየተናነቁ ያሉ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ሳይቀሩ የሚሳተፉበት መራር ትግል መሆኑ ነው።

ህወኃት ወዴትም ይሂድ ይምጣ ጀግኖቹ ወራሪውን በሚገባው ቋንቋ እያናገሩት ነው። ከተማ ለከተማ ስናይፐር አዝለህ የምትንገላወደው ወዳጄም ሁን በባዶ እጅህ ቤትህን ጥለህ የወጣህ የሀገር ልጅ መሪህን መርጠህ ወይም ከመሪዎቹ ተጠግተህ የወረረህን ሃይል ታገል!!»

ራያ ወርቄ የወንዶቹ መለኪያ!!🙏

ምንጭ Voice Of Wollo

እዚህ እየመጣህ አታላዝንብኝ እኔ ይህን ፀጉሬ ተንጨባሮ ከንፈሬ ደርቆ ኦነግ ሸኔ መስዬ የተነሳሁትን ፎቶ የመልቀቅ አባዜ ኖሮብኝ ሳይሆን፤ ሽብሩ ቢበዛ ወሬው ቢናፈስ ደሴን አልፎ ኮምቦልቻ ሱቅ...
30/08/2022

እዚህ እየመጣህ አታላዝንብኝ እኔ ይህን ፀጉሬ ተንጨባሮ ከንፈሬ ደርቆ ኦነግ ሸኔ መስዬ የተነሳሁትን ፎቶ የመልቀቅ አባዜ ኖሮብኝ ሳይሆን፤ ሽብሩ ቢበዛ ወሬው ቢናፈስ ደሴን አልፎ ኮምቦልቻ ሱቅ እየተዘጋ፣ ባንክ በወረፋ ተጨናንቆ ለመቶ ሃያ ኪ.ሜ ከወልዲያ ደሴ በግድያ፣ በድብድብ፣ በባጃጂ ጭምር ለአንድ ሰው ሶስት ሽህና አራት ሽህ ብር እየተከፈለ፤ ህዝብ እየተንገላታ ባለበት ሰዓት አካባቢው ሰላም መሆኑን በመግለጽ ህዝብን ለማረጋጋት እንጂ ድሉንማ አፍኘ ይዥዋለሁ።

ለማንኛውም ባንዳው ይህኛው ያልተዋጠልህ ትልቁን ድል ልቦናህ ስለሚያውቀው ነው፤ ሌሎቻችሁ ማወቅ ካለባችሁ ድሉን በደንብ ለማብሰር ይቆየኝ የህወሓት ወራሪ ቡድን ግን እመኑኝ በየትኛውም መንገድ ወልዲያን ድጋሚ ሊረግጥ አይችልም።

"የመነን ዘር አይሸጥ አይመነዘር!"
ዳጊ ነኝ
ከአለውሃ ወንዝ ማዶ!

Belay dagi

የወሎ ፋኖ ጎራርባና መሀል አንባ  ኒኒ በሮች በዛሬው እለት ተቀላቅሏል! ጀኔራል ሀሰን ከረሙ! ወልድያ ድረስ ተገኝተው ተቀብለውታል‼️
29/08/2022

የወሎ ፋኖ ጎራርባና መሀል አንባ ኒኒ በሮች በዛሬው እለት ተቀላቅሏል! ጀኔራል ሀሰን ከረሙ! ወልድያ ድረስ ተገኝተው ተቀብለውታል‼️

 #ወልዲያ‼ በወልዲያ መከላከያ ሸሺቷል! የሐውሐት ሐይል መጣላችሁ ሺሹ! በማለት ሕብረተሰቡን የማዋከብ ስራ ሲሰሩ የነበሩ የጁንታው የፕሮፓጋንዳ መልዕክተኞች በፀጥታ ሐይሎች'ና በሕዝቡ ትብብር...
29/08/2022

#ወልዲያ‼

በወልዲያ መከላከያ ሸሺቷል! የሐውሐት ሐይል መጣላችሁ ሺሹ! በማለት ሕብረተሰቡን የማዋከብ ስራ ሲሰሩ የነበሩ የጁንታው የፕሮፓጋንዳ መልዕክተኞች በፀጥታ ሐይሎች'ና በሕዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል‼

ከዚህ በፊት ወልዲያን ያስወረሩበትን የማዋከብ'ና በሕብረተሰቡ ላይ ፍርሐትን የማንገስን ዘመቻ በተደራጀ ሁኔታ ሲያናፍሱ የነበሩ መኖሪያቸውን በወልዲያ ያደረጉት'ና በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ የተጋሩት አክራሪ ሐይሎች በቁጥጥር ስር የማዋል ስራው በተቀናጀ ሁኔታ መሰራት አለበት!!!

