Gion Media Network _GMN

  • Home
  • Gion Media Network _GMN

Gion Media Network _GMN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gion Media Network _GMN, Media/News Company, .

29/05/2022
22/05/2022
አቶ   የምዕ/ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾመዋል‼ብልህ መሪ ህዝቡን ለማገልገል...መልካም ስምና ታሪክ ለመትከል በጥበብና በማስተዋል በማወቅም ጭምር ወደ ስልጣን ይመጣል... #መልኬ ...
10/10/2021

አቶ የምዕ/ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾመዋል‼

ብልህ መሪ ህዝቡን ለማገልገል...መልካም ስምና ታሪክ ለመትከል በጥበብና በማስተዋል በማወቅም ጭምር ወደ ስልጣን ይመጣል... #መልኬ እንደዚያ ነው።

እንደ መልኬ ያለ ወጣት አመራር የሚመራውን ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃልና ለገጠመንም ለሚገጥመንም የበዛ ችግር ተስማሚ መድሃኒት እንዳለው አምናለሁ...እናም
የሚተገብረውን ማስተዋል የተመላበት ተግባራቶቹ የማከብር ይሆናል።

ይህ በሳል፣ነበልባልና የተረጋጋ ወጣት አመራር እንደ እኛ እንደ ተመሪዎቹ በችግር ደንብሮ በተስፋ መቁረጥ እንደማይመላ በመተማመን ዞናችን ላይ የልቦናችንን ሰላም የሚመልስ መልካም መፍትሄውን በፍቅር ይዞ ብቅ እንደሚል በጉጉት እጠብቃለሁ።

"የጁንታው ቆሻሻ ከእምየ ኢትዮጵያ ቤት ሳይፀዳ የግዮንን ምድር አልረግጥም"‼ሀምሳ አለቃ   የሀገር መከላከያ አባል🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏በምዕ/ጓጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ግዮን(ግሽ ዓባይ) ከተማ ተወልዶ ...
02/09/2021

"የጁንታው ቆሻሻ ከእምየ ኢትዮጵያ ቤት ሳይፀዳ የግዮንን ምድር አልረግጥም"‼ሀምሳ አለቃ የሀገር መከላከያ አባል🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

በምዕ/ጓጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ግዮን(ግሽ ዓባይ) ከተማ ተወልዶ ያደገው ሀምሳ አለቃ አድማሱ ይታይህ ከ10 ዓመት በላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልነት ያገለገለ እና አሁንም እያገለገለ ያለ ጀግና ነው።

ሀምሳ አለቃ አድማሱ ይታይህ "የጁንታው ቆሻሻ ከእምየ ኢትዮጵያ ሳይፀዳ የግዮንን ምድረ አልረግጥም"በማለት ሁላችንም ለዘመቻ እንድንነሳሳ የሚያበረታ መልዕክት ለትውልድ ቀየው ወጣቶች መልዕክት አስተላልፏል።

ሀምሳ አለቃ ፈጣሪ ካንተ ጋ ይሆን ዘንድ ፀሎታችን ነው።

 ❗በአሜሪካ ኒው ዮርክ የሚታተመው   የተሰኘው መፅሄት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን በአፍሪካ የተገኘ ታምረኛው መሪበማለት በፊት ገፁ አውጥቶታል።
22/08/2021



በአሜሪካ ኒው ዮርክ የሚታተመው የተሰኘው መፅሄት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን በአፍሪካ የተገኘ ታምረኛው መሪበማለት በፊት ገፁ አውጥቶታል።

አቶ   የሰከላ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወታደራዊ ስልጠናውን ተቀላቅሏል።ወጣቶች ከአመራሩ ጋር መናበብ አለብን፤ወታደር ለመሆን እንዘጋጅ።
08/08/2021

አቶ የሰከላ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወታደራዊ ስልጠናውን ተቀላቅሏል።

ወጣቶች ከአመራሩ ጋር መናበብ አለብን፤ወታደር ለመሆን እንዘጋጅ።

 #ጥንቃቄ‼share ይደረግየጁንታው ተላላኪወችና ውላጆቹ በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ተሰግስገው ዝርፊያና የሽብር ስራ እየሰሩ ስለሆነ ሁላችንም አካባቢያችንን በንቃት እንጠብቅ።በየአካባቢው...
08/08/2021

#ጥንቃቄ‼
share ይደረግ

የጁንታው ተላላኪወችና ውላጆቹ በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ተሰግስገው ዝርፊያና የሽብር ስራ እየሰሩ ስለሆነ ሁላችንም አካባቢያችንን በንቃት እንጠብቅ።

