Badeg Fantaye Gafaro

  • Home
  • Badeg Fantaye Gafaro

Badeg Fantaye Gafaro Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Badeg Fantaye Gafaro, .

29/08/2023
ህዝበ ውሳኔው የመራጮች ተሳትፎ የተረጋገጠበት ነው - የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሰኔ 12/2015 በወላይታ ዞን በተካሄደው ድጋሚ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ የመራጮች ተሳትፎ የ...
20/06/2023

ህዝበ ውሳኔው የመራጮች ተሳትፎ የተረጋገጠበት ነው - የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ

ሰኔ 12/2015 በወላይታ ዞን በተካሄደው ድጋሚ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ የመራጮች ተሳትፎ የተረጋገጠበት መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ገልፀዋል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫው መጠናቀቁን ተከትሎ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል::

በመግለጫቸውም በዞኑ የሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ የምርጫ ሂደቱን አጠናቀዋል ብለዋል:: የመምረጥ ዕድል ላላገኙ መራጮች 12 ሰዓት ላይ መጠናቀቅ የነበረበትን የምርጫ ሂደት ወደ አንድ ሰዓት ቦርዱ ማራዘሙን ተናግረዋል::

በመሆኑም እስከ አንድ ሰዓት ከ20 ድረስ በምርጫ ጣቢያዎች መገኘት የቻሉ ሁሉም መራጮች ድምፅ ሳይሰጡ አለመመለሳቸውንም ነው ያስታወቁት::

ጣቢያዎቹ ወደ ድምፅ ቆጠራ ሂደት የገቡ ሲሆን እስከ ጧት ድረስ ቆጠራው የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል::

ቦርዱ በ12 ማዕከላት እና በ1 ሺ 812 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ 9 ሺ 60 የምርጫ አስፈፃሚዎችን መድቦ መንቀሳቀሱን ያስታወቁት ሰብሳቢዋ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ከአስፈፃሚዎች ጋር ተያይዞ የቀረበ ችግር የለም ብለዋል::

ቦርዱ ምርጫውን ለምታዘቡ ለ2 የሀገር ውስጥ ተቋማትና ለ206 ታዛቢዎች እውቅና በመስጠት ከእነዚህ ውስጥ 168 ታዛቢዎችን በዞኑ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ አስማርቷል::

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን 7 የሰብዓዊ መብት ተከታታዮችን ማሰማራቱም ተገልጿል::

ሰብሳቢዋ መራጮች ለ6 ወር በአካባቢው መቆየታቸውን የማያሳይ መታወቂያ ይዘው መገኘታቸው፣ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ መራጮች መታወቂያ ይዘው መገኘታቸው፣ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ድልቦአውጥሮ 1 የምርጫ ጣቢያ ላይ አንድ ግለሰብ ባዶ መታወቂያ ከቀበሌ አውጥቶ ሲሞላ እጅ ከፍንጅ መያዙን፣ በሁምቦ ምርጫ ጣቢያ አስፈፃሚ ሳይሆን የሌላ ሰው ባጅ አንጠልጥሎ በክትትል መያዙን እና በገሱባ ምርጫ ጣቢያ ላይ ስርዝ ድል ያለበት መታወቂያ ይዞ የተገኘ ግለሰብ መኖራቸው በህዝበ ውሳኔው የምርጫ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን አብራርተዋል::

ከመታወቂያ ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮችን በምስክርና ተጨማሪ ሰነድ እንዲያቀርቡ በማድረግ ችግሩ ተፈትቶ ድምፅ መስጠታቸውን ተናግረዋል::

እጅ ከፍንጅ የተያዙ አካላት ደግሞ ወደ ፖሊስ ተላልፈዋል ብለዋል::

እስከቀኑ 8 ሰዓት ድረስ 514 ሺ 620 መራጮች መሳተፋቸውንም በመግለጫቸው አስታውቀዋል::

የመራጮች ተሳትፎ የተረጋገጠበት መሆኑ እንደ ስኬት የሚወስድ ነው ብለዋል::

ቦርዱ ሰኔ 19 ላይ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ የገለፁ ሲሆን ከተቻለም ከተገለፀው ቀን ቀደም ብሎ ውጤት ለመግለፅ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት::
#ደሬቴድ

አቶ ያዕቆብ ወልደማሪያም 94ኛ ዓመት ልደታቸውን አከበሩ   | አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም የኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና አዘጋጅ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ጋዜጠ...
20/06/2023

አቶ ያዕቆብ ወልደማሪያም 94ኛ ዓመት ልደታቸውን አከበሩ

| አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም የኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና አዘጋጅ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ለ56 ዓመታት ያለማቋረጥ በመሥራት ይታወቃሉ::

እርሳቸው የዛሬ 64 ዓመት በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ ሲቀጠሩ ደሞዛቸው 300 ብር አይደርስም ነበር፡፡ በጊዜው ሄራልድን ሲቀላቀሉ 30 አመት የሞላቸው አቶ ያዕቆብ በዓመቱ በ1952 የሄራልድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና አዘጋጅ ለመሆን ችለዋል፡፡ በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትን በበላይነት የሚመሩት አቶ ዓምደ ሚካኤል ደሳለኝ ኢትዮጵያዊ ዋና አዘጋጅ እንዲሠራ ይመኙ ስለነበር አቶ ያዕቆብ በሄራልድ ዐቅማቸውን እንዲያወጡ ዕድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡

ርእሰ አንቀጽና መጣጥፎችን በመጻፍ ችሎታቸውን ያሳዩት አቶ ያዕቆብ ጥረታቸውን በማጠናከር ቀጠሉበት፡፡ ያኔ እርሳቸው ዋና አዘጋጅ ከመሆናቸው አስቀድሞ ዶክተር ዴቪድ ታልቦት የሄራልድ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡

አቶ ያዕቆብ በሄራልድ በሠሩበት ዓመት ጠንካራ አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ሙያዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል ነዋሪዎች ገንዘብ ቆጥበው የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል ሲሉ በርእሰ አንቀጻቸው ሙግት ገጥመዋል፡፡ ያን ጊዜ ለንጉሡ ቀረቤታ ያላቸው ብቻ ቤት ያገኙ ስለነበር ደሃውም የቤት ባለቤት ይሁን ሲሉ አቶ ያእቆብ በርእስ አንቀጻቸው ላይ አስፈረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ሠራተኛው የጡረታ መብቱ ሊከበርለት ይገባል ሲሉ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል፡፡

ከሄራልድ ከለቀቁ በኋላ በመነን መጽሔት፤ በቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ ሪፖርተር በኤዲተርነት የሠሩ ሲሆን በሚሠሩትም ሥራ ደስተኛ ነበሩ፡፡ በንጉሡ ዘመን ለ15 ዓመታት፤ በደርግ ዘመን ለ17 ዓመታት፤ ከዚያ በኋላ ላለፉት 24 ዓመታት በጠቅላላ ለ56 ዓመታት በሙያቸው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አቶ ያዕቆብ ከ1983 በኋላ ዘሰን፤ ዘሪፖርተር፤ ፎከስ ለተሰኙ የኅትመት ውጤቶች ሠርተዋል፡፡ በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማሳተም ለሚፈልጉ ሰዎችም ሙያዊ ምክር በመስጠት ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

አቶ ያዕቆብ ሄራልድ ከመግባታቸው በፊት አምኃ ደስታ ትምህርት ቤት የሳይንስ መምህር ሳሉ የትምህርት ቤት ጋዜጣ እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ አቶ ያዕቆብ አልፎ አልፎ የጋዜጠኝነት ኮርስ ከመውሰዳቸው ሌላ በመደበኛነት ጋዜጠኝነትን አልተማሩም፡፡ ይልቁንም በእንግሊዝ ስኩል ኦፍ ለንደን ምሕንድስናን ለተወሰነ ዓመት አጥንተዋል፡፡ በለንደን እያሉ ጋዜጦችን በማንበብ ራሳቸውን በራሳቸው ጋዜጠኝነት ማስተማር ችለዋል፡፡ አቶ ያዕቆብ የራሳቸውን ግለ ታሪክ በ1995 ያሳተሙ ሲሆን አሁን ዕድሜያቸው 94 ነው፡፡ አንድ ዓይናቸው ማየት ያቆመው አቶ ያዕቆብ ባለትዳርና የ ልጆች አባት ናቸው፡፡ የትውልድ ቦታቸውም ወለጋ ነቀምት ሲሆን አዲስ አበባ መጥተው በኮተቤ ተምረዋል፡፡

ለአገራችን የእንግሊዘኛ ጋዜጦችና መጽሔቶች እድገት ከወጣትነት እስከ አረጋዊነት እድሜያቸው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አስተዋጽኦ ያደረጉትና እያደረጉ ያሉት እኚህ አንጋፋ ጋዜጠኛ በ2007 የበጎ ሰው ሽልማትን ወስደዋል::

በአንደኛ ሊግ ተሳትፎውን ማረጋገጥ የቻለው የቡኢ ከነማ እግር ኳስ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የአርባምንጭ አቻውን ለዋንጫ ፍልሚያው ለመድረስ ተፋጠዋል።ቡድኑ በሩብ ፍፃሜ ጨዋታው የሶዶ ከተማ ተወካ...
30/05/2023

በአንደኛ ሊግ ተሳትፎውን ማረጋገጥ የቻለው የቡኢ ከነማ እግር ኳስ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የአርባምንጭ አቻውን ለዋንጫ ፍልሚያው ለመድረስ ተፋጠዋል።

ቡድኑ በሩብ ፍፃሜ ጨዋታው የሶዶ ከተማ ተወካይ የሆነውን ብሩህ ተስፋን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ጥሎ ግማሽ ፍፃሜ መቀላቀሉ በስነ ልቦና የተሻለ ዝግጆት እንዲያገኝ ሲያስችለው ደጋፊዎች በሜዳውና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰጡዋቸው ማበረታቻ ቃላቶች ደግሞ ሌላኛው የክለቡ ስኬት አንዱ አካል ይመስለኛል።