ሰበር መረጃ ትናንት በህውሃት ወረራ የተፈፀመባቸው የደቡብ ቆቦ አካባቢዎች ሮቢትን ጨምሮ ዛሬ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ እየመጣ የነበረው ወራሪ ሃይል ...
28/08/2022

ሰበር መረጃ

ትናንት በህውሃት ወረራ የተፈፀመባቸው የደቡብ ቆቦ አካባቢዎች ሮቢትን ጨምሮ ዛሬ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ እየመጣ የነበረው ወራሪ ሃይል በመከላከያ፣ልዩ ሃይሉ እና ፋኖ በተወሰደበት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ፊቱ አዞሮ ቆቦን ለቆ ወደ አላማጣ በመውጣት ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።በግዳን በኩል ጠዋት 4:30 ሙከራ ቢያደርግም ተመቶ መመለሱን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ባለንበት ተረጋግተን አካባቢያችንን እንጠብቅ።ጥምር ጦሩን እናግዝ‼ከሌላ አቅጣጫ ሌላ ሰበር መረጃ እየተሰማ ነው።እመለሳለሁ።
Mohammed

የወሎ አመራሮች ምነው ተኛችሁ ?ቆራጥ እርምጃ ውሰዱ እንጅ ?ሁሉም ዞኖች ወረዳዎች ቀበሌዎች ተመካክራችሁ ሁሉም መሳሪያ ያለው እንድዘምት ቆራጥ ውሳኔ ስጡ‼️ሁለተኛ ውርደት ይበቃናል ‼️
27/08/2022

የወሎ አመራሮች ምነው ተኛችሁ ?ቆራጥ እርምጃ ውሰዱ እንጅ ?ሁሉም ዞኖች ወረዳዎች ቀበሌዎች ተመካክራችሁ ሁሉም መሳሪያ ያለው እንድዘምት ቆራጥ ውሳኔ ስጡ‼️ሁለተኛ ውርደት ይበቃናል ‼️

ቆቦ ሰላም አድራለች። የጦርነት ሜዳው ተቀይሯል። አሁን ጦርነቱ እነሱ ይዘዉት ከነበረ ሜዳ ሁኗል። ምናልባት ዛሬ የናፈቅናት ከተማችን(አላማጣ) ልናያት ይሆናል። ለሁሉም ትናንት ዛሬ አይደለም።...
27/08/2022

ቆቦ ሰላም አድራለች። የጦርነት ሜዳው ተቀይሯል። አሁን ጦርነቱ እነሱ ይዘዉት ከነበረ ሜዳ ሁኗል። ምናልባት ዛሬ የናፈቅናት ከተማችን(አላማጣ) ልናያት ይሆናል። ለሁሉም ትናንት ዛሬ አይደለም። ዛሬ ከትናንት ስህተታችን ተምረን አንድ ሁነን፣ ጠንክረን፣ በጠላት ወሬ ሳንሸበር ጠላታችን እያሳፈርን እንገኛለን።

ራያ ቆቦ በሁሉም ግንባሮች አገር ሊያፈርስ የመጣው የህወሓት ቡድን እልቂት በሚባል ደረጃ ሰራዊቱን ገብሮ ወደመጣበት ተመልሷል። በዚህ ድል የወሎ ፋኖ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር አንድ ላይ በመሆን...
26/08/2022

ራያ ቆቦ በሁሉም ግንባሮች አገር ሊያፈርስ የመጣው የህወሓት ቡድን እልቂት በሚባል ደረጃ ሰራዊቱን ገብሮ ወደመጣበት ተመልሷል።

በዚህ ድል የወሎ ፋኖ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር አንድ ላይ በመሆን ታሪክ እየሰራ ይገኛል በብዙ የመከላከያ አመራሮችም ምስጋና እየተቸረው ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን ወቅቱ ሲፈቅድ እንገልፃለን በየትኛውም የግንባር ቀጠና አካባቢ ያላችሁ አካባቢያችሁን ከሰርጎ ገብ ከመጠበቅ በዘለለ የወራሪው ሀይል አካባቢውን ተቆጣጠርኩ ልቆጣጠር ነው ከሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ስጋት ነፃ ሁናችሁ እደሩ።

አገሬን አላስደፍርም ብሎ የወጣው ሀይል በሁሉም ግንባር ድል በድል ሁኗል ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልና አብረው እየተዋደቁ ድል እያመጡ ላሉ የኢትዮጵያ ብርቅና ድንቅ የፋኖ ልጆች።

