Ahmed Abebaw media & communication

  • Home
  • Ahmed Abebaw media & communication

Ahmed Abebaw media & communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ahmed Abebaw media & communication, Media/News Company, .

i can't  breath !!  pls don't kill me !!እነዚህ የተማፅኖ ቃላት የጥቁሩ አፋሪካ-አሜሪካዊውን የGeorge Floyd ን ህይወት ሊታደጉ አልቻሉም።   የሚንያፓሊስ ከተማ ...
29/05/2020

i can't breath !!
pls don't kill me !!
እነዚህ የተማፅኖ ቃላት የጥቁሩ አፋሪካ-አሜሪካዊውን የGeorge Floyd ን ህይወት ሊታደጉ አልቻሉም።
የሚንያፓሊስ ከተማ የሆነው ፖሊስ ጥቁሩ George Floyd አንገት ላይ ለ 9 ያክል ደቂቃዎች በጉልበቱ በመቆም አፍኖ ገድሎታል።
አለማችን ላይ በተለያዩ ጊዚያት ነጮች በጥቁሮች ላይ በርካታ ግፍ ፈፅመዋል ይህኛውን ለየት የሚያደርገው በ 21ኛው ክ/ዘመን የ democracy ተምሳሌት ናት በምትባለው ሀገረ አሜሪካ ጎዳና ላይ መሆኑ ነው!!
when racism ends ?

where is humanity ?
29/05/2020

where is humanity ?

አሜሪካ፣ ሚኒያፖሊስ ከተማ ውስጥ አንድ የፖሊስ ባልደረባ ከመኪና ያስወረደው ጥቁር አሜሪካዊ ግለሰብ አንገት ላይ በጉልበቱ ለስምንት ደቂቃ ይዞት በመቆየቱ ተጠርጣሪው ጆርጅ ፍሎይድ ታፍኖ ህይወቱ አልፏል!

ጆርጅ በተደጋጋሚ "መተንፈስ አልቻልኩም" እያለ የሚያሳይ ቪድዮ በስፋት እየታየ ነው። ዜናውን ሳይ የጫረብኝ ጥያቄ: ተጠርጣሪው ነጭ ቢሆን ፖሊሱ እንዲህ ያደርግ ነበር?

01/05/2020

Found on Google from facebook.com

09/12/2019

በኢትዮጵያ የዘር ፍጅት ምልክቶችና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች መከሰታቸውን በመጠቆም፤ በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ የሚመራው ‹‹ቄሮ›› በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለተባበሩት መንግስታት አቤቱታ ማቅረባቸው ተጠቆመ፡፡
በአሜሪካ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኙት ‹‹የአዲስ አበባ ባለደራ ም/ቤት›› ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንጋፋው ምሁር ፕ/ር ጌታቸው ሀይሌ ባለፈው ረቡዕ ኒውዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽ/ቤት አቤቱታውን በአካል ተገኝተው ማቅረባቸውን ጋዜጠኛ እስክንድር አስታውቋል፡፡
በአሜሪካ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ባደረጓቸው ስብሰባዎች ከሕዝቡ የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግስታት ሃላፊዎች ማስታወቃቸውን የገለፁት ጋዜጠኛ እስክንድር፤ በዋናነት በቅርቡ 86 ሰዎች የሞቱበትን ጥቃት መነሻ በማድረግ ስለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማብራሪያ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡
በአገሪቱ የዘር ማጥፋት ምልክቶች ስለመኖራቸውና ይህንንም በዋናነት እየፈፀመ ያለው በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ የሚመራው “የቄሮ ቡድን” መሆኑን ላነጋገሯቸው ከፍተኛ የመንግስታቱ ድርጅት ባለሥልጣናት መግለፃቸውን አመልክተዋል፡፡
“ኃላፊዎቹ አቤቱታችንን በሚገባ አድምጠዋል፤ ስለ ኢትዮጵያም ጥሩ መረጃ እንዳላቸው ተገንዝበናል” ብሏል ጋዜጠኛው:: ጠ/ሚኒስትሩ ስለተፈጠረውና ስለሞቱት ሰዎች የሰጡትን መግለጫም እንደማስረጃ ማቅረባቸውም ተገልጿል፡፡
ፕ/ር ጌታቸው ሃይሌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በጥቃት ስለተፈናቀሉ ሰዎችና እየተፈፀመባቸው ስላለው የመብት ጥሰት ለመንግስታቱ ድርጅት ሃላፊዎች ማስረዳታቸውን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል:: ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ድርጊቶች በአገሪቱ ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተፈፀመ መሆኑንም በዝርዝር አስረድተናል ብለዋል - ፕ/ር ጌታቸው::
ሁለት አይነት የቄሮ ቡድን እንዳለ የሚገልፁት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር፤ አንደኛው አምባገነናዊ አገዛዝን ለመቃወም የተሰባሰበና አላማውን አሳክቶ የተቀመጠ ሲሆን በሌላ በኩል በአቶ ጀዋር የሚመራ ጽንፈኛ የቄሮ ቡድን እንዳለ ለሃላፊዎቹ ማስረዳታቸውንም ጋዜጠኛ እስክንድር ብለዋል፡፡ ‹‹በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ የተጠየቀውም ጥፋቶችን እያደረሰ ያለው በአቶ ጀዋር መሃመድ የሚመራው የቄሮ ቡድን ነው›› ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በአውሮፓ ሃገራት ከደጋፊዎቹ ጋር ስብሰባ ሲያደርግ የሰነበተው አክቲቪስት ጀዋር መሐመድ በበኩሉ፤ “እኔን ለመቃወም ሲባል የኦሮሞን ወጣት በሽብርተኝነት መፈረጅና መሳደብ አደገኛ አካሄድ ነው” ብሏል:: በኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ችግር የበለጠ የተጐዱት የኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ የሚናገረው ጀዋር፤ በኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር እሱ ካስተላለፈው ጥሪ ጋር የተያያዘ እንዳልነበር በመጠቆም የዶ/ር ዐቢይን መንግስት እንደግፋለን ብለው አደባባይ በወጡ ሃይሎች የተፈፀመ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን መግለፁ አይዘነጋም፡፡