በየአካባቢው ያለ አመራር ወጣቱንና የፀጥታ ሀይሉን በማደራጀትና በመምራት ግንባር ቀደም ሆኖ የአካባቢውን ሰላም ማስከበር አለበት።

የህልውና ጉዳይ ላይ ነን‼ተጋብዘሀል ክተት‼ #ትግራይ ላይ   ብቻ ነው ያለው!!!✅ትግራይ ላይ የመንግስት ሠራተኛ የለም፣✅ትግራይ ላይ ነጋዴ የለም፣✅ትግራይ ላይ ምሁር የለም፣✅ትግራይ ላይ ተ...
07/08/2021

የህልውና ጉዳይ ላይ ነን‼
ተጋብዘሀል ክተት‼

#ትግራይ ላይ ብቻ ነው ያለው!!!

✅ትግራይ ላይ የመንግስት ሠራተኛ የለም፣
✅ትግራይ ላይ ነጋዴ የለም፣
✅ትግራይ ላይ ምሁር የለም፣
✅ትግራይ ላይ ተማሪ የለም፣
✅ትግራይ ላይ ባለስልጣን የለም፣
✅ትግራይ ላይ ሀብታም/ድሃ የለም፣
✅ትግራይ ላይ የቤት ሠራተኛ የለም፣
✅ትግራይ ላይ የአካል ጉዳተኛ የለም፣
✅ትግራይ ላይ ከሰፈር ጎረምሳ ጋር የተጣላ እስካርፕ
አንገቱ ላይ ጥሎ ኳስ ሜዳ ያለ የሚመስል በአንድ ጋንታ
ወዳድል ጎረምሶች የሚታጀብ ሚኒስቴር የለም፣
✅ትግራይ ላይ ከሆቴል ሆቴል አማርጦ አልጋ ይዞ የሚያድር ባለሰልጣን የለም፣
✅ትግራይ ላይ የሰርግ ምላሽ የተጠራ ይመስል ከጥዋት
ጀሞሮ ጃምቦ ጨብጦ ሲያውካካ የሚውል ወጣት የለም፣

#ትግራይ ላይ #ወታደር ብቻ ነው ያለው።
ሁሉም አማራን እና አጠቃላይ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ግንባር ላይ ነው ያለው!
#እኛስ❓❓

በወገኖቸ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እቃወማለሁ ዶክተር አብይን እቃወማለሁ ፍትህና አንድነትን እደግፋለሁ!!ገለታው ዘለቀየባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፅ/ቤት ሀላፊ
20/04/2021

በወገኖቸ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እቃወማለሁ ዶክተር አብይን እቃወማለሁ ፍትህና አንድነትን እደግፋለሁ!!
ገለታው ዘለቀ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፅ/ቤት ሀላፊ

12/08/13 ወልዲያ የወገናችን ሞት ለማውገዝ አደባባይ ወጥታለች!! #እናመሰግናለን
20/04/2021

12/08/13 ወልዲያ የወገናችን ሞት ለማውገዝ አደባባይ ወጥታለች!!
#እናመሰግናለን

01/04/2021

የጭፍጨፋው አስፈፃሚወች እነሱ ቢሆኑም አመቻቾች እኛው #አማራዎች ነን!!

በምናለ ዋለ

የአማራ ብሄር ተወላጆች ተለይተው እየታረዱት ያለው ዛሬ ላይ ባሉ የኦሮሚያ ፅንፈኛ አመራሮች እቅድና አላማ ቢሆንም የተጠነሰሰው ግን ከዛሬ 30 አመት በፊት መሆኑን ማመን አለብን። ስለ ፅንፈኛው የኦሮሞ ብልፅግና በየጊዜው መናገር አስፈላጊ አይመስለኝም እነሱ ባጭሩ ፀረ-አማራ፣ፀረ-ኢትዮጵያዊ ፣በተረኝነት መንፈስ የሰከሩ፣በአማራዊያን ደም የተጨማለቁ ናቸው። ስለዚህ አሁን ወደ ውስጣችን ተመልክተን እራሳችን የመፍትሄው አካል መሆን ነው እሚያዋጣን።