ሰበር መረጃ  የህወሃት ቡድን በተኩለሽ በኩል መከላከያን ሰብሮ ሊገባ የኘበረው በርካታ ሐይል ተደምስሶ የጦር ጀነራሉ ተማርኳል።በዞብል እና ራማ ላይ የማጥቃት ሙከራ አድርጎ የነበረው ትህነግ ...
26/08/2022

ሰበር መረጃ

የህወሃት ቡድን በተኩለሽ በኩል መከላከያን ሰብሮ ሊገባ የኘበረው በርካታ ሐይል ተደምስሶ የጦር ጀነራሉ ተማርኳል።

በዞብል እና ራማ ላይ የማጥቃት ሙከራ አድርጎ የነበረው ትህነግ በጀግናው የመከላከያ ሐይል እየተመታ ነው። አሁን የሰላም አማራጭ ያልተጠቀመው ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ይደመሰሳል። ድል ራሱን ለሰጠው ለጀግናው መከላከያ ሐይል።

ሰበር...ዜና ከትላንት ሌሊት 9ሰአት ጀምሮ ወራሪው ጁንታ እስትራቴጂካዊውን ሰንሰለታማውን የዞብል ተራሮችን ለመቆጣጠር በመድፍና በታንክ የታገዘ ከፍተኛ ውጊያ ቢከፍቱም ሳታናው መከላከያ ሰራዊ...
25/08/2022

ሰበር...ዜና

ከትላንት ሌሊት 9ሰአት ጀምሮ ወራሪው ጁንታ እስትራቴጂካዊውን ሰንሰለታማውን የዞብል ተራሮችን ለመቆጣጠር በመድፍና በታንክ የታገዘ ከፍተኛ ውጊያ ቢከፍቱም ሳታናው መከላከያ ሰራዊታችን እና የምድር ድሮኖች በሁለት አቅጣጫ ቀለበት ውስጥ አስገብተው እየገረፉት ነው። ወራሪው ህወሃት ከ1983 ጀምሮ የሚጠቀምበት የውጊያ ስልት አለመቀየሩ ለተወርዋሪዎቹ ሰራዊታችን ዉጊያውን አቅሎታል የትኛውም የወራሪውን ምሽግ ለመስበር ከሰአታት በላይ አይፈጅበትም። Ahmed Habib Alzarkawi

ድል ለጀግና መከላከያ ሰራዊትና ለምድር ድሮኖች

በሀሰን ከረሙ የሚመራው የወሎ ፋኖ በፊት ለፊት የመጣውን ጠላት ለመፋለም አደረጂጀት ሰርቶ  ከአማራ ልዩ ሀይል እና ከመከላከያ ሰራዊታችን  ጋር በቅንጂት ጠላትን ለመፋለም  መዘጋጀቱን ገለፁ
25/08/2022

በሀሰን ከረሙ የሚመራው የወሎ ፋኖ በፊት ለፊት የመጣውን ጠላት ለመፋለም አደረጂጀት ሰርቶ ከአማራ ልዩ ሀይል እና ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር በቅንጂት ጠላትን ለመፋለም መዘጋጀቱን ገለፁ

ሰበር...🇪🇹ወራሪው ሃይል የአፋር ክልልን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ያደረገው ሙከራ በጀግናው መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ህዝባዊ ሰራዊት ከሸፈ።ወራሪው ህወሃት በአፋር ያሎ ወረዳ የመድፍ ደብዳ...
24/08/2022

ሰበር...🇪🇹

ወራሪው ሃይል የአፋር ክልልን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ያደረገው ሙከራ በጀግናው መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ህዝባዊ ሰራዊት ከሸፈ።

ወራሪው ህወሃት በአፋር ያሎ ወረዳ የመድፍ ደብዳብ የፈፀመ ሲሆን። አሸባሪው ቡድን አሁንም በንፁሃን ላይ መተኮሱን አላቆመምወራሪው ሃይል ወደ አፋር ገብቶ መነሻ መድረሻ የአፋር ያሎ ከተማን ለማድረግ ከፍተኛ ውጊያ ቢያደርግም የምድር ድሮኖች ከጀግናው ሰራዊት ጋር በመተባበር የጁንታውን አክሽፏል። በዚህ ውጊያም ጀግናው ሰራዊታችን አመርቂ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

👉አማራጭ የሌለው ምርጫችን || ክፍል -1*****************************************የደሴ ኮምቦልቻ አቋራጭ የዋሻ መንገድ ከደሴ ከተማ እና ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ...
23/08/2022