09/12/2019

የ27 ዓመቱን ውክልናና ስሌት መከለስ!
=====================================
አሁን ከህወሓት ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ ከትግራይ ልሂቃን እየተሰማ ያለው ጩኸትና የውክልና ጦርነት ውስጥ እጅን መዘፈቅ ምንጩ የኢህአዴግ ውህደት ነው ። ውህደቱ የሃገሪቱን ዘውጎች የህዝብ ብዛት ታሳቢ ያደረገ ውክልና ይይዛል ከመባሉ ጋር በተያያዘ ÷ ህወሓት ከላዕላይ ወደ ታህታይ ትወርዳለች ። ይሄ ደግሞ ቀዳሚነትን እና የበላይነትን ሲያስብ ለኖረው ለትግራይ ልሂቅ የሚዋጥ አይደለም ።

እናም ሲፈሩት የኖሩት የቁጥር ፖለቲካን ለመቀልበስ ሀገር ማተራመስ የመጨረሻ አማራጫቸው አድርገውታል ። ከሰሞኑ በወጣው መረጃ መሰረት ኦሮሚያን በሰልፍና በአመፅ ለማተራመስ 400 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ሰምተናል ። ይሄ የጥፋት ድርጅት ሙሉ በሙሉ እስካልተደመሰሰ ድረስ ነገም ተጨማሪ ውድመቶች ይቀጥላሉ ።
-
ህወሓት ውህደቱ የሚያመጣበት መርዶ እንደተጠበቀ ሆኖ ÷ የፌዴራል ፓርላማ ውክልናን በእውነቸኛው የሕዝብ ቁጥር መሰረት ይከለስ ቢባል ሃሳቡን ይቀበላል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው ። የታሪክ መነሻውም ሆነ የትግል ጉዞው እንዲህ ላለ ፍትሃዊ ጥያቄ ቦታ የለውም ። ህገ-መንግስቱ እኮ የአናሳ የበላይነት ለመፍጠር ያለመ ሰነድ ነው ። ይህ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ተቋማቱ ከቁመቱ በላይ ድርሻ ጨብጧል። ከመሠረታዊው ውክልና በሚፃረር መልኩ የፓርላማ ወንበር መቀመጫ ይዞ ይገኛል ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየክልሉ ያላቸው ኮታ ይሄን ይመስላል :-

1. ኦሮሚያ 178
2. አማራ 138
3. ደቡብ 123
4. ትግራይ 38
5. ሶማሌ 23
6. በቤኒሻንጉል 9
7. አፋር 8
8. ጋምቤላ 3
9. ሐረሪ 2
10. ድሬዳዋ 2 [በልዩ ሁኔታ የሚታይ]
11. አዲስ አበባ 23 [በልዩ ሁኔታ የሚታይ]

ከዚህ በላይ በተመለከትነው አሃዛዊ መረጃ መሰረት የክልሎች የህዝብ ውክልና ወንበር በህዝብ ብዛት ነው ማለት አይቻልም! ለምሳሌ በሀገሪቱ በህዝብ ብዛት ደረጃ 3ኛ ነው ከሚባለው ሱማሌ ይልቅ ÷ የትግራይ የወንበር ውክልናው ይበልጣል ።

ይህ ለምን ሊሆን ቻለ?