በተለይም በውድድሩ ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ እዛው ወላይታ የሚገኙ የማህበረሰቡ ተወላጆችና ከዚህም ከትላንትናው በተሻለ መልኩ ደጋፊዎች በአካል ሄደው ማበረታታት ያስፈልጋል።

አንደኛ ሊጉ ላይም የተሻለ ውጤት እንዲያገኝና ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው የተቋቋሙት ኮሚቴዎች የደጋፊዎች ማህበር በማቋቋም በአጭር ጊዜ ፕሪሜርሊግ ተሳታፊ የሚሆን ክለብ ማድረግ ይቻላል።

መልካም ውጤት ከወዲሁ ተመኘው

የደቡብ_ክልል_ክለቦች_ሻምፕዮ👉 ቡኢ ከተማ 2:1 ብሩህ ተስፋኮርታችሁ አኮራችሁን !!!!!"""""""""
29/05/2023

የደቡብ_ክልል_ክለቦች_ሻምፕዮ

👉 ቡኢ ከተማ 2:1 ብሩህ ተስፋ
ኮርታችሁ አኮራችሁን !!!!!"""""""""

እንደቀልድ ከተመረቅን ስድስት ዓመታት በዚህ ስድስት ዓመታት ጥሩም መጥፎም እንደግለሰብ እንደሀገርም አሳለፍን።ውድ የጓደኞቼ ባለችሁበት ሰላም ጤና ለእናንተ በትግራይ ኢትዮ ሶማሌከአፋር አማራ ...
28/05/2023

እንደቀልድ ከተመረቅን ስድስት ዓመታት በዚህ ስድስት ዓመታት ጥሩም መጥፎም እንደግለሰብ እንደሀገርም አሳለፍን።

ውድ የጓደኞቼ ባለችሁበት ሰላም ጤና ለእናንተ በትግራይ ኢትዮ ሶማሌ
ከአፋር አማራ ከደቡብ ጋምቤላ
ከቤንሻንጉልጉሙዝ ሃረር ከአዲስ ድሬደዋ ከኦሮሚያ እንዲሁም በሀገሪቱዋ አራቱም አቅጣጫ የተሰባሰባችሁ እንደምን አላችሁ።

የአፍሪካ ህብረትና የፖርላማ ጉዞና ቅኝት ፎቶ ማስታወሻ

ስንቅና ዝናር !!!"""""!!!!!!!!!!!በትላንትህ መኖር አትችልም በወቅታዊና አቋምህ እንጂ ቡኢ ከነማ በዞናል ጨዋታው ሶስተኛ ቢወጣም  በሜዳ ላይ ክፍተቶቹን በማረምእንዲሁም አመራሮችና ...
26/05/2023

ስንቅና ዝናር
!!!"""""!!!!!!!!!!!
በትላንትህ መኖር አትችልም በወቅታዊና አቋምህ እንጂ ቡኢ ከነማ በዞናል ጨዋታው ሶስተኛ ቢወጣም በሜዳ ላይ ክፍተቶቹን በማረምእንዲሁም አመራሮችና ማህበረሰቡ ያደረጉላቸው ድጋፍና ትብብር በክልል ሻምፒዮናው ውድድሩ ስንቅና ዝናር ሆኗቸዋል ብዬ አምናለው።

በሻምፒዮናው ምንም እንኳን ሶስት ክለቦች ጉራጌ ዞን ቢወክሉም ለሩብ ፍፃሜው መድረስ የቻለው የሶዶ ክስታኔዎቹ ፈርጦች ናቸው።

መልካም ዕድል!!!!!!

በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቡኢ ከነማ  የጂንካ ተወካይ የሆነው ብሩህ ተስፋ እግር ኳስ ቡድን ይገጥማል📆ሰኞ ግንቦት 21🕐 ከቀኑ 9:00🏟 በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስቴድየምመልካም ዕድልመረጃው የቡኢ ከነ...
26/05/2023

በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቡኢ ከነማ የጂንካ ተወካይ የሆነው ብሩህ ተስፋ እግር ኳስ ቡድን ይገጥማል

📆ሰኞ ግንቦት 21

🕐 ከቀኑ 9:00

🏟 በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስቴድየም

መልካም ዕድል

መረጃው የቡኢ ከነማ የፌስቡክ ገፅ

እንኳን ደስ አለን አላችሁ።ቡኢ ከነማ የእግር ኳስ ክለብ በክልል ክለቦች ሻምፒዮና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን ከነማው በቀጣይ የተሻለ ድል እንድያስመዘግብ መልካም ምኞታችን ነው!!ወደፊት...
26/05/2023

እንኳን ደስ አለን አላችሁ።

ቡኢ ከነማ የእግር ኳስ ክለብ በክልል ክለቦች ሻምፒዮና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን ከነማው በቀጣይ የተሻለ ድል እንድያስመዘግብ መልካም ምኞታችን ነው!!
ወደፊት !!!!!!!!!!!!!

ከፎቶ ማህደር በሚለው
23/04/2023

ከፎቶ ማህደር በሚለው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Badeg Fantaye Gafaro posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share