👉አማራጭ የሌለው ምርጫችን || ክፍል -1
*****************************************
የደሴ ኮምቦልቻ አቋራጭ የዋሻ መንገድ ከደሴ ከተማ እና ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እንድሁም ከማህበረሰቡ ተወካዮች ለአማራ ክልል መንግስት በተደጋጋሚ ጥያቄው ቢቀርብለትም የክልሉ መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ ለክልል ምክር ቤት በማቅረብ ውሳኔ እንዲሰጥበት ማቅረብ ቢኖርበትም የክልሉ መንግስት ጥያቄውን በመግፋት ለክልል ምክር ቤት ሊቀርብ አልቻለም።

ይህ ፕሮጀክት በክልሉ ምክርቤት ቀርቦ ቢፀድቅ በቀጥታ ለፌደራል መንግስት ተላልፎ የአመት እቅድ እና በጀት ተይዞለት ወደ ትግበራ ይገባ ነበር። ነገር ግን የክልሉ መንግስት ከወሎ አካባቢ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን የሚያነሱ ተወካዮችን በመፈረጅ እና በመግፋት ዳግም የልማት ጥያቄ እንዳይነሳ ሲሰራ መሰንበቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የዚህ ፕሮጀክት ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደሞከርኩት በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ያለው የሃረጎ መንገድ በተፈጥሮው ተራራማ ከመሆኑም ባሻገር በክረምት ወቅት መሬቱ እየተንሸራተተ ጉዳት እያደረሰ ያለ እንድሁም አገልግሎት እየተስተጓጎለ ይገኛል።
ይህነንም ተከትሎ ከአመታት ቡሃላ ይህ መንገድ ከነ ጭራሹ ይቋረጣል ማለት ነው። ስለዚህ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዋና አስፈላጊነት እንደሚከተለው አቀርባለሁ ፦

1- የደሴ ኮምቦልቻ ቀድሞ የነበረውን 25ኪሜ ወደ 7 ኪሜ ይቀንሳል ( ይህ ሲሆን ደሴን ለስራ ኮምቦልቻን ለመኖሪያ Vice Verse መጠቀም ይቻላል )
2- በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስር በእጅጉ ይጨምራል።
3- አሁን ላይ ያለውን የመንገድ አገልግሎት ችግር ለዘላቂነት ይቀርፋል።
4- ቦታው ተራራማ በመሆኑ እየተከሰተ ያለውን የመኪና አደጋ ሙሉ በሙሉ ይቀርፋል።
5- ማህበረሰቡ ለትራንስፖርት የሚያወጣውን ጊዜ በ95%ይቀንሳል ፤ ክፍያውንም እንዲሁ።
7- በደሴ ለወደፊት ሊጠየቅ የሚችለውን የአየር ማረፊያ ከወድሁ ይቀርፋል። ( ምክኒያቱም ደሴ ማለት ኮምቦልቻ ይሆናልና )

እነዚህ ለአብነት የተጠቀሱ ጥቅሞቹ ሲሆኑ ከሰሞኑ እንኳን የሀረጎ መንገድ በተለያዩ ቦታዎች መንሸራተት እያጋጠመው በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ወደ ሙያዊ ጥናቶች ስመለስ ፡ ከዚህ በፊት በወንድማችን ኢንጂነር Abdulkerim Aman ማህበራዊ ገፅ እንደተመለከትነው ይህ ፕሮጀክት የሚኖሩት የዋሻ ብዛት ሁለት ባለ 2.01ኪሜ ( 4.02KM ) ሲሆን ይህን ስራ ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ ከ1.6 ዓመት እስከ 1.9 ዓመት እንደሚወስድ በጥናት እና ከልምድ አሳውቆናል። ይህም ጥናት የያፒ መርከዝ ቡድን 3 ጊዜ ከቱርክ በመምጣት እንድሁን የ Wollo University ምህንድስና ክፍል ከኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን እንደተሰራ ሰምተናል።

ይህ ሁሉ ጥናት የተደረገበት ፣ ጊዜ እና አዕምሮ እንድሁም ገንዘብ የፈሰሰበት ፕሮጀክት ግብር የምንከፍለው መንግስት ፣ ህዝቡ አስር ጣቱን አውጥቶ በመረጠው ተወካይ ሲከለከል እውነትም ክልሉ አሁንም ህዝባዊ መሪ እየመራው መሆኑን ሳይሆን ገዥ መንግስት እና የሞግዚት አስተዳደር ውስጥ እንዳለን እንድናስብ እንገደዳለን።

ስለዚህ የክልሉ መንግስት ይህን ፕሮጀክት በልዩ ትኩረት ወስዶ እንዲያፀድቅልን እና ትግበራ እንዲገባልን እንጠይቃለን።

በቀጣይ የወሎ ህዝብ ትልቅ ተስፋ የነበረው ከክልል
እስከ ፌደራል መንግስት ተዘርፎ እንደ ማሌዥያ አውሮፕላን ዜናው ስለጠፋብን የወሎ ተሪሸሪ እና ኬር ሆስፒታል የማቀርብ ይሆናል .....

