03/07/2021
የደቡብ ክልል "1.4ቢሊዮን ብር ተመዝብሬያለሁ!።" አለ።
በደቡብ ክልል ተመዝብሯል የተባለውን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የማስመልስ ተግባር በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት አስታወቀ ።
የክልሉ መንግስት ይህን ያስታወቀው ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የመንግስታቸውን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ነው።
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ርእስቱ ይርዳው በሪፖርታቸው ያቀረቡት ሰነድ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሙስና ፣ በታክስ ማጭበርበር እና በውል አስተዳደር 1, 439, 635, 699 ብር ተመዝብሯል ብሏል።
የተመዘበረውን የህዝብ ሀብት በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አማካኝነት የማስመለስ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ያለው የምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ሪፖርት > በማለት አብራርቷል ።
ሪፖርቱ በክልሉ ተካሂዷል ያለው ምዝበራ በየትኞቹ ተቋማትና በእነማን እንደተፈመ ግን የጠቀሰው ነገር ያለም ።
አቶ ርእስቱ ከዚህ በተጨማሪ በእርሻ ፣ በጤና፣ በትምህርት ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ፣ በሰላምና ፀጥታ ረገድ ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በሪፖርታቸው ዘርዝረዋል።
ዛሬ ጠዋት የተጀመረውና እስከ ነገ የሚቆየው ጉባኤ በአሁኑሰዓት በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቀረበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እየተወያየ ይገኛል ።
ምክር ቤቱ በቆይታው አዳዲስ ሹመቶችንና የተጨማሪ በጀት ጥያቄዎችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ DW ዘግቧል።
The Hawassa post