የአማራን መከራ፣ስቃይና እልቂት በተዘዋዋሪ መንገድ እምናመቻቸው እኛው ጭምር መሆናችንን አምነን አሁንም የትግል ስልት ካልነደፍን ለበዓል እንደተዘጋጀ በግ እራስህን አዘጋጅ እና ላትኖር ሙት። የምናመቻችበት መንገዶች ማሳያ:-
👉በመጀመሪያ ያልተደራጀ ህዝብ እንደሚጠፋ በማመን ህዝቡን ጠንካራ አድርገን ማደራጀት ሲገባን ባልሰከነ የፖለቲካ አካሄድ በመዘፈቅ የሚፈጠሩትን አደረጃጀቶች ከፖርቲ ጋር በማላተም ማክሰምና ማጥፋት ላይ ተጠመድን።ከዚህ አንፃር ነፍሱን ይማርና #አሳምነው በተለያየ አካባቢ ይቋቋሙ የነበርን የወጣት አደረጃጀቶች በአካል በመገኘት ይሰጠው የነበርን የማነቃቃት መንፈስ ለአንድ ህዝብ እንታገላለን እያሉ የማይገናኙ የሚመስሉት #አብንና #አዴፓ እነዚህን አደረጃጀቶች በጋራ እንዲከስሙና እንዲሆኑ አደረጓቸው። ማለትም #አዴፓ የአማራ ወጣቶች ማህበር የአብን ክንፍ ነው በማለት አደረጃጀቱን ፖለቲካዊ ስዕል እንዲይዝ በማድረግ ውጤታማ ስራ ሰርቷል እንዲያውም ተመሳሳይ የአማራ ወጣቶች ማህበር ብሎም ሰብስቧል። #አብንም አደረጃጀቶቹ የሱ እስኪመስሉ ድረስ የተለየ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ሲታትር የነበረ መሆኑን እንረዳለን። #ሁለቱም ወጣቱን ነፃ አድርገው አደራጅተው ህዝቡ እንዲደራጅ ከማድረግ ይልቅ ለራሳቸው የስልጣን መቆናጠጫ መንገድ በማድረግ ተደራጅቶ እራሱን እንዳይከላከል በማድረግ ህዝባችን በየቦታው መሞቱን እያመቻቹለት ይገኛሉ።
👉የፈረሰችን ሀገር በካርድ ለመምራት መሞከር አጉል ቅዠት ውስጥ መግባት ነው!! ወደድንም ጠላንም አመንም አላመንም ሀገር ፈርሳለች( in any parameter i can say ethiopia is a failed state) የዘር ጭፍጨፋ የሚካሄደው፣ ብሄራዊ መግባባት የጠፋው፣ ተቋማቶች የደከሙት፣ ጦርነቱ የተካሄደ በሙሉ የሀገሪቱ መፍረስ ማሳያወች ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ኢላማ የሆነው ደግሞ አማራው መሆኑ እና አማራውን የወከሉት ድርጅቶች ደግሞ "በጊዜው አሁን ነው" እና "አሻጋሪያችን ብልፅግና" በሚሉ በቁም ቅዠት ተጠምደው ባለመደራጀቱ እየታረደ ያለውን ህዝብ በአማራነቱ ተበታትኖ እንዲገደል ዝቅ ሲል ደግሞ እርስ በእርሱ እንዲባላ እያደረጉ መሞቱን እያመቻቹለት ይገኛሉ።
#ንገሩኝ አማራ ክልል ላይ በካርድ አሸንፎ መንግስት እሚሆን አለ? አሸንፈህ ስልጣን በሰላም እምሰጥ ይመስልሀል? ትግልክን ከማን ጋ እየታገልክ እንደሆነ ግልፅ ሁኖልሀል? እነ እስክንድር እንዴት እንደታሰሩ ግን ግልፅ ሆኖልሀል? በዚህ ሂደት የአማራ የዘር ጭፍጨፋን ማስቆም ይቻላልን?
#ንገሩኝ እስኪ በየሰፈሩ ተወሽቀህ ያስገደለህ አብን ነው አሸባሪው አብን ነው እምትል አብንን በሽብርተኝነት ፈርጀን አማራውን መታደግ እንችላለንን? ትግልህ ከአብን ጋ ነውን ከአብን ጋ እምትታገለው አማራውን ለማዳን ነውን? ብሄርተኝነቱ ነው የግድያው ምክንያት ብለህ አመንክ? በጠላትነት የፈረጀ መቸ እንደሆነ ታውቃለህን?
#ንገሩኝ የአማራ በልፅግና ነው ያስገደለህ እኔ መጥቸ አድንሀለሁ እምትል እስኪ ንገረኝ እንዴት ነው ምታድነው። አራት ኪሎ እኮ በፅንፈኛው ኦሮሞ እጅ ነው ያለው። የባህርዳሩን ቤተ መንግስት በመያዝ አማራውን ማዳን ይቻላልን? የህዝባችሁን እንባ ምታብሱት በጋራ በመነጋገር ነው ወይስ በካርድ በማሸነፍ ነው እስኪ ንገሩኝ? የፅንፈኛው የኦሮሞ ብልፅግና 1000 አመት እመራለሁ ያለ በካርድ እያሸነፈ ለመምራት አስቦ ይመስልሀል?
#ንገሩኝ እስኪ የአብን ሴራ ሲጋለጥ የአማራ ብልፅግና ባንዳነት እያልን በመከፋፈል አዙሪት ተወሽቀን ስንባላ ፅንፈኛው የኦሮሞ ብልፅግና የሚገድላቸውን አማራወች ሞቱልክ ብለን በስም ዝርዝር በመለጠፍ እምንድን፣ እምናሸንፍ፣ ስልጣን ይዘን እምናሻግር ወይም ጊዜውን እምናሳይ ይመስልሀል?