ያለ ጥርጥር የህወሓት የበላይነት የተጫነው ፖለቲካዊ ውሳኔ ስለነበር ነው!! ከሶማሌ ያነሰ ቁጥር ያለው ትግራይ ÷ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የወንበር ኮታ የቁጥር ብልጫ ሊኖረው ችሏል ።

በሌላ በኩል አሁን ባለው ሁኔታ የአዲስአበባ ህዝብ ብዛት ከአብዛኞቹ ክልሎች ይበልጣል። የከተማዋ ህዝብ በሁለትና ሦስት እጥፍ ቢጨምርም የወንበር ውክልናው በ1987 ስሌት እንደተተመነ አለ ።

ቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ ከሴራ የፀዳ ትክክለኛውን የማንነት መረጃ የሚያሳይ ካልሆነ በዚህ በኩል የሚቀርብን ውዝግብ ከማባባስ የሚተርፍ ሚና ያጣል።

ቆጠራው ትክክለኛ የመሆኑ አሳሳቢነት እንዳለ ሆኖ በህዝብ ቁጥር ልክ የፌዴራል ፓርላማ ውክልና ማግኘትና የቀደመውን ስሌት መከለስ መሰረታዊ ጉዳይ ነው!!

09/12/2019



SBS "በአገርኛ ሪፖርት" የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 12 ይደረጋል ሲል ዘግቧል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዲህ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው፤ የምርጫው ቀን ገና አልታወቀም ሲል መረጃውን አጣጥሎታል። ያንብቡ👇

"ግንቦት 12 በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ ነው። ግንቦት 12, 2012 በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የምርጫ ቦርድ ቀኑ እንደሁኔታው ሊሸጋሸግም እንደሚችል ከወዲሁ ፍንጭ ሰጥቷል። - (SBS RADIO)
"የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ" ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን አሳወቀ በሚል በተለያዩ ሚዲያዎች እየታየ ያለው ዘገባ ከእውነት የራቀ ሲሆን ቦርዱ አገራዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን እና ጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ሲጨርስ የሚያሳውቅ ሲሆን ዜጎች ከቦርዱ ኦፌሴላዊ መግለጫ ውጪ የሚወጡ ሪፓርቶችን እና “ውስጥ አዋቂ መረጃዎችን” ችላ እንዲሉ ቦርዱ ያሳስባል፡፡"

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምር

23/11/2019

Is freedom of expression getting better?

Ethiopia has a long track history of limiting the rights to freedom of expression. Since recently, the government has been undertaking many reforms to change this reality and renew a sense of optimism.

Elias Meseret has been practising journalism for almost a decade. He tells The Ethiopian Herald previously journalists faced various challenges while preparing a news story.

“Officials used to force journalists to prepare stories in their interest. Even, after the stories are published, they gave warnings to reporters. In short, the situation did not permit journalists to work freely.”

Relatively speaking, the situation is improving. Journalists are now expressing their ideas and opinions, Elias says.

“But this does not mean that freedom of expression is perfect in Ethiopia. Recently some journalists who are working in the private media have been arrested,” Elias says. “Committee to Protect Journalists (CPJ) and Amnesty International also expressed their concerns.”

Elias says though it is not appropriate to comment on court cases, he shares the concerns.

On the other hand, Elias says, though the country is freer than before, it has become difficult for journalists to access information from government offices. “Now, there is no responsible body assigned to do the job.”

Obang Metho, human rights activist, says the situation of freedom of expression was worse when he left the country to the US. “There is no doubt that things are improving now.”

But some challenges are hindering its progress. “As ethnicity has got a special place in the current political discourse, citizens and political parties are facing difficulties to go to different places and express their views.”

He also expresses his concern over the arrest of individuals including jouralists in relation to the recent failed coup attempt without conducting a thorough investigation.

“Though the current situation is incomparable with the previous state, there is also a need to further improve the situation,” Obang says.

Noting it is difficult to ensure progress in freedom of expression without press freedom, he urges the media to stand in support of the interests of the public. He also urges the government to prioritize building strong institutions to ensure freedom of expression.

Activist Seyoum Teshome on his part says freedom of expression is one of the most important rights for human beings. Freedom of expression is directly related to the essence of humanity and should never be restricted.

Previously, citizens were thrown to jail or forced to leave the country, simply because they expressed their views. “That is the main reason that led us into a political turmoil in the past.”

The previous regimes in Ethiopia did not want to protect the people’s right for freedom of expression, Seyoum says. “That is why they were toppled down through revolutions.”

In today’s Ethiopia, the state of freedom of expression is relatively getting better. But it is difficult to change the whole situation at once, he adds.

“Our culture and readiness as a society to entertain freedom of expression is also questionable. We have to work harder to bring change at societal level,” says Seyoum.

The Ethiopian Herald
Sept 19/2019

BY GIRMACHEW GASHAW

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahmed Abebaw media & communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share