ሸር ይደረግ
ዘመን ተሻጋሪው

ጀግናው የውሎ ህዝብ ሆይ! ራስህን ቀና አድርገህ የምተኮራበት ከማንም የተሻል ታሪክ እያለህ፣ በብሔር እና በሀይማኖት ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር እሴት ሚስጥራዊ ቁልፉ በጂህ ሆኖ ፣ በቂ ሀብት...
16/08/2022

ጀግናው የውሎ ህዝብ ሆይ!

ራስህን ቀና አድርገህ የምተኮራበት ከማንም የተሻል ታሪክ እያለህ፣ በብሔር እና በሀይማኖት ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር እሴት ሚስጥራዊ ቁልፉ በጂህ ሆኖ ፣ በቂ ሀብት አያለህ ፣የሙህራን ምንጭ ሆነህ ሳለህ እናት ሀገርህ ፍቅሪቷ ወሎ ስትመነምንና ስትራቆት፣ የአባቶችህን ታሪክ ደብዛውን አጥፍተው ባንተ ጫንቃ ላይ ሲሸጋገሩ ፣አንተን እንደ ባሪያ መገልገያ አድርገው ሲይዙህ አይሆንም እኔም የጀግና አያቶቼና አባቶቼ ጀግና ልጂ ነኝ የምትልበትን ወኔ እንዴትአጣህ?!

የታሪክ መዛግብት ቢገለጥ የውሀ ሺታ የነበሩ ሀገር ገንብተው ፣ከተማ መስርተው አዲስ ታሪክን ሲያስመዘግቡ አንተ እንደ ሌሎች ከታሪክ ላይ ታሪክን፣ከከፍታ ላይ ከፍታን መጨመር ቢያቅትህ ያባቶችህን ታሪክ አጥብቀህ፣ ያስረከቡህን ክፍለ ሀገር ጠብቀህ ለመጪው ትውልድ ማስረከብ እንዴት ይሳንሀል‼

ለረጂም ዘመናት በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የነበረውን የደርግ ሰረዎ መንግስት ያስረከበህን ክፍለ ሀገር የተነጠከው የህዝብህ ቁጥር አንሶ ወይስ ምድር ተሰብስባ አውራጃህ ጠቦ ነው?

ንገረ ኝ እስኪ‼ የነበረህን ዝና፣የክፍለ ሀገርህን ግዛት ማስቀጠል ተሰኖህ ታሪክህን ጥለህ ንግስናህን ለሌሎች ያስረከብከው ከውስጥህ ሙህራንን አተህ ነው?

ነገ በመቼው ትውልድ ተጠያቂ ከመሆንህ በፊት ዛሬ እራስህን ጠይቀህ በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን እራስህን ተደግ‼

16/08/2022

የወሎ የክልልነት ጥያቄ አሁንም ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ተሰማ"

የወሎ ክልልነት ጥያቄ ከአስባልትም በላይ ነው!!!ወሎ እራሱን በራሱ የሚያስተዳድር አካባቢ ነበር እንደሚታወቀው በኢህአድግ  መንግስት ግዜ ወደ አማራ ክልል እንድጠቃለል ተደርጎ ጉዳዩ ዉይይት ...
15/08/2022

የወሎ ክልልነት ጥያቄ ከአስባልትም በላይ ነው!!!

ወሎ እራሱን በራሱ የሚያስተዳድር አካባቢ ነበር እንደሚታወቀው በኢህአድግ መንግስት ግዜ ወደ አማራ ክልል እንድጠቃለል ተደርጎ ጉዳዩ ዉይይት ይፈልጋል ከሁለት አመት በኋላ ምላሽ ይደረግለታል በሚል ድፍን ሃሳብ መጨፍለቁ የሚታወቅ ነው።
የወሎ ክልልነት ጥያቄ የአስፓልት ጥያቄ ብቻ አይደለም!!

ጥያቄው.
#የብሄርም
#የቋንቋም አይደለም!

ወሎ በብሄርተኝነት እና በቋንቋ መሰረት ተመስርቶ ከሌላ ጋር የሚጋጭ ብሄር አይደለም።

ወሎ እራሱን ችሎ ሁሉን ህዝብ በስሩ እቅፎ እራሴን በራሴ ላስተዳድር የሚል ክልል ነው!

#ወሎ
በብሄር እና በቋንቋ ጠቦ የሚፈሰፈስ አካባቢ አይደለም ጥያቄው ከዚህ በላይ ነው!!

የወሎየነት ጥያቄ

ከአስፋልቱም በላይ ነው!
ከቋንቋውም በላይ!
ከብሄርም በላይ ነው!