#አይደለም!!!!!!

የአማራው ችግር እሚፈታው በእኔ እምነት
1. political democratization ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ከምርጫ ይልቅ የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ በመፍጠር ፖለቲካዊ መፍትሄ መፈለግ። በፖለቲካ ብልሽት የፈረሰን ሀገር በካርድ ለመጠገን መሞከር መፍረስን ማፋጠን መሆኑን በማመን ዜጎች በማንነታቸው በሚገደሉባት ሀገር ምርጫ አንሳተፍም በማለት አቋም መያዝና ህዝቡን መታደግና ሀገርን ማዳን ያስፈልጋል።

በል አንተ ብልፅግና፤አሻግርሀለሁ ያልከውን ህዝብ እየሞተብህ ነውና ከምርጫ ውጣ ሰላሙን አምጣልን ያለ ካርድ ስልጣን በዉይይት እንስጥህ። አደራጀን፣ አወያየን፣ አድነን፣ ድረስልን ሞተን እኮ ልናልቅ ነው ተመርጠህ የቱን ህዝብ ትመራለህ በል አሳየን የኛ መሆንክን? በል በየቦታው ከፖለቲካ ነፃ የሆነ የወጣት ማህበራት፣የአረበኞች ማህበራት፣ልዩልዩ አደረጃጀቶችን እንድንፈጥር እድል ስጠን

በል አንተ አብን፤ጊዜው አሁን ነው ምረጠኝ ያልከው ህዝብ ሞቶ ሊያልቅ ነውና ሳይሞት እራስክን ከምርጫው እንደ አማራ ብልፅግና አግል፣ጥምረት ፍጠር፣አንድ ሁነናል አንድ ሁኑ በለን፣አወያየን፤አደራጀን፣አድነንም፤ነፃ አድርግና የድርሻህን ተወጣ።ከመንግስት ጎን ቁምና ችግሩን ገምግም፤ የመፍትሄ አቅጣጫ አምጣ።የትግል ስልት ፍጠርና አድነን!!

በሉ ሁለታችሁም ስለ ልማት፣ፓሊሲና ስትራቴጅ ወሬውን ተውና ልማትና የፖሊሲ ስትራቴጅያችሁን እምትተገብሩበት ሰላማዊ ህዝብና ሰላማዊ ሀገር ገንቡ። እኔ ላልበላው ልማት ምን ያደርግልኛል፣ አስከሬኔ እንኳ ተጓጉዞ ለማይቀበርበት መንገድ ምን ይሰራልኛል፤እየሞትን እኮ ነው። ስለዚህ ይህንን ህዝብ ለማዳን መሬት ላይ የሚወርድ ስራ ስሩ።
በል አንተ በየሰፈሩ እምትፎክር፣ አጉል ሙገሳ እምትሻ፣ በድንቁርና ጥግ እርስ በእርስህ እምትባላ በል አልመርጥም በል፣ በል አብንም አማራ ብልፅግናም ነኝ በል፣ በል ተደራጅ፣ በል አንድነትን አሳየን፣ በል ለምትጮህለት አማራ በተግባር አሳይ።

አብን እና የአማራ ብልፅግና ላይ ብቻ ያተኮርኩ ዝግ በሆነ የፖለቲካ ስርአት ውስጥ የነሱ ተፅዕኖ ጎልቶ ስለሚታየኝ ነው!!!
ፍትህ ለፍትህ አልባው አማራ!!
የተደራጀ ህዝብ እራሱን ያድናል!!
ያልተደራጀ ህዝብ ይጠፍል!!


መጋቢት 22/2013
ባህር ዳር!!

የክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በስንኝ ቋጠሮ!! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለንየእንስሳት ብርቅ ----- ውብ ተፈጥሮበሀገራችን በተራራ. ---- ላይ ተ...
30/03/2021

የክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በስንኝ ቋጠሮ!!


እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን
የእንስሳት ብርቅ ----- ውብ ተፈጥሮ
በሀገራችን በተራራ. ---- ላይ ተቸንክሮ
ተክለ ሰውነቱ ---- የሚደንቅ ውብ
ቀንደ ሞጋጋ ---- ዥንጉርጉር ድልብ
ታሪክ ጠገብ ---- አይን ማረፊያ
የቱሪስቶች መገናኛ ---- መተያያ
የተራራው ሞገስ ----- ንጉስ ዋልያ
ብርቅዬው ደልቃቃ ---- ኩራት ለኢትዮጵያ
ሀገራዊ መፃኢ ---- ዘመን አብሳሪ
ርዕይ ተላሚ ------ ሩቅ ጉዞን ተናጋሪ
የአንድነት ሸማን ሰቃይ ---- የብቻዬን ናቂ ኮናኝ
የቡድን ስራን ናፋቂ ----- የግል ሽፍንፍንን አብናኝ
የውስጥ መሻትን ገላጭ ----- የሁሌ ቁጭትን ጠጋኝ
አንተ ሞጋጋው ዋልያ ----- ተንደላቀክ ቀንድህ ወጋኝ
ለካስ አርማዬ ኖሯለህ ----- ዞሮ ማረፊያዬ እልፍኝ
ደስታ እንዲህ ---- ጭንቅ ሲል
እርካታ ቢስ ----- መሮጥ መዝለል
ብቻ ጭንቀት ---- ብቻ ጥበት
ከዚህ እዚያ ------ ሲቃ ጭንቀት
ረቂቅ ዘሊቅ ----- ሀገር ማለት
የቀንዳሙ ዋልያ ----- ከፍታ ላይ መታዬት
መዳረሻ ግባችን ----- የመተሳሰራችን እትብት
ኩራት አርማ መለያችን ---- ሁሌም ኢትዮጵያዊነት

ባለሀብቱ ብሄራዊ ቡድኑን ለመሸለም ተዘጋጁ!!ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው ዋሊያወቹ ከ ኮቲዲቯር ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ካሸነፉ የ 5,000,000 ብር በሽልማት እንደሚያቀርቡ በድህረ ገፃቸ...
29/03/2021

ባለሀብቱ ብሄራዊ ቡድኑን ለመሸለም ተዘጋጁ!!

ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው ዋሊያወቹ ከ ኮቲዲቯር ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ካሸነፉ የ 5,000,000 ብር በሽልማት እንደሚያቀርቡ በድህረ ገፃቸው አስነብበዋል።

ድል ለዋልያወቹ!!

ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!! #ሰከላበአማራ ክልል ምዕ/ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ በጉንድል ቆርጣይታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአካባቢው ተወላጅ ሙህራን ከ158,000 ብር በላይ በማሰ...
26/03/2021

ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!!
#ሰከላ

በአማራ ክልል ምዕ/ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ በጉንድል ቆርጣይታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአካባቢው ተወላጅ ሙህራን ከ158,000 ብር በላይ በማሰባሰብ የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የወረዳው ት/ት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ የሻምበል ዘውዴ በድህረ ገፃቸው አስነብበዋል።
ተወላጆች ካደረጉት ድጋፍ መካከልም፤
የቤተ መፅሀፍት አጋዥ
መፅሀፎች፣ፕሪንተር፣እስካነርና ኮፒ ማሽን ይገኙበታል።

የጉንድል ቆርጣይታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቀሌው ሀብትና ተሳትፎ በ12.3 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ እየተገነባ የሚገኝ፤አፈፃፀሙም ከ89% በላይ የደረሠ መሆኑንና በዞንና በክልል ትብብር በተጠናቀቁ ብሎኮች የ9ኛ ክፍል መማር ማስተማር ስራ የተጀመረ መሆኑን ሀላፊው ገልፀው ፤ትም/ት በመጀመሩ የተደሠቱ የካባቢው ተወላጆችና ምሁራን እንዲሁም
የትም/ት ጥራት ተቆርቋሪዎች ያደረጉትን ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል።

ሌሎች የወረዳው ተወላጅ ሙህራንና እና ባለሀብቶች መሰል የበጎ ተግባሮችን ትምህርት ላይ እንዲያውሉም ጥሪ አስተላለፈዋል።

መጋቢት 17/2013 ዓ.ም

24/03/2021

ሀገር አፍራሹ ነው"!!


ሀገር እንደ ሀገር የመቀጠል ስጋት እና አማራው በየቦታው የደረሰበት የዘር ጭፍጨፋና መፈናቀል በዋናነት የሚፈፀመው በፅንፈኛው የኦሮሞ ብልፅግና ሀገር የመበታተን ተልዕኮ አማካኝነት
መሆኑን ማመን አለብን።የዚህን ፅንፈኛ ሀይል ሀገረ የማፍረስ ተልዕኮ መገለጫ ደግሞ የሰሞነኛ የአቋም መግለጫ ብቻ ሳይሆን ከጅምሩም ፀረ ብልፅግና መሆኑን ማሳያወች አሉ።
ከነዚህ ትቂቶቹን ስንመለከት፡-
1. የኦሮሞ ብልፅግና በብልፅግና ስም ከተዋሀዱ የብሄር የፖለቲካ ፓርቲወች መካከል አፈንጋጭና ዳብል ፌስ ፅንፈኛ ለይል መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት አሳይቶናል። መጋቢት 2011 የተከናወነውና ሽመልስ የተናገረው የዚህ ማረጋገጫ ምስክር
ነው። አሀዳዊና ጨፍላቂው ስርአት መጣልህ እሚሉም እነሱ ናቸው። ስለዚህ ብልፅግናን የጊዜአዊ አላማ ማሳኪያ እንጅ to the long run ብልፅግናን አይፈልጉትም።

2. ሌላው የኦሮሞ ብልፅግና ፅንፈኛ እና የፀረ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ማሳያ ብልፅግና የሚያምንበትን የዜጋ ተኮር ፖለቲካ ተፈፅሞ
የሚቃወምና የማይቀበል ይባስ ብሎ በክልሉ የሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆችን እንዳይኖሩ እያስገደለ እየገደለ ያለ ፅንፈኛ ሀይል ነው።

3. የኦሮሞ ብልፅግና ፅንፈኛ እና ሀገር አፍራሽ መሆኑን ሌላው ማሳያ በመተከል፣ በወለጋ፣ በከማሴና ሰሜን ሸዋ አጣየ እየተደረጉ ያሉ
የዘር ማጥፋት ፍጅቶች ናቸው። አንድ ሀገር የመንግስትን ለውጥ ስታደርግ ግጭቶችና ግድያዎች የሚጠበቁ ናቸው ምክንያቱም
በጫና የቀየርከው መንግስት የነበረውን መዋቅር ተጠቅሞ እንደነዚህ አይነት ግጭቶችን እንዲከሰቱ ሊያደርግ ስለሚችል።

ከዚህ አንፃር ሰኔ 16/210 የተደረገው ክስተት፣በአማራና ቅማንት፣ሶማሊ እና አፋር ኢሳ፣ በሶማሊና በኦሮሞ እነዚህን ጥፋቶች ግን በጊዜ ሂደት ምንጫቸውን በማድረቅ ችግሩን
መፍታት ተችሏል። ከዚህ በተቃራኒ በኦሮሚያ ወለጋ፣በመተከል፣በከሚሴ፣ አጣየና ሌሎች ኦሮሚያ አካባቢ የሚከሰቱት ፅንፈኛው የኦሮማያ ብልፅግና እሚፈልገውና ተግባራዊ እያደረገ ያለው ሀገር የማፍረስ ልምምድ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

4. የኢትዮጵያ ብልፅግና ብሎ የተነሳ አለመሆኑን ሌላው ማሳያ ደግሞ የሀገሪቱን ርዕሰ መዲና በኦሮሙማ አስተሳሰብ ዲሞግራፊ ቅየራ ላይ በፅንፈኛ ኦነጋዊ አመራሮች ሲያከናውን
መቆየቱ ነው። ብልፅግና በህብረ ብሄራዊ አንድነት እና ዜጋ ተኮር ፖለቲካ አራምዳለሁ ላለው ብልፅግና የኬኛ ጉዳይ መመልከት ፓርቲው የማይግባቡ ተራራቂ ፍላጎት ያላቸው ጥምረት መሆኑን
መረዳትና የኦሮሞ ብልፅግና ፅንፈኛና ሀገር አፍራሽ መሆኑን መረዳት አለብን።
የሶማሊ ብልፅግና አዲስ አበባ የኔ ናት አላለም፣
እንደቆረቆራት ህዝብነቱ የአማራ ብልፅግና አዲስ አበባ የኔናት አላለም፣ አሸባሪ ብለው ወህኒ ቤት የወረወሩት እስክንድር አዲስ አበባ የኛ ናት አላለም፣የተለያዩ የብሄር ድርጅቶች አዲስ አበባ የኛ ናት አላሉም ሁሉም በአንድ ድምፅ አዲስ አበባ የነዋሪወቿ ናት ነው ያሉ።ፅንፈኛው የኦሮሞ ብልፅግና ግን አዲስ አበባ የኔ ናት እያለ ለዘመናት ተዋዶና ተከባብሮ የኖረውን የአዲስ አበቤን ህዝብ ሊያገዳድሉት ሲሽቀዳደሙ ይታያሉ።