የወሎ ጥያቄ
የማንነት ጥያቄም ጭምር ነው!!!
በአማራነት በኦነግ እገደላለሁ
በኦነግነት በአማራ ክልል እከሰሳለሁ ስለዚህ

እኔ ለብቻየ ክልል ሆኜ ሁለቱንም መመከት እፈልጋለሁ!ጭምር ነው የወሎ ክልልነት ጥያቄ

ከ1983 በፊት በሀገራችን ከሚገኙት 70% ባለሀብቶች መገኛቸው በደጋጎቹ መሬት ወሎ ነበር።አሁን ግን በክልሉ ከሚገኙት ባለሃብቶች 1% ነው የሚሆነው!!--------=----------------...
27/07/2022

ከ1983 በፊት በሀገራችን ከሚገኙት 70% ባለሀብቶች መገኛቸው በደጋጎቹ መሬት ወሎ ነበር።አሁን ግን በክልሉ ከሚገኙት ባለሃብቶች 1% ነው የሚሆነው!!
--------=------------------=----------------=-------

በ1983 ኢህአዴግ ኢትዮጲያን ሲቆጣጠር ከአዲስ አበባ በእስከ ሰሜን ባለው ሀገር በሰሜን ኢትዮጲያ ውስጥ ከሚገኙ የናጠጡ ሀብታም ነጋዴወች ውስጥ 70% የሚሆኑት የሚገኙት በደጋጎቹ ምድር ወሎ ነበር በተለይም ደግሞ ደሴ። የደርግ መንግስት ካዝናው ባዶ ሆኖበት ለትግራይ እና ለወሎ ክፍለ ሀገር መንግስት ስራተኞች የሚከፍለው ደመወዝ ሲያጣ በተደጋጋሚ ካላቸው ቀንሰው ከካዝናቸው መዝርጠው በመስጠት ለመንግስት የሚያበድሩት ወሎዬ ባለጠጋወች ነበሩ። የመንግስት ሰራተኛውም በዚህ መልኩ በሚያገኘው ምንዳ ህይወትን አስቀጥሎ ሌላ ሥርአትን ተቀብሏል።

ከ30 ዓመታት በኋላ የዛሬ አመት ገደማ የአማራ ክልል መንግስት ወደ 30 ባለሀብቶችን ሰብስቦ ሲያወያይ ከታደሙት ባለጠጋወች መካከል ለምልክት እንዲሆን 1 ባለሀብት ብቻ ከወሎ አካባቢ ያስተዋልነው። በዚህ ደረጃ በሚያስደነግጥ መልኩ ወሎ እና ወሎዬወች ሲቆረቁዙ ያየነው በእኛ በወጣቶቹ ዕድሜ ነው። የሰሜን ኢትዮጲያ የንግድ ማዕከል የሆነችው ደሴ ወደኋላ እየተጓዘች አሮጌ ፎቅና አሮጌ አስፓልቶቿን ታቅፋ ቀርታለች። ባለፉት 30 ዓመታት ከወያኔ ህወሓት እና ከብአዴን ጋር እጅና ጓንት ሆነው ከሀብት ማማ የደረሱት የትግራይ ባለሀብቶች እና ከወሎ ውጭ ያሉ አሁን የአማራ ባለሀብቶች እየተባሉ የሚጠሩት ሀብታሞች ፖለቲካውን የገንዘብ ማካበቻ መሳሪያ በማድረግ ቀደምቶቹን ለፍቶ አዳሪ ባለጠጋወች ከጨዋታ ውጭ አድርገዋል። የብአዴን እና የህወሀት ፖለቲካ ደግሞ ወሎን በተለይም ደሴን ከልማት ውጭ በማድረግ ጥርሷን ያራገፈች ከተማ እና አካባቢ ፈጥረዋል። (የድሮ አራዳ ጥርስ የለውም እንዲሉ)።

ህወሓት የወለዳቸውን የትግራይ ባለሀብቶች ባለፉት አራት አመታት በነበረው የፖለቲካ ወጀብ ቀስ በቀስ እየተፋታናቸው ሲሆን፤ ከብአዴን እና ከአማራ ብልጽግና ጋር መርህ አልባ ጥምረት የተጣመሩት የአንድ ሰፈር ባለጠጎች ግን ከንግዱ ባሻገር ፖለቲካችንን እስከ ማሽከርከር ደርሰዋል። ከጨው ጀምሮ ለገዳዮቻችን ጦር መሳሪያ እስከ ማቅረብ ያለውን ህጋዊም ሆነ ህገወጥ ንግድ የአማራ ብልጽግና ባለስልጣኖችንና የመንግስትና የፓርቲ መዋቅርን በመጠቀም በመዳፋቸው አድርገዋል። የአማራ ብልጽግና ከፍተኛ ባለስልጣኖችም ሆኑ ጡረተኞች ከገንዘብ ውጭ ምንም ነገር የማይታያቸው መርህ አልባ ባለሀብቶች ጋር በፈጠሩት የትስስር ሰንሰለት የንግዱ አልበቃ ብሏቸው አገራችንን ወደ ዘላለማዊ ቀውስ ሊወስድ የሚችል የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ እየተርመጠመጡ ነው። ከዶ/ር አምባቸው እና አሳምነው ፅጌ ህልፈት እስከ ወለጋው ጭፍጨፋ ሰንሰለቱ ተቀጣጥሎ የሚሄድበት ድርጊት ብዙ አይነት ነው።

ብዙ የምናወራውና ግንዛቤ የምናስጨብጠው ጉዳይ እያለን፤ ነገን ለመኖር በመመኘት በራሳችን ላይ የንግግር እቀባ ማድረጉን መረጥን። አይታወቅም ምናልባት ሊገድሉን ይችላሉ፤ ደግሞ ከመግደል ወደኋላ አይሉም። ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጃችንን ለመግደል ቤቱ ድረስ ማስክ የለበሱ የታጠቁ ገዳዮች ተሰማርተው ሳያገኙት ቀርተዋል። ቢገድሉንም ባይገድሉንም ለእውነትና ለብዙሀን መታመናችንን መቼም ቢሆን አናቆምም። የሚያሳዝነው 10 የማይሞሉ ዓመታትን በምድር ላይ ሊኖሩ የማይችሉ አድራጊ ፈጣሪ ባለሀብቶችና ፖለቲከኞች ተጣምረው ለብዙሀን ወጣቶች ሞት እና ጥፋት ምክንያት ሲሆኑ ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም። ስምሪት በተሰጣቸው ሰወች ከፌስቡክ የሚለቀቅ ቅራቅንቦ ወሬ በማኘክ በፈቃድህ አእምሮህን በመሸጥ ፖለቲካውን የተገነዘብከው መስሎህ አጉል እምቡር እምቡር የምትለው ወሬ ለቃሚ ሁሉ የምታደርገውን ባለማስተዋል በደመነፍስ በራስህ ላይ ሸምቆቆውን ስበህ ጥፋት እንዳታስከትል አስተውል። እንኳን በደመነፍስነት በማስተዋልም ከመጥፋት በተቆጠብነ። (ምናልባት ካልገባችሁ ከዚህ በላይ መግለፅ ስለማልፈልግ ነው!)

ለማንኛውም ፖለቲካ ማለት ሄዶ ሄዶ መዳረሻው ለህዝቡ የተሻለ ኑሮ ማሻሻያወችን መፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው። በተለይ ለብዙሀን የወሎ ፖለቲከኞች፣ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች፣ ሙህራን ፣ ባለሀብቶች እና ሌላውም ላለፉት 30 ዓመታት ወደ ምዕራብ አንጋጠህ ከመቆርቆዝ ውጭ ያተረፍከው ነገር ቢኖር ለባለጠጎች የሚላላኩ ጡረተኛ ካድሬወችን ነው። አሁን ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ፤ የወሎ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ አቅም ከ90ዎቹ በፊት ወደነበረበት ከፍታ የሚመለስበት እድሎች አሁንም በእጃችን ናቸው። ባለፉት 30 ዓመታት በፖለቲካ ውሳኔ አቅጣጫ ምክንያት ያጣነውን እድልና ያልተጠቀምንበትን ምቹ ሁኔታ በፖለቲካ ውሳኔወች በሚሰጥ አቅጣጫ ብቻ አካባቢ ተኮር እቅዶችን አዘጋጅቶ ከአጠቃላይ አገራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር በማቀናጀት ተጨባጭ እምርታ የምንፈጥርበት ዕድል ከፍ ያለ ነው። ቀዳሚው ነገር ወደ ውስጥ መመልከትና መነፀርን ማስተካከል ነው። ሽራፊ ገንዘብ እየተወረወረልህ የማንም ፖለቲካ አስፈጻሚ አሽከር ከመሆን ወደ ውስጥ ተመልክቶ ራስን፣ ወገንና አካባቢን ለመጥቀም አቅጣጫን ማስተካከል ለነገ የማይተው የዛሬ ስራ ነው።

ዳይ ወደ ውስጥህ ተመልክተህ ውጭውን የምታይበትን መነፀርህን አስተካክል‼
@ብሩክ አበጋዝ

ጠላትን ተስፋ ያስቆረጠው የህዳሴ ግድባችን አዲስ የወጡ ምስሎች ...👌👌የህዳሴ ግድባችን 3ተኛ ዙር ሙሊት በአስገራሚ ፍጥነት እየሄደ ነው። በግድባችን ሃይቅ ላይ ያሉ ደሴቶች በፍጥነት እየጠፉ...
24/07/2022

ጠላትን ተስፋ ያስቆረጠው የህዳሴ ግድባችን አዲስ የወጡ ምስሎች ...👌👌

የህዳሴ ግድባችን 3ተኛ ዙር ሙሊት በአስገራሚ ፍጥነት እየሄደ ነው። በግድባችን ሃይቅ ላይ ያሉ ደሴቶች በፍጥነት እየጠፉ ነው። የአፍሪካውያን ግድብ ጠላትን እንቅልፍ ለማሳጣት በሚመስል መልኩ ከተጠበቀው በላይ እየፈጠነ ነው። ግብፆች በተራ ውሸት አንዴ ግድቡ ተሰንጥቋል አንዴ በቂ ውሃ አላገኙም ሲሉ ግድባችን ፍጥነቱ እንደምትመለከቱት ነው።



ከአንድ ወር ተኩል እስከ ስድስት ወር በወረራ ስር የቆዩ የወሎ ከተሞችና ወረዳወችን አማራ ክልል ምን ቢላቸዉ ጥሩ ነዉ ከአንድና ሁለት አመት በፊት ከወስጥ ገቢያችሁ ሰብስባችሁ ትሸፍኑ የነበረ...
21/07/2022

ከአንድ ወር ተኩል እስከ ስድስት ወር በወረራ ስር የቆዩ የወሎ ከተሞችና ወረዳወችን አማራ ክልል ምን ቢላቸዉ ጥሩ ነዉ ከአንድና ሁለት አመት በፊት ከወስጥ ገቢያችሁ ሰብስባችሁ ትሸፍኑ የነበረዉን በጀት ዘንድሮም ከየትም ወልዳችሁ ቢሆን ሸፍኑ..

የዚያን ሰፈር ፍትህና ፍርድ አጀኢብ ነው ግለሰቡ ቀርቶ የወደሙበት እዉነታ ነዉ ያለዉ ያም አለ ይህ ይሄን ተብሎ የተፈረደባቸዉ አመራሮች የሰኔ ወር ደመወዝ ከባለሀብቶች ብድር ናዉዘዉ ከፈሉ ግን ብድሩ ከየት ነዉ የሚከፈለዉ

የሚለዉ ነገር ግልፅ ነዉ አማራጫቸዉ ልማቱን፣የስራ ቅጥሩን ወዘተ ዘግተዉ ከ2015በጀት ላይ አንስተዉ መክፈል ነዉ እሰቡት በናዚላዉ ክልል ምክንያት ቀጣይም የሰራ ቅጥር ልማት ወሎ ላይ ዝግ ነዉ ማለት ነዉ

እናንተምኮ ራሱ በጣም ትገርሙናላችሁ ቆይ ገዳዮች ማን እንደሆኑ ለየሀቸው? ገዳዮችን ጨርሰህ ከዚህ ምድር አጠፋቸው እንደ? ወይም ገዳዮችን ታግለህ ዳግም የቀረው ህዝብ እንዳይጨፈጨፍ በቂ ማረጋ...
14/07/2022

እናንተምኮ ራሱ በጣም ትገርሙናላችሁ ቆይ ገዳዮች ማን እንደሆኑ ለየሀቸው? ገዳዮችን ጨርሰህ ከዚህ ምድር አጠፋቸው እንደ? ወይም ገዳዮችን ታግለህ ዳግም የቀረው ህዝብ እንዳይጨፈጨፍ በቂ ማረጋገጫ የመኖር ዋስትና ሰጠሀቸው ቆይ?

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ለሞቱት ስለክብር ቀብር፡ ስለ ብሄራዊ ሀዘን ቀን አጀንዳ ለፍጠር መሞከር አሁን በህይወት ያሉት ሌላ እልቂት ውስጥ እንዲገቡ ክፍተት መፍጠር አይሆንብህም ወይ?

መጀመሪያ ገዳዩን ለመለየት ታገል፡ ማነው? አሸባሪው ነው ወይስ ሌላ? ከዛስ ወይ ህግ ፊት የሚመጡበትን አልያም ጨርሰው ከምድር የሚጠፉበትን እርምጃ ጠይቅ!

በመጨረሻም ለሞቱት የሀዘን ቀን ብቻ ሳይሆን እስከዘላለሙ በየአመቱ የብሄራዊ ሀዘን ቀን ይሁን ብለህ መታገል ትችላለህ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Media News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share