5. የፖለቲካ አመራሮች ከሀገር ይልቅ ለተወሸቁበት የህዝብ ወገኝተኝነት ሲታትሩ መመልከት ሌላው የፅንፈኝነት መገለጫ ነው። በብልፅግና መርህ የፖለቲካ አመራሩ በጋራ እየመከረ እየተስማማ የህዝብ ወገንተኝነትን ሳያራምድ ጠንካራ ሀገረ
መንግስት መገንባት የሚለውን የኮንሰንሴሽናል ዲሞክራሲ በፅንሰ ሀሳብ ለመሳብ ወደ ጎን በመተው መጣልህና መጣብህን የህዝበኝነት
ስራውን እየሰራ ሀገር ለማፍረስ ዳዴ እያለ ያለ ፓርቲ መሆኑን መገንዘብ ነው።

በየከተሞቹ ዘራፍ የሚሉት የአጣዬ ሰላም ፈላጊዎች?? ወይስ እንዲባባስ አቀጣጣዮች???አጣዬን የተኩስ ሜዳ የተደረገችው ከምሽት ጀምሮ ሲሆን የነገር ጥንስሱ ግን የአንድ ቀን አይመስልም።ለአጣዬና...
21/03/2021

በየከተሞቹ ዘራፍ የሚሉት የአጣዬ ሰላም ፈላጊዎች?? ወይስ እንዲባባስ አቀጣጣዮች???

አጣዬን የተኩስ ሜዳ የተደረገችው ከምሽት ጀምሮ ሲሆን የነገር ጥንስሱ ግን የአንድ ቀን አይመስልም።ለአጣዬና አካባቢው ሰላም
ለማምጣት መንግስት የፀጥታ አካሉን በበቂ ቁጥር ወደ ቦታው አስገብቶ መስራት ይኖርበታል።
ለዚህ እኛም የምንችለው ነገር ካለም ልንደግፍ እንችላለን።

በዚህ ሂደት ውስጥ ከተማ ውስጥ እየዞሩ መንግስት እየሰራ አይደለም በማለት ውጥረት ለመፍጠር መሞከር ግን የፀጥታ አካሉ በሙሉ አቅሙ መድረስ ላለበት ወገን እንዳይደርስ #ሀይል የማድከማያ ነው።
ደብረብርሃን ከተማ ላይ የተወሰኑ ወጣቶች መንገድ ላይ በመውጣት አንበተንም የማለት ስሜት አሳይተው አስቸግረው እንደነበር ሰማን።
እጅግ ገራሚ አወናባጅነት ናት ይህችን ከተማ እየተውረገረጉ የፀጥታ አካል የመፈታተን ሙከራ።ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች የአጣዬን ወደ ሰላም መምጣት ፈላጊዎች ናቸው ወይስ በመከራዋ
ነጋዴዎች የሚለውን ማንም ይረዳዋል።

ወኔ አለኝ እምቢ ለወገኔ ያለማ ቦታው ላይ ለወገኑ ይድረስለት።ያን ባይችል እንኳን ደግሞ ፀጥታ አስከባራውን ሀይል አቅም ለማሳጣት ተጨማሪ የቤት ሥራ ለመሆን አይሞክርም።
የወገኖቻችንን ችግር በማራዘምና የፀጥታ አካሉን አቅም በመስለብ የምትጠቅሙት ወገን እንደሌለ ይታወቃል።

ከመተጋገዝ፣ከመግባባት እና አንድነት ከመፍጠር ይልቅ የፀጥታ ሀይሉን ስንካር በመሆን የጠላት በር ለመክፈት የምትሯሮጡ ሁሉ ልትማሩ ይገባል።
!!!

"'ለውጡን ያመጣው ሀይል፣ ለውጡን ማስከንና መጠበቅ ይጠበቅበታል"!!!እስካሁን የተደረገው ትግል አሮጌውንአስተሳሰብ ለማስወገድ ሲሆን፣ ቀጣዩና ዋነኛው ደግሞ አዲሱን ስርዓት ለመትከል ነው። አ...
21/03/2021

"'ለውጡን ያመጣው ሀይል፣ ለውጡን ማስከንና መጠበቅ ይጠበቅበታል"!!!

እስካሁን የተደረገው ትግል አሮጌውን
አስተሳሰብ ለማስወገድ ሲሆን፣ ቀጣዩና ዋነኛው ደግሞ አዲሱን ስርዓት ለመትከል ነው። አዲሱን ስርዓት መትከልና መጠበቅ ደግሞ ለውጡን ለማምጣት የተከፈለውን መሥዋዕትነት ያህል
ባይጠይቅም፣ የበለጠ #ትዕግስትና #ጥንቃቄ የሚጠይቅ ለውጡን ልብ ሊባል ይገባል። ... "

20/03/2021

...

ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ሳይሆን፣ ማይክን እና አንደበትን ያለአግባብ መጠቀም ነው!!

ብልጽግና ፓርቲ  ለሃገራዊ ህመሞቻችን ፈዋሽ መድሃኒት ነዉ!! የደጃች ዘለቀ ደስታ ማረፊያ የታለቁ እና ፈዋሹ ፀበል(የግሽ ዓባይ ዘርዓብሩክ) የአባይ /ጊዬን ወንዝ መናገሻ ጥንታዊቷ የድሮዋ ስ...
20/03/2021

ብልጽግና ፓርቲ ለሃገራዊ ህመሞቻችን ፈዋሽ መድሃኒት ነዉ!!



የደጃች ዘለቀ ደስታ ማረፊያ የታለቁ እና ፈዋሹ ፀበል
(የግሽ ዓባይ ዘርዓብሩክ) የአባይ /ጊዬን ወንዝ መናገሻ ጥንታዊቷ የድሮዋ ስም ምደረ-ገነት የአሁኗ ግሽ-ዓባይ ሰከላ ወረዳ መናገሻ ና የብዙ ወንዞች መነሻ( ከአስራ አራት በላይ)እንዲሁም የብዙ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች የከበቧት ከተማ #ግዮን ሆይ እንኳን ደስ አለሽ!!

የፖለቲካ ሀሁ መምህሩ ፤ በቤተ ዕውቀት ፣ ቤተ ዕምነትና ቤተ መንግስት ተኮትኩተዉ ያደጉ ፤ የእነ አለማየሁ ሞገስ ሃገር ራሱ ቋንቋ መፃሐፍ ፅፎ ያሰተማረ በአዲስ አበባ መምህር ና የነ ዶ/ር ዳኛቸዉ ፈላስፋዉ መምህር ሀገር ነች # ጌታነህ ... የብዙ መኳንንቶች ና ጅግኖች ሃገር የብዙ ደራሲያን ፣አትሌቶችና ተኳሽ፣ቀዳሽ፣አራሽ ና የሊቃዉንት ሃገር ልጆች እና የበኩር ልጅ የሆኑት፤ ወ/ሮ ቸኮልን ለተወካዮች ምክር ቤት ፣የብልጽግና ፓርቲን በመወከል እና ወጣት አለማየሁን ለክልል ም/ቤት ዕጩ ሆነዉ ቀርበዉልሻልና እልል ብለሽ ተቀበያቸው!!

የአማራን የዘመናት ጥላት #ትህነግን ላይመለስ ከሸኙ የፊት አመራሮች መካከል ዋና ተዋናኝ ና የነፃነት ካባ ሊያጎናጽፍሽ ዝግጅታቸዉን ጨርሰዋልና ዕጆችሽን ዘርግተሽ ተቀበያቸው ዘንድ እነሆ ብለናል።
ይህንን መነሻ በማድረግ የሰከላ ወረዳ ብልፅግና
ፓርቲ የሴቶች እኩልነትና ተሳትፎ፤ የአካታችንነት ባህሪ የፓርቲያችን መርህ በመሆኑ ከ50% በላይ የህብረተሰባችን ክፍል የሆኑትን ሴቶችን በማካተት ብስልትና አስተዋይነትን እንዲሁም ለእውነት ትክክለኛ መቆምንና ታጋይነትን የተላበሰች ባለስብዕናዋ ጀግና ሴት፤ለሴቶች ተቆርቋሪ የሆነችዉን ወካይ ወ /ሮ ገዙ ምናየ ቸኮልን ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርበናል።

ብሩህና ሞጋች ሀሳብ አፍላቂ፣ባመነበት ፊት ለፊት የቆመ ወጣት መልካሙ ተሾመን አለማየሁን ለክልል ም/ቤት እጩ አቅርበናል፡፡
ብልፅግና የብርሀን የተስፋ፣የለውጥና ዕድል ይዞ ትብብርንና ፍክክርን ሚዛን በማስጠበቅ ለመስራት በአዚም በወደቅንበት ወቅት ብቅ ብሏል፡፡ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እይታ ያለዉ ፓርቲ ነዉ፡፡ፓርቲያችን ተግባሩን በብርሃን ውስጥ
የሚከውን የጨለማን አስተሳሰብ በመድፈቅ በፊት ለፊት የሚደረግ የፓለቲካ ክርክርን፣ውይይትንና ትግልን የሚያበረታታ ለአማራጭ አስተሳሰቦች ቦታ የሚሰጥና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ትኩረት የሚያደርግ ፓርቲ በመሆኑ የብርሃን ተምሳሌት
የሆነውን የአምፖል ምልክትን መርጧል።

#ምርጫችን ይሁን!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gion Media Network _